Fragen und Antworten zum christlichen Glauben
Thema 1: Die Wiedergeburt aus Wasser und Geist
1-11. ኢየሱስን ያጠመቀው አጥማቂው ዮሐንስ ማነው?
እግዚአብሄር ለእስራኤል በሙሴ አማካይነት ሕጉንና የመስዋዕት ስርዓቱን የሰጣቸው ለሐጢያቶቻቸውና ለበደሎቻቸው ስርየትን ያገኙ ዘንድ ነው፡፡ እርሱ የሙሴ ታላቅ ወንድም የነበረውን አሮንን ሊቀ ካህን አድርጎ በመሾም የእስራኤሎች ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ ይነጹ ዘንድ የስርየት ቀን በሆነው በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የስርየትን መስዋዕት እንዲያቀርብ አደረገው፡፡ (ዘሌዋውያን 16)
እግዚአብሄር በስርየት ቀን የሚቀርበው መስዋዕት በአሮንና በእርሱ ዘሮች መካከል ባሉ የእርሱ ምትክ ሊቀ ካህናት ብቻ እንዲቀርቡ ግልጽ አድርጎዋል፡፡ እግዚአብሄር እስራኤሎች አሮን በሚለቀቀው ፍየል ራስ ላይ በሚጭናቸው እጆቹ አማካይነት ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ እንዲያስተሰርዩ መንገድን ከፈተላቸው፡፡ እግዚአብሄር የመሰረተላቸው የስርየት ሕግ ነው፡፡
በዚህ ጥላ ኢየሱስ የሰው አዳኝ እንደነበር በግልጽ እንዲታወቅ አደረገ፡፡ እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳን ዘመን የአሮን ዘር፤ (1ኛ ዜና 24፡10፤ሉቃስ 1፡5) የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ሊቀ ካህን (ማቴዎስ 11፡1-13) የሆነውን አጥማቂውን ዮሐንስን ላከው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ እግዚአብሄር የላከው ነቢይ፣ የሰው ዘር ወኪልና ሊቀ ካህን በመሆኑ ሐጢያተኞችን ለማዳን በመጣው በእግዚአብሄር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለማስተላለፍ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡
ሰዎች ሁሉ በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት ሐጢያቶቻቸውን ወደ ኢየሱስ ማስተላለፍ በመቻላቸው በእርግጥም ተባርከዋል፡፡ የዮሐንስ ሚና የሰውን ዘር የወከለ ሊቀ ካህንና ሐጢያቶችን ሁሉ ወደ ኢየሱስ ያስተላለፈ የእግዚአብሄር አገልጋይ መሆን ነበር፡፡
አጥማቂው ዮሐንስ በእግዚአብሄር የተላከ የሰው ዘር ወኪልና ሊቀ ካህኑ ከኢየሱስ 6 ወር በፊት ቀድሞ የተላከም መልዕክተኛ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ዮሐንስ የዓለምን ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ ያስተላለፈ የመጨረሻው ሊቀ ካህን ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ የእግዚአብሄር ባርያ ነበር፡፡
- Vor
1-32. Wenn wir sagen, dass Jesus bereits alle unsere Sünden der Vergangenheit, der Gegenwart und der Zukunft gemäß Ihrer Behauptung beseitigt hat, wie würde sich dann die Zukunft einer Person gestalten, wenn sie ständig Sünden begeht, indem sie daran denkt, dass ihr ihre Sünden bereits durch den Glauben an die Taufe und das Kreuz Jesu vergeben wurden? Selbst wenn dieser Mensch einen anderen Menschen tötet, wird er denken, dass er selbst für diese Art von Sünde durch Jesus am Kreuz gesühnt worden ist. Daher wird er weiterhin ohne zu zögern sündigen, indem er einfach glaubt, dass Jesus bereits auch die Sünden beseitigt hat, die er in der Zukunft begehen wird. Bitte erklären Sie mir diese Dinge.