Amharic 31

  • ㆍISBN : 9788928238156
  • ㆍPáginas : 315

በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተሰጡ ስብከቶች (Ⅴ) - የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚያምኑ አማኞች እንዲህ አሉ

Paul C. Jong

እኛ እያሰራጨነው ባለነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግም የተወለዱ በርካታ አዳዲስ ክርስቲያኖች በመላው አለም አሉ፡፡ እኛ በእርግጥም ለእነርሱ የሕይወት እንጀራን ልንመግብ እንናፍቃለን፡፡ ነገር ግን ከእኛ በጣም ርቀው ያሉ በመሆናቸው በእውነተኛው ወንጌል ከእነርሱ ጋር ሕብረት ማድረግ አስቸጋሪ ነው፡፡
ስለዚህ የእነዚህን የነገስታት ንጉስ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝቦች መንፈሳዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ደራሲው በኢየሡስ ክርስቶስ ቃል በማመን የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የተቀበሉ ሰዎች እምነታቸውን ለመከላከልና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለመደገፍ ንጹሕ የሆነውን የእርሱን ቃል መመገብ እንዳለባቸው ይናገራል፡፡ በእነዚህ መጽሐፎች ውስጥ ያሉት ስብከቶች መንፈሳዊ ዕድገታቸውን ለማነጽ ሲባል ዳግም የተወለዱትን የሚመግቡ ትኩስ የሕይወት እንጀራ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡
እግዚአብሄር በቤተክርስቲያኑና በአገልጋዮቹ አማካይነት ይህንን የሕይወት እንጀራ በማቅረብ ይቀጥላል፡፡ የእግዚአብሄር በረከቶች ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም በተወለዱና ከእኛም ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕብረት እንዲኖራቸው ከሚሹ ሰዎች ሁሉ ጋር ይሁኑ፡፡

Audiolivro
undefined
Devido ao COVID-19 e à interrupção do Serviço de Correio Internacional,
suspendemos temporariamente o nosso 'Serviço de Impressão Gratuita de Livros'.
Diante dessa situação, não podemos enviar os livros para você neste momento.
Ore para que esta pandemia termine em breve e retorne o serviço postal.