ከእግዚአብሄር የራቀ ሰው ሐጢያቶቹን ተገንዝቦ ኢየሱስ እንዳስወገዳቸው እርሱን በማመስገን ወደ እግዚአብሄር ሲመለስ ይህ ንስሐ ተብሎ ይጠራል፡፡
ሁላችንም የሐጢያት ክምሮች ነን፡፡ እውነተኛ ንስሐ ቀጣዩን እውነት መቀበል ነው፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች እንደሆንን፣ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ሐጢያት እንደምንሰራና ስንሞት ሲዖል እንደምንወርድ፣ ኢየሱስ እንደ እኛ አይነት ሐጢያተኞችን ለማዳን ወደዚህ ዓለም እንደመጣ በማመን እርሱን አዳኛችን አድርገን መቀበል እንደሚኖርብን፣ እኛን ለማዳንም ሐጢያቶችን ሁሉ (በጥምቀቱ አማካይነት) እንደወሰደ፣ እንደሞተና እንደተነሳ ማመን አለብን፡፡ እውነተኛ ንስሐ የራሳችንን አስተሳሰቦች መተውና ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነው፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)
ንስሐ ሐጢያቶቻችንን ማመንና ከሙሉ ልባችንም የውሃውንና የደሙን ደህንነት ለመቀበል ወደ እግዚአብሄር ቃል መመለስ ነው፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡6)
እውነተኛ ንስሐ እኛ ፈጽመን ሐጢያተኞች መሆናችንን መቀበልና የእግዚአብሄርን ልጅ ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ማመን ነው፡፡ ለመዳንና ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለመንጻት በራሳችን ሥራዎች አማካይነት መቀደስ መሞከርን ማቆምና እኛ በእግዚአብሄርና በሕጎቹ ፊት ፈጽመን ሐጢያተኞች መሆናችንን ማመን አለብን፡፡ ከዚያም ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ የሰጠንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማለትም የደህንነቱን እውነት መቀበል ይኖርብናል፡፡
አንድ ሐጢያተኛ የራሱን አስተሳሰቦች ሁሉ መተውና ፈጽሞ ወደ ኢየሱስ መመለስ አለበት፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ የወሰደበት እንደሆነ ወደ ማመን ስንመጣ እንድናለን፡፡
በሌላ አነጋገር የኢየሱስ ጥምቀት፣ ስቅለቱና ትንሳኤው ለሐጢያተኞች ሁሉ ደህንነት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ፈጽመዋል፡፡ ኢየሱስ በሥጋ መጣ፡፡ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለማስወገድም ተጠመቀ፤ ተሰቀለ፡፡ እውነተኛ ንስሐና ትክክለኛ እምነት በእነዚህ ሁሉ ላይ ሙሉ እምነት መያዝና ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ አዳኝ ለመሆን እንደተነሳ ማመን ነው፡፡