Perguntas Frequentes sobre a Fé Cristã
Assunto 2: O Espírito Santo
2-1. በኢየሱስ አምናለሁ፤ ፍጹም የሆነ የሐጢያት ስርየትም እንተቀበልሁ አስባለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጤ እንዳለም አምናለሁ፡፡ የዳነ ሰው የእግዚአብሄር መቅደስ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ሁልጊዜ በተሳሳትሁና ሐጢያትን ባደረግሁ ጊዜም በውስጤ ያለው መንፈስ እኔን በመክሰስና ይቅርታን ለማግኘትም ሐጢያቴን እንድናዘዝ በማገዝ ከእግዚአብሄር ጋር ያለኝን ግንኙነት በአዲስ መልክ ይመልሳል፡፡ ይህንን ካላደረግሁ እግዚአብሄር እንደሚቀጣኝ ተማርሁ፡፡ ሐጢያቶቻችንን ካልተናዘዝንና ለእነርሱም ይቅርታን ካላገኘን መንፈስ ቅዱስ ለጊዜው በውስጣችን የማይኖር መሆኑ በእርግጥም እውነት ነውን?
ጉዳዩ በተጨባጭ ይህ አይደለም፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ጽድቅን ሰራን ወይም አልሰራን በእኛ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ በሌላ አነጋገር ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ በእኛ ፈቃድ ወይም ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ታዲያ እንዴት ሊገኝ ይችላል? መንፈስ ቅዱስ ሐጢያቱን ስለተናዘዘና ይቅርታም ስላገኘ በግለሰቡ ውስጥ አያድርም፡፡ በፈንታው መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ውስጥ ለዘላለም የሚኖረው እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ለሐጢያቶቹ ይቅርታን ሲያገኝ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ኢምንት ሐጢያት ባለበት ሰው ውስጥ እንኳን ሊኖር አይችልም፡፡
ሆኖም ብዙ ሰዎች ሐጢያቶቻቸውን ቢናዘዙና ይቅርታን ቢለምኑ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው እንደሚያድር ያስባሉ፡፡ ይህንን ካላደረጉ በውስጣቸው የማያድር ይመስላቸዋል፡፡ ይህ በተጨባጭ ስህተት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ ቀን በሐዋርያቶች ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደ ይናገራል፡፡ እነርሱ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት በጸሎቶቻቸው ሳይሆን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሐጢያቶቻቸ ይቅር በመባላቸው ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ የሚመጣውም የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ በመቀበል በተቀደሱት ላይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ቅዱስ›› ብሎ የሚጠራው ቃል ‹‹ከሐጢያት መለየት›› ማለት ነው፡፡ መተላለፍን በፈጸምህ ጊዜ ሁሉ ለይቅርታ በመናዘዝና በመጸለይ ሐጢያቶችህን ማስወገድ በእግዚአብሄር ፊት እንከን የለሽ ይቅርታ አይደለም፡፡ ያለ ምንም ግድፈት ሐጢያቱን ሁሉ እንዴት በእግዚአብሄር ፊት መናዘዝ እንደሚችል የሚናገር ማንኛውም ሰው ምንኛ ቢደፍር ነው?
በእግዚአብሄር ፈቃድ መሰረት ለደህንነታቸው ኢየሱስ በዮሐንስ እንደተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰ የሚያምኑ ብቻ ፍጹም የሆነውን የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ የእግዚአብሄር ስጦታ ከሆነው ዘለቄታዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር አብረው ይቀበላሉ፡፡ ሆኖም ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን በራሳቸው ጥረቶች አማካይነት ለማግኘት የሚፈልጉበት ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ፍጹም የሆነውን የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ባለማግኘታቸው ነው፡፡
እውነተኛው መንፈስ ቅዱስ በኑዛዜ ወደ ሰዎች አይመጣም፡፡ እርሱ ወዲያውኑ የሚመጣው እነርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይቅርታን ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለማግኘት መሰረታዊው የእምነት ስረ ነገር ይህ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ በእኛ በኩል ከሚመጣ ማንኛውም አይነት ጥረት ወይም ምግባር አይመጣም፡፡ እርሱ በሰው ላይ የሚመጣው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሐጢያቶቹ ፈጽመው ይቅርታን ካገኙ ነው፡፡ እኛ ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ ከሐጢያቶቻችን በሙሉ ከ2,000 ዓመት በፊት ይቅር ተብለናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚያድረው የዚህ አይነቱን እምነት በሚገልጥ ሰው ውስጥ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ባለበት ሰው ውስጥ መኖር አይችልም፡፡ አንድ ሰው ሐጢያት በሚሰራበት ጊዜ ሁሉ በእውነተኛው ወንጌል እምነት ፋንታ በኑዛዜ አማካይነት ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ የሚለምን ከሆነ በጭራሽ መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችልም፡፡ ይህ የሚያሳየው እርሱ በኢየሱስ ቢያምንም አሁንም በልቡ ውስጥ ሐጢያት እንዳለበት ብቻ ብቻ ነው፡፡
የሚኮንነን ሰይጣን ነው፡፡ በሮሜ 8፡1 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እንግዲህ እንደ ስጋ ሳይሆን እንደ መንፈስ በሚመላለሱ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡››
አንድ ሰው የሐጢያትን ይቅርታንና ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ እንደተቀበለ በእርግጠኝነት ቢናገርም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ለሐጢያቶቹ ሁሉ ይቅርታን ካላገኘ ሐጢያት በልቡ ውስጥ ይቀራል፡፡ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ትክክለኛ የሆነ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውቀት ሊኖርህ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ይበልጥ በዝርዝር መማር የምትፈልግ ከሆነ የፖል ሲ. ጆንግን የመጀመሪያ መጽሐፍ ‹‹በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ዳግም ተወልዳችኋልን?›› የሚለውን የመጀመሪያ መጽሐፍ እንድታነብ ከልባችን እናቀርብልሃለን፡፡
- Antes
2-10. Eu passei muitos dias tristes, após um médico ter diagnosticado meu caso de câncer estomacal. Um dia, um amigo cristão me visitou e me disse que alguém, frequentando um encontro de avivamento em sua Igreja, havia sido curado de um tipo de doença muito grave. Para mim, um ateu naquele tempo, a cura de uma doença pelo poder de Deus parecia boa demais para ser verdade. No último dia do encontro, todos foram até o Ministro para receberem a imposição de mãos. Enquanto colocava suas mãos em mim, ele me falou para repetir algumas palavras ininteligíveis e me perguntou se eu acreditava no poder de cura de Jesus Cristo. Apesar de eu realmente não acreditar, estava nervoso e falei que sim. E naquele mesmo instante eu senti algo quente, como eletricidade, correndo pelo meu corpo. Eu podia sentir o meu corpo todo tremer e senti que o meu câncer havia sido curado. Eu decidi crer no Senhor Jesus naquele lugar, e após aquilo, uma grande felicidade e paz vieram encher o meu coração e assim comecei uma nova vida. Eu também me dediquei a espalhar o evangelho. Eu acho que o Espírito Santo fez todas estas coisas, e creio que Ele habita em mim. Você não pensa da mesma forma?