Search

በነጻ የሚታደሉ የታተሙ መጽሐፎች፣
ኢመጽሐፎችና የኦዲዮ መጽሐፎች፤

የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል፤

በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?
  • ISBN8983147512
  • ገጾች፤392

አማርኛ 1

በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?

Rev. Paul C. Jong

ማውጫ
 
መቅድም 
 
ክፍል አንድ—ስብከቶች 
1. ለመዳን አስቀድመን ስለ ሐጢያቶቻችን ማወቅ አለብን (ማርቆስ 7፡8-9,20-23) 
2. ሰዎች ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው (ማርቆስ7፡20-23) 
3. ነገሮችን በሕጉ መሰረት ብናደርግ ሕጉ ሊያድነን ይችላልን? (ሉቃስ10፡25-30) 
4. ዘላለማዊ ቤዛነት (ዮሐንስ 8፡1-12) 
5. የኢየሱስ ጥምቀትና የሐጢያቶች ስርየት (ማቴዎስ 3፡13-17) 
6. ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በውሃ፣ በደምና በመንፈስ ነው (1ኛ ዮሐንስ 5፡1-12) 
7. የኢየሱስ ጥምቀት ለሐጢያተኞች የደህንነት ምሳሌ ነው (1ኛ ጴጥሮስ 3፡20-22) 
8. የተትረፈረፈው የስርየት ወንጌል (ዮሐንስ 13፡1-17) 

ክፍል ሁለትአባሪ 
1. የደህንነት ምስክርነቶች 
2. ተጨማሪ ማብራሪያ 
3. ጥያቄዎችና መልሶቻቸው 
 
የርዕሱ ዋናው ጉዳይ ‹‹ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ›› ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ለየት ያለ ርዕስ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ መጽሐፍ ዳግመኛ መወለድ ምን እንደሆነና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በጥብቅ በተስማማ መልኩ እንዴት ከውሃና ከመንፈስ መወለድ እንደሚቻል በግልጽ ይነግረናል፡፡ ውሃው በዮርዳኖስ የሆነውን የኢየሱስ ጥምቀት ያመለክታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ይናገራል፡፡ ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪልና የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘር ነው፡፡ አሮን በስርየት ቀን በሚለቀቀው ፍየል ራስ ላይ እጆቹን ጫነና የእስራኤላውያንን አመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ በእርሱ ላይ አስተላለፈ፡፡ ይህ ሊመጡ ያሉ ነገሮች ጥላ ነበር፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት የእጆች መጫን ምሳሌ ነው፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ በእጆች መጫን መልክ ተጠመቀ፡፡ ስለዚህ በጥምቀቱ አማካይነት የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደና ለሐጢያቶች ዋጋ ለመክፈልም ተሰቀለ፡፡ የዚህ መጽሐፍ ቁልፍ ቃል የኢየሱስ ጥምቀትና የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡ ዳግመኛ ልንወለድ የምንችለው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ስናምን ብቻ ነው፡፡
ኢመጽሐፍ አውርድ፤
PDF EPUB
በነጻ የሚታደል የታተመ መጽሐፍ፤
ይህንን የታተመ መጽሐፍ ጋሪው ላይ ጨምር፤
ኦድዮ መጽሐፍ፤
ኦድዮ መጽሐፍ፤

ከአንባቢዎች የተሰጡ የመጽሐፍ ግምገማዎች

  • ክብር ሁሉ በውኃና በደም ለመጣው(1ዮሐ5:6) ለኢየሱስ ይሁን! ሃሌሉያ!
    Daniel Tesfaye Heramo, Ethiopia

    "የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል" የሚባል የወንጌል ትምህርት እንዳለ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወኩት ከዛሬ 15 ዓመት በፊት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሳለሁ ነበር።
    ያኔ ኃጢአተኛ ክርስቲያን ነበርኩ፤ ነገር ግን ኃጢአት እያለብኝም "ዳግም ተወልጃለሁ" ብዬ አስብ ነበር።
    ስለዚህም ይህንን <<በዕውኑ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም ተወልዳችኋልን?>> ከሚለው መጽሐፍ ጋር በአጋጣሚ ስገናኝ "እኔ ዳግመኛ ተወልጃለሁ ይህን ሌሎች ያንብቡ" ስል በማሰብ ተውኩት። ከተወሰኑ ወራት በኋላ ግን ስለዚህ መጽሐፍ ማወቅ ጀመርኩ።
    መጽሐፉ ትክክለኛ የኃጢአት ግንዛቤ እንዲኖረኝ ረድቶኛል።
    ይህ መጽሐፍ እግዚአብሔር ሕግን የሰጠበትን ዓላማ በጥልቀት እንድረዳ አግዞኛል። ይህ መጽሐፍ በሕግ ስራ፣በሃይማኖታዊ ጥረቶች ከኃጢአት ለመንጿት አደርገው የነበረው ጥረት ምን ያህል ከእግዚአብሔር ጋር መገዳደር እንደሆነና በእርግማን መኖር እንደሆነ አስተምሮኛል።
    ይህ መጽሐፍ ስህተቶቼን ብቻ ነግሮኝ አላበቃም፤ በስርየት ህጉ መሰረት እግዚአብሔር እንዴት በኢየሱስ ጥምቀት፣ሞትና ትንሣኤ ኃጢአት አልባ እንዳደረገኝ በጥልቀት ነግሮኛል። የኢየሱስን ዘላለማዊ ቤዛነት አስተምሮኛል።
    በፊት እምነቴ ያለ ምስክር ነበር፤ አሁን ግን የውኃ፣የደሙንና የመንፈሱን ምስክር ይዣለሁ።
    ክብር ሁሉ በውኃና በደም ለመጣው(1ዮሐ5:6) ለኢየሱስ ይሁን! ሃሌሉያ!
    ዳንኤል ተስፋዬ ነኝ. ከኢትዮጵያ

    ተጨማሪ
  • ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ስለተወለድኩ፣ ጻዲቅ የእግዚአብሄር ልጅ ሆኛለው!
    Teferi Oshine, Ethiopia

    የቄስ ፖል ሲ ጆንግን "በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?" መጽሀፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነብ የ 10 አመት ልጅ እንደነበርኩ አስታውሳለው፣ በጊዜው በነበረኝ የማንበብ አቅም መጽሃፉን በፍጥነት መረዳት አልቻልኩም ነበር እናም መጽሀፉን የሰጠኝ ሰው ዳጋግሜው እንዳነብ ያበረታታኝ ነበር፤ እኔም በድጋሚ ማንበቤን ቀጠልኩ፣ መጽሀፉንም መረዳት ጀመርኩ! ስለሀጢአት፣ ስለህግ፣ ስለኢየሱስ ጥምቀት፣ ስለሀጢአት ስርየት፣ አጠቃላይ ስለሰው ተፈጥራአዊ ማንነትና ስለክርስቶስ ጽድቅ፤ አሜን ያ በጣም ድንቅ ነበር! በስጋ ቤተሰቤ አማካኝነት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነበርኩ ያውም አጥባቂ አማኝ ነበርኩ አሁን ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ የእድሜልክ ሀጢአቶቼን እንደተሸከመ የእኔንም ሞት በመስቀል ላይ እንደሞተልኝና በሶስተኛውም ቀን ከሞት እንደተነሳ አመንኩ! በሀይማኖታዊ ህይወቴ ስለኢየሱስ ጥምቀት ትክክለኛ መጽሀፍ ቅዱሳዊ መረዳት ስላልነበረኝ ከሀጢአቶቼ መዳን አልቻልኩም ነበር፤ በብሉይ ኪዳን የነበረው የስርየት ህግ(ዘሌዋዊያን 16:21 እና ማቲዮስ 3:15 ) በአዲስ ኪዳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ እንደነበር ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ተገነዘብኩ! መንፈስ ቅዱስ በቄስ ፖል ሲ ጆንግ በኩል ይህ ድንቅ እውነት ስለገለጠልኝ አመሰግነዋለው! ዛሬ ላይ ኢየሱስ በጥምቀቱ የመላውን አለም የዛሬውን፣ የነገውንና የወደፊት ሀጢአቶች በሙሉ መሸከሙን ዮሃንስ 1፡29 ሰባኪና ጻዲቅ የክርስቶስ ልጅ ሆኛለው ሃሌሉያ ዛሬም ነገም ኢየሱስ በአርግጥም ሁሉን ቻይ አምላክ ነው!

    ተጨማሪ
  • በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?
    Teferi Oshine, Ethiopia

    የታመመ ሰው ከህመሙ ለመዳን መታመሙን ማመንና ከህመሙ ሊያድነው የሚችለውን ማንኝውንም ነገር ሁሉ ሊያደርግ ይገባዋል!
    ይህ መጽሀፍ የሰው ልጅ ሁሉ ከእድሜ ልክ አጢአቱ ለመዳን ምን ማድረግ እንዳለበት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ያስተምራል፡፡ መጽሀፉ የየትኛውም ሀይማኖት ተቋምን የማይወክል ሲሆን የአዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ እንደ መርህ በመከተል እኛ የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበትን የደህንነት እውቀት በግልጽ የሚሰብክ የዘመናችን የመጀመሪያው መጽሀፍ ነው! ለዚህም ድንቅ የስብከት መጽሀፍ እግዚአብሔር ቄስ ፓውል ሲ ጆንግን ተጠቅሟል!
    ስምንት የስብከት ርዕሶችን የተጠቀመው ይህ መጽሀፍ በአንደኛው ስብከት፡ ለመዳን አስቅድመን ስለሀጢአቶቻችን ማወቅ እንዳለብን ያስተምራል! ማርቆስ 7፥8-9/20፥23ን በስፋት ይዳስሳል! ስለሀጢአት ምንነት; ሀጢአት ከየት እንደመጣ; ሀጢአት በእኛ መለኪያና በእግዚአብሔር መለኪያ እንዴት እንደሚመዘን; እኛ የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ምን አይነት ሰዎች እንደሆንን; በራሳችን መለኪያዎች ፍጽሞ መዳን እንደማንችል ሞትም የተገባን መሆማችንን በስፋት ያብራራል፡፡
    በሁለተኛው ስብከት፡ እኛ ሰዎች የተወልድነው ሀጢአተኞች ሆነን እንደሆነ ያስተምራል! በማርቆስ 7፥20-23 ላይ የተዘረዘሩ ሀጢአቶች ከእኛ ጋር አብረው የመጡ እንደሆኑ እነርሱም እስክንሞት ድረስ ከውስጣችን እንደሚፈልቁ እየፈለቁም እንደሚያረክሱን በግልጽ ይብራራል! ይበልጥ የመዳን እድል ያለው እነዛ 12 ሀጢአቶች ከልቡ ያለማቋረት እንደሚወጡና በራሱ ምንም ማድረግ እንደማይችል የሚያምን ሰው ነው!
    በሶስተኛው ስብከት፡ ነገሮችን በህጉ መሰረት ብናደርግ ህጉ ሊያድነን ይችላልን በማለት ይጠይቃል! በሉቃስ 10፡25-30 መሰረት ማናችንም ከሀጢአቶቻችን ለመዳን በህግ የተጻፈው ምን እንደሆነና እንዴትስ መረዳት እንዳለብን በግልጽ ተብራርቷል! እንዲሁም ህግ የተሰጠበትን ዓላማና ማናችንም ህግን መጠበቅ የማንችል ሰዎች መሆናችንን ያስረዳል!
    በአራተኛው ስብከት፡ ስለዘላለማዊ ቤዛነት እንረዳለን! በዩሐንስ 8፥1-12 ላይ ሴቲቱ በኢየሱስ ቤዛነት ተባርካለች! ኢየሱስም ያልፈረደባት ሀጢአቶቿን በሙሉ አስቀድሞ በጥምቀቱ ስለአስወገደላት ነበር! ኢልየሱስ የእድሜ ልክ ሀጢአቶቻችንን በሙሉ በማስወገድ ዘላለማዊ ቤዛነትን ሰጠን ይህም ማለት ያለምንም ልዩነት ለሁላችንም በእኩል ያለፈውን፡ የአሁኑንና የወደፊት ሀጢአቶቻችንን ሁሉ በጥምቀቱና በሞቱ አስወገደልን ማለት ነው፡፡ ሀሌሉያ!!! ሁላችንም ይህን ድንቅ ቤዛነት ማግኘት አለብን!
    በአምስተኛው ስብከት፡ የኢየሱስ ጥምቀትና የሀጢአቶች ስርየትን እናገኛለን! በዚህ ስብከት ማቲ 3፥13-17 ይዳሰሳል! ኢየሱስ በመጥምቁ ዩሐንስ ዮርዳኖስ ላይ ተጠምቋል ዩሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ በመጫን የዓለምን ሀጢአት ወደ ኢየሱስ አስተላልፏል ይህም ሲሆን ሰማያት ተቀደዱ መንፈስ ቅዱስም በኢየሱስ ላይ አረፈ እግዚአብሔር አብም ከሰማይ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት አለ! የዓለምን ክርስትና ሚዛን ያሳተ ታላቅ መንፈሳዊ ሚስጢር በክርስቶስ ጥምቀት ውስጥ ተብራርቷል!
    በስድስተኛው ስብከት፡ ኢየሱስ በውሃ በደምና በመንፈስ እንደመጣ እንማራለን! 1ዩሐንስ 5፡1-12ን በመጠቆም ኢየሱስ በውሃ በደምና በመንፈስ የመምጣቱን መንፈሳዊ ሚስጢር እናገኛለን! መንፈስም ውሃም ደምም ሶስቱም በአንድ እንደሚስማሙ ያረጋግጣል ይህም ማለት ማናችንም በክርስቶስ ስናምን የእርሱን አምላክነት ጥምቀቱንና ሞቱን ከሞትም መነሳቱን ምንም ሳንቀንስ እንዲሁም ሳንጨምር በክርስቶስ ማመን እንዳለብን በጥብቅ ያሳስባል!
    በሰባተኛው ስብከት፡ የኢየሱስ ጥምቀት ለሀጥአተኞች ምሳሌ መሆኑን እንማራለን! 1ጴጥሮስ 3፡ 20-22 ላይ የምናገኘው የጥፋት ውሃ! ከውሃውም በኖህ መርከብ ገብተው ስለተረፉት ስምንት ሰዎች ተብራርቷል በክፍሉ እንደምናየው ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡ ስለዚህ ማናችንም ሙሉ ከሆነው የኢየሱስ ድንቅ ስራ ውስጥ የኢየሱስን ጥምቀት ቀንሰን ብናምን እኛም በጥፋት ውሀው እንደጠፉት እንጥፋለን! ያም ማለት ወደ ገሀነም እሳት እንጣላለን!
    በመጨረሻው ስብከት፡ ኢየሱስ ለሁላችንም በእኩል በሰራል ድንቅ ስራ እስከመጨረሻው እንደወደደን በዩሐንስ 13፡1-17 የደቀመዝሙሩን እግር በማጠብ አስረድቶናል ይህም ማለት ኢየሱስ በአምላክነቱ(መንፈስ) በጥምቀቱ(ውሃ) በደሙ(ስቅልት) እና ትንሳኤው የእድሜ ልክ ሀጥአቶቻችንን በማስወገድ ለዘላለም አጽድቆናል ሀሌሉያ!
    እኔ በዚህ ስጋዬ ማሰብና መግለጽ ከምችለው በላይ ደካማና ሀጢአተኛ ነኝ! ለዚህም ሀጢአተኛ ማንነቴ የገሀነም ፍርድ የተገባኝ ነኝ ነገር ግን ኢየሱስ የእድሜ ልክ ድካሜን ሁሉ አንድም ስያስቀር በጥምቀቱ በሞቱና በትንሳኤው ደምስሶልኛል! ምስጋና፡ ክብር፡ ውዳሴ፡ አምልኮ ሁሉ ላዳነኝ ለኢየሱስ ይሁን!!!
    ማንም ሰው ይህን መጽሀፍ ቢያነብ እና ቢያምንበት እውነተኛ የክርስቶስ ደቀምዝሙር ይሆናል!

    ተጨማሪ
  • ክብር ሁሉ ለውሃና ለመንፈሱ ወንጌል ይሁን።
    Yonas Kuliso, Ethiopia

    በነገር ሁሉ መረዳትን የሰጠኝ እግዚአብሔር የተመሰገ ይሁን። እኔ ይህንን መጽሐፍ በአንድ አጋጣሚ ነው የተገናኘሁት። በonline ላይ ብዙ ጊዜዬን አጠፋ ነበረ። በአንድ አጋጣሚ አንድ መልዕክት በfacebook ስመላለስ አየሁ። ምንም ያህል በሳሙና ብትታጠብም ከሰልን ነጭ ማድረግ እንደማይቻልና በየቀኑ በምናቀርበው የንሰሐ ጸሎት ከሐጢአት እስራት ነጻ መውጣት እንደማንችል ጽሑፉ ያወሳ ነበር።
    እኔም ተገረምኩና ጽሑፎቹን ማንበብ ጀመርኩ። እጅግም እንግዳ ነገር እንደሆነ አስቤ ነጻ የምታደል መጽሐፍ የምለውን አይቼ ለራሴም እንድደርሰኝ መልዕክት አስቀመጥኩ። መጽሐፉም በደረሰኝ ጊዜ ማንበብን ጀመርኩ። ገና እንደጀመርኩ ውስጤ በጥያቄዎች ተሞልቶ ነበረ።
    መጽሐፉን እስካነበብኩበት ቀን ድረስ እውነተኛ የሰው ልጅ ማንነት ምን እንደሆነ፣ ሐጢአት በትክክል ምን እንደሆነ፣ እግዚአብሔር ሕግን ለምን እንደሰጠ፣ በብሉይ ኪዳን የነገረው የእጆች መጫን ምን ማለት እንደሆነ፣ ኢየሱስ በዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ለምን እንደተጠመቀ፣ እናም የአለም ሐጢአት ስባል ምን እንደነበረ፣ ኢየሱስ የትኛውን ሐጢአት እንዳስወገደና አሁን ያልተወገደ ሐጢአት አለ ወይ? ለምሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ ከመጽሐፉ ሳገኝ ገና ሳቅ ይቀድመኝ ጀመረ።
    በፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ አንድም ቀን ስለ ኢየሱስ ጥምቀትና ስለ እጆች መጫን ሰምቼ አላውቅም። በዚህ መጽሐፍ ግን እግዚአብሔር አይኖቼን ሙሉ በሙሉ ገለጣቸው።
    አሁን በውሃውና በመንፈስ ወንጌል በማመን የሐጢአት ስርየትን አግንቻለሁ። በኢየሱስ ጥምቀትና ሞት ሙሉ በሙሉ ሐጢአት አልባ ሆኛለሁ። እግዚአብሔር እንደ እኔ አይነቱን ደካማ ሰው ለማዳን መጣ። በጥምቀቱም ሐጢአቶቼን በሙሉ በስጋ ተሸከመ። ለእነዚያ ሐጢአቶችም በመስቀል ላይ ተቸነከረ። በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነስቶ አዲስ ሕይወት ሰጠኝ። እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ኑሮዬ በእምነት ነው። በማየት አልመላለስም። ክብር ሁሉ ለውሃና ለመንፈሱ ወንጌል ይሁን

    ተጨማሪ

ከዚህ ርዕሰ ጋር የተዛመዱ መጽሐፎች