ከእኛ ጋር ሕብረት፤
የመጽሐፍ ግምገማዎች፤
መጽሐፎቻችንን ያነበቡ ሰዎች ተከታዮቹን ግምገማዎች ልከዋል፡፡ በእነርሱ በኩል ሁላችሁም ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ እንድንወለድ ያስቻለንን የእግዚአብሄር ጸጋ እርስ በርሳችሁ እንደምትካፈሉ ተስፋችን ነው፡፡ ልጥፍህ የሚታየው የእኛን ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡
የታመመ ሰው ከህመሙ ለመዳን መታመሙን ማመንና ከህመሙ ሊያድነው የሚችለውን ማንኝውንም ነገር ሁሉ ሊያደርግ ይገባዋል! ይህ መጽሀፍ የሰው ልጅ ሁሉ ከእድሜ ልክ አጢአቱ ለመዳን ምን ማድረግ እንዳለበት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ያስተምራል፡፡ መጽሀፉ የየትኛውም ሀይማኖት ተቋምን የማይወክል ሲሆን የአዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ እንደ መርህ በመከተል እኛ የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበትን የደህንነት እውቀት በግልጽ የሚሰብክ የዘመናችን የመጀመሪያው መጽሀፍ ነው! ለዚህም ድንቅ የስብከት መጽሀፍ እግዚአብሔር ቄስ ፓውል ሲ ጆንግን ተጠቅሟል!ስምንት የስብከት ርዕሶችን የተጠቀመው ይህ መጽሀፍ በአንደኛው ስብከት፡ ለመዳን አስቅድመን ስለሀጢአቶቻችን ማወቅ እንዳለብን ያስተምራል! ማርቆስ 7፥8-9/20፥23ን በስፋት ይዳስሳል! ስለሀጢአት ምንነት; ሀጢአት ከየት እንደመጣ; ሀጢአት በእኛ መለኪያና በእግዚአብሔር መለኪያ እንዴት እንደሚመዘን; እኛ የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ምን አይነት ሰዎች እንደሆንን; በራሳችን መለኪያዎች ፍጽሞ መዳን እንደማንችል ሞትም የተገባን መሆማችንን በስፋት ያብራራል፡፡ በሁለተኛው ስብከት፡ እኛ ሰዎች የተወልድነው ሀጢአተኞች ሆነን እንደሆነ ያስተምራል! በማርቆስ 7፥20-23 ላይ የተዘረዘሩ ሀጢአቶች ከእኛ ጋር አብረው የመጡ እንደሆኑ እነርሱም እስክንሞት ድረስ ከውስጣችን እንደሚፈልቁ እየፈለቁም እንደሚያረክሱን በግልጽ ይብራራል! ይበልጥ የመዳን እድል ያለው እነዛ 12 ሀጢአቶች ከልቡ ያለማቋረት እንደሚወጡና በራሱ ምንም ማድረግ እንደማይችል የሚያምን ሰው ነው!በሶስተኛው ስብከት፡ ነገሮችን በህጉ መሰረት ብናደርግ ህጉ ሊያድነን ይችላልን በማለት ይጠይቃል! በሉቃስ 10፡25-30 መሰረት ማናችንም ከሀጢአቶቻችን ለመዳን በህግ የተጻፈው ምን እንደሆነና እንዴትስ መረዳት እንዳለብን በግልጽ ተብራርቷል! እንዲሁም ህግ የተሰጠበትን ዓላማና ማናችንም ህግን መጠበቅ የማንችል ሰዎች መሆናችንን ያስረዳል! በአራተኛው ስብከት፡ ስለዘላለማዊ ቤዛነት እንረዳለን! በዩሐንስ 8፥1-12 ላይ ሴቲቱ በኢየሱስ ቤዛነት ተባርካለች! ኢየሱስም ያልፈረደባት ሀጢአቶቿን በሙሉ አስቀድሞ በጥምቀቱ ስለአስወገደላት ነበር! ኢልየሱስ የእድሜ ልክ ሀጢአቶቻችንን በሙሉ በማስወገድ ዘላለማዊ ቤዛነትን ሰጠን ይህም ማለት ያለምንም ልዩነት ለሁላችንም በእኩል ያለፈውን፡ የአሁኑንና የወደፊት ሀጢአቶቻችንን ሁሉ በጥምቀቱና በሞቱ አስወገደልን ማለት ነው፡፡ ሀሌሉያ!!! ሁላችንም ይህን ድንቅ ቤዛነት ማግኘት አለብን!በአምስተኛው ስብከት፡ የኢየሱስ ጥምቀትና የሀጢአቶች ስርየትን እናገኛለን! በዚህ ስብከት ማቲ 3፥13-17 ይዳሰሳል! ኢየሱስ በመጥምቁ ዩሐንስ ዮርዳኖስ ላይ ተጠምቋል ዩሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ በመጫን የዓለምን ሀጢአት ወደ ኢየሱስ አስተላልፏል ይህም ሲሆን ሰማያት ተቀደዱ መንፈስ ቅዱስም በኢየሱስ ላይ አረፈ እግዚአብሔር አብም ከሰማይ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት አለ! የዓለምን ክርስትና ሚዛን ያሳተ ታላቅ መንፈሳዊ ሚስጢር በክርስቶስ ጥምቀት ውስጥ ተብራርቷል!በስድስተኛው ስብከት፡ ኢየሱስ በውሃ በደምና በመንፈስ እንደመጣ እንማራለን! 1ዩሐንስ 5፡1-12ን በመጠቆም ኢየሱስ በውሃ በደምና በመንፈስ የመምጣቱን መንፈሳዊ ሚስጢር እናገኛለን! መንፈስም ውሃም ደምም ሶስቱም በአንድ እንደሚስማሙ ያረጋግጣል ይህም ማለት ማናችንም በክርስቶስ ስናምን የእርሱን አምላክነት ጥምቀቱንና ሞቱን ከሞትም መነሳቱን ምንም ሳንቀንስ እንዲሁም ሳንጨምር በክርስቶስ ማመን እንዳለብን በጥብቅ ያሳስባል!በሰባተኛው ስብከት፡ የኢየሱስ ጥምቀት ለሀጥአተኞች ምሳሌ መሆኑን እንማራለን! 1ጴጥሮስ 3፡ 20-22 ላይ የምናገኘው የጥፋት ውሃ! ከውሃውም በኖህ መርከብ ገብተው ስለተረፉት ስምንት ሰዎች ተብራርቷል በክፍሉ እንደምናየው ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡ ስለዚህ ማናችንም ሙሉ ከሆነው የኢየሱስ ድንቅ ስራ ውስጥ የኢየሱስን ጥምቀት ቀንሰን ብናምን እኛም በጥፋት ውሀው እንደጠፉት እንጥፋለን! ያም ማለት ወደ ገሀነም እሳት እንጣላለን!በመጨረሻው ስብከት፡ ኢየሱስ ለሁላችንም በእኩል በሰራል ድንቅ ስራ እስከመጨረሻው እንደወደደን በዩሐንስ 13፡1-17 የደቀመዝሙሩን እግር በማጠብ አስረድቶናል ይህም ማለት ኢየሱስ በአምላክነቱ(መንፈስ) በጥምቀቱ(ውሃ) በደሙ(ስቅልት) እና ትንሳኤው የእድሜ ልክ ሀጥአቶቻችንን በማስወገድ ለዘላለም አጽድቆናል ሀሌሉያ! እኔ በዚህ ስጋዬ ማሰብና መግለጽ ከምችለው በላይ ደካማና ሀጢአተኛ ነኝ! ለዚህም ሀጢአተኛ ማንነቴ የገሀነም ፍርድ የተገባኝ ነኝ ነገር ግን ኢየሱስ የእድሜ ልክ ድካሜን ሁሉ አንድም ስያስቀር በጥምቀቱ በሞቱና በትንሳኤው ደምስሶልኛል! ምስጋና፡ ክብር፡ ውዳሴ፡ አምልኮ ሁሉ ላዳነኝ ለኢየሱስ ይሁን!!!ማንም ሰው ይህን መጽሀፍ ቢያነብ እና ቢያምንበት እውነተኛ የክርስቶስ ደቀምዝሙር ይሆናል!Teferi Oshine from Ethiopia/Hawassa
ብዙዎቻችን ገናን የምናከብረው በዘልማዳዊ መንገድ ነው። ስለ ክርስቶስ ልደት ያለን መረዳት ጥራዝ ነጠቅ ነው። ይህን መጽሐፍ ካነበባችሁ ግን ገናን በዘልማዳዊ መንገድ አታከብሩም። ሰው ሆኖ በከብቶች በረት ተወልዶ፣ በመጠቅለያ ተጠቅልሎ በግርግም በተኛው ሕጻኑ ኢየሱስ እጅግ ትደነቃላችሁ። ድንቅና ትልቅ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ይኖራችኋል። ይህን ድንቅ መጽሐፍ እንድታነቡ ልባዊ ግብዣዬ አቀርባለሁ። Yohannes Make Mara, Ethiopia
Copyright © 2021 by The New Life Mission