Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

አጋር ሠራተኛ ከሆንክና "መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች" በሚለው ላይ መልዕክትና ፎቶዎችን መለጠፍ የምትወድ ከሆነ "መልዕክት ለጥፍ" የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግና ግባ፡፡ ልጥፍህ የሚታየው የእኛን ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡

መልዕክት ለጥፍ
ጠቅላላ፤ 12
 • ቁ.12

  ክርስትና ውስጥ በጣም ስር የሰደደው አደገኛው በሽታ የቀስ በቀስ ቅድስና ትምህርት ነው፡፡

  ክርስትና ውስጥ በጣም ስር የሰደደው አደገኛው በሽታ የቀስ በቀስ ቅድስና ትምህርት ነው፡፡ብዙዎችን ገድለዋል፡፡ የእምነት ሕይዎታቸውንም አሰልቺ አድርጎባቸዋል፡፡ይህ ትምህርት ምንድ ነው? የሰው ልጅ አንድ ጊዜ ይጸድቃል ግን #በቅድስና ቀስ በቀስ እያደገ ይመጣል የሚል ትምህርት ነው: ወይም የህደት ቅድስና ይባላል፡፡ሰው በክርስቶስ ካመነ በኃላ ኃጢአትን መስራት እያቆመ፣ እያቆመ፣ እያቆመ፣ እያቆመ ይሄድና መጨረሻ ላይ ክርስቶስን መስሎ ቁጭ ይላል የሚል ትምህርት ነው፡፡ይህ ትምህርት በጣም ማራኪና ደስ የሚል ትምህርት ይመስላል፡፡.ይህን ለመጀመራያ ጊዜ ሲትሰሙ ልባችሁ ይነካል፡፡ከዚያም በኃላ ዘመናችሁን ኢየሱስን ለመምሰል እየታገላችሁ ትጨርሳላችሁ፡፡ እውነታው ግን ይበልጥ በሞከራችሁ ቁጥር የማይቻል መሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ ብዙ ኃጢአት ውስጥ ትወድቃላችሁ፡፡ ሕሊናችሁ ሲወቅሳችሁ ደግሞ የንሰሀ ጸሎት ትጸልያላችሁ፡፡አሁንም ትሞክራላችሁ ከዚያም ትወድቃላችሁ፡፡እንደገና ደግሞ የንስሀ ጸሎት ትጸልያላችሁ፡፡ ይህ አሰልቺ ዑደት ይቀጥላል፡፡ ሲያቅታችሁ የማስመሰል/የግብዝነት ሕይወት ትለማመዳላችሁ፣ምን ታደርጋላችሁ ምንም አማራጭ የለማ፡፡ ይህ የተሳሳተ ትምህርት ነው ብሎ የሚያስብ ማንም የለም፡፡ምንክንያቱም ብዙ ማሳመኛ በሚመስሉ ጥቅሶች ታጅቡዋል ፡፡.ለምሳሌ ጳውሎስ…..‹‹እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ›› ብልዋል፤ኢየሱስ ደግሞ ‹‹አባቴ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ›› ብልዋል….‹‹#በቅድስና #ተመላለሱ››…የሚሉ .ሌላ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፡፡ዳሩ ግን እነዚህ ጥቅሶች ብዙዎች እንደሚረዱ አይደሉም፡፡ጳውሎስ በእውነት ኢየሱስን የመሰለው ኃጢአትን ባለመስራት ነውን? ኢየሱስ ፍጹማን ሁኑ ሲለን በስጋችሁ ምንም ኃጢአት መስራት የለባችሁም እያለ ነውን? እነዚህ መልዕክቶች ምን ማለት ናቸው? በቅድስና መመላለስ ማለት ምን ማለት ነው?.እነዚህን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎችን ለመረዳት መጀመረያ የራስችሁን አስተሳሰብና አረዳድ አሽቀንጥራችሁ ጣሉ፡፡በመቀጠል የሚከተሉትን እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎችን በማንበብ እምነተችሁን አስተካክሉ፡፡ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሰተ መንገድ በመረዳት የእምነት ሕይዎታችውን ለመኖር ሲሞክሩ በጣም ይከብዳችሁዋል፤ መጨረሻ ላይ ተስፋ ይቆርጡና ተራ ሃይማኖተኛ ሆኖ በአለም ይመላለሳሉ፡፡ ትክክለኛውን የእምነት መንገድ፣ #ዳግም #የመወለድ ምስጢርና #ድል #ነሺ #የእምነት #ሕይወት እንዴት መኖር እንደምንችል የሚያሳዩ ድንቅ መጽሐፍት አሉን፡፡.የበለጠ ለመረዳት እነዚህን ነፃ የክርስቲያን መንፈሳዊ መጽሐፍ ያግኙ፡፡ጌታ ኢየሱስ ‹‹በነፃ ተቀብላቿዋል በነፃ ስጡ›› ሲላለ፣ የኃጢያትን ስርየትን የሚያሰገኝ የመዳንን እውቀት የሚሰጡትን መጽሐፍት #በነፃ እንሰጣለን፤ በአድራሻችሁ እንልካለን፡፡ አድራሻችሁን ፃፉልን፡፡ . የኃጢአታችሁን ስርየት በማግኘት በመንፈሳዊ በረከት ተባረኩ!09105551900910367615bjnewlife.orgYohannes Make Mara, Ethiopia

  • Yohannes Make Mara
  • Ethiopia
  • 04/09/202313
 • ቁ.11

  መዳን የለም ከሥርዓቱ መንገድ ተሸሽቶ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ)

    ርዕስ፦ መዳን የለም ከሥርዓቱ መንገድ ተሸሽቶ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ) (1). መዳን የለም ከሥርዓቱ መንገድ ተሸሽቶደም አንጠልጥሎ እጆች የመጫን ህጉ ተከድቶአብ ያቀደው ነውርና እንከን ዕድፍ የሌለውምታመንበት መቆሚያ ዓለት አለኝ የምለው ውኃ ነው፣ ደሙ ነው፣ መንፈሱ ሰማይ ያወቀው  ውኃው ነው፣ ደሙ ነው፣ መንፈሱ አብ ያረቀቀው (2). ተቀብያለሁ በነፍስ ያደረ ምስክርነት  ይሄ ነው ደንህነት የማያሳፍር ድንቅ ልጅነት በላይ በሰማይ የእ/ር አብ ዕቅድ የሆነበኢየሱስ ሥራ ከዓለማት በፊት የተወሰነበሰማያዊ በቀይ ሐምራዊ ጥልፍ የተሰራጥሩ በፍታ ነው ያደመቀው እጅግ የጠራ። (3). የኢየሱስ ጥምቀት ነው የዓለምን ኃጢአት የወሰደው በሞት ኩነኔ ፍርድ የራቀበት የፈጸመው የእኔ በደሎች አንዲትም ሳትቀር ተሽሮልኛልየእግዚአብሔር ፍቅር በልጁ በኩል እኔን ምሮኛል። (4). የማዳኑን ቃል አላጓድልምከሥርዓቱ ውጭ ንቅንቅ አልልምእርሱ በላከው በዮሐንስ እጅ በተደረገው ዮርዳኖስ ሄጄ በኢየሱስ አምኜ እኔ ድኛለው፡፡ (5). በተጠረገው መንገድ ኃጢአት በሌለው ጎዳናከላይ በተመረቀው በአዲስ ኪዳን በጸናበኢየሱስ በበሩ በኩል በሕይወቴ ብርሃን በርቶ ጻድቅ ሰው ሆኜ እጓዛለሁ ሥራዬ ሁሉ ተሰርቶ፡፡ (6). መስዋቴን ይዤ እንከን አልባውን እንደተጻፈውእጄን ጭኜበት ክፋት በደሌ ሁሉ ተላልፈውምህረት የሚያስገኝ ደምን ይዤ ነው ምቀርብ ከፊቱደወል ይሰማል የምስራች ነው  አውደ ምህረቱ።

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 12/12/202226
 • ቁ.10

  መከሩ ብዙ ነው (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ)

    ርዕስ፦ መከሩ ብዙ ነው (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ) መከሩ ብዙ ነው ምናያቸው ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸውየመከሩ ባለቤት ጌታችን ሠራተኞችን አንሳን ስጠን (1). የጠፉ በጎች ከፊትህይሳቡ ባንተ ምህረትህከጎተራው ውስጥ ፍሬ ይግባቤትህ በጻድቃን ይገንባ (2). በምድረ በዳ በራብ ያሉተጨንቀው በክፉ የተጣሉጌታ ምህረትህ ያግኛቸውእግዚአብሔር ክንድህ ይስባቸው (3). የቤትህ አገልጋይ ሰራተኞች ጽድቅን የሚያወሩ ወታደሮች በየከተማው በገጠሩ ለሠማይ መንግስት የሚሰሩ ውኃ ደም መንፈስ ዓላማቸው የቤትህ ቅናት ሚበላቸውየሰይጣንን ግንብ የሚያፈርሱየቤቱን ቅጥር የሚያድሱ                              ጌታ ይነሱ                                 ዛሬ ይነሱ                                    ኦ ይነሱ ጌታ ይነሱ  ዛሬ ይነሱ  አዎ ይነሱ  አሜን ይነሱ ።

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 12/12/202219
 • ቁ.9

  ለመዳን አስቀድመን (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ)

    ርዕስ፦ ለመዳን አስቀድመን (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ) ለመዳን አስቀድመን ኃጢአቶችንንማወቅ አለብንለመዳን አስቀድመን ክፋቶቻችንንመገንዘብ አለብን።   (1)   ኃጢአት ሰሪ መሆናችንን ሁል ጊዜ አመንዛሪ መሆናችንን ሁል ጊዜ ሰራቂ መሆናችንን እንድናውቅ ይፈልጋል እግዚአብሔር ራሳችንን። (2)  ይፈልቃል ከእኛ ልብ በየቀኑ የኃጢአት ዓይነትዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነትመጎምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራትስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና፣ ምቀኝነትእነዚህ ኃጢአት ይፈልቃሉ  ዘውትር ከእርኩስ ልባችንመዳን ከቶ አንችልም ካላወቅን ራሳችንን። (3)   አውቃለሁ ኃጢአቴን፣ የኃጢአቴንም ደመወዝ አመለጥኩኝ ባንተ ኢየሱስ ፣ ዳንኩኝ እኔ ከሞት መዘዝበውኃና በደም መጥተህ በአንዴ እኔን አጸደቅከኝ በዘላለም ቤዛነትህ በአዲስ ኪዳን ምህረት ማርከኝ።በዓመፃዬ ጽድቅህን  አይቻለሁናአመሰግናለሁ ኢየሱስ ይድረስ ለአንተ ምስጋና። (4) ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርግርነቱንይለውጥ ዘንድ ይችላል ወይ የተፈጥሮ ማንነቱንምንም ያህል ብንለፋ ከሰል አጥበን አናነጣምበሕግ ኑሮ ብንታገል የልብ ኃጢአት ከቶ አይጠራም ከቶም አንጸድቅም በጽድቃችንበትንቢት ቃል ተጽፎ አለ የክፉ ዘር መሆናችን። (5)መዳኛችን የእኛ ቤዛ አዲስ ፍጥረት ምንሆንበትበኢየሱስ ጥምቀትና በሞቱ ላይ ያለን እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ ትምክታችን የሚያቆመን የቆምንበትየዘላለም ተስፋችን ነው ብድራቱን ምናይበት።

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 12/12/202214
 • ቁ.8

  አሁን ኃጢአተኛ አይደለሁም።

  እኔ ኃጢአተኛ የነበርኩት የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባላመንኩ ሰዓት ብቻ ነበረ፤ አሁን ኃጢአተኛ አይደለሁም።ደካማ ሥጋ ስለለበስኩ በሥጋዬ ስበት ኃጢአትን ልሰራ እችላለሁ፤ ነገር ግን የሚያጸድቀኝን የእግዚአብሔር ጽድቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እስካልጣልኩ ድረስ ለዘላለሙን ጻድቅ ነኝ እንጂ ዳግመኛ ኃጢአተኛ አልሆንም። ሃሌሉያ!!! ኃይማኖት ሰዎችን አጠፋ! እንዴት ያሳዝናል የኃጢአትን ስርየት የተቀበለ ማንም የለም። ምክንያቱም የኃጢአት ስርየት ወንጌል የሆነው የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል አይሰበክምና!Mesfin Berhanu Ubba, Ethiopia

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 10/23/202230