Perguntas Frequentes sobre a Fé Cristã
Assunto 2: O Espírito Santo
2-10. ሐኪሙ የጨጓራ ካንሰር እንዳለብኝ ከነገረኝ በኋላ ብዙ የሐዘን ቀኖችን አሳለፍሁ፡፡ አንድ ቀን አንድ ክርስቲያን የሆነ ጓደኛዬ ጎበኘኝና በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረገውን የመነቃቃት ስብሰባ የሚካፈል ማንኛውም ሰው ከማንኛውም አይነት በሽታ እንደሚፈወስ ነገረኝ፡፡ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሄር መኖር ለማላምነው ለእኔ በሽታ በእግዚአብሄር ሐይል የመፈወሱ ነገር ለማመን የሚከብድ ነበር፡፡ በስብሰባው የመጨረሻው ቀን የእጆችን መጫን ለመቀበል ሁሉም ሰው ወደ አገልጋዩ ቀረበ፡፡ እጆቹን በእኔ ላይ በጫነብኝ ጊዜ አንዳንድ የማይስተዋሉ ቃሎችን እንድደጋግም ነገረኝና በኢየሱስ ክርስቶስ የፈውስ ሐይል አምን እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ በልቤ በትክክል ባላምንም ደነገጥሁና አዎ ብዬ መለስሁ፡፡ በዚያው ቅጽበት ልክ እንደ ኤሌክትሪክ ያለ ሙቀት በውስጥ ሲፈስስ ተሰማኝ፡፡ መላው ሰውነቴ ሲንቀጠቀጥ ይሰማኛል፡፡ ካንሰሬም እንደተፈወሰ ታወቀኝ፡፡ እዚያው እያለሁ በጌታ ለማመን ወሰንሁ፤ ከዚያ በኋላ ታላቅ ሐሴትና ሰላም በልቤ ውስጥ ገባ፡፡ አዲስ ሕይወትም ጀመርሁ፡፡ ራሴንም ለወንጌል ስርጭት ቀደስሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዳደረገ አስባለሁ፤ እርሱ በውስጤ እንደሚኖርም አምናለሁ፡፡ አንተም ስለ መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ አታስብምን?
በእርግጥ በጣም የሚያስገርም ልምምድ ነበረህ፡፡ እግዚአብሄር ጸሎቶቻቸውን ከመለሰላቸው በኋላ ሕይወታቸውን ለጌታ ቀድሰው ከሰጡ ሰዎች ብዙ ምስክርነቶችን ሰምቻለሁ፡፡ ሆኖም ይህ አስገራሚ መለኮታዊ ልምምድ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበልህ አስተማማኝ ማስረጃ መሆን ስለመቻሉ ልጠይቅህ እወዳለሁ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች ከላይ ለተነሳው ጥያቄ ‹‹አዎ›› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ቁሳዊነት በማደጉ ምዕራባዊው ክርስትና ባሽቆለቆለ ጊዜ ጴንጤቆስጤያዊ ካራዝማቲክ እንቅስቃሴ ተብሎ የሚጠራው ተነሳና ክርስትና በሚያስደንቅ መልኩ በተለይም ባላደጉት ወይም በማደግ ላይ ባሉት አገሮች ተነቃቃ፡፡
ከዚህ የተነሳ ብዙ ክርስቲያኖች ከልዕለ ተፈጥሮ በላይ በሆኑ ልምምዶች ላይ በሚያተኩረው የጴንጤቆስጤያዊ ካርዝማቲክ እንቅስቃሴ ተጽዕኖ ስር ወደቁ፡፡ የመነቃቃት ስብሰባዎችን የሚመሩ ሰዎችም አንዳንድ ጊዜ ወንጌላውያን አነቃቂዎች ሆነው በመላው አለም ዝናን ያገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የራሳቸው የሆኑ አስገራሚ ምስክርነቶች ስላሉዋቸውና እምነታቸውንም በልምምዶቻቸው አማካይነት ስለሚገልጡ ተከታዮቻቸውም ልክ እንደ እነርሱ በልምምድ ላይ የተመሰረተ እምነትን ይከተላሉ፡፡
ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ከላይ ለቀረበው ጥያቄ ‹‹አይደለም›› ይላል፡፡ በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ ከልዕለ ተፈጥሮ በላይ የሆኑ ልምምዶችን ለመስጠት ችሎታ አለው፡፡ ሆኖም እርሱ የእውነት መንፈስ ስለሆነ (ዮሐንስ 15፡26) መንፈስ ቅዱስ መቀበል የምንችለው በእውነት ቃል አማካይነት ነው፡፡
ጴጥሮስ በበዓለ ሃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስን ተቀበለና ‹‹እግዚአብሄር እናንተ የሰቀላችሁትን ይህንን ኢየሱስ ጌታና ክርስቶስ አደረገው›› በማለት ወንጌልን በድፍረት ሰበከ፡፡ ከዚያም ይህንን የሰሙት አይሁዶች ለጴጥሮስና ለሌሎቹ ሐዋርያት እንዲህ አሉ፡- ‹‹ወንድሞች ሆይ ምን እናድርግ?›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡36-37) እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፡- ‹‹ንስሐ ግቡ፤ ሐጢአታችሁ ይሰረይ ዘንድም እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፡፡ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡ የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡38-39)
በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በማመን የሐጢያት ስርየትን ለተቀበሉ ጻድቃን መንፈስ ቅዱስን እንደ ስጦታ እንደሚሰጥ በግልጽ ተናገረ፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ለመኖሩ ብቸኛው ማረጋገጫ የእውነት ቃል ነው፡፡
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የሐጢያት ስርየትን ተቀብለሃልን? እንደዚያ ከሆነ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ቀድሞውኑ በአንተ ውስጥ ለመኖሩ እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ፡፡
ሆኖም ምንም ያህል አስገራሚ ልምምዶች የነበረህ ቢሆንም ወይም ምንም ያህል ድንቅ ነገሮችን ያደረግህ ቢሆንም አሁንም ልብህ ውስጥ ሐጢያት ካለ በእርግጠኝነት መንፈስ ቅዱስ የለህም፡፡ ምክንያቱ በእግዚአብሄር ቃል የተመሰረተ የሐጢያት ስርየት የሌለህ መሆኑ ነው፡፡ ጨለማ በብርሃን ውስጥ ሊገኝ እንደማይችል ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በሐጢያተኛው ላይ ሊመጣም ሆነ በሐጢያት ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፡
እኔ ከእነዚህ ባሻገር ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን ተቀብያለሁ፡፡ አንተም በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ የሚያምን እምነት በመያዝ ለጥያቄዎቹ መልሶችን ሁሉ ማግኘት ትችላለህ፡፡ አሁን በኢየሱስ የሚያምን እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን በሁሉም ላይ እንደሚያፈስሰው ተስፋ የሰጠውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል ይችላል፡፡ ለጌታ ምስጋናን እናቀርባለን፡፡ ሐሌሉያ!
ይህ መጽሐፍ በመንፈስ ቅዱስ ላይ በዛ ያለ መረጃን ይዦዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ጥያቄዎችህን ለመመለስ ያግዛል፡፡ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ጨምረህ ለማወቅ የምትፈልግ ከሆነ እባክህ የደራሲውን ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፎች የመጀመሪያ ሁለት መጽሐፎች አመሳክር፡፡
በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ዳግም ተወልዳችኋልን?
ሴኡል፤ ሔፕዚባህ 1999 ዓ.ም
ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ተመለሱ
ሴኡል፤ ሔፕዚባህ 1999 ዓ.ም
እግዚአብሄር ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ እንድትቀበልና የጌታን ምጽዓት እንድትጠባበቅ ይፈልጋል፡፡ አንተም ከደራሲው ጋር አብረህ በእግዚአብሄር ቃሎች የምታምን ከሆነ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ትቀበልና ለእግዚአብሄር ክብርን ትሰጣለህ፡፡
- Antes
2-10. Eu passei muitos dias tristes, após um médico ter diagnosticado meu caso de câncer estomacal. Um dia, um amigo cristão me visitou e me disse que alguém, frequentando um encontro de avivamento em sua Igreja, havia sido curado de um tipo de doença muito grave. Para mim, um ateu naquele tempo, a cura de uma doença pelo poder de Deus parecia boa demais para ser verdade. No último dia do encontro, todos foram até o Ministro para receberem a imposição de mãos. Enquanto colocava suas mãos em mim, ele me falou para repetir algumas palavras ininteligíveis e me perguntou se eu acreditava no poder de cura de Jesus Cristo. Apesar de eu realmente não acreditar, estava nervoso e falei que sim. E naquele mesmo instante eu senti algo quente, como eletricidade, correndo pelo meu corpo. Eu podia sentir o meu corpo todo tremer e senti que o meu câncer havia sido curado. Eu decidi crer no Senhor Jesus naquele lugar, e após aquilo, uma grande felicidade e paz vieram encher o meu coração e assim comecei uma nova vida. Eu também me dediquei a espalhar o evangelho. Eu acho que o Espírito Santo fez todas estas coisas, e creio que Ele habita em mim. Você não pensa da mesma forma?