• 所有新生命宣教會 The New Life Mission 網站上的電子書和有聲書均可免費下載
  • 探索以多種語言提供的全球性講道
  • 查看我們已翻譯成27種語言的網站
  • 第1、2卷新修訂版已全新推出
Search

關於基督教信仰的常見問題解答

話題 1:重生於水和聖靈

1-8. ሐጢያቶቻችንን መናዘዝ እንዲጠፉ ሊያደርጋቸው ይችላልን? 

አይችልም፡፡ ሐጢያቶች በኑዛዜ አይወገዱም፡፡ የሚወገዱት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እምነት ነው፡፡ ከሐጢያቶቻችን ባነጻን በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ስናምን ብቻ ነው፡፡ በዮርዳኖስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ያነጻው የኢየሱስ መንፈሳዊ ደህንነት ወንጌል ይህ ነው፡፡  
የሐጢያቶች ኑዛዜ አንድ ሰው የእግዚአብሄርን ሕግ የሚያውቅበት ብቸኛው መረጃ ነው፡፡ ነገር ግን ቤዛነት ሊሰጠን የሚችለው በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል ስናምን ብቻ ነው፡፡
እርሱ የተጠመቀበት ውሃና የኢየሱስ ደም ሰዎችን ሁሉ ከሐጢያት ያዳነ የሰማይ እውነት ነው፡፡ ደህንነታችን የተመሰረተው ኢየሱስ የሰዎችን ሁሉ ሐጢያት እንደወሰደ በማመን ላይ እንጂ በሐጢያቶች ኑዛዜ ላይ አይደለም፡፡ የኢየሱስ ስቅለት ከእኛ ከሐጢያተኞች ለወሰዳቸው ለእነዚያ ሐጢያቶች በሙሉ የተቀበለው ቅጣት ነው፡፡  
ስለዚህ እውነተኛው ደህንነታችን ያለው በዮርዳኖስ በሆነው ጥምቀትና በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ላይ ነው፡፡ እኛ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ የነጻነው ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ባነጻው በኢየሱስ በማመናችን ነው፡፡     
ሐጢያቶቻችንን በመናዘዝ መዳን እንደምንችል የሚሰብኩ ሰዎች የእግዚአብሄርን ደህንነት የማያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡ 
ስለዚህ የእግዚአብሄር ደህንነት በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማመን አለብን፡፡ መቼም ቢሆን የሰው ዘር ሐጢያቶች እነርሱን ለእግዚአብሄር በመናዘዝ ይቅር ሊባሉ ይችላሉ አትበሉ፡፡ 
ሐጢያቶቻችን ሲዖል እንዳስቀመጡን እወቁ፡፡ ነገር ግን ባዳነንና በእግዚአብሄር ፊት ጻድቃን ባደረገን በኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ማመናችን ሐጢያቶቻችንን ማስወገድ ይችላል፡፡ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡ ሁላችንም በአንድ ጊዜ ከሐጢያቶቻችን የነጻነው የውሃውንና የደሙን የእውነት ቃሎች በማመናችን መሆኑን እንወቅ፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡4-8)   
በተናዘዝን ጊዜ ሁሉ ሐጢያቶቻችንን አይደመስሱም፡፡ በኑዛዜ ላይ በመደገፍ ሙጭጭ የምትሉ ከሆነ መጨረሻችሁ ሲዖል ይሆናል፡፡ በልባችን ውስጥ ያሉት ሐጢያቶች ይነጹ ዘንድ በእውነተኛው ወንጌል እንመን፡፡ በጭንቅላታችሁ ብቻ ሳይሆን በልባችሁም እመኑ፡፡ ለዘላለምም ከሐጢያቶቻችሁ ነጻ ሁኑ፡፡  
The New Life Mission

參加我們的調查

您是如何得知我們的?