Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 8፡ መንፈስ ቅዱስ

[8-2] ማንም ሰው በግል ጥረቱ መንፈስ ቅዱስን ሊገዛ ይችላልን? ‹‹ የሐዋርያት ሥራ 8፡14-24 ››

ማንም ሰው በግል ጥረቱ መንፈስ ቅዱስን ሊገዛ ይችላልን?
‹‹ የሐዋርያት ሥራ 8፡14-24 ››  
‹‹በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው፡፡ እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስን ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና፡፡ በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ፡፡ ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና፡- እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ፡፡ ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፡- የእግዚአብሄርን ስጦታ በገንዘብ ልታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ፤ ልብህ በእግዚአብሄር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም፡፡ እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንስሐ ግባ፤ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደሆነ ወደ እግዚአብሄር ለምን፤ በመራራ መርዝና በዓመጽ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና፡፡ ሲሞንም መልሶ፡- ካላችሁት አንዳች እንዳይደርስብኝ እናንተው ወደ ጌታ ለምኑልኝ አላቸው፡፡››   
 

ሰው እጆችን በመጫን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን ሊቀበል ይችላልን?
አይችልም፡፡ እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለበት፡፡
 
በዋናው ምንባብ ላይ በመመርኮዝ ‹‹አንድ ሰው በራሱ ጥረት መንፈስ ቅዱስን ማግኘት ስለመቻሉ›› መልዕክት ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያት ከእግዚአብሄር ሐይልን በመቀበል ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተልከው ነበር፡፡ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ በርካታ መለኮታዊ ክስተቶች ተከናውነዋል፡፡ ከእነዚህ አንዱ ሐዋርያት እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ በጫኑባቸው ጊዜ በምዕመናን ላይ መንፈስ ቅዱስ መውረዱ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስን ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና፡፡ በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ፡፡››
ታዲያ እጆችን በመጫን አማካይነት እንዴት መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ? በዚያን ወቅት የእግዚአብሄር ቃሎች ገና በመጻፍ ላይ ነበሩ፤ ስራውም ገና አልተጠናቀቀም ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር የእርሱን ተልዕኮ እንዲያከናውኑ ለሐዋርያት ልዩ ሐይሎችን ሰጣቸው፡፡ እርሱ ከሐዋርያቱ ጋር ስለነበረም በእነርሱ በኩል ብዙ ተዓምራትንና ድንቆችን አደረገ፡፡ ይህ ጊዜ እግዚአብሄር ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅና መድህን መሆኑን ያምኑ ዘንድ በሰው አይን ሊታዩ የሚችሉ ድንቆችና ተዓምራቶች ያደረገበት ልዩ ጊዜ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ከሐዋርያት ጋር በመተባበር ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና መድህን የሆነ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ለማረጋገጥ የመንፈስ ቅዱስን ስራ በሐይል ማሳየት የሚያስፈልግበት ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን በተዓምራቶችና በድንቆች ባይሰራ ኖሮ ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ማንም አያምንም ነበር፡፡
ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የተጠናቀቀ በመሆኑ ዛሬ እኛ መንፈስ ቅዱስን በሚታዩ ድንቆችና ተዓምራቶች በኩል መቀበል አያስፈልገንም፡፡ በፈንታው አሁን በውስጥ የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ ያረፈው እምነት ላይ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የእውነትን ወንጌል በማመን ነው፡፡ እግዚአብሄር በውስጣቸው የሚያድረውን መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው በእግዚአብሄር ፊት በእውነት ወንጌል ላይ እምነት ላላቸው  ብቻ ነው፡፡ በውስጥ የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ የሚከሰተው በኢየሱስ ወደዚህ አለም መምጣት፤ በጥምቀቱና በደሙ የተፈጸሙትን የእግዚአብሄር ቃሎች ለሚያምኑት ነው፡፡
በዚህ ዘመን ብዙ መጋቢዎች የሚታዩ ተአምራቶች ክስተት የመንፈስ ቅዱስ ዘለቄታዊ መገኘት ምልክቶች ናቸው ብለው ምዕመናኖቻቸውን ያስተምራሉ፡፡ በዚያው መንገድም መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ይመሩዋቸዋል፡፡ በልሳን መናገር የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ምልክት ነው የሚሉ የሐሰት ትምህርቶችን በማስተማርም ሰዎችን ያስታሉ፡፡ እነዚህ መጋቢዎች ራሳቸውን ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች የሚያደርጉ ሐዋርያት አድርገው ይቆጥራሉ፤ እግዚአብሄርን በስሜቶቻቸው አማካይነት ለመለማመድ የሚፈልጉ የሐይማኖት አክራሪዎችን ትኩረት ይስባሉ፡፡      
ይህ አክራሪነት በመላው አለም ወደ ክርስቲያኖች ተሰራጭቷል፡፡ እነርሱ ብዙዎቹም የእነርሱን አመኔታዎች በመከተል ከልዕለ ተፈጥሮ በላይ በሆኑ መንገዶች ክፉ መናፍስቶችን ተቀብለዋል፡፡ አሁንም እንኳን በሐይማኖታዊ አክራሪነት ተጽዕኖ ስር የወደቁ ሰዎች በእጆች መጫን አማካይነት ሌሎችም መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ማድረግ እንደሚችሉ ያስባሉ፡፡
ሆኖም እነዚህ እንደ ሲሞን የተወናበዱ ሰዎች በምንባቡ ዋና ክፍል ላይ የተጠቀሰውን ጠንቋይ ይመስላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በራስ ወዳድነትና በቁሳዊ ስግብግብነት የተሞሉ ናቸው፡፡ ተግባሮቻቸው በሰዎች መካከል የሚፈጥሩት ነገር ውዥንብር ብቻ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የሐሰት ትምህርት በእግዚአብሄር ፊት ለዘለቄታ የሚኖረውን መንፈስ ቅዱስ ከመቀበያው እውነተኛ መንገድ ያፈነገጠ ነው፡፡
ዛሬም የመንፈስ ቅዱስን ስራ እየሰራን ነው በማለት እያስመሰሉ በተሳሳተው ሐይማኖታዊ ምግባሮቻቸው አማካይነት የሰይጣንን ሥራ የሚሰሩ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያቶች አሉ፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች በውስጣቸው የሚያድረውን መንፈስ ቅዱስ ይቀበሉ ዘንድ እውቀትን ከሚሰጣቸው የእግዚአብሄር ቃል ጋር መጣበቅ አለባቸው፡፡ በሥጋ ልምምዶች በሚገለጠው መንፈስ ቅዱስ ላይ ብዙ ትኩረት የሚያደርጉ ጴንጤ ቆስጤያውያን ተብዬዎች የማይመስሉ እምነቶቻቸውን ትተው ወደ እግዚአብሄር ቃሎች በመመለስ መንፈስ ቅዱስን ወደ መቀበል በሚመራቸው እርግጠኛ እውነት ማመን አለባቸው፡፡
ሲሞን በወቅቱ በሰማርያ ታዋቂ ጠንቋይ ነበር፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለሰዎች መንፈስ ቅዱስን ሲሰጡ ሲመለከት መንፈስ ቅዱስን በገንዘብ ለመግዛት አሰበ፡፡ የዚህን አይነት እምነት ያላቸው ሰዎች የእርሱን ስራ ለመስራት የሚጠቀምባቸው የሰይጣን ባርያዎች ሆነዋል፡፡ ሲሞን መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት ፈልጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ፍላጎቱ ከስግብግብነት የዘለለ አልነበረም፡፡ የዚህ አይነቱ እምነት መንፈስን የመቀበያ እምነት እንዳልሆነ ማየት እንችላለን፡፡
ሲሞን መንፈስ ቅዱስን በገንዘብ ለመግዛት የሞከረው ሐይሉን ለማግኘት በራስ ወዳድነት ስለናፈቀ ብቻ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ የእግዚአብሄር ባርያ የሆነው ጴጥሮስ አጥብቆ ወቀሰው፡፡ ምንም እንኳን ሲሞን በኢየሱስ እንዳመነ ቢናገርም እርሱ በሐጢያት ስርየት አማካይነት መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ሰው አልነበረም፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ ለእግዚአብሄር አለማዊ ነገሮችን በመስጠት መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚቻል አሰበ፡፡ 
ውጫዊ ገጽታዎቹ በኢየሱስ የሚያምን አማኝ እንደነበር የጠቆመ ቢሆንም እውነተኛ ውስጣዊ አስተሳሰቦቹ ከኢየሱስ ቃሎች ጋር የተዛመዱ አልነበሩም፡፡ በፈንታው በቁሳዊ ስግብግብነት የተሞላ ነበር፡፡ የሲሞንን አስተሳሰቦች ያወቀው ጴጥሮስ የእግዚአብሄር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስ በገንዘብ ለመግዛት በመሞከሩ ወቀሰው፡፡ ጴጥሮስ ለሲሞን ከገንዘቡ ጋር አብሮ ሊጠፋ እንደሚችልም ነግሮታል፡፡ 
ዛሬም በክፉ መናፍስቶች የተያዙ ሐሰተኛ ነቢያት ተዓምራቶችና ድንቆች ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ስራዎች መሆናቸውን እንዲያስቡ በማድረግ ሰዎችን ለማሳት ይሻሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ የዚህ አይነቱን ሐይል የሚያደንቁና መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በትጋት የሚጸልዩ ሰዎችን እናያለን፡፡ ሆኖም ማንም ሰው ከአለማዊ ስስቱ በመነጩ ልመናዎች አማካይነት መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደማይችል ማሰብ ይኖርበታል፡፡    
እንዲያው በአጋጣሚ በጸጋ ስጦታ የሚያምኑ ሰዎች በዙሪያችሁ አላጋጠሙዋችሁምን? ከእንደ እነዚህ አይነት ሰዎች መጠንቀቅ ይኖርባችኋል፡፡ ሌሎችን አክራሪ በሆነ እምነት ይቀርቡዋቸዋል፤ አጋንንትን ማውጣት እንደሚችሉና በእጆች መጫን አማካይነትም ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ እንደሚያደርጉዋቸው ይናገራሉ፡፡ ሆኖም እነርሱ የያዙት ሐይል ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ ሐይል ሳይሆን ከክፉ መናፍስቶች የመጣ ሐይል ነው፡፡ በእጆች መጫን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ የሚናገሩ ራሳቸውንም ሌሎችንም ክፉ መናፍስቶችን እንዲቀበሉ ይነዳሉ፡፡
እውነተኛው ዘለቄታዊ የመንፈስ ቅዱስ መኖር ሊመጣ የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ቃል በሚያምኑት ላይ ብቻ ነው፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡3-7) የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ ቢሆንም ብዙ ሰዎች በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት ስላለባቸው እግዚአብሄርን ከልዕለ ተፈጥሮ በላይ በሆኑ ሐይሎችና በራዕይ እንደ መወሰድ፣ በልሳን እንደ መናገር፣ ወደ ሰማይ እንደመነጠቅና አጋንንቶችን እንደ ማስወጣት ባሉ ልምምዶች አማካይነት ወደ እግዚአብሄር ለመድረስ ይሞክራሉ፡፡ ሐሰተኛ ነቢያት ከዲያብሎስ ተጨምቆ በወጣ ባዕድ አምልኮአዊ ክርስትና እንዲያምኑ ብዙ ሰዎችን ማሳት የቻሉት ለዚህ ነው፡፡ 
ጴጥሮስ ሲሞንን እንዲህ በማለት ገሰጸው፡- ‹‹የእግዚአብሄርን ስጦታ በገንዘብ ልታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ፤ ልብህ በእግዚአብሄር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም፡፡ እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንስሐ ግባ፤ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደሆነ ወደ እግዚአብሄር ለምን፤ በመራራ መርዝና በዓመጽ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና፡፡›› በዚህ ዘመን ይህንን የመሰሉ ብዙ አገልጋዮች መኖራቸውን በማወቃችን ልናዝን ይገባናል፡፡ አብዛኞቹ በጸጋ ስጦታ የሚያምኑ ሰዎች ከመንጎቻቸው ገንዘብን ይጠይቃሉ፡፡ ከእንደዚህ አይነቱ እምነት ሸሽተን በእውነተኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን መንፈስ ቅዱስን ማመን ይኖርብናል፡፡ (ማቴዎስ 3፡15፤1ኛ ጴጥሮስ 3፡21፤ ዮሐንስ 1፡29፤ ዮሐንስ 19፡21-23)  
 
 

የካራዝማቲክ ሰዎች እጆችን በመጫን ይሰራሉ!

 
ከዚህ አይነት እምነት ራሳችንን መጠበቅ አለብን፡፡ በዚህ ዘመን አንዳንድ ሰዎች ሐይልን የተቀበሉ ሰዎች እጆቻቸውን ቢጭኑባቸው መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሐዋርያቶች እጆቻቸውን በጫኑባቸው ጊዜ ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ ስለሚናገር እነርሱም ይህንኑ ማድረግ እንደሚችሉ ያስባሉ፡፡ አንዳንድ አስመሳዮችም እጆቻቸውን በመጫን ለሰዎች ዘለቄታውን መንፈስ ቅዱስን መስጠት እንደሚችሉ የሚያምነውን ከንቱ እምነት ይዘዋል፡፡ የዚህ አይነት ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አለብን፡፡   
ሆኖም እምነታቸው በጥንቷ ቤተክርስቲያን ከነበረው የሐዋርያት እምነት እጅጉን የተለየ እንደሆነ ማወቅ አለባችሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለአንዳንድ ክርስቲያኖች አመኔታዎች እጅግ ከባዱ ተግዳሮት በእውነተኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ላይ እምነት የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እነርሱ በእግዚአብሄር እናምናለን ይላሉ፤ ነገር ግን ክብርን አይሰጡትም፡፡ በፈንታው ራሳቸውንና ሌሎችን ያስታሉ፡፡ ሐጢያተኛ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበልም ሆነ ሌሎች እንዲቀበሉ ሊያደርግ አይችልም፡፡ መንፈስ በሐጢያተኛ ላይ እንደወረደ የሚናገር ሰው ካለ ይህ መንፈስ በእርግጥም መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን እውነተኛውን መንፈስ ተመስሎ የመጣ የሰይጣን መንፈስ ነው፡፡   
በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን የነበሩት ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደ መድህን እንደነበር ያውቁና ያምኑ ነበር፡፡ እነርሱ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የቻሉት በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ እውነት ስላመኑ ነበር፡፡ እነርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሌሎች በመስበክ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ረድተዋቸዋል፡፡
በዚህ ዘመን ግን ብዙ ክርስቲያኖች አክራሪ የሆኑ እምነቶችን ይዘዋል፡፡ በዚህ ዘመን ሐጢያተኛ በሌላ ሐጢያተኛ አገልጋይ እጆች ተጭነውለት መንፈስ ቅዱስን ሊቀበል ይችላልን? ይህ ፈጽሞ ስሜት የማይሰጥ ነው፡፡ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ቢኖርም መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ የሚናገሩ ሰዎች አሉ፡፡ አንድ ሰው በእነዚህ ምዕመናን አይኖች ፊት ጥሩ እረኛ መስሎ ቢታይም በልቡ ውስጥ ሐጢያት ካለ ማንም ሰው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ እንዲቀበል ሊያደርገው አይችልም፡፡  
ሆኖም የዚህን አይነት የተሳሳተ እምነት ያላቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያትም የሚፈልጉትን ያህል ሰው ወደ ገሃነም ለመምራት የቻሉት በዚህ የተነሳ ነው፡፡ የዚህን አይነት እምነት የሚያስተምሩ ሰዎች የሐሰት ነቢያት መሆናቸውን ማወቅ አለባችሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በክፉ መናፍስት የተያዙ ናቸው፡፡  
አንድ ሰው በውስጡ ሐጢያት ካለበት መንፈስ ቅዱስ በዚህ ሰው ውስጥ ሊኖር ይችላልን? መልሱ አይችልም ነው፡፡ በውስጡ ሐጢያት ያለበት ሰውስ ሌሎች መንፈስ ቅዱስን ያገኙ ዘንድ መርዳት ይችላልን? ታዲያ በዚህ ዘመን በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸው የካራዝማቲክ ሰዎች በክርስትና ውስጥ ተዓምራትንና ድንቆችን እንዲያደርጉ ያደረጋቸው ምንድነው? እንዲህ የሚያደርጉት ክፉ መናፍስቶች ናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐጢያተኛ ልብ ውስጥ መቼም ቢሆን ሊኖር አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚኖረው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑት ሰዎች ልብ ውስጥ ነው፡፡ በእናንተ ውስጥ ያለው መንፈስ ትክክለኛው መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ እርግጠኞች ናችሁን? 
በዮሐንስ 3፡5 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡›› ስለዚህ እውነተኛው ዘለቄታዊ መንፈስ ቅዱስ ሊገኝ የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖች የሚሰሩት ስህተት ሰው ሐጢያተኛ አገልጋዮች እጆቻቸውን በሚጭኑበት ጊዜ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል ብለው ማመናቸው ነው፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖችና አገልጋዮች እጆችን በመጫን መንፈስ ቅዱስን ማግኘት ይቻላል የሚል እምነትና አመኔታ አላቸው፡፡
 
 

በእውነተኛው የሐጢያት ስርየትና እጆችን በመጫን መካከል ያለው ግንኙነት

 
‹‹እጆችን መጫን›› ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ መንገድ አስቡት፡-  በማይክራፎን ውስጥ ስንናገር ድምጹ በገመዶቹ ውስጥ ተጉዞ ወደ አምፕሊፋየሩ ይገባና እያንዳንዱ ሰው ሊሰማው እንዲችል ከስፒከሮቹ ይወጣል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በብሉይ ኪዳን  አንድ ሐጢያተኛ እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ በሚጭንበት ጊዜ ሐጢያቱ በሙሉ ወደ ፍየሉ ስለሚተላለፍ ሐጢያቱ ይቅር ይባልለታል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የእርሱ አገልጋዮች እጆቻቸውን በእነርሱ ላይ በሚጭኑ ጊዜ የእግዚአብሄር ሐይል ወደ ሕዝቡ ይተላለፋል፡፡ በዚህ መንገድ እጆችን መጫን ‹‹ማስተላለፍ ወይም ማሻገር›› የሚለውን ትርጉም ወስዶዋል፡፡ የካራዝማቲክ ሰዎች በእጆች መጫን አማካይነት ሰዎች ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ አያደርጉም፡፡ በፈንታው ክፉ መናፍስቶችን እንዲቀበሉ ያደርጋሉ፡፡ የክፉ መናፍስቶች ሐይል ያለው ሰው በእጆች መጫን አማካይነት መናፍስቶችን ማሻገር እንደሚችል ማስታወስ ይኖርባችኋል፡፡ አጋንንት ያደረበት ሰው እጆቹን በሌላው ሰው ላይ ሲጭን በእርሱ ውስጥ ያለው አጋንንት ወደዚያ ሰው ይተላለፋል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣን በሐጢያተኞች በኩል ይሰራልና፡፡ ከዚህ የተነሳ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ከፈለገ እያንዳንዱ ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለበት፡፡ ሰይጣን በኢየሱስ ቢያምኑም የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ካላገኙ በሐጢያት ውስጥ ባሉት ላይ ይሰለጥናል፡፡ 
አንድ ሰው በአጋንንት ከተያዘ ሰው እጆችን በመጫን ስርዓት መንፈስን ከተቀበለ ይህ ሰው አጋንንቶች ይገቡበትና እርሱም ደግሞ ሐሰተኛ ተዓምራቶችን ያደርጋል፡፡ አጋንንቶች እጆችን በመጫን በሌሎች ውስጥ ሊኖሩ እንደሚመጡና ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል የሚቻለውም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡
እጆችን የመጫን ዘዴ አንድን ነገር ወደ ሌላው ለማስተላለለፍ በእግዚአብሄር የተደነገገ ዘዴ ነው፡፡ ሰይጣን ግን በእጆችን መጫን አማካይነት ብዙ ሰዎች ክፉ መናፍስትን እንዲቀበሉ ያደርጋል፡፡፡ በዚህ ዘመን መንፈስ ቅዱስን በገንዘብ ለመግዛት የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር መበራከቱም ሌላው ትልቅ ችግር ነው፡፡
 
 

ብዙ ክርስቲያኖች ዘለቄታውን መንፈስ ቅዱስ እውነት በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል 

 
ብዙ ሰዎች ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን የሚቀበሉት እንዴት እንደሆነ ሲጠየቁ የሚመልሱት በትጋት በመጸለይ ወይም በፆም እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ይህ እውነት አይደለም፡፡ ለእግዚአብሄር ልዩ ጸሎት በማድረጋችሁ መንፈስ ቅዱስ ይወርድባችኋልን? አይወርድባችሁም፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የሚወርድባቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑት ብቻ ናቸው፡፡ 
እግዚአብሄር እውነት ስለሆነ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ሕግ ደንግጎዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ሐጢያት ባለበት ሰው ውስጥ ሊኖር ይችላልን? መልሱ በፍጹም አይችልም ነው፡፡ ሰው እጆችን በመጫን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችልም፡፡ አንድ ሰው በመነቃቃት ስብሰባዎች ላይ ቢገኝና የመንፈስ ቅዱስን ሐይል ለመቀበል ወደ እግዚአብሄር ቢቃትት መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችልም፡፡ ሐጢያተኞች ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ  መቀበል እንደማይችሉ ግልጽ ነው፡፡ ሐጢያተኞች ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ እንደ ስጦታ መቀበል የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምነው የሐጢያትን ስርየት ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማያውቅ ማንኛውም ሰው ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችልም፡፡ በዚህ ዘመን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በክርስቲያን ጽሁፍ፣ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች፣ በበይነ መረብ (ኢንተርኔት) እና በኤሌክትሮኒክ መጽሐፎች አማካይነት በመላው አለም በፍጥነት እየተሰራጨ ነው፡፡ ስለዚህ እውነተኛውን ወንጌል የሚሻ ማንኛውም ሰው በዚህ ወንጌል አምኖ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበል ይችላል፡፡ ገና መንፈስ ቅዱስን ካልተቀበላችሁ ይህንን ለማድረግ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን እንዳለባችሁ መገንዘብ ያስፈልጋችኋል፡፡
 
 
የሐሰተኛ እምነት ቁልፍ ምሳሌ!
 
በዚህ ዘመን ሐሰተኛ መናፍስት የተቀበሉ ሰዎች የሚያሳዩዋቸውን ምልክቶች ስንመረምር አጋንንቶች በተጨባጭ እንዳሉ ማየት እንችላለን፡፡ ‹‹መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት የመነቃቃት ጉባኤ›› የሚባሉት ስብሰባዎች  መንፈስን ቅዱስን የሚፈልጉ ሰዎች የሞት ሽረት አድርገው የሚገኙባቸው ስብሰባዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ሰዎች እየፆሙና እየጸለዩ እጆቻቸውን ያጨበጭባሉ፡፡ የንስሐ ጸሎቶችንም ይጸልያሉ፡፡ ሰባኪውም ይህንን እስካላደረጉ ድረስ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ እንደማይወርድ እየነገራቸው ግብታዊ ጸሎቶችን እንዲጸልዩ ይነግራቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ሰዎች ‹‹አቤቱ!›› እያሉ በመጮህ ግብታዊ ጸሎቶቻቸውን ይጀምራሉ፡፡
እነዚህ ጥራዝ ነጠቆች በዚህ መንገድ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ማግኘት ይችላሉን? አይችሉም፡፡ እንደ እነዚህ ባሉ  ስብሰባዎች ላይ ሰዎች ሲንቀጠቀጡ፣ ያልተለመዱ ድምጾችን ሲፈጥሩና ሲወድቁ፣ በልሳንም ሲናገሩ ልትመለከቱ ትችላላችሁ፡፡ አንዳንዶችም እዚህና እዚያ መሬት ላይ ወድቀው ይንቀጠቀጣሉ፡፡ ሲጮሁና በልሳናት መናገር ሲጀምሩ እናያለን፡፡ አንድ ሰው ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚያልቅ ጊዜ ድረስ ጸጉሩን እየነጨ ይጮሃል፤ ሕዝቡም በስሜት ይናጣል፡፡ ከእነርሱ አንዳንዶቹ መንቀጥቀጥና በልሳናት መናገር ይጀምራሉ፡፡ ሰዎች እነዚህ ክስተቶች መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ለመውረዱ ማስረጃ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ይህንን ያደርጋልን? በፍጹም እንዲህ አያደርግም፡፡
 
 
ሰይጣን ብዙ ክርስቲያኖችን አታሎዋል
 
በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች ሰይጣን የሚፈልገውን ሐይማኖታዊ ሕይወት ይመራሉ፡፡ ሰይጣን መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ አንድ ብርቱ አገልጋይ እጆቹን ሊጭንባቸው እንደሚገባ በመንገር ሰዎችን እያሳተ ነው፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን እንደ መደበኛ የቤተክርስቲያን ትምህርት አድርገው ወደ መቀበሉ ያዘነብላሉ፡፡ ሰይጣን ከመጠን በላይ ቢጸልዩ መንፈስ ቅዱስን እንደሚቀበሉ በሰዎች አእምሮ ውስጥ አሳቦችን ተክሎዋል፡፡ ሰይጣን የዚህ አይነት እምነት ያላቸውን ሰዎች በሁለትና በሦስት ዕጥፍ ለማሳደግ እየሞከረ ነበር፡፡ 
ስለዚህ ብዙ ሰዎች ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል አያውቁም፡፡ ለመማርም አይፈልጉም፡፡ ሰይጣን በጭንቅላታችን ውስጥ ለመጨመር የሚፈልገውን ሃሳብ አሸንፈን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ወደ ማመን መምጣት አለብን፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑ ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ማመን ይገባችኋል፡፡
 
 
ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ ያላቸው የተሳሳቱ አስተሳሰቦች
 
በመጀመሪያ ደረጃ የካራስማቲክን ክርስትና የተቀበሉ ተከታዮች በሚያራምዱዋቸው እምነቶች ውስጥ ትልቅ የተሳሳተ ግንዛቤ አለ፡፡ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት እያለ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይሞክራሉ፡፡ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ቢኖርም መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚችሉ በተሳሳተ መንገድ ያምናሉ፡፡ ሆኖም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አንዳች እምነት የሌለው ሰው የመንፈስ ቅዱስን ሙላት መቀበል አይችልም፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የሰዎች ዕብሪት ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስን ከመቀበል እንደሚያግዳቸው ይነገራል፡፡ ታዲያ ይህ ማለት አንድ ሰው በዕብሪተኝነት ባይኮፈስ መንፈስ ቅዱስን መቀበል ይችላል ማለት ነውን? በዚህ ምድር ላይ ትንሽ እንኳን ዕብሪተኛ ያልሆነ ሰው አለን? እግዚአብሄር ይቅር የማይለው ዕብሪተኛ ሰው የራሱን አስተሳሰቦች በእግዚአብሄር ቃል ላይ የሚጨምረውን ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ቸል ብለው መንፈስ ቅዱስን በራሳቸው ዘዴዎች ለመቀበል ሞክረዋል፡፡ ሆኖም መንፈስ ቅዱስ የሚወርደው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑት ላይ ብቻ ነው፡፡  
ሶስተኛ መንፈስ ቅዱስ የሚወርደው አንድ ሰው ከልቡ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያቶቹን ሲናዘዝ እንደሆነ ተነግሮዋል፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን መቀበል ከፈለጉ ሐጢያቶቻቸውን እንዲናዘዙ ተመክረዋል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው እንዲያው ሐጢያቶቹን ስለተናዘዘ ብቻ መንፈስ ቅዱስ እንደማይወርድበት ማስታወስ አለባችሁ፡፡ በዚህ ዘመን አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስና ሙላቱን በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡ ነገር ግን በልቦቻቸው ውስጥ አሁንም ሐጢያት ስላለ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበሉ አይችሉም፡፡ የዚህ አይነት ድንገተኛ እምነት ያለው ሰው በአጋንንቶች ይያዛል፡፡
አራተኛ አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሄር በረከቱን እንዲሰጠን ከልባችን ብንለምነው መንፈስ ቅዱስን ይሰጠናል ይላሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ግን በልመና የሚገኝ አይደለም፡፡ ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡
አምስተኛ አንዳንዶች ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ መንፈሳዊ ሐይሎችን ከመያዝ ጋር ያመሳስሉታል፡፡ በልሳን መናገር ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ለመኖሩ የተለመደ ማስረጃ ሆኖ ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በኢየሱስ ስም አጋንንትን ስላስወጣ ወይም በልሳን ስለተናገረ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ውስጥ አያድርም፡፡ ሐጢያት የሰይጣን ነው፡፡ በልቡ ሐጢያት ያለበት ሰው አንዳንድ እንግዳ የሆኑ ሥልጣኖች ስላሉት ብቻ መንፈስ ቅዱስን ስለ መቀበሉ ሊናገር ይችላልን? በፍጹም አይችልም፡፡  
ኢየሱስ የሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ወደ መቀበል ሊመራን የሚችል ብቸኛው እውነተኛ ወንጌል ነው፡፡ አሁንም ድረስ መንፈስ ቅዱስንና የሐጢያቶች ስርየትን በሌሎች ዘዴዎች አማካይነት መቀበል እንደምትችሉ የምታስቡ ከሆነ በጣም ተታላችኋል፡፡ ከተሳሳቱት እምነቶቻችሁ ራሳችሁን ነጻ አድርጋችሁ ወደ መንፈሳዊ እሳቤዎችና እውነተኛ እምነት እንደምትመጡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡  
በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖች በክፉ መናፍስት ተይዘዋል ብሎ መናገር የተጋነነ ነገር አይደለም፡፡ በዚህ ዘመን ብዙ ክርስቲያኖች በክፉ መናፍስት ቁጥጥር ስር መውደቅ የቻሉት መንፈስ ቅዱስን በጸሎትና እጆችን በመጫን ዘዴ ማግኘት እንችላለን ብለው ከማሰባቸው የተነሳ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን አግኝተዋል ብለው ወደሚያስቡዋቸው የተወሰኑ ሰዎች ማለትም የጸሎት ቤቶች ሐላፊዎች፣ ከፍ ያሉ ዲያቆናቶች፣ አነቃቂዎች ወይም መጋቢዎች በመሄድ መንፈስ ቅዱስን ይሰጡዋቸው ዘንድ ይጠይቃሉ፡፡ በእጆች መጫን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን እንደሚቀበሉ ተስፋ በማድረግ ወደ እነርሱ ይሄዳሉ፡፡ ሆኖም ምንም ያህል በርትቶ በኢየሱስ ቢያምንም ማንም ሰው በዚህ አይነት እምነት ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር ከእግዚአብሄር ውጪ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መስጠት የሚችል ሌላ ማንም የለም፡፡  
ልክ እንደ ሲሞን በዚህ ዘመንም ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ለመግዛት ይፈልጋሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስን በወንጌል ሳይሆን በዓለማዊ ትምህርቶች በማመን ለማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ በመላው አለም ያሉ ብዙ ክርስቲያኖችም በዚህ እሳቤ ተይዘዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚወርድባቸው እርሱን ለመቀበል አስፈላጊ የሆኑትን መስፈርቶች ባሟሉት ላይ ብቻ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ብቸኛው ቀመር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ነው፡፡ ትክክለኛው የእውነት መልስም ይኸው ነው፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)   
በጥንቷ ቤተክርስቲያን እጆችን በመጫን መንፈስ ቅዱስን የማስተላለፉ ድርጊት የተከናወነው ለጥቂት ጊዜ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አውቀው ሲያምኑ በተመሳሳይ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ቃል በማመን ከሚሆነው የመንፈስ ቅዱስ ስራ ውጪ ሌላው ነገር ሁሉ የአጋንንቶች ስራ ነው፡፡ እግዚአብሄር አጋንንቶች የሰይጣን ባሮች መሆናቸውን ተናግሮዋል፡፡ ሰይጣን ደግሞ ሰዎች በኢየሱስ ቢያምኑም የሐጢያት ስርየትን እንዳያገኙ በማድረግ በኩል በብልሃት ሰርቷል፡፡ ሰይጣን በኢየሱስና በእጆች መጫን የሚያምኑ ከሆነ መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጣቸው በመናገር ሰዎችን ዋሽቶዋቸዋል፡፡ ሰይጣን በመላው አለም ግዛቱን ያስፋፋው በዚህ አይነቱ ማጭበርበሪያ ነው፡፡  
አሁን ደግሞ በአጋንንት የተያዙ ሰዎች የሚያሳዩዋቸውን ምልክቶች እናያለን፡፡ በመጀመሪያ በጠንቋይ ወይም ከመንፈስ ጋር በሚገናኝ ሰው አማካይነት በአጋንንት የተያዙ ሰዎች የሚያሳዩዋቸውን ምልክቶች ስንመረምር ራሳቸውን መቆጣጠር እስከማይችሉ እንደሚንቀጠቀጡ፣ እንደሚፈዙና ራሳቸውንም እንደሚስቱ እንመለከታለን፡፡ ከዚያም ምላሶቻቸው ይተሳሰሩና ከአንደበታቸው ያለ ፈቃዳቸው እንግዳ የሆኑ ቃሎች ይወጣሉ፡፡ እንግዳ በሆኑ ልሳኖች ይናገራሉ፡፡ 
በእጆች መጫን አማካይነት በአጋንንት የተያዙ ጠንቋዮችና ክርስቲያኖች ሁለቱም የዚህ ልምምድ ባለቤቶች ናቸው፡፡ አንድ የካራዝማቲክ የመነቃቃት መሪ ድምጽ ማጉያውን ይዞ ‹‹ከእሳት ጋር፣ ከእሳት ጋር፣ ከእሳት ጋር›› እያለ ሲጮህ ጉባኤው ከመጠን በላይ ስለሚነቃቃ ራሱን መቆጣጠር አይችልም፡፡ ሰዎች እጆቹን እንዲጭንባቸው ወደፊት ይመጣሉ፡፡ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ እንቅጥቃጤ ይገጥማቸዋል፡፡ በልሳንም ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ምልክቶች የመንፈስ ቅዱስን ስራ እየሰሩ መሆናቸውን የሚያስመስሉ የአጋንንቶች ስራ ናቸው፡፡
በእያንዳንዱ ጥንታዊ ሐይማኖት ውስጥ ባሉ መንፈሳዊ መሪዎችና ጠንቋዮች በተጠሩ ክፉ መናፍስት የተያዙ ሰዎች በእጆች መጫን አማካይነት በአጋንንቶች የተያዙ ክርስቲያኖች የሚያሳዩትን ተመሳሳይ ምልክቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች የዚህ አይነት መረጃ እያላቸውም ይህንን በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል፡፡ እነዚያ ክርስቲያኖች ጥልቅ ውዥንብር ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ምክንያቱም የዚህ አይነት ምልክቶች እየታዩባቸው መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ ያስባሉና፡፡ 
 
 
ሰይጣን ልክ እንደ ጠንቋይ በክርስቲያኖች በኩልም ይሰራል
 
ሰይጣን በአጋንንት የተያዙ ሰዎች የትንቢት ጸሎቶች እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡ እንደዚህ በማለት ይተብያሉ፡- ‹‹የከበርህ መሪ ትሆናለህ፤ በፊትህ በሺህ የሚቆጠሩ በጎች ይመገባሉ፤ እግዚአብሄር ወደፊት አሰልጥኖህ የከበርህ መሪ አድርጎ ያወጣሃል፡፡›› ለሌሎች ደግሞ እንደዚህ ያሉ አሳሳች ቃላትን ይናገራሉ፡- ‹‹የከበርህ የእግዚአብሄር አገልጋይ ትሆናለህ፤ በጣም የከበርህ የእግዚአብሄር አገልጋይ ትሆናለህ፤ በጣም የተከበርህ የእግዚአብሄር ባርያ ትሆናለህ፡፡›› ይህንን የሚያደርጉት ሰዎች እነርሱን እንዲከተሉዋቸውና በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ የአጋንንቶች ባሮች ሆነው እንዲኖሩ ለማደፋፈር ነው፡፡  
ጠንቋዮችም ስለ ሰዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይተነብያሉ፡፡ ‹‹ወደፊት ስለምትጠጣው ውሃ መጠንቀቅ ይኖርብሃል›› ‹‹ብዙ ገንዘብ ታገኛለህ፡፡›› ‹‹ከምስራቅ የሚመጣ ዝነኛ ሰው ይረዳሃል፡፡›› እነዚህ ከሚናገሩዋቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በአጋንንት የተያዙ ሰዎች የሚያሳዩት የመጀመሪያው ምልክት ሐሰተኛ ትንቢቶችን መናገር ነው፡፡
ከዚያም ራሳቸው እንኳን ለመረዳት የማይችሉትን ልሳን ይናገራሉ፡፡ ይንቀጠቀጣሉ፤ ከባህሪያቸው ውጪ የሆኑ ነገሮችንም ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ከአንድ መንፈሳዊ መሪ ወይም ጠንቋይ ጋር ብትገናኙ ትክክለኛ ማንነት ሊኖረው ይችላል ብላችሁ ልታረጋግጡ ትችላላችሁን? እነርሱ በዕድሜ የሚበልጡዋቸውን ሰዎች እንኳን ሊሳደቡ ይችላሉ፡፡
ሆኖም ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ ማንጻቱን በሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያመኑ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ይቀበላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሌሎችም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዲያውቁና እንዲያምኑ የሐጢያቶቻቸውንም ስርየትና መንፈስ ቅዱስንም እንዲቀበሉ ያግዙዋቸዋል፡፡ እነርሱ ራሳቸው የጽድቅ ሕይወትን ለመኖር ይሞክራሉ፡፡ ማንነታቸውም ማራኪና ግሩም ስለሆነ ሌሎችን ወደተባረከው የእግዚአብሄር እምነትና እግዚአብሄር ወደሚሻው የሕይወት አይነት ይመራል፡፡ አንዳንዴ አእምሮዋቸው ወደ ዓለም በሚያዘነብልበት ጊዜ ቅዱሳን አድርጎ ሊጠብቃቸው እግዚአብሄር ይገስጻቸዋል፡፡ 
የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙ ጻድቃን ማንነታቸው በክፉ መናፍስቶች ከወደመባቸው ሰዎች በእርግጥም የተለዩ ናቸው፡፡ እውነተኛው ማንነት እንደገና ሕያው የሚሆነው የሐጢያቶችን ስርየት በማግኘትና በዚያውም መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ነው፡፡ በተጨማሪም ጻድቃን አመቺ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ለሆኑ ሰዎች በእግዚአብሄር ቃሎች ውስጥ በእርግጥም ስለሚያስፈልጋቸው ነገር በጣም ስለሚጨነቁ ነጻ እንዲወጡ ይጸልዩላቸዋል፡፡ እነርሱን ለመርዳትም በትክክል ከራስ የመነጩ መስዋዕቶችን ያቀርባሉ፡፡
በሌላ በኩል በአጋንንት የተያዙ ሰዎች ማንነት ክፉኛ የተበላሸ እንደሆነ ማየት እንችላለን፡፡ ሰይጣን ተቆጣጥሮዋቸዋል፡፡ ወደ ገዛ ፈቃዱም እንዲያዘነብሉ አድርጓቸዋል፡፡ ምክንያቱም እንደ መንቀጥቀጥና በልሳን እንደ መናገር ያሉ ነገሮች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እንደሆኑ ያስባሉና፡፡ ነገር ግን እነዚህ ልምምዶች ጨርሶ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አይደሉም፡፡    
በእግዚአብሄር ስም ትንቢቶችን መናገር፣ ብዙ ድንቆችን ማድረግ መቻልና በልሳን መናገር ሥልጣኖቻቸው የሚኩራሩ ብዙ አገልጋዮች አሉ፡፡ ነገር ግን አሁንም በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት ካለ ሥልጣኖቻቸው በአጋንንት የተያዙ ለመሆናቸው እውነተኛና አሳማኝ ማስረጃ ናቸው፡፡ ስለዚህ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለሌሎች አይሰጡም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉት የአጋንንቶችን መንፈስ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን አታላይ ስለሆነ እነርሱ ያደረጉዋቸው ተአምራቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ይጠፋሉ፡፡  
በመንፈስ ቅዱስ ስራና በአጋንንት ስራ መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ስራ በመጀመሪያ የተለዩ ልምምዶችን ወይም ድንቅ ስጦታዎችን የሚያቀርብ ባይመስልም ጊዜ እየነጎደ ሲሄድ የእግዚአብሄር ሐይል ልክ እንደ ጠዋት ጸሐይ በጻድቃን ልቦች ውስጥ ያለ ማቋረጥ እያደገ ይሄዳል፡፡
 
 
በአጋንንት የተያዙ ክርስቲያኖች
 
ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ቢሞክሩም በአጋንንት ቁጥጥር ስር የሚወድቁት ለምንድነው?ምክንያቱም በእጆች መጫን አማካይነት አጋንንትን ከሐሰተኛ ነቢያት ስለሚቀበሉ ነው፡፡ 
አካሎቻቸውና ነፍሶቻቸው የተበላሹ በኢየሱስ የሚያምኑ ብዙ ምዕመናን ማየት መቻላችን አስገራሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ሐሰተኛ ነቢያቶች እጆቻቸውን በጫኑባቸው ጊዜ አጋንንቶችን ተቀብለዋልና፡፡ እነዚህ ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም እምነታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ላይ የተመሰረተ አይደለምና፡፡ አገልግሎታቸው ብዙ ሰዎችን የሰይጣን አገልጋዮች እያደረገ እንደሆነ ሳያውቁ ስልጣናቸውን በትጋት ይጠቀማሉ፡፡ በክርስትና ውስጥ ሥልጣኖቻቸውን ለመተግበር በትጋት የሚሰሩት ለምንድነው? እነርሱ ያላቸው ሥልጣን ተብዬ ካልተጠቀሙበት በፍጥነት ይጠፋልና፡፡ በጣም ባተሌ የሚሆኑት ለዚህ ነው፡፡  
እነርሱ ያለ ማቋረጥ መጸለይና በኢየሱስ ስም ድንቆችንና ምልክቶችን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ‹‹እኔ ወንጌልን የመስበክ ስጦታ ተቀብያለሁ›› የሚሉ ሰዎች ያለ ማቋረጥ ወንጌልን መስበክ ይኖርባቸዋል፡፡ እንደዚያ ካላደረጉ አስመሳዩ ደስታቸው ፈጥኖ ይጠፋል፡፡ እነዚህ ሰዎች አጋንንት ለሚሰጡት በልሳን የመናገር፣ የፈውስ ወይም የትንቢት ስጦታዎች ታማኝ ካልሆኑ ማለትም ለሰይጣን ስራዎች ታማኝ ካልሆኑ ሰይጣን ያለ ምንም ምክንያት እንዲታመሙ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ነገሩ አንድ ጠንቋይ ወይም አስማተኛ የሰይጣን አገልጋይ የመሆኑን ሚና ቸል በሚልበት ጊዜ እንደሚገጥመው ጽኑ ሕመም ነው፡፡ ስልጣኖቻቸውን መጠቀም ከጨረሱ በኋላ በጉስቁልና ውስጥ እንዳይቀሩ ከሰይጣን የተቀበሉዋቸውን ስጦታዎች መጠቀም ያለባቸው ለዚህ ነው፡፡
በአንድ ወቅት በኢየሱስ ከሚያምንና ከእግዚአብሄር ዘንድ ብዙ ስጦታዎች እንደያዘ ተደርጎ ከሚታሰብ ብርቱ ምዕመን ጋር ተገናኘሁ፡፡ እርሱ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ሙላት እንዲቀበሉ በማደፋፈር እጆችን በመጫን አጋንንትን በሚያወጣባቸው የመነቃቃት ስብሰባዎች ላይ መሪ ነበር፡፡ በልሳን መናገርና ፈውስን የመሳሰሉ ድንቆችንም ያደርጋል፡፡ በሚሰራቸው ድንቅ ስራዎች የሚቀናበት የተከበረ ሰው ሆነ፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችም ነበሩት፡፡ ነገር ግን ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ወድቆዋል፡፡ እርሱ የእግዚአብሄር ልጅ አይደለም›› በማለት ወዲያው ኢየሱስን መካድ ጀመረ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ረገመው፡፡ እንዲያውም እርሱ ራሱ እግዚአብሄር እንደሆነ ተናገረ፡፡ በመጨረሻም ኢየሱስ ክርስቶስን በራሱ ልብና በብዙ ክርስቲያኖች ልብ ውስጥ ገደለው፡፡  
የዚህ አይነት ሰዎች መሪያቸው ሰይጣን ስለሆነ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አይቀበሉም፡፡ ከመጀመሪያውም የተሳሳተ እምነትን ተቀብለዋል፡፡ ምክንያቱም የእነርሱን ችሎታዎች ለማየት ሰዎችን በሌላ ልሳን እንዲናገሩ በማድረግ፣ በእጆች መጫን አማካይነትም አጋንንትን በማስወጣት ሐዋርያቶች የነበሩዋቸውን እነዚህን ስልጣኖች ይዘናል የሚል ምናብ አላቸውና፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ እንደወረደም አጥብቀው ያምናሉ፡፡
የንስሐ ጸሎቶችን በመጸለይ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚቻል በማሰብ መንፈስ ቅዱስን የመቀበያ ዘዴዎችን ለሰዎች ያሥተምራሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አይነቱ መንፈስ ቅዱስን የመቀበያ ዘዴ በእግዚአብሄር ቃሎች ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ነገሩ ይህ ሆኖ ሳለ በኢየሱስ የሚያምን ምዕመን በልሳን ከተናገረና ትንቢቶችን ከተነበየ ይህ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ለመውረዱ ማረጋገጫ ነው ይላሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በትክክል ስላልተረዱ የሐሰተኛ ነቢያትን ትምህርቶች በመማርና በመከተል መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ ሰይጣን ክርስቲያኖችን በአጋንንት መናፍስቶች መሙላትና በእነዚህ ሰዎች ላይ መንገስ የቻለው በዚህ መንገድ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ዘዴዎች የሰይጣን ወጥመዶች ናቸው፡፡ 
በርካታ ሰዎች ከሐሰተኛ ነቢያት ትምህርቶች የተነሳ በአጋንንቶች ተይዘዋል፡፡ ተራ ምዕመናን አሰልቺ የሆነ ሐይማኖታዊ ሕይወትን ይመራሉ፡፡ በአጋንንት የተያዙ ሰዎች ግን የክፉ መናፍስትን ሐይል ይጠቀማሉ፤ የጋለ ሐይማኖታዊ ኑሮ የሚኖሩም ይመስላሉ፡፡ የሚያሳዩዋቸው ልዩ ችሎታዎች ምንድናቸው? የፈውስ፣ በእንግዳ ልሳን የመናገር፣ በእጆች መጫን አማካይነት ሌሎችንም በአጋንንት እንዲያዙ የመምራት ችሎታዎች አሉዋቸው፡፡ እጆችን መጫን አንድን ነገር ወደ ሌሎች የማስተላለፍ ዘዴ እንደሆነ ማወቅ ይገባናል፡፡ በዚህ ዘዴ የአጋንንቶች መንግሥት በአያሌው ሰፍቷል፡፡ 
 
 
ክፉ መናፍስት የሰውን ስግብግብነት ይጠቀማሉ!
 
በዋናው ምንባብ ላይ እንዳነበብነው ሰይጣን እንደ ሲሞን ባሉ ሰዎች ውስጥ ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባያምኑም በእጆች መጫን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች በሰይጣን ተታለዋል፡፡ በንስሐ ጸሎቶች፣ በፆም፣ ራስን በመሰዋት ወይም በእጆች መጫን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን በአጋንንት ተይዘው የተረገመ ሕይወትን ይኖራሉ፡፡
የዛሬው ዘመን ክርስትና ‹‹እጆችን መጫን›› ተብሎ በሚጠራው በዚህ ዘዴ አማካይነት አጋንንቶች በእያንዳንዱ ነፍስ ውስጥ ስራዎችን እንዲሰሩ በማድረግ ረገድ አጋዥ እንደሆነ በሚገባ ማወቅ አለብን፡፡ እንደ ሲሞን አይነት ተመሳሳይ ባህርይ ያላቸው ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ሐሰተኛ ነቢያት ናቸው፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ምዕመናን እንኳን በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ካለባቸው በአጋንንቶች ሊያዙ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በዲያብሎስ አሰራር አማካይነት ተአምራቶችን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ሰይጣን በአጋንንቶች የመያዛቸውን ዕድል ለማመቻቸት ሲል ሰዎች ከባሮቹ የእጆችን መጫን እንዲቀበሉ ይመራቸውና በመላው አለም መንግስቱን ይገነባል፡፡ በዚህ ዘመን 2የካራዝማቲክ ጴንጤ ቆስጤ እንቅስቃሴ በመላው አለም መደበኛ የክርስቲያን የእምነት ድርጅቶች ሆኖ ዕውቅና አግኝቷል፡፡    
 
[2] የምዕራባውያን ክርስትና ከ20ኛው ክፈለ ዘመን አጋማሽ በኋላ በምድረ ገጽ ላይ ከፍተኛ ተቀባይነትና ያለውም ሐብት እየቀነሰ መጣ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜም ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ ይፈልጉ የነበሩ ብዙ ክርስቲያኖች በመውደቅ ላይ ከነበሩት ከእነዚህ ቤተክርስቲያናት ሊደሰቱ አልቻሉም፡፡ አንዳንዶቹ በራሳቸው ድክመት ወይም ደግሞ በዝግመታዊው የመንፈሳዊ ዕድገት ሲበሳጩ ለሎቹ ደግሞ እምነታቸውን ወደ እውነተኛው የጌታ ፍቅር ለመለወጥ በመቻላቸው ተሰላችተው ነበር፡፡
የጴንጤቆስጤ ካራዝማቲክ እንቅስቃሴ የተነሳው በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ነው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሞላቀቁ ሰዎች ግለት የተሞላባቸው ልምምዶችን ይሻሉ፤ በልሳን መናገርን ትንቢት መናገርን ተአምራቶችንና ድንቆችን መፈጸምን ይተገብራሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹን የጴንጤ ቆስጤ ሁነቶችንም ያደንቃሉ፡፡ በግለታቸው ውስጥ ሆነውም ራሳቸውን በፈቃደኝነት የመንፈስ ቅዱስ ግዛት ተብሎ ለሚጠራው ራሰቸውን በአደራ ይሰጣሉ፡፡ ነገር ግን በግልጽ እንነጋገር ከተባለ አብዛኞቹ አስተምህሮቶቻቸውና ምግባሮቻቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ አይደሉም፡፡
በማደግ ላይ ባለው አለም ይህ እንቅስቃሴ ከፍላጎቶቻቸው አገባብ አንጻር በእጅጉ አድጎዋል፡፡ መሪዎቻቸው በማደግ ላይ ባለው አለም ውስጥ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ከሐይማኖታዊ ግለት ጋር አዛምደው በሐብትና በጤና በረከቶች ስበዋቸዋል፡፡ እንደ ኒኦ-ጴንጤ ቆስጤያውያን ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ ያለው የተወሰነ ፍንገጣ እንቅስሴው የኒው ኤጅ እንቅስቃሴን ተመሳሳይ አስተምህሮቶች እንደሚጋራ ሪፖርት ተደርጎዋል፡፡
 
ይህ ዓለም ቀስ በቀስ ወደ ፍጻሜ እየተቃረበ ነው፡፡ በመጨረሻው ዘመን ዳግም መወለድ ከፈለግን ዲያብሎስ እንዴት እንደሚሰራ ማወቅና ዕቅዶቹን በጽናት መቋቋም አለብን፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻም ከሐጢያቶቻችን ድነን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምነን በስጦታ መልክ የቀረበውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል አለብን፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚወርድብን የሚገልጠውን ፍጹም እውቀት ይዘን ወደ እውነቱ መመለስ አለብን፡፡
እግዚአብሄር ‹‹ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል›› (ሆሴዕ 4፡6) እንዳለ ሁሉ በዚህ ዘመንም ብዙ እውነትን የሚፈልጉ ሰዎች በድንቁርናቸው የተነሳ የካራዝማቲክ ሰዎች ስላሳቱዋቸው ጠፍተዋል፡፡ የካራዝማቲክና የጴንጤ ቆስጤ ቤተክርስቲያኖች ተብለው የሚጠሩት በምድረ በዳ ላይ ቢመሰረቱ እንኳን ሰዎች ወደዚያ ይመጣሉ የሚሉ አሉ፡፡ ለምን እንደዚያ ይሆናል? የካራዝማቲክ ሰዎች ቤተክርስቲያኖቻቸውን የሚያስፋፉት ሌሎችን በአስመሳይ ሐይሎቻቸው በማወናበድና በእጆች መጫን አማካይነት በአጋንንት እንዲያዙ በመምራት ነው፡፡ ከልዩ ልዩ መክሊቶቻቸው አንዱ ሰዎች አንድ ጊዜ በእጆች መጫን አማካይነት በአጋንንቶች ከተያዙ ሐይማኖታዊ ሕይወትን ለመምራት የጋሉ መሆናቸው ነው፡፡
ሌላው የካራዝማቲክ ሰዎች ልዩ መለያ ለቤተክርስቲያኖቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ መለገሳቸውና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አክራሪ ምዕመናን መሆናቸው ነው፡፡ በርካታ ክርስቲያኖች በአጋንንት ሐይል የወንጌልን ስራ ለመስራት ይበረታሉ፡፡ ነገር ግን ፍጻሜያቸውን አያውቁም፡፡ ወደ ሲዖል መውረዳቸው የማይቀር ነው፡፡ የዲያብሎስ ሐይል የደህንነታቸው ማረጋገጫ እንደሆነ አድርገው የሚያምኑ እነዚህ ሰዎች ያለ አንዳች ጥርጣሬ ሰማይን አርቀው ይመለከታሉ፡፡ ነገር ግን በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት ስላለ ለጥፋት የተኮነኑ ናቸው፡፡  
እነዚህ ሰዎች ‹‹በእግዚአብሄር ብታምኑም በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት አለን?›› ተብለው ቢጠየቁ ያለ ምንም ጥርጥር መልሳቸው ሊሆን የሚችለው ከሐጢያት ጋር መኖር ተፈጥሮአዊ ነው የሚል ነው፡፡ አንድ ሰው በኢየሱስ ቢያምንም በልቡ ውስጥ ሐጢያት የማይኖርበት ሊሆን እንደማይችል ያስባሉ፡፡
ሰዎች በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ቢኖርም በኢየሱስ የሚያምኑ ስለሆኑ ብቻ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ለመግባት እንደሚችሉ አድርገው ያስባሉ፡፡ ምክንያቱም አስመሳይ የሐይል ማስረጃ ይዘው በኢየሱስ በማመናቸው ምቾት ይሰማቸዋልና፡፡ 
ይህ ምን አይነት የማይመስል ተስፋ ነው! ጽኑ የሆነው አመኔታቸው ምክንያቱ አንዳች አይነት ከልዕለ ተፈጥሮ በላይ የሆነ ችሎታ መያዛቸው ነው፡፡ እነርሱ በልሳን መናገርን፣ ራዕዮችን መቀበልን፣ ሕሙማንን መፈወስን ስለተለማመዱ እነዚህ ልምምዶች የመንፈስ ቅዱስ ስራ እንደሆኑ በማሰብ አጥብቀው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ በእነዚህ ልምምዶች አማካይነት በትክክል ቤዛነትንና መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ ለራሳቸው ይነግሩታል፡፡
እነዚህ ሰዎች ስለ ደህንነት ቃሎች ያላቸው ዕውቀት የተዛባ በመሆኑ አንዳች አይነት የሚታይ ችሎታ ካልተገለጠላቸው በመዳናቸው አይተማመኑም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች የሚታዩ የደህንነት ማረጋገጫዎች ለማግኘት አብዝተው ይሞክራሉ፡፡ በኋላም በእርሱ ስራ ውስጥ የሰይጣን መጠቀሚያዎች ሆነው ይቀራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ፋንታ የእግዚአብሄርን መልሶች በንስሐ ጸሎቶች ወይም ራስን በመሰዋት ለማግኘት ስለሚሞክሩ ውሎ አድሮ መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ፋንታ ክፉ መናፍስትን ይቀበላሉ፡፡
ዲያብሎስ ‹‹ሐጢያትን ሰርተሃል አልሰራህምን?›› ብሎ በጆሮዋቸው በማንሾካሾክ ሰዎችን ይከስና ራሳቸውን እንዲወቅሱ ያደርጋቸዋል፡፡ አሁን የሐጢያት ይቅርታንና መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ አንድ የማውቀው ሰው ነበር፡፡ ይህ ዳግም ከመወለዱ በፊት የጋለ ነገር ግን ግድየለሽ የሆነ የኢየሱስ ምዕመን በነበረ ጊዜ የገጠመው ነገር ነው፡፡ ይህ ሰው በልሳን ይናገር ነበር፡፡ ብዙ ተአምራቶችንም አድርጓል፡፡ በኢየሱስ እምነት እያለው ሌሊቱን በሙሉ ቢያለቅስና የንስሐ ጸሎቶችን ቢጸልይም በልቡ ውስጥ ያለው ሐጢያት እርሱን ማሰቃየቱን ቀጠለ፡፡ የሰይጣን ሹክሹክታ የጀመረው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ ‹‹ሐጢያት ሰርተሃል፤ ስለዚህ በሕይወት ከምትኖር መሞት ይሻልሃል፡፡›› ሰይጣን ሁሌም እየመጣ ሐጢያቶቹን በማስታወስ ይከሰውና ያሰቃየው ነበር፡፡ ሰይጣን ራሱን እንዲኮንንና በራሱ ላይ እንዲፈርድ መራው፡፡ ነገር ግን እርሱ ማድረግ የቻለው ነገር ቢኖር በልቡ ውስጥ ያሉትን ሐጢያቶች መናዘዝ ብቻ ነበር፡፡ ውብ የሆነውን ወንጌል ሰምቶ በእርሱ እስኪያምን ድረስ ራሱን ከሰይጣን ክስ ነጻ ማድረግ አልቻለም፡፡  
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ የዲያብሎስ ሰለባ እንደሚሆኑ ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡ የሐጢያቶችን ይቅርታ ያላገኘ ሰው ዲያብሎስን እምቢ ለማለት ሐይል ይኖረዋል ብላችሁ ታስባላችሁን? እውነተኛውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ያልያዘ ማንኛውም ሰው በሰይጣን ይማረክና ይሰቃያል፡፡ የእግዚአብሄር የውሃና የመንፈስ ወንጌል ሰይጣንን ለማስወጣት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ የሚያምን ሰው ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመንና ለዓለም ሕዝብ ሁሉም መስበክ ይኖርበታል፡፡ ይህንን የሚሰሙ ይህንን ወንጌል ሊታዘዙትና ሊያምኑት ይገባቸዋል፡፡
 
 
የአመጽ ምስጢር ቀደሞውኑም በዚህ አለም ላይ እየሰራ ነው!
 
በአሁኑ ጊዜ መላው ዓለም በአጋንንቶች እንቅስቃሴዎች ተሸፍኖዋል፡፡ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ የሚመራቸውን ወንጌል መስበክ ከፈለግን ስለ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያለውን ጥልቅ የሆነ የተሳሳተ አስተውሎት ማስወገድ አለብን፡፡
በቅድሚያ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው በእጆች መጫን ነው የሚለውን ውሸት ማጥራት አለብን፡፡ ‹‹የእጆችን መጫን ከተቀበሉ በኋላ በሌላ ልሳን መናገር፣ በንስሐና በጾም አማካይነት አንዳች የጋለ ስሜት መሰማትና ከኢየሱስ በቀጥታ መልዕክቶችን መስማት›› የመሳሰሉ ልምምዶች የዲያብሎስ ሥራ መሆናቸውን በይፋ መመስከር ይገባናል፡፡ ሰዎች ከዲያብሎስ ማታለያ ነጻ መውጣት የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ ከሐጢያቶቻችን መዳን የምንችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ 
‹‹የሐሰት ሁሉ አባት›› የሆነውን ዲያብሎስን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ልንረታው ይገባናል፡፡ ሰይጣን በዓለም ሁሉ ሰዎችን በሙሉ ራስን በመኮነን ባርነት ስላሰራቸው የተዛቡ ልምምዶቻቸውና ስሜቶቻቸው የሰይጣን ማጭበርበሪያዎች መሆናቸውን እንዲገነዘቡ በማድረግ እነዚህን ሰዎች ወደ እውነቱ ልንመልሳቸው ይገባል፡፡   
በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ እያገለገሉ ያሉ ሰዎች እንደ ሰማርያዊው ሲሞን መንፈስ ቅዱስን በገንዘብ ለመግዛት የሚሞክሩ ናቸው፡፡ እነርሱ ዕውርን የሚመሩ ዕውራን መሪዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ለሰዎች ወደ ደህንነት የሚያደርሰውን ፍጹም መንገድ አያሳዩም፤ ምክንያቱም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አያውቁምና፡፡ በልባቸው ውስጥም ሐጢያት አለ፡፡ ስለዚህ ሌሊቱን በሙሉ የሚደረጉ ጸሎቶችን በማድረግ፣ ለንስሐ ጸሎቶች ጥሪ በማቅረብንና እጆችን መጫንን በመጠቀም ሰይጣን በተከታዮቻቸው ልቦች ውስጥ እንዲያድር ያደርጉታል፡፡ እነዚህ ሰዎች በተጨባጭ በዲያብሎስ ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡ ወደ እግዚአብሄር ቃል እንዲመለሱ ከፈለግን ፍጹም የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በፊታቸው በማቅረብ የሰይጣንን ስራ ማፍረስ አለብን፡፡ ሰዎች የሰይጣንን ስትራቴጂዎች የማያውቁ ከሆነ ረዳተ ቢስ ሆነው ከመሰቃየት በቀር ምርጫ የላቸውም፡፡ 
እንዳልሁት ከእጆች መጫን በኋላ በልሳን መናገርና ትንቢትን መተንበይ የመሳሰሉትን ተዓምራቶች ማድረግ በሙሉ የዲያብሎስ ተግባራቶች ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር የካራዝማቲክ ሰዎች ሐይል የሚገለጠው በዲያብሎስ አሰራሮች ነው፡፡ እኛ ልናስተምራቸው ይገባናል፡፡ ‹‹በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት ካለ በእናንተ ውስጥ በመስራት ላይ ያለው ዲያብሎስ ነው፡፡ በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት እያለ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ እንደሚኖር የምታስቡ ከሆነ ተታልላችኋል፡፡›› 
የሐዋርያትና በሐዋርያት ሥራ 8 ዋና ምንባብ ላይ እጆች የተጫነባቸው ሰዎች እምነት በተመሳሳይ መደብ ላይ ተቀምጦዋል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የውሃና የመንፈስ ወንጌል አውቀዋልና፡፡ የሐዋርያት እምነት ግን በእጆች መጫን ብቻ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚቻል ከሚያምኑ ከዛሬዎቹ ክርስቲያኖች እምነት ፈጽሞ የተለየ ነበር፡፡
አንድ ሰው የሐጢያት ስርየትን ባገኘ ሰው አማካይነት እጆች ቢጫንበት መንፈስ ቅዱስን ይቀበላልን? አይቀበልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር መንፈስ በውሆች ላይ ሰፍፎ እንደነበር ይናገራል፡፡ ይህ ማለት አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስን የሚቀበል ከሆነ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማወቅና ማመን አለበት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለሚያምን ዳግም የተወለደ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ስጦታ አድርጎ ይልክለታል፡፡
ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ የእጆችን መጫን መሻት እንዳለባቸው የምናስተምር ከሆነ እግዚአብሄር እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን ያቀደበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቃወም ማለት እንደሆነ በአእምሮዋችን መያዝ አለብን፡፡ አንድ ሰው ለሌላ ሰው መንፈስ ቅዱስን መስጠት እንደሚችል ማሰብ እግዚአብሄርን መገዳደር ነው፡፡ የዚህ አይነት እምነት ያላቸው ሰዎችም በቀላሉ በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ይህ በፍጹም እንዲሆን ሊፈቀድለት አይገባም፡፡  
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባመንን ጊዜ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ይቅር ተብለዋል፤ መንፈስ ቅዱስም ለዚህ ምስክር ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን ሰው በልቡ ውስጥ ሐጢያት የለበትም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ሐጢያት ስላልሰራ ሳይሆን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሐይል ስላመነ ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በልቡ ውስጥ ሐጢያት እንደሌለ ይመሰክራል፤ መንፈስ ቅዱስም የሚመሰክረው ይህንኑ ነው፡፡ አንድ ሰው የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጡ ሳይኖር ኢየሱስን አዳኙ አድርጎ ሊጠራው ይችላል፡፡
በአጋንንት የተያዙ ሰዎች ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል አያውቁም፡፡ እንዲያውም በጭራሽ የውይይት ርዕሰ ጉዳይ አያደርጉትም፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንኳን አያውቁትም፡፡ ከዚህም በላይ እውነቱን መረዳት አይችሉም፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚወርደው እጆችን መጫንን ሲያከናወኑና ሲቀበሉ ብቻ ነው ይላሉ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእጆች መጫን አማካይነት በጭራሽ አይወርድም፡፡ አሁን የዲያብሎስ አሰራር በሐሰት ትምህርቶቹ በኩል በመላው አለም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉትን ሕዝቦች በተጽዕኖ ስር እንዳደረጋቸው ማወቅ አለባችሁ፡፡ ከዚህ የተነሳ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ መቀበል ወሳኝ ነው፡፡