Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 3፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል

[3-7] የተለወጠው ክህነት፡፡ ‹‹ ዕብራውያን 7፡1-28 ››

የተለወጠው ክህነት፡፡
‹‹ ዕብራውያን 7፡1-28 ››
‹‹የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሄር ካህን የሆነ መልከ ፄዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፡፡ ለእርሱም ደግሞ አብርሃም ካለው ሁሉ አሥራትን አካፈለው፡፡ የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፤ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ማለት ነው፡፡ አባትና እናት የትውልድም ቁጥር የሉትም፡፡ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፡፡ ዳሩ ግን በእግዚአብሄር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል፡፡ የአባቶች አለቃ አብርሃም ከዘረፋው የሚሻለውን የሰጠው ይህ ሰው እንዴት ትልቅ እንደነበር እስቲ ተመልከቱ፡፡ ከሌላ ልጆችም ካህንነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለትም ከወንድሞቻቸው እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡም ከእነርሱ አሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትዕዛዝ አላቸው፡፡ ከእነርሱ የማይቆጠረው ግን ከአብርሃም አሥራትን አውጥቷል፡፡ የተስፋ ቃል የነበረውንም ባርኮዋል፡፡ ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው፡፡ በዚህስ የሚሞቱ ሰዎች አሥራትን ያስወጣሉ፡፡ በዚያ ግን የሚያስወጣ በሕይወት እንዲኖር የመሰከረለት እርሱ ነው፡፡ ይህንም ለማለት ሲፈቅድ አሥራትን ሰጥቶአል፡፡ መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና፡፡  
እንግዲህ ሕዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሰረተን ሕግ ተቀብለዋልና፡፡ በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን እንደ አሮን ሹመት የማይቆጠር እንደ መልከ ፄዴቅ ሹመት ግን ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል? ክህነቱ ሲለወጥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ የግድ ነውና፡፡ ይህ ነገር የተነገረለት እርሱ በሌላ ወገን ተካፍሎአልና፡፡ በዚያ መሠዊያውን ያገለገለ ማንም የለም፡፡ ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፡፡ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ክህነት አልተነገረም፡፡    
በማያልፍም ሕይወት ሐይል እንጂ በሥጋ ትዕዛዝ ሕግ ሳይሆን ሌላ ካህን በመልከ ጼዴቅ ምሳሌ ቢነሳ ይህ እጅግ አብልጦ የሚገለጥ ነው፡፡ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ይመሰክራልና፡፡ ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፡፡ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትዕዛዝ ተሽራለች፡፡ ወደ እግዚአብሄርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል፡፡  
እነርሱም ያለ መሃላ ካህናት ሆነዋልና፡፡ እርሱ ግን ጌታ፡- አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሃላ ጋር ካህን ሆኖአልና፡፡ ያለ መሃላ ካህን እንዳልሆነ መጠን እንዲሁም ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል፡፡ 
እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፡፡ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፡፡ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፡፡ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሄር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፡፡  
ቅዱስና ያለ ተንኮል፣ ነውርም የሌለበት፣ ከሐጢአተኞችም የተለየ፣ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናልና፡፡ እርሱም እንደነዚያ ሊቀ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ሐጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ሐጢአት ዕለት ዕለት መስዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፡፡ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና፡፡ ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፡፡ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሃላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል፡፡››     
 
 

ኢየሱስ ሰማያዊውን ክህነት አገለገለ፡፡ 

 
የላቀው ማነው? ሊቀ ካህኑ መልከ ጼዴቅ ወይስ እንደ አሮን ስርዓት የሆነው ምድራዊው ሊቀ ካህን?
ሊቀ ካህኑ መልከ ጼዴቅ ነው፡፡  

በብሉይ ኪዳን ዘመን መልከ ጼዴቅ የሚባል ካህን ነበር፡፡ በአብርሃም ዘመን ኮልዶጎሞርና ነገሥታቶቹ ተባብረው የሰዶምንና የገሞራን ንብረቶች ሁሉ ዘረፉ፡፡ አብርሃምም በቤቱ ያደጉትንና የሰለጠኑትን አገልጋዮች በማስታጠቅ ወደ ጦርነት መራቸው፡፡ 
በዚያም የኤላምን ንጉሥ ኮልዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የተባበሩትን ነገሥታት ሁሉ አሸንፎ የአጎቱን ልጅ ሎጥንና ንብረቶቹን በሙሉ አስመለሰ፡፡ አብርሃም ጠላቶቹን አሸንፎ ከተመለሰ በኋላ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሄር ካህን መልከ ጼዴቅ ዳቦና የወይን ጠጅ ይዞ በመምጣት አብርሃምን ባረከው፡፡ አብርሃምም ከሁሉም ነገር አስራትን ሰጠው፡፡ (ዘፍጥረት ምዕራፍ 14)  
በመጸሐፍ ቅዱስ የሊቀ ካህኑ መልከ ጼዴቅና በእርሱ ስርዓት ውስጥ ያሉ ሊቀ ካህናት ታላቅነት በስፋት ተዘርዝሮዋል፡፡ ሊቀ ካህን መልከ ጼዴቅ ‹‹የሰላም ንጉሥ›› ‹‹የጽድቅ ንጉሥ›› አባት፣ እናትና የዘር ግንድ የሌለው ነበር፡፡ ለዘመኑ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የአዲሱን ኪዳን የኢየሱስ ክህነት ከብሉይ ኪዳኑ ከአሮን ክህነት ጋር በማነጻጸር እንደ መልከ ጼዴቅ ስርዓት ሊቀ ካህናት የነበረውን የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅነት በጥንቃቄ እንድንመለከት ይነግረናል፡፡  
የሌዊ ዝርያዎች ከአብርሃም ዘር የመጡ ቢሆኑም ካህናት ሆኑና ከሕዝቡ ማለትም ከወንድሞቻቸው አስራትን ሰበሰቡ፡፡ ነገር ግን አብርሃም ለሊቀ ካህኑ መልከ ጼዴቅ አስራትን በሰጠ ጊዜ ሌዊ ገናም በአባቱ ወገብ ውስጥ ነበር፡፡ 
የብሉይ ኪዳን ካህናት ከኢየሱስ ይበልጡ ነበር? ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተብራርቷል፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ ከነበሩ ካህናት በሙሉ ይበልጥ ነበርን? ማን በማን መባረክ አለበት? የዕብራውያን መጽሐፍ ከመጀመሪያውም ስለዚህ ተናግሮዋል፡፡ ‹‹ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው፡፡›› አብርሃም በሊቀ ካህኑ በመልከ ጼዴቅ ተባርኮ ነበር፡፡  
በእምነታችን መኖር ያለብን እንዴት ነው? መደገፍ የሚገባን በብሉይ ኪዳን ቅዱስ ድንኳን መስዋዕታዊ ስርዓት አማካይነት በእግዚአብሄር ትዕዛዛት ላይ ነውን? ወይስ መደገፍ ያለብን በውሃና በመንፈስ መስዋዕቱ አማካይነት ሰማያዊ ሊቀ ካህን ሆኖ በመጣልን በኢየሱስ ክርስቶስ?   
በምንመርጠው አተረጓጎም ላይ በመመርኮዝ ወይ እንባረካለን አለበለዚያም እንኮነናለን፡፡ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት እየኖርን በየቀኑ መስዋዕቶችን እናቀርባለን ወይስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራሱን በመስቀል ላይ በመሰዋት ለእኛ ዘላለማዊ ደህንነትን ባመጣልን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እንመርጣለን? ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን በመምረጥ መኖር መቻል አለብን፡፡   
በብሉይ ኪዳን ዘመን የእስራኤል ሕዝቦች የአሮንና የሌዊን ዝርያዎች ይመለከቱ ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳን ዘመን ደግሞ ከሁለቱ ከኢየሱስና የአሮን ስርዓት ካህናት የትኛው ታላቅ እንደሆነ ብንጠየቅ ያለምንም ጥያቄ ኢየሱስ ታላቅ መሆኑን  መናገር እንችላለን፡፡ ነገር ግን ሰዎች ይህንን ሐቅ በሚገባ ቢያውቁም በእምነታቸው የሚከተሉት ጥቂቶች ናቸው፡፡   
መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ የሆነ መልስ ይሰጠናል፡፡ በመሰውያው ላይ አገልግሎ ከማያውቅ የተለየ ነገድ የመጣው ኢየሱስ ሰማያዊውን ክህነት ወሰደ፡፡  ‹‹ክህነቱ ሲለወጥ ሕጉም ደግሞ ይለወጥ ዘንድ ግድ ነው፡፡››
እግዚአብሄር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝቦች ትዕዛዛቱንና 613 የሕጉን አንቀጾች ሰጣቸው፡፡ ሙሴም ለሕዝቡ በትዕዛዛቱና በሕጎቹ መሰረት መኖር እንዳለባቸው ነገራቸው፡፡ ሕዝቡም ያንኑ ለማድረግ ተስማማ፡፡  
 
እግዚአብሄር የመጀመሪያውን ኪዳን የተወውና ሁለተኛውን ኪዳን ያጸናው ለምንድነው?
ምክንያቱም ሰው በመጀመሪያው ኪዳን መሰረት ለመኖር በጣም ደካማ ስለነበር ነው፡፡ 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእስራኤል ሕዝቦች በፔንታቱክ ማለትም በዘፍጥረት፣ በዘጸአት፣ በዘሁልቁና በዘዳግም ውስጥ ባሉት የእግዚአብሄር ትዕዛዛት ለመኖር ቃል ገብተው ነበር፡፡ እግዚአብሄር እያንዳንዱን ትዕዛዝ ለእነርሱ አወጀላቸውና እነርሱም ለእያንዳንዱ ትዕዛዝ ያለ ምንም ማመንታት ‹‹አዎ›› አሉ፡፡
ሆኖም ከዘዳግም በኋላ ከኢያሱ ዘመን ጀምሮ በእግዚአብሄር ትዕዛዛት መሰረት በጭራሽ መኖር እንዳልቻሉ እናያለን፡፡ ከመሳፍንት ጀምሮ እስከ 1ኛ ነገሥትና 2ኛ ነገሥት ድረስ መሪዎቻቸውን ማሳጣት ጀመሩ፡፡ በኋላም በተቀደሰው ድንኳን ውስጥ የሚከናወነውን የመስዋዕት ስርዓት እስከለውጡ ድረስ በሰበሱ፡፡ 
በመጨረሻም በሚልክያስ ውስጥ ምንም እንኳን እግዚአብሄር ነውር የሌለበት ቁርባን እንዲያቀርቡ ያዘዛቸው ቢሆንም ሊቀርቡ ብቃት የሌላቸው እንስሶችን አቀረቡ፡፡ ካህናቶቹንም ‹‹እባካችሁ እለፉትና ይህንን ተቀበሉ›› በማለት ለመኑዋቸው፡፡ በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት መስዋዕቶችን በማቅረብ ፋንታ ሕጉን በዘፈቀደ ለወጡት፡፡   
የእስራኤል ሕዝቦች በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ጊዜም እንኳን የእግዚአብሄርን ሕግ ሙሉ በሙሉ ጠብቀውት አያውቁም፡፡ በሥርዓቱ ውስጥ የተገለጠውን ደህንነት ረሱትና ቸልም አሉት፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር የመስዋዕት ስርዓቱን መለወጥ ነበረበት፡፡ እግዚአብሄር በኤርምያስ ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን አደርጋለሁ፡፡››   
ኤርምያስ 31፡31-34ን እንመልከት፡- ‹‹እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል እግዚአብሄር፡፡ ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝኩበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፡፡ እነርሱ በቃል ኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ቸል አልኩዋቸው ይላል እግዚአብሄር፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል እግዚአብሄር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፡፡ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፡፡ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፡፡ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን እያንዳንዱም ወንድሙን እግዚአብሄርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፡፡ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና ይላል እግዚአብሄር፡፡ በደላቸውን እምራቸዋለሁና ሐጢአታቸውን ከእንግዲህ ወዲያ አላስብምና፡፡››      
እግዚአብሄር አዲስ ኪዳን እንደሚያደርግ ተናግሮዋል፡፡ አስቀድሞ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ኪዳን ተጋብቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱ በእግዚአብሄር ቃል መኖር ተሳናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ ከሕዝቡ ጋር አዲስ የደህንነት ኪዳን ለማድረግ ወሰነ፡፡  
እነርሱ በእግዚአብሄር ፊት ‹‹አንተን ብቻ እናመልካለን፡፡ በቃሎችህና በትዕዛዛቶችህም እንኖራለን›› በማለት ማሉ፡፡ እግዚአብሄርም ‹‹በፊቴ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑላችሁ›› ብሎ ነገራቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝቦችም ‹‹በእርግጥም አንዳች ሌላ አምላክን አናመልክም፡፡ የእኛ ብቸኛ አምላካችን አንተ ነህ፤ አንዳች ሌላ አምላክ አይሁኑላችሁ›› ብሎ ነገራቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝቦችም ‹‹በእርግጥም አንዳች ሌላ አምላክን አናመልክም፡፡ የእኛ ብቸኛ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሌላ አንዳች አምላክ በጭራሽ አይኖረንም›› አሉ፡፡ ነገር ግን መሃላቸውን መጠበቅ ተሳናቸው፡፡  
የሕጉ መሰረት አስርቱን ትዕዛዛት ይዞዋል፡፡ ‹‹በፊቴ አንዳች ሌሎች አማልክቶች አይኑሩዋቸው፡፡ ለራሳችሁ አንዳች የተቀረጸ ምስል ወይም የማንኛውም ነገር ምሳሌ አይሁንላችሁ፡፡ አትስገዱላቸው፤ አታምልኩዋቸውምም፡፡ የሰንበትን ቀን ትቀድሱት ዘንድ አስቡ፡፡ የጌታ አምላካችሁን ስም በከንቱ አትጥሩ፡፡ አባትና እናታችሁን አክብሩ፤ አትግደሉ፤ አታመንዝሩ፤ አትስረቁ፡፡ በባልንጀራችሁ ላይ በሐሰት አትመስክሩ፡፡ የባልንጀራችሁን ቤት አትመኙ፡፡ (ዘጸአት ምዕራፍ 20)     
ሕጉ በ613 ዝርዝር አንቀጾች በንዑስ ተከፋፍሎ በዘመናቸው ሁሉ እንዲጠብቁዋቸው ተሰጥተዋቸው ነበር፡፡ ‹‹በሴቶች ላይ ማድረግ የማይገባቸውን፣ በወንዶች ልጆች ላይ ማድረግ የማይገባቸውን፣ በእንጀራ እናቶች ላይ ማድረግ የማይገባቸውን…›› የእግዚአብሄር ሕግ መልካም ነገሮችን ሁሉ እንዲያደርጉና አንዳች ክፉ ነገሮችን እንዳያደርጉ አዘዛቸው፡፡ አስርቱ ትዕዛዛትና 613 አንቀጾች እነዚህ ናቸው፡፡    
ሆኖም በሰው ዘር መካከል የሕጉን አንቀጾች በሙሉ መጠበቅ የቻለ አንድም ሰው አልነበረም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይድኑ ዘንድ ሌላ መንገድ ማዘጋጀት ነበረበት፡፡
ክህነቱ የተለወጠው መቼ ነው? ኢየሱስ ወደዚህ አለም ከመጣ በኋላ የክህነት ስርዓቱ ተለውጦዋል፡፡ ኢየሱስ ክህነቱን ከአሮን ዘር ስርዓት ካህናት በሙሉ ተቀበለ፡፡ እርሱ በሌዊ ስርዓት ውስጥ ላሉት ካህናት የውርስ መብት የነበረውን የድንኳኑን መስዋዕት የመገናኛውን ድንኳን መስዋዕት ገለል አደረገ፡፡ እርሱ ብቻ ሰማያዊውን ሊቀ ክህነት አገለገለ፡፡
እርሱ ወደዚህ ዓለም የመጣው የአሮን ዘር ሆኖ ሳይሆን የነገሥታት ቤት የሆነው የይሁዳ ዝርያ ሆኖ ነው፡፡ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት መስዋዕት ሆኖ ራሱን በማቅረብ የሰውን ዘር ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው አዳነ፡፡  
ራሱን በማቅረብም የሐጢያትን ችግር መፍታት አስቻለን፡፡ የሰውን ዘር ሐጢያት በሙሉ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ መስዋዕት አማካይነት አነጻ፡፡ እርሱ ለሐጢያት ሁሉ አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቀረበ፡፡  
 
 
ከክህነት ሥርዓቱ መለወጥ ጋር ተያይዞ የሕግ ለውጥ ነበር፡፡ 
 
የተለወጠው የደህንነት ሕግ ምንድነው? 
አንዱ የኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መስዋዕት፡፡ 

ውድ ጓደኞቼ የብሉይ ኪዳን ክህነት ሥርዓት በአዲስ ኪዳን ተለውጦዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከሌዊ ቤት ከሆኑት የአሮን ዝርያዎች መካከል የሆነው ሊቀ ካህን ባለፈው ዓመት እስራኤሎች ለሰሩዋቸው ሐጢያቶች የማስተሰርያ መስዋዕት አቀረበ፡፡ ሊቀ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባ፡፡ መስዋዕት የሆነውን እንስሳ ደም ይዞ ወደ ስርየት መክደኛው ሄደ፡፡ ከመጋረጃውም በስተ ጀርባ ወዳለው ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለው ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር፡፡   
ነገር ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት በኋላ የአሮን ክህነት ወደ እርሱ ተላልፎዋል፡፡ ኢየሱስ ዘላለማዊውን ክህነት ወሰደ፡፡ የሰው ዘር ከሐጢያቶቻቸው በሙሉ እንዲድኑም ራሱን በማቅረብ ዘላለማዊውን ክህነት አገለገለ፡፡  
በብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህኑ ለራሱ ሕዝብ ማገልገል ከመቻሉ በፊት እጆቹን በወይፈኑ ራስ ላይ በመጫን የራሱን ሐጢያቶች ማስተሰረይ ነበረበት፡፡ እጆቹን ጭኖ ‹‹አቤቱ ሐጢያት ሰርቻለሁ›› በማለት ሐጢያቶቹን ያሻግራል፡፡ ከዚያም እንሰሳውን በማረድ ደሙን በስርየት መክደኛው ላይና ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ 
ሊቀ ካህኑ አሮን ራሱ ብቁ ካልሆነ ሕዝቡም ምን ያህል ደካማ እንደሚሆን ማሰብ ትችላላችሁ፡፡ የሌዊ ልጅ የሆነው ሊቀ ካህኑ አሮን ራሱ ሐጢያተኛ ስለነበር የራሱንና የቤተሰቡን ሐጢያቶች ለማስተሰረይ ወይፈን ማቅረብ ነበረበት፡፡ 
ጌታ በኤርምያስ ምዕራፍ 31 ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል፡- ‹‹ኪዳኑን አፈርሳለሁ፡፡ ኪዳንን ከእናንተ ጋር ገብቻለሁ፡፡ እናንተ ግን አልጠበቃችሁትም፡፡ ስለዚህ ሊቀድሳችሁ ያልቻለውን የመጀመሪያውን ኪዳንም አስወግድና አዲስ የደህንነት ኪዳንን እሰጣችኋለሁ፡፡ ከእንግዲህ በትዕዛዛቶቼ አማካይነት አላድናችሁም፡፡ ነገር ግን ይልቁንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ደህንነትን አቀርብላችኋለሁ፡፡››  
እግዚአብሄር አዲስ ኪዳንን ሰጠን፡፡ ጊዜው በደረሰ ጊዜ ኢየሱስ በሰው አምሳል ወደዚህ ዓለም መጣ፤ የዓለምን ሐጢያቶች ለመውሰድ ራሱን አቀረበና በእርሱ የምናምነውን ለማዳን በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ በጥምቀቱ አማካይነትም የሰውን ዘር ሁሉ ሐጢያቶች ወሰደ፡፡     
የእግዚአብሄርም ሕግ ተገለለና በሌላ ተተካ፡፡ የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት ኖረው ቢሆን ኖሮ መዳን ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደዚያ ማድረግ ተሳናቸው፡፡ ‹‹ሐጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡›› (ሮሜ 3፡20) 
እስራኤሎች ሐጢያተኞች መሆናቸውንና ሕጉም ሊያድናቸው እንዳልቻለ ይገነዘቡ ዘንድ የእግዚአብሄር ፍላጎት ነበር፡፡ እርሱ ያዳናቸው በውሃውና በመንፈሱ የደህንነት ወንጌል እንጂ በሥራቸው አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ወሰን በሌለው ፍቅሩ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም አማካይነት ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ መዳን የምንችልበትን አዲስ ኪዳን ሰጠን፡፡ 
የጥምቀቱንና የደሙን ትርጉም ሳታውቁ በኢየሱስ የምታምኑ ከሆነ እምነታችሁ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ ያንን ስታደርጉ ልክ በኢየሱስ ፈጽሞ እንዳላመናቸሁ ሁሉ ይበልጥ ትታወካላችሁ፡፡ 
እግዚአብሄር የሰውን ዘር ከሐጢያቶቹ ለማዳን አዲስ ኪዳን ማድረግ እንደነበረበት ተናገረ፡፡ ከዚህ የተነሳ እኛ በሕግ ሥራዎች ሳይሆን በውሃና በደም አማካይነት ጻድቅ በሆነው የደህንነት ሕግ ድነናል፡፡  
ይህ ዘላለማዊ ተስፋው ነበር፤ በኢየሱስ ለምናምነውም ለእኛ ተስፋውን ፈጸመልን፡፡ ስለ ኢየሱስ ታላቅነትም ነገረን፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉት የአሮን ካህናት ስርዓት ጋር በማነጻጸርም እንዴት ታላቅ እንደሆነ ነገረን፡፡  
እኛ በኢየሱስ ውሃና ደም አማካይት በደህንነት በማመን ልዩ ሆነናል፡፡ እባካችሁ ይህንን በጥንቃቄ አጢኑት፡፡ መጋቢያችሁ ምንም ያህል የተማረና የተነገረለት ቢሆንም እንዴት ከኢየሱስ ሊበልጥ ይችላል? ይህ ሊሆን የሚችልበት ምንም አይነት መንገድ የለም፡፡ እኛ ልንድን የምንችለው በእውነተኛው የውሃና የደም ወንጌል ብቻ እንጂ የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት በመታዘዝ ብቻ አይደለም፡፡ የክህነት ስርዓቱ እንደተለወጠ ሁሉ የደህንነት ሕጉም እንዲሁ ተለውጦዋል፡፡ 
 
 
የእግዚአብሄር ፍቅር በላጭነት፡፡ 
 
ከእግዚአብሄር ሕግና ከፍቅሩ የሚበልጠው የትኛው ነው?
ፍቅሩ ነው፡፡

እኛ ልንድን የምንችለው በኢየሱስ ስናምን ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ እንዴት እንዳዳነን ማወቃችን እግዚአብሄር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ ታዲያ በትዕዛዛቶቹ በማመንና በእግዚአብሄር ፍቅር በማመን መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?   
ሕግ አክባሪዎች ከእግዚአብሄር ይልቅ በቤተክርስቲያን ትምህርቶችና በግል ልምምዶች ላይ የበለጠ ያተኩራሉ፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ከልብና ሙሉ በሙሉ ማመን የሚመጣው በውሃና በመንፈስ አማካይነት በተፈጸመው ታላቅ ደህንነት በማመን ነው፡፡  
ዛሬም እንኳን ብዙዎች የአዳም ሐጢያት ይቅር ተብሎዋል ይላሉ፤ ነገር ግን ለዘወትር ሐጢያቶቻቸው ንስሐ መግባት እንዳለባቸው ያምናሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ይህንን አምነው በብሉይ ኪዳን ትዕዛዛቶች መሰረት ለመኖር ይሞክራሉ፡፡ እነርሱ በውሃና በመንፈስ የመጣውን ኢየሱስን ደህንነት በላጭነት አሁንም አልተረዱትም፡፡  
እስራኤሎች በብሉይ ኪዳን ከሐጢያቶቻቸው ለመዳን በእግዚአብሄር ሕግ መኖር ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን መዳን አልቻሉም፡፡ እግዚአብሄር ድካማችንንና ብቁ አለመሆናችንን ስለሚያውቅ ትዕዛዛቱን ገለል አደረጋቸው፡፡ በሥራዎቻችን ብቻ ፈጽሞ መዳን አንችልም፡፡ ኢየሱስ የሚያድነን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት እንደሆነ ተናግሮዋል፡፡ እርሱ ‹‹እኔ ራሴ ሁላችሁንም ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ›› አለ፡፡ እግዚአብሄርም በዘፍጥረት ውስጥ የተነበየው ይህንን ነው፡፡   
‹‹እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ፡፡›› (ዘፍጥረት 3፡15) አዳምና ሔዋን ሐጢያትን ከሰሩና ከወደቁ በኋላ ሐጢያቶቻቸውን ከእግዚአብሄር ለመደበቅ የበለስ ቅጠል ልብሶችን አበጁ፡፡ እግዚአብሄር ግን ጠራቸውና የደህንነት ምሳሌ ይሆናቸው ዘንድ የቆዳ ልብሶችን አበጀላቸው፡፡ ዘፍጥረት ስለ ሁለት አይነት የደህንነት ልብስ ይናገራል፡፡ አንዱ የተሰራው ከበለስ ቅጠሎች ሲሆን ሌላው የተሰራው ከቆዳዎች ነበር፡፡ የትኛው የበለጠ ጥሩ እንደሆነ ታስባላችሁ? በእርግጥ የእንስሳ ሕይወት ሰው ለመጠበቅ የተሰጠ በመሆኑ የቆዳው ልብስ የበለጠ ተመራጭ ነው፡፡   
የበለስ ቅጠል ልብስ በቶሎ ያረጃል፡፡ እንደምታውቁት የበለስ ቅጠል በሰው እጅ ላይ ያሉ አምስት ጣቶችን ይመስላል፡፡ ስለዚህ የበለስ ቅጠል ልብሶችን መልበስ ማለት የአንድን ሰው ሐጢያት ከመልካም ምግባሮች ጀርባ መደበቅ ማለት ነው፡፡ ይህንን ቅጠል ለብሳችሁ ብትቀመጡ ወዲያውኑ ይቀደዳል፡፡ ልጅ እያለሁ ከተመሳሳይ ቅጠሎች የጦር መሳርያ መስራት አዘወትር ነበር፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጅ ሥጋ ቅድስናን የማይቻል ያደርገዋል፡፡    
ሆኖም የውሃውና የደሙ ደህንነት የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ሐጢያተኞችን በሙሉ ማዳኑ የእግዚአብሄርን ፍቅር በላጭነት ለመመስከር ከበቂም በላይ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር ይህን ያህል ታላቅ ነው፡፡  
 
 
አሁንም ድረስ በእግዚአብሄር ሕግ የሚያምኑ ሰዎች፡፡  
 
ሕግ አክባሪዎች በሥራዎቻቸው በየቀኑ አዳዲስ መጎናጸፊያዎችን የሚሰሩት ለምንድነው?
ሥራዎቻቸው ጻድቅ ሊያደርጉዋቸው እንደማይችሉ ስለማያውቁ ነው፡፡  

መጎናጸፊያዎቻቸውን ከበለስ ቅጠል የሚሰሩ ሰዎች በሕግ ላይ የተመሰረተ ሕይወትን ይመራሉ፡፡ እነዚህ የተደናበሩ ምዕመናን በየጊዜው መጎናጸፊያዎቻቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ አዳዲስ መጎናጸፊያዎችን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ‹‹ውድ እግዚአብሄር ባለፈው ሳምንት ብዙ ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡ ነገር ግን ጌታ አንተ በመስቀል ላይ እንዳዳንከኝ አምናለሁ፡፡ አቤቱ እባክህ ሐጢያቶቼን በመስቀሉ ደም እጠብልኝ!›› በዚያው ጊዜና እዚያው አዲስ መጎናጸፊያ ይሰፋሉ፡፡ ‹‹ኦ! ጌታ ይመስገን ሃሌሉያ!››
ነገር ግን ወዲያውኑ ቤታቸው ሲደርሱ አዲስ መጎናጸፊያ መስፋት ይኖርባቸዋል፡፡ ለምን? አሮጌው አርጅቷልና፡፡ ‹‹አቤቱ ባለፉት ሦስት ቀናት እንደገና ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡ እባክህ ይቅር በለኝ፡፡›› በተደጋጋሚ አዳዲስ የንስሐ መጎናጸፊያዎችን ይሰሩና ይለብሳሉ፡፡    
በመጀመሪያ ልብሶቹ ለተወሰኑ ቀናት ያህል ሊያገለግሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ በየቀኑ አዳዲስ መጎናጸፊያዎች ያስፈልጉዋቸዋል፡፡ በእግዚአብሄር ሕግ ለመኖር ስለማይችሉ ሁልጊዜም በራሳቸው የሚያፍሩ ይሆናሉ፡፡ ‹‹ኦ! ይህ በጣም የሚያሳፍር ነው፡፡ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ አሁንም ሐጢያትን አድርጌአለሁ!›› አዳዲስ የንስሐ ልብሶችን መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ዛሬ ከበለስ ቅጠል ልብስን መስራት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡›› አዲስ ልብስ ለመስፋትም ይለፋሉ፡፡    
እንደዚህ አይነት ሰዎች ሁልጊዜም ወደ ጌታ ሲጮሁ ሐጢያቶቻቸውን ለመናዘዝ ነው፡፡ ከንፈሮቻቸውን ይነክሱና ‹‹እግዚአብሄር ሆይ!›› በማለት አምላክን ይጠራሉ፡፡ በየቀኑም አዳዲስ መጎናጸፊያዎችን በመስፋት ይቀጥላሉ፡፡ ይህንን ማድረግ ሲሰለቻቸውስ ምን ያደርጋሉ?   
በዓመት አንዴ ወይም ሁለት ጊዜ ወደ ተራሮች በመሄድ ይጸልያሉ፤ ይፆማሉ፡፡ ጠንካራና በቀላሉ የማያረጁ መጎናጸፊያዎችን ለመስራት ይሞክራሉ፡፡ ‹‹አቤቱ ሐጢያቶቼን ሁሉ አንጻልኝ፡፡ እባክህ አድሰኝ፡፡ ጌታ ሆይ በአንተ አምናለሁ፡፡›› ሌሊት መጸለይ የተሻለ ይመስላቸዋል፡፡ ስለዚህ ቀን ያርፋሉ፤ ሲጨልም ወዲያውኑ ባለ በሌለ ሐይላቸው ዛፎችን የሙጥኝ ብለው ወይም ወደ ጨለማ ዋሻዎች በመሄድ ወደ እግዚአብሄር ይጮሃሉ፡- ‹‹ጌታ ሆይ አምናለሁ!›› ‹‹♪ንስሐ እገባለሁ፡፡ በተደቆሰ አእምሮም ልቤን እሞላለሁ♪›› ድምጻቸውንም ከፍ አድርገው ‹‹አምናለሁ›› ብለው ይጮሃሉ፡፡ በዚህ መንገድ ለረጅም ጊዜ እንደሚቆይ ተስፋ የሚያደርጉትን የተለየ መጎናጸፊያ ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን በጭራሽ አይዘልቅም፡፡
በተራራ ላይ ከሚደረጉ ጸሎቶች መውረድ ምንኛ የሚያነቃቃ ነው! ልክ ሕይወትን እንደሚያድስ ነፋሻማ አየር ወይም በዛፎችና በአበቦች ላይ እንደሚርከፈከፍ የጸደይ ዝናብ ነፍሶቻቸው በሁሉን ቻዩ አምላክ ሰላምና ጸጋ የተሞሉ ናቸው፡፡ ከተራራው መንፈስ በላይ ይበልጥ ንጹህ የሆነ ስሜት እየተሰማቸውም ልዩ የሆኑትን አዳዲስ መጎናጸፊያዎች ለብሰው ዓለምን ይጋፈጣሉ፡፡
ነገር ግን ወደ ቤታቸውና ወደ ቤተክርስቲያናቸው እንደተመለሱና እንደገና መኖር እንደጀመሩ ወዲያውኑ ይቆሽሹና ማርጀት ይጀምራሉ፡፡  
ጓደኞቻቸው ‹‹የት ነበራችሁ?›› ብለው ይጠይቃሉ፡፡
‹‹ለጥቂት ጊዜ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄጄ ነበር፡፡›› 
‹‹የተወሰነ ክብደት የቀነሳችሁ ትመስላላችሁ!›› 
‹‹አዎን ነገር ግን ያ ሌላ ታሪክ ነው፡፡›› 
በጭራሽ ስለ መጾማቸው አይናገሩም፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው ይጸልያሉ፡፡ ‹‹ሴቶችን በጭራሽ ለፍትወት አልፈልጋቸውም፡፡ በጭራሽ አልዋሽም፡፡ የባልንጀራዬን ቤት አልመኝም፡፡ ሰውን ሁሉ እወዳለሁ፡፡›› 
ነገር ግን ያማሩ ቅልጥሞች ያሉዋት ውብ ደልዳላ ሴት በሚያዩበት ቅጽበት በልቦቻቸው ውስጥ ያለው ቅድስና ወዲያውኑ ወደ ንጹህ ፍትወት ይቀየራል፡፡ ‹‹ያ ቀሚስ ምን ያህል አጭር እንደሆነ ተመልከት! ቀሚሶች እያጠሩ በመሄድ ላይ ናቸው! እነዚያን ቅልጥሞች እንደገና አየሁ! ኦ! አይሆንም! ጌታ ሆይ እንደገና ሐጢያት ሰራሁ!››     
ሕግ አክባሪዎች ጻድቃን ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ በየቀኑ አዳዲስ መጎናጸፊያዎችን እንደሚሰሩ ማወቅ አለባችሁ፡፡ ሕግ አጥባቂነት በበለስ ቅጠሎች ማመን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የተሳሳተ እምነት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት ጻድቅ ሆነው ለመኖር አጥብቀው ይሞክራሉ፡፡ በተራራ ላይ ቆመው ላንቃቸው እስኪበጠስ ድረስ ይጮሃሉ፡፡ 
ሕግ አክባሪዎች በቤተክርስቲያን የጸሎት ስብሰባዎችን ሲመሩ የተለዩና መስህብ ያላቸው ይመስላሉ፡፡ ‹‹በሰማይ ያለኸው ቅዱስ አባታችን! ያለፈውን ሳምንት በሙሉ በሐጢያት አሳልፈናል፡፡ እባክህ ይቅር በለን፡፡…›› እንባዎችን ያፈሳሉ፤ ጉባኤውም ይከተላቸዋል፡፡ ለራሳቸውም ‹‹ይህ ሰው በተራሮች ላይ በመጾምና በመጸለይ ረጅም ጊዜ ያሳለፈ መሆን አለበት›› ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን የዚህ ሰው እምነቱ በሕግ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ የጸሎቱ ጊዜ እንኳን በአግባቡ ሳያበቃ የሕግ አክባሪው ልብ በዕብሪትና በሐጢያት መሞላት ይጀምራል፡፡
ሰዎች ከበለስ ቅጠል አንድ የተለየ ልብስን ቢሰሩ ምናልባትም ለሁለት ሦስት ወራት ድረስ ሊቆዩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እነዚህ ልብሶች እያረጁና የአገልግሎት ዘመናቸውም እያለቀ ይመጣል፡፡ አዲስ መጎናጸፊያ በመስራትም ግብዝ የሆነውን ሕይወታቸውን መኖር ይቀጥላሉ፡፡ ሕግ አክባሪዎች ለመዳን ሲሉ የሚኖሩት ሕይወት ይህ ነው፡፡ ያለ ማቋረጥ ከበለስ ቅጠሎች አዳዲስ መጎናጸፊያዎችን ይሰራሉ፡፡   
ሕግ አጥባቂነት በበለስ ቅጠሎች የተመሰለ እምነት ነው፡፡ ሕግ አክባሪዎች ‹‹ሁላችሁም ባለፈው ሳምንት ሐጢያት ሰርታችኋል፡፡ አልሰራችሁም? እንግዲያውስ ንስሐ ግቡ›› ብለው ይነግሩዋቸዋል፡፡   
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ‹‹ንስሐ ግቡ! ጸልዩ!›› በማለት ይጮሁባችኋል፡፡  
ሕግ አክባሪ ድምጹን እንዴት ቅዱስ እንደሚያስመስል ያውቅበታል፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ አዝናለሁ፡፡ በሕጉ አልኖርሁም፡፡ ትዕዛዛቶችህን አልጠበቅሁም፡፡ አቤቱ ይቅር በለኝ፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ ይቅር በለኝ፡፡››   
ምንም እንኳን በሕጉ መሰረት በጥብቅ ለመኖር የሚፈልጉ ቢሆንም እንደዚያ ሊኖሩ ግን ፈጽሞ አይችሉም፡፡ በእርግጥም እንዲህ በማድረጋቸው እነርሱ የእግዚአብሄርን ሕግና እግዚአብሄርን ራሱንም እየተፈታተኑት ነው፡፡ እነርሱ በእግዚአብሄር ፊት ዕብሪተኞች ናቸው፡፡    
 
 
የቹዳል ቤይ ፍላጎቶች፡፡  
 
እግዚአብሄር ሕጉን ወደ ጎን የተወው ለምንድነው?
እኛን ከሐጢያት ለማዳን ጥቅም ስለሌለው ነው፡፡ 

በአንድ ወቅት ቹዳል ቤይ ተብሎ የሚጠራ ወጣት ነበር፡፡ በ1950ዎቹ የኮርያውያን ጦርነት ወቅት የኮሚዩኒስት ወታደሮች መጥተው ጽኑ የሆነውን ሃይማኖታዊ እምነቱን አስጥለው ኮሚዩኒስት ሊያደርጉት በሰንበት ቀን ግቢያቸውን ያጸዳ ዘንድ ጠየቁት፡፡ ይህ ሃይማኖታዊ ሰው ግን ትዕዛዞቻቸውን ለመታዘዝ እምቢተኛ ሆነ፡፡ እነርሱ ቢወተውቱትም ይህ ወጣት ግን እምቢተኛ ሆነ፡፡  
በመጨረሻም ወታደሮቹ ይህን ሰው ከዛፍ ጋር አሰሩትና መሳሪያዎችን ደገኑበት፡፡ ‹‹የምትመርጠው የትኛውን ነው? ግቢውን መጥረግ ወይስ መሞት?›› ብለው ጠየቁት፡፡   
ውሳኔ እንዲወስን ባስገደዱት ጊዜ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹በተቀደሰው የሰንበት ቀን ከምሰራ መሞት ይሻለኛል፡፡››  
‹‹አንተ ራስህ ምርጫህን መርጠሃል፡፡ እኛም ግዴታችንን በደስታ በአንተ ላይ እንወጣለን፡፡›› 
ያን ጊዜ በጥይት መተው ገደሉት፡፡ በኋላም ያልተናወጠውን ሃይማኖታዊ እምነቱን ለማስታወስ የቤተክርስቲያን መሪዎች ዲያቆን አድርገው ሾሙት፡፡ 
ጽናቱ ጠንካራ ቢሆንም ሃይማኖታዊ እምነቱ ፈሩን የለቀቀ ነበር፡፡ ግቢውን ያልጠረገውና ወንጌልን ለእነዚያ ወታደሮች ያልሰበከው ለምንድነው? ለምን እልኸኛ ሆኖ ሞተ? እግዚአብሄር በሰንበት ቀን ስላልሰራ ያመሰግነዋልን? አያመሰግነውም፡፡ 
እኛ መንፈሳዊ ሕይወትን መምራት ይገባናል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት አስፈላጊው ነገር እምነታችን እንጂ ሥራዎቻችን አይደሉም፡፡ የቤተክርስቲያን መሪዎች እንደ ቹዳል ቤይ ያለን ሰው ማወደስ ይሻሉ፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያናቸውን የበላይነትና ትክክለኛነት ማሳየት ይፈልጋሉና፡፡ ነገሩ ኢየሱስን ከተገዳደሩት ግብዝ ፈሪሳውያን ጋር ይመሳሰላል፡፡  
ከሕግ አክባሪዎች ልንማር የምንችለው ምንም ነገር የለም፡፡ መማር ያለብን ስለ መንፈሳዊ እምነት ነው፡፡ ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰ ማወቅና በትክክለኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ማመን አለብን፡፡  
በመጀመሪያ ለጥያቄዎቻችን መልስ ማግኘት አለብን፡፡ ከዚያም ዳግም ይወለዱ ዘንድ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ወንጌልን ለማሰራጨት መሞከር አለብን፡፡ ሕይወታችን ለመንፈሳዊ ሥራዎች አሳልፈን መስጠት ይገባናል፡፡  
አንድ ሰባኪ ‹‹እንደ ወጣቱ ቹዳል ቤይ ሁኑ፤ ሰንበትንም አክብሩ!›› ቢላችሁ ይህ ሰው ያለ ምንም ጥርጥር የሚፈልገው እናንተ በየእሁዱ ቤተክርስቲያን እንድትሄዱለት እየሞከረ ብቻ ነው፡፡   
አብርሆትን የሚያረጋግጥ ሌላ ታሪክ ይኸውላችሁ፡፡ በየእሁዱ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ስትል በብዙ መከራዎች ውስጥ ያለፈች አንዲት ሴት ነበረች፡፡ አማቶችዋ ክርስቲያኖች ስላልነበሩ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳትሄድ ለመከልከል አብዝተው ይሞክሩ ነበር፡፡ በዕለተ እሁድ ሥራ እንድትሰራ ነገርዋት፡፡ ነገር ግን በየቅዳሜዎቹ ምሽት ወደ እርሻ ሄዳ በጨረቃ ብርሃን በመስራት ቤተሰቡ በዕለተ እሁድ ወደ ቤተክርስቲያን ከመሄድ ለመከልከል አንዳች ማማኻኛዎችን እንዳያቀርቡ አደረገች፡፡ 
በእርግጥም ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን በየእሁዱ ምን ያህል ታማኞች እንደሆንን ለማሳየት ስንል ብቻ ወደ አምልኮ መምጣት በቂ ነውን? እውነተኛ ታማኝ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም ተወልዶዋል፡፡ እውነተኛ እምነት የሚጀምረው በዳግም ውልደት ነው፡፡
በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት በመኖር ልትድኑ ትችላላችሁን? በፍጹም፡፡ እኔ እየነገርኋችሁ ያለሁት ሕጉን እንድትተዉት አይደለም፡፡ ነገር ግን በሰውኛ የሕጉን አንቀጾች በሙሉ መጠበቅ የማይቻል መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ 
በያዕቆብ መልዕክት 2፡10 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፡፡›› ስለዚህ በመጀመሪያ እንዴት ከውሃና ከመንፈስ ወንጌል መወለድ እንደምትችሉ አስቡ፡፡ በመቀጠልም ይህን ወንጌል ወደምትሰሙበት ቤተክርስቲያን ሂዱ፡፡ ዳግም ከተወለዳችሁ በኋላም የታመነ ሕይወት ልትኖሩ ትችላላችሁ፡፡ በመጨረሻም ጌታ በሚጠራችሁ ጊዜ በፊቱ በደስታ ልትቀርቡ ትችላላችሁ፡፡ 
ወደ ሐሰተኛ ቤተክርስቲያኖች በመሄድ ጊዜያችሁን አታባክኑ፤ የተዛቡ ምጽዋቶችን በመስጠት ገንዘባችሁን አታባክኑ፡፡ ሐሰተኛ ካህናት ወደ ሲዖል ከመሄድ ሊጠብቁዋችሁ አይችሉም፡፡ በመጀመሪያ ዳግም ለመወለድ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አድምጡና ዳግም ተወለዱ፡፡ 
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበትን ምክንያት አስቡ፡፡ በሕጉ መሰረት በመኖር የእግዚአብሄርን መንግሥት መውረስ የምንችል ቢሆን ኖሮ እርሱ ወደዚህ ምድር መምጣት ባላስፈለገው ነበር፡፡ እርሱ ከመጣ በኋላ የክህነቱ ሥርዓት ተለወጠ፡፡ ሕግን መጠበቅ ያለፈ ጊዜ ትዝታ ሆነ፡፡ ከመዳናችን በፊት በሕጉ መሰረት በመኖር መዳን እንደምንችል እናስብ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የእውነተኛ እምነት ምልክት አይደለም፡፡  
ኢየሱስ በፍቅሩ በጥምቀቱ ውሃ፣ በደሙና በመንፈሱ ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ አዳነን፡፡ በዮርዳኖስ በመጠመቁ፣ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰሱና በትንሳኤው ደህንነታችንን ፈጸመው፡፡ 
እግዚአብሄር የመጀመሪያዎቹን ስርዓቶች ገለል ያደረጋቸው ደካማና ረብ የለሽ በመሆናቸው ነው፡፡ ‹‹ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፡፡ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትዕዛዝ ተሸራለች፡፡ ወደ እግዚአብሄርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል፡፡ እነርሱም ያለ መሃላ ካህናት ሆነዋልና፡፡›› (ዕብራውያን 7፡19-20) ኢየሱስ መሃላ አደረገና በጥምቀቱና በደሙ ከሐጢያት ሁሉ አዳነን፡፡ ከሕግ አክባሪነት የመነጨ ሰማዕትነት ፍሬ አልባ ሞት ነው፡፡ ብቸኛው እውነተኛ እምነት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ነው፡፡    
ፍሬያማ እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡ ለነፍሳችሁ ጥሩ የሚመስላችሁ የትኛው ነው? በየጊዜው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድና ሕጉን በመጠበቅ መኖር ይሻላል ወይስ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ወደሚሰበክበት ትክክለኛው የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በመሄድ ዳግም መወለድ? የትኛው ቤተክርስቲያን ወይም ሰባኪ ነው ለነፍሳችሁ የሚበጀው? ይህንን በደንብ አስቡበትና ለነፍሳችሁ ጥሩ ይሆናል የምትሉትን ምረጡ፡፡  
እግዚአብሄር ነፍሳችሁን የሚያድነው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌለ ቃላቶች በያዘ ሰባኪ አማካይነት ነው፡፡ ሁሉም ሰው ለራሱ ነፍስ ሐላፊነቱን መውሰድ አለበት፡፡ እውነተኛ ጠቢብ አማኝ ነፍሱን ለእግዚአብሄር ቃል አሳልፎ የሚሰጥ ነው፡፡  
 
 

ኢየሱስ በመሃላ ካህን ሆነ፡፡ 

 
የሌዊ ስርዓት ዘሮች ካህናት የሆኑት በመሃላ ነበርን?
አልነበረም፡፡ ክህነትን በመሃላ የተቀበለው ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ 

ዕብራውያን 7፡20-21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እነርሱም ያለ መሃላ ካህናት ሆነዋልና፡፡ እርሱ ግን ጌታ፡- አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሃላ ጋር ካህን ሆኖአልና፡፡ ያለ መሃላ ካህን እንዳልሆነ መጠን እንዲሁም ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል፡፡›› 
 መዝሙረ ዳዊት 110፡4 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሄር ማለ አይጸጸትም፡፡›› ጌታ መሃላ አደረገ፡፡ ከእኛም ጋር ቃል ኪዳን ተጋባና ኪዳኑን በተጻፈው ቃሉ አማካይነት አሳየን፡፡ ‹‹እኔ በመልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህን እሆናለሁ፡፡ መልከ ጼዴቅ የጽድቅ ንጉሥ፣ የሰላም ንጉሥና ለዘላለምም ሊቀ ካህን ነው፡፡ ለደህንነታችሁ በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት መሰረት ለዘላለም ሊቀ ካህን እሆናለሁ፡፡››   
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣና ለተሻለው ኪዳን ዋስ ሆነ፡፡ (ዕብራውያን 7፡22) በኮርማዎችና በፍየሎች ደም ፋንታ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለማንጻት በመጠመቅና በመስቀል   ላይ በመድማት መስዋዕት አድርጎ ራሱን አቀረበ፡፡     
በብሉይ ኪዳን ዘመን ሊቀ ካህኑ ሲሞት ልጁ 30 ዓመት በሚሆነው ጊዜ ክህነቱን ይረከባል፡፡ እርሱ ሲያረጅና ልጁም 30 ዓመት ሲሆነው ክህነቱን ለልጁ ያስረክባል፡፡   
በጣም ብዙ የሊቀ ካህናት ዘሮች ነበሩ፡፡ ስለዚህ ዳዊት ሁሉም በየተራ የራሳቸውን ሚና የሚጫወቱበትን ስርዓት ቀየሰ፡፡ ሁሉም የአሮን ዘሮች በሙሉ በክህነት ለማገልገል ቃል ስለተገባላቸው ሁሉም በክህነት የማገልገል መብቱ ነበራቸው፡፡ ሉቃስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡…እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሄር ፊት ሲያገለግል…›› 
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣና የክህነቱን አገልግሎት ለዘላለም ወሰደ፡፡ ሊመጣ ላለው በጎ ነገር ካህን ሆኖ መጣ፡፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድንም ደህንነት ፈጸመ፡፡ 
የአሮን ዘሮች በሥጋቸው ደካሞችና ጎዶሎ ነበሩ፡፡ አንድ ሊቀ ካህን ሲሞት የሚሆነው ምንድነው? ልጁ በተራው ክህነቱን ይረከባል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ያሉ መስዋዕቶች የሰውን ዘር ደህንነት ለማረጋገጥ በጭራሽ በቂ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በሰው ዘር በኩል የሚሆን እምነት በጭራሽ እውነተኛና ሙሉ እምነት ሊሆን አይችልም፡፡ 
በአዲስ ኪዳን ዘመን ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ነገር ግን እርሱ ለዘላለም የሚኖር በመሆኑ በየጊዜው መስዋዕትን ማቅረብ አላስፈለገውም፡፡ በጥምቀቱም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለዘላለም ወሰደ፡፡ በእርሱ የሚያምኑትን በሙሉ ከሐጢያት ነጻ ለማድረግ ራሱን አቀረበና ተሰቀለ፡፡  
አሁን እርሱ ሕያው ነው፤ ስለ እኛ ሊመሰክር በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ውድ አባት እነርሱ አሁንም ጎዶሎ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በእኔ አምነዋል፡፡ ሐጢያቶቻቸውን ከረጅም ጊዜ በፊት አልወሰድሁላቸውምን?›› ኢየሱስ ለደህንነታችን የዘላለም ሊቀ ካህን ነው፡፡  
ምድራዊ ካህናት ሙሉ ሆነው አያውቁም፡፡ በሚሞቱበት ጊዜ ልጆቻቸው ክህነቱን ይወርሳሉ፡፡ ጌታችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ወደዚህ ምድር በመምጣት፣ በአጥማቂው ዮሐንስ  በመጠመቅና ለሐጢያቶቻችን ሁሉ በመስቀል ላይ በመድማት የዘላለም ደህንነትን ፈጸመ፡፡  
‹‹የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› (ዕብራውያን 10፡18) ኢየሱስ እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስ ስለ ደህንነታችን ይመሰክራል፡፡ ከውሃውና ከመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን? 
‹‹ቅዱስና ያለ ተንኮል፣ ነውርም የሌለበት፣ ከሐጢአተኞችም የተለየ፣ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፡፡›› (ዕብራውያን 7፡26) ‹‹ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፡፡ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሃላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል፡፡›› (ዕብራውያን 7፡28)   
ልነግራችሁ የምወደው ነገር ቢኖር ነውር የሌለበት ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ ውሃና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ለአንዴና ለመጨረሻ ከሐጢያቶቻችን እንዳነጻን ነው፡፡ እርሱ ከሐጢያቶቻችን ያዳነን በሕግ ሥራዎች ሳይሆን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውስዱና ለዘላለም ፍርድን በመቀበሉ ነው፡፡ 
እርሱ በዘላለም ደህንነት አማካይነት እኛን ለዘላለም ከሐጢያቶቻቸን ሁሉ እንዳዳነን ታምናላችሁን? ካመናችሁ ድናችኋል፡፡ ካላመናችሁ ስለ ኢየሱስ የዘላለም ደህንነት ብዙ መማር ይኖርባችኋል፡፡ 
እውነተኛ እምነት በጥብቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተመሰረተው ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ይመጣል፡፡ ዘላለማዊው ሰማያዊ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት የዘላለም አዳኛችን ሆነ፡፡   
 
 
እምነታችንን በሚገባ መረዳት አለብን፡፡ 
 
‹‹በኢየሱስ ማመን›› ማለት ምን ማለት ነው?
በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ ማመን ማለት ነው፡፡ 

በትክክለኛው መንገድ እንዴት በኢየሱስ ማመን እንደምንችልና እምነታችንን እንደምናቀና ማሰብ ይኖርብናል፡፡ ተገቢና ትክክለኛ በሆነ መንገድ በኢየሱስ ማመን የምንችለው እንዴት ነው? ይህንን ማድረግ የምንችለው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ ወንጌል በማመን ነው፡፡   
ትክክለኛ እምነት የራሳችንን የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ሳንጨምር በኢየሱስ ሥራ፤ በጥምቀቱና በደሙ ማመን ነው፡፡ ይህ እውነት እንደሆነ ታምናላችሁን? መንፈሳዊ ሁኔታችሁ እንዴት ነው? በራሳችሁ ሥራዎችና ጥረቶች ላይ አብዝታችሁ ትደገፋላችሁን?  
በኢየሱስ ማመን ከጀመርሁ ብዙ ጊዜ ባይሆነኝም ከሕግ አጥባቂነት የተነሳ ለ10 ዓመታት ያህል ተሰቃይቻለሁ፡፡ ውሎ አድሮም በእንደዚያ አይነቱ ሕይወት ተሰላቸሁ፡፡ ስለዚያ ጊዜ ማስታወስ እንኳን አልፈልግም፡፡ ባለቤቴ እዚሁ ተቀምጣለች፡፡ ነገሩ ለእኛ ምን ያህል አስከፊ እንደነበር ታውቃለች፡፡
በየእሁዱ ባለቤቴን ‹‹የእኔ ማር እስቲ ዛሬ እንዝናና!›› እላታለሁ፡፡ 
‹‹ነገር ግን ዛሬ እሁድ ነው!›› 
እሁድ ልብስ እንኳን አታጥብም፡፡ አንድ እሁድ ቀን የውስጥ ሱሪዬ ተቀደደብኝ፡፡ እስከ ሰኞ መጠበቅ እንደሚኖርብኝ ነገረችኝ፡፡ እንዲያውም ሰንበትን በትክክል መጠበቅ እንዳለብን ስሟዘዝ የነበርሁት እኔ ነኝ፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪ ነበር፡፡ በእሁድ ቀናቶች በጭራሽ አርፈን አናውቅም፡፡ ምክንያቱም ሰንበትን በትክክል መጠበቅ አስቸጋሪ ነበር፡፡ እነዚያን ቀናት አሁንም አስታውሳቸዋለሁ፡፡   
ውድ ጓደኞቼ በኢየሱስ በትክክል ለማመን በጥምቀቱና በደሙ ሐጢያቶቻችን በሙሉ መንጻታቸውን ማመን ይኖርብናል፡፡ እውነተኛ እምነት በኢየሱስ መለኮታዊነትና ሰብአዊነት እንደዚሁም በዚህ ዓለም ላይ ባከናወናቸው ነገሮች ሁሉ ማመን ነው፡፡ እውነተኛ ምዕመን በኢየሱስ ቃሎች ሁሉ ያምናል፡፡ 
‹‹በኢየሱስ ማመን›› ማለት ምን ማለት ነው? ይህ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማመን ማለት ነው፡፡ ይህን ያህል ቀላል ነው፡፡ ማድረግ የሚጠበቅብን መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እውነተኛውን ወንጌል ማመን ነው፡፡ እኛ ሁላችን በትክክለኛው መንገድ ማመን አለብን፡፡  
‹‹ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሁን በእኔ ጥረት እንዳልሆነ አውቃለሁ! ሐጢያት በሕግ ይታወቃል፡፡ (ሮሜ 3፡20) አሁን ሁሉንም ነገር ተረድቻለሁ፡፡ እኔ እንደዚያ ያሰብሁት ሕጉ ጥሩ ስለነበር፣ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ስለሆነና በእርሱ መኖር እንዳለብኝ ስላሰብሁ ነው፡፡ አሁንም ድረስ በዚያ ለመኖር ብዙ እጥር ነበር፡፡ ነገር ግን በሕጉ ለመኖር መሞከሬ ስህተት መሆኑን አሁን ተገነዘብሁ፡፡ አሁን የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት መጠበቅ እንደማልችል አየሁ! ስለዚህ በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት ልቤ በክፉ አሳቦችና መተላለፎች የተሞላ እንደሆነ አወቅሁ፡፡ አሁን ሕጉ የተሰጠን በውስጣችን የሐጢያትን እውቀት ለማስቀመጥ እንደሆነ አስተዋልሁ፡፡ ጌታ ሆይ ተመስገን፡፡ ፈቃድህን በተሳሳተ መንገድ ተረድቼ ሕጉን ለመጠበቅ ብዙ ጣርሁ፡፡ ንስሐ እገባለሁ፡፡ አሁን ኢየሱስ ለእኔ ደህንነት እንደተጠመቀና እንደደማ አውቃለሁ! አምናለሁ!››
በግልጽና በንጽህና ማመን አለባችሁ፡፡ ማመን ያለባችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፉት ቃሎች ብቻ ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ዳግም ልትወለዱ የምትችሉበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡  
በኢየሱስ ማመን ማለት ምን ማለት ነው? በጊዜ ሒደት ልናጠናቅቀው የምንችለው ነገር ነውን? እምነታችን የምትለፉበት ሃይማኖት ነውን? ሰዎች ጣዖታትን ሰርተዋል፡፡ ለእነዚያ ጣዖታት የሚስማሙ ሃይማኖቶችንም አበጅተዋል፡፡ ሃይማኖት ሰዎች ወደ አንድ ግብ ለመድረስ የሰውን መልካምነት ለማነሳሳት የሚሰሩበት ሒደት ነው፡፡ 
እምነት ምንድነው? እምነት በእግዚአብሄር ማመንና ወደ እርሱ መመልከት ማለት ነው፡፡ እኛ ወደ ኢየሱስ ደህንነት በመመልከት ለዚህ በረከትም እርሱን እናመሰግነዋለን፡፡ ይህ እውነተኛ እምነት ነው፡፡ በእምነትና በሃይማኖት መካከል ያለውን ልዩነት ካወቃችሁ ስለ እምነት በመረዳታችሁ 100 ማርክ ታገኛላችሁ፡፡     
ዳግም ያልተወለዱ የቃለ እግዚአብሄር ምሁራን በኢየሱስ ማመን ጥብቅ ሃይማኖተኛ ሆነን መኖር እንደሚገባን ይነግሩናል፡፡ ጥብቅ ሃይማኖተኛ ሆነን በመኖር ብቻ ታማኞች ልንሆን እንችላለን? በእርግጥ ጥሩ መሆን አለብን፡፡ ከእኛ ዳግም ከተወለድነው የበለጠ ጥብቅ ሃይማኖተኛ የሆነ ማን አለ?  
ነገር ግን ዋናው ጉዳይ ይህንን የሚናገሩት ለሐጢያተኞች መሆኑ ነው፡፡ በአማካይ በአንድ ሐጢያተኛ ውስጥ 12 አይነት ሐጢያቶች አሉ፡፡ እንዴት በቅድስና ሊኖር ይችላል? ምናልባትም ይህንን በአእምሮው ቢያምንበትም በልቡ ግን አይቀበለውም፡፡ አንድ ሐጢያተኛ ከቤተክርስቲያን ሲወጣ በቅድስና መኖር ከጽንሰ ሐሳብ የዘለለ አይሆንም፡፡ ደመ ነፍሱ ወደ ሐጢያት ይነዳዋል፡፡   
ስለዚህ በመንግሥት ሰማይ የዘላለም ሊቀ ካህን በሆነው አምነን በሕጉ ለመኖር ወይም በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ለማመን በልባችን መወሰን ይኖርብናል፡፡ 
ለሚያምኑ ሰዎች ኢየሱስ እውነተኛ ሊቀ ካህን እንደሆነ ይታወስ፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም አማካይነት የተገኘውን እውነተኛ ደህንነት በማወቅና በማመን ሁላችንም እንዳን፡፡  
 
 
ዳግም የተወለዱት የዓለምን መጨረሻ አይፈሩም፡፡ 
 
ዳግም የተወለዱት ስለ ዓለም መጨረሻ የማይፈሩት ለምንድነው?
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ያላቸው እምነት ነጻ ስለወጣቸው ነው፡፡  

ዳግም የተወለዳችሁ ከሆነ የዓለም መጨረሻ ቢቃረብ ምንም የሚያስጋችሁ ነገር አይኖርም፡፡ ብዙ በኮርያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ዓለም በጥቅምት 28፤ 1992 ዓ.ም ትጠፋለች ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ይህ እንዴት ያለ ምስቅልቅልና አስፈሪ ቀን ይሆን ይላሉ፡፡ ነገር ግን የተናገሩት ሁሉ ውሸት ሆነ፡፡ በተጨባጭ ዳግም የተወለዱ እስከ መጨረሻዋ ቅጽበት ድረስ ወንጌልን እያሰራጩ ጥብቅ ሃይማኖተኛ ሆነው ይኖራሉ፡፡ የዚህ ምድር መጨረሻ እስከሚመጣ ድረስ ማድረግ ያለብን አንድ ነገር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መስበክ ነው፡፡  
ሙሽራው ሲመጣ በተጨባጭ ከውሃና ከመንፈስ የተወለዱት ሙሽሮች ‹‹ኦ በመጨረሻ መጣህ! ሥጋዬ አሁንም ድረስ ጎዶሎ ነው፡፡ አንተ ግን ወደኸኝ ከሐጢያቶቼ ሁሉ አዳንኸኝ፡፡ ስለዚህ በልቤ ውስጥ ሐጢያት የለም፡፡ አቤቱ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ አዳኜ ነህ!›› በማለት በታላቅ ደስታ ይገናኙታል፡፡    
ኢየሱስ ለጻድቃን ሁሉ መንፈሳዊ ሙሽራ ነው፡፡ ሠርጉ የሚከናወነው ሙሽራው ሙሽራይቱን ስለወደዳት እንጂ ሙሽራይቱ ስለወደደችው አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በዚህ ዓለም ላይ እንደዚሁ እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡ በሰማይ ግን ሠርጉ ስለመከናወን የሚወስነው ሙሽራው ነው፡፡ ሙሽሮቹ ማንም ይሁኑ በፍቅርና በደህንነት ስጦታው ላይ ተመስርቶ ማግባት የመረጠው ሙሽራው ነው፡፡ ሠርጉ በሰማይ የሚከናወነው እንደዚህ ነው፡፡    
ሙሽራው ስለ ሙሽሮቹ በሙሉ ያውቃል፡፡  የሚወዳቸው ሙሽሮች በሙሉ ሐጢያተኞች ስለነበሩ በመጠመቅና በመስቀል ላይ በመድማት ራራላቸውና ከሐጢያት ሁሉ አዳናቸው፡፡  
ጌታችን ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ከአሮን ወገን ሆኖ አይደለም፡፡ ወደዚህ ምድር የመጣው ምድራዊ መስዋዕትን ለማቅረብ አይደለም፡፡ ይህንን የሚሰሩ ከአሮን ዘሮች የሆኑ ብዙ ሌዋውያን ነበሩ፡፡    
በእርግጥም የብሉይ ኪዳን መስዋዕቶች ዋናው ተዋናይ ራሱ ኢየሱስ ነበር፡፡ ስለዚህ እውነተኛው ነገር ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ጥላው ምን ሆነ? ጥላው ተወገደ፡፡ 
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ አሮን እንዳደረገው ፈጽሞ መስዋዕቶችን አላቀረብም፡፡ እርሱ ለሐጢያተኞች ደህንነት   በመጠመቅና ደሙን በማፍሰስ ራሱን ለሰው ዘር አቀረበ፡፡ ደህንነትንም በመስቀል ላይ ፈጸመ፡፡  
በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም የሚያምኑ ደህንነት በማያሻማ መልኩ ይመጣላቸዋል፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ያነጻልን ግልጽ ባልሆነ መንገድ አይደለም፡፡ እርሱ ይህን ያደረገው በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ነው፡፡ ‹‹እኔ መንገድና እውነትም ሕይወትም ነኝ፡፡›› (ዮሐንስ 14፡6) ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጣና በጥምቀቱ በሞቱና በትንሳኤው አዳነን፡፡ 
 
 
ብሉይ ኪዳን የኢየሱስ ምሳሌ ነው፡፡ 
 
ሌላ ኪዳን ማጽናት ያስፈለገበት ምክንያት ምንድነው?
ምክንያቱም የመጀመሪያው ኪዳን ደካማና ጥቅም የለሽ ስለነበረ ነው፡፡  

ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ጥላ ነው፡፡ ምንም እንኳን ኢየሱስ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ፈጽሞ መስዋዕቶችን ባያቀርብም ዘላለማዊው የሆነውን ሰማያዊ ክህነት ማለትም የተሻለውን ክህነት አገለገለ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሲወለዱ ጀምሮ በሐጢያት የተሞሉ ስለሆኑ ሐጢያተኞች ሆኑ፡፡ እነርሱ በእግዚአብሄር ሕግ አማካይነት በጭራሽ ጻድቃን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ሌላ ኪዳን አጸና፡፡   
በሰማይ ያለው አባታችን አንድያ ልጁን ወደዚህ ዓለም ላከና በፈንታው በእርሱ ጥምቀት፣ ሞትና ትንሳኤ እምነት እንዲኖረን ጠየቀን፡፡  ይህ የእግዚአብሄር ሁለተኛው ኪዳን ነው፡፡ ሁለተኛው ኪዳን እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንድናምን ይጠይቀናል፡፡ 
ጌታ መቼም ቢሆን መልካም ሥራዎቻችን እየጠየቀን አይደለም፡፡ እርሱ ለመዳን እንዴት እንደምንኖር አይነገረንም፡፡ እርሱ የሚጠይቀን በልጁ አማካይነት በደህንነት እንድናምን ብቻ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙ እንድናምን ይጠይቀናል፡፡ እኛም እሺ ማለት አለብን፡፡  
በመጽሐፍ ቅዱስ የይሁዳ ነገድ የነገሥታት ዘር ነበር፡፡ እስከ ንጉሥ ሰሎሞን ድረስ ያሉት የእስራኤል ነገሥታት በሙሉ የተወለዱት ከይሁዳ ዘር ነበር፡፡ ከመንግሥቱ መከፈል በኋላም እንኳን የይሁዳ ቤት እስከ 586 ዓ.ዓ ድረስ የእስራኤልን ደቡባዊ ግዛት ያዘ፡፡ በዚህ መንገድ የይሁዳ ሕዝብ እስራኤላውያንን ይወክላል፡፡ የሌዊ ነገድ ካህናቶቹ አንዱ ነበር፡፡ የእስራኤል እያንዳንዱ ነገድ የራሱ ሚና ነበረው፡፡ እግዚአብሄር ለይሁዳ ነገድ ኢየሱስ ከእነርሱ እንደሚነሳ ቃል ገበላቸው፡፡       
እርሱ ከይሁዳ ነገድ ጋር ለምን ይህን ኪዳን አደረገ? እስራኤላውያን የአለምን ሕዝብ ስለሚወክሉ ይህንን ኪዳን ማድረግ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ ጋር ኪዳን ከመግባት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ፣ በመስቀል ላይ ሞቱና በትንሳኤው አማካይነት የሰው ዘር ደህንነት የሆነውን አዲሱን ኪዳን ፈጸመ፡፡ 
 
 

የሰው ዘር ሐጢያት በንስሐ ጸሎት ሊወገድ አይችልም፡፡ 

 
የሰው ሐጢያቶች በንስሐ ታጥበው ይወገዳሉን?
አይወገዱም፡፡ 

በኤርምያስ 17፡1 ላይ የሰው ዘር ሐጢያት በሁለቱ ቦታዎች ላይ መመዝገቡ ተጽፎዋል፡፡ ‹‹የይሁዳ ሐጢአት በብረት ብዕርና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፎአል፡፡ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ተቀርጾዋል፡፡››  
ሐጢያቶቻችን በልቦቻችን ውስጥ ተመዝግበዋል፡፡ ሐጢያተኞች መሆናችንንም የምናውቀው በዚህ ነው፡፡ አንድ ሰው በኢየሱስ ከማመኑ በፊት ሐጢያተኛ መሆኑን አያውቅም፡፡ ለምን? ምክንያቱም የእግዚአብሄር ሕግ በልቡ ውስጥ የለም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው አንድ ጊዜ በኢየሱስ ሲያምን በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኛ መሆኑን ይገነዘባል፡፡  
አንዳንዶች ሐጢያተኞች መሆናቸውን የሚገነዘቡት በኢየሱስ ካመኑ ከ10 ዓመታት በኋላ ነው፡፡ ‹‹ውድ ሆይ! እኔ ሐጢያተኛ ነኝ! ድኛለሁ ብዬ አስቤ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ ሐጢያተኛ ነኝ!›› ግንዛቤው የሚመጣው አንድ ቀን መጨረሻ ላይ እውነተኛ ማነንታችን ስናይ ነው፡፡ እነርሱ ለአስር ዓመታት ደስተኞች ነበሩ፤ ነገር ግን ድንገት እውነቱን ተረዱ፡፡ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ይህ ግንዛቤ የመጣው ሐጢያቶቻቸውና መተላለፎቻቸው በመጨረሻ በእግዚአብሄር ሕግ አማካይነት ግልጽ ስለሆኑ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ዳግም ሳይወለድ ለ10 ዓመታት በኢየሱስ አምኖዋል፡፡ 
ሐጢያተኛው ሐጢያቶቹን ከልቡ መፋቅ ስለማይችል በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኛ ሆኖ ይኖራል፡፡ አንዳንዶች ወደዚህ ግንዛቤ ለመድረስ 5 ዓመታቶች ሲወስድባቸው ሌሎች ደግሞ 10 ዓመታት ይወስድባቸዋል፡፡ አንዳንዶች ወደ ግንዛቤ የሚደርሱት ከ30 ዓመታቶች በኋላ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ከ50 ዓመታት በኋላ ነው፡፡ አንዳንዶች እስከነአካቴው እውነቱን ፈጽመው አይገነዘቡትም፡፡ ‹‹አቤቱ አምላኬ ትዕዛዛቶቹ በልቦናዬ ውስጥ ከመሆናቸው በፊት ጥሩ ነበርሁ፡፡ ሕጉን በሚገባ እየጠበቅሁ እንደነበር እርግጠኛ ነበርሁ፡፡ አሁን ግን በየቀኑ ሐጢያት እንደምሰራ ተረድቻለሁ፡፡ ሐዋርያው እንደተናገረው፡- ‹‹እኔ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፡፡ ትዕዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ሐጢያት ሕያው ሆነ እኔ ሞትሁ፡፡›› (ሮሜ 7፡9) በክርስቶስ ባምንም ሐጢያተኛ ነኝ፡፡››       
በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት እንዳትኖሩ የሚከለክሉዋችሁ የእናንተው ሐጢያቶች ናቸው፡፡ ሐጢያቶቻችሁ በልቦቻችሁ ውስጥ ተጽፈዋል፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችሁን በዚያ ስለመዘገባቸው አንገታችሁን ለጸሎት በምታጎነብሱበት ጊዜ ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ ብቅ ይላሉ፡፡ ‹‹ይደንቃል! እኔ እናንተ የሰራችሁኝ ሐጢያት ነኝ›› ይላችኋል፡፡ 
‹‹ነገር ግን እኔ ከሁለት ዓመት በፊት አላነጻሁህምን? ለምን እንደገና በድንገት ትከሰታለህ? ለምን አልጠፋህም?›› 
‹‹ኦ! አስጠሊታ አትሁን! እኔ በልብህ ውስጥ ተመዝግቤያለሁ፡፡ የምታስበው ምንም ይሁን አሁንም ድረስ ሐጢያተኛ ነህ፡፡››  
‹‹አይደለሁም! አይደለሁም!›› 
ስለዚህ ሐጢያተኛው ከ2 ዓመት በፊት ለሰራቸው ሐጢያቶች እንደገና ንስሐ ይገባል፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ እባክህ አድነኝ በፊት በሰራሁት ሐጢያት አሁንም ድረስ እየተሰቃየሁ ነው፡፡ በፊት ለሐጢያቶቼ ንስሐ የገባሁ ብሆንም አሁንም ድረስ ግን በውስጤ ናቸው፡፡ እባክህ ሐጢያትን ሰርቻለሁና ይቅር በለኝ፡፡››   
ነገር ግን እነዚያ ሐጢያቶች በንስሐ ይወገዳሉን? ምክንያቱም የሰዎች ሐጢያቶች በልቦቻቸው ውስጥ ስለተጻፉ ያለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል በጭራሽ ሊፋቁ አይችሉም፡፡ እውነተኛ ስርየት ሊገኝ የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በኩል ብቻ ነው፡፡ ልንድን የምንችለው በእውነተኛው የኢየሱስ ወንጌል በሚያምን እምነት አማካይነት ብቻ ነው፡፡ 
 
 
አዳኛችሁ እሆናለሁ፡፡ 
 
ለአዲሱ ኪዳን ምላሽ መስጠት ያለብን እንዴት ነው?
በልቦቻችን ልናምነውና በመላው  ዓለም ልንሰብከው ያስፈልገናል፡፡ 

በሰማይ ያለው አምላካችን ከእኛ ጋር አዲስ ኪዳን አደረገ፡፡ ‹‹አዳኛችሁ እሆናለሁ፡፡ በውሃውና በደሙ አማካይነት ሙሉ በሙሉ ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ነጻ አደርጋችኋለሁ፡፡ በእኔ የሚያምኑትንም ሁሉ በእርግጠኝነት እባርካቸዋለሁ፡፡››   
እግዚአብሄር በሰጠን በዚህ አዲስ ኪዳን ታምናላችሁን? በኪዳኑ እውነትና በውሃውና በደሙ ደህንነት በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳንና ዳግም መወለድ እንችላለን፡፡ 
አንድ ሐኪም በትክክል ካልመረመረን አናምነውም፡፡ አንድ ሐኪም በመጀመሪያ በሽተኛውን በደምብ መመርመርና አስፈላጊውን ሕክምና ማዘዝ አለበት፡፡ ብዙ አይነት መድሃኒቶች አሉ፡፡ ነገር ግን የሚጠቅመው የትኛው መድሃኒት እንደሆነ ሐኪሙ በትክክል ማወቅ አለበት፡፡ ሐኪሙ በሽተኞቹን ከመረመረ በኋላ ሊፈውሱዋቸው የሚችሉ በርካታ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ምርመራው የተሳሳተ ከሆነ ግን እነዚያ ጥሩ መድሃኒቶች በሽተኛውን ከመጉዳት በቀር ለውጥ አያመጡም፡፡ 
ልክ እንደዚሁ በኢየሱስ በምታምኑበት ጊዜ በእግዚአብሄር ቃል ላይ በመመርኮዝ የመንፈሳችሁን ሁኔታ ማወቅና መረዳት አለባችሁ፡፡ መንፈሳችሁን በእግዚአብሄር ቃል ስትመረምሩት የመንፈሳችሁን ሁኔታና ደረጃ በትክክል ልትገነዘቡ ትችላላችሁ፡፡ የመንፈስ ሐኪም ሕሙማኑን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ይፈውሳቸዋል፡፡ ሁሉም ዳግም መወለድ ይችላሉ፡፡ 
‹‹እኔ መዳን ወይም አለመዳኔን አላውቅም›› የምትሉ ከሆነ አልዳናችሁም ማለት ነው፡፡ አንድ መጋቢ በትክክል የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ከሆነ የተከታዮቹን የሐጢያት ችግር መፍታት መቻል ይኖርበታል፡፡ ከዚያም የእምነታቸውን ችግሮች መፍታትና በመንፈሳዊ መልኩ ሊመራቸው ይችላል፡፡ እርሱ የተከታዮቹን ትክክለኛ መንፈሳዊ ሁናቴ ማየት መቻል ይኖርበታል፡፡   
ኢየሱስ የዓለም ሐጢያት በሙሉ ለመውሰድ መጣ፡፡   እርሱ ወደዚህ ምድር መጥቶ ተጠመቀና በመስቀል ላይ  ሞተ፡፡ ለሐጢያት ሁሉ ስርየት ሲያደርግ ሐጢያቶቻችሁን አላሰወገደምን? የውሃውና የመንፈሱ ቃል የምዕመናንን ሐጢያቶች በሙሉ ደመሰሰ፡፡
ወንጌል እንደ ድማሚት ነው፡፡ ከረጃጅም ሕንጻዎች  አንስቶ ተራሮችንም ጭምር ይንዳል፡፡ የኢየሱስም ሥራ በትክክል እንዲሁ ነው፡፡ እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ሰዎች ሐጢያቶች ይጠርጋል፡፡ አሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተብራራውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እንመልከት፡፡  
 
 

በብሉይ ኪዳን የነበረው እጆችን የመጫን ወንጌል፡፡ 

 
በብሉይ ኪዳን ዘመን እጆችን የመጫኑ አላማ ምን ነበር?
አላማው ሐጢያትን ወደ መሥዋዕቱ ማስተላለፍ ነበር፡፡ 

በዘሌዋውያን 1፡3-4 የተጻፈውን የስርየት ወንጌል እውነት እንመልከት፡- ‹‹መባውም የሚቃጠል መስዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርባል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል፡፡ እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ ያሰተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆናል፡፡››  
ይህ ምንባብ የሚቃጠለው ቁርባን በቁርባኑ ራስ ላይ በሚሆን እጆችን በመጫን በጌታ ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መቅረብና ቁርባኑም ነውር የሌለበት ሕያው ቁርባን  መሆን እንዳለበት ይነግረናል፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሐጢያተኛው ለዘወትር ሐጢያቶች ስርየትን ለማድረግ እጆቹን በቁርባኑ ላይ ይጭናል፡፡ የሐጢያቱን ቁርባን በእግዚአብሄር ፊት ያርደውና ካህኑም ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በሚቃጠለው መስዋዕት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ይቀባዋል፡፡ ከዚያም የቀረውን ደም ከመሰውያው በታች ያፈስሰዋል፡፡ ሐጢያተኛውም በየቀኑ ከሰራው ሐጢያት ይቅርታን ያገኛል፡፡
ዓመቱን ሙሉ ስለተሰራው ሐጢያት በዘሌዋውያን 16፡6-10 እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹አሮንም ለእርሱ ያለውን የሐጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፡፡ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፡፡ ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን አጠገብ በእግዚአብሄር ፊት ያቆማቸዋል፡፡ አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፡፡ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሄር ሌላውንም ለሚለቀቅ፡፡ አሮንም የእግዚአብሄር ዕጣ የሆንበትን ፍየል ያቀርባል፡፡ ስለ ሐጢአትም መሥዋዕት ያደርገዋል፡፡ የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሄር ፊት ያቆመዋል፡፡›› በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተብራራው አዛዜል ማለት ‹‹ማስወገድ›› ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የዓመቱ ሐጢያት በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን ይወገዳል፡፡   
በዘሌዋውያን 16፡29-30 ላይም እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ይህ የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፡፡ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተሰርያ ይሆንላችኋልና፡፡ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፡፡ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፡፡ በእግዚአብሄርም ፊት ከሐጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፡፡››     
ይህ እስራኤላውያን ለአንድ ዓመት የሰሩትን ሐጢያት የሚያስተሰርዩበት ቀን ነው፡፡ ይህ የሚሆነው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ሊቀ ካህኑ አሮን መስዋዕቱን ማቅረብ አለበት፡፡ የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክለው ማነው? አሮን ነው፡፡ እግዚአብሄር አሮንንና የእርሱን ዘሮች በሙሉ ካህናት ይሆኑ ዘንድ ሾማቸው፡፡   
አሮን ወይፈኑን በመስዋዕትነት ያቀረበው የራሱንና የቤተሰቡን ሐጢያት ለማስተሰረይ ነው፡፡ መስዋዕቱን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ካረደው በኋላ ከደሙ የተወሰነውን በስርየት መክደኛው ፊትና ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ በመጀመሪያ ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰረይ ነበረበት፡፡  
ስርየት ማለት የአንድን ሰው ሐጢያት ወደ ሐጢያቱ ቁርባን ማስተላለፍና የሐጢያት ቁርባን በአንድ ሰው ቦታ እንዲሞት መፍቀድ ነው፡፡ ሐጢያተኛው መሞት የሚገባው ሰው ነበር፤ ነገር ግን ሐጢያቶቹን ወደ ቁርባኑ በማስተላለፍና በእርሱ ፋንታ እንዲሞት በማድረግ ለሐጢያቶቹ ያስተሰርያል፡፡ 
የራሱንንና የቤተሰቡን ሐጢያት ካስወገደ በኋላ አንዱን ፍየል ለእግዚአብሄር ሲያቀርብ ሌላውን ፍየል በእስራኤል ሕዝብ ፊት የሚለቀቅ ፍየል አድርጎ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል፡፡  
አንዱ ፍየል የሐጢያት መስዋዕት ሆኖ ቀረበ፡፡ አሮን እጆቹን በሐጢያት ቁርባኑ ራስ ላይ ጫነና ‹‹እግዚአብሄር ሆይ ሕዝብህ እስራኤል አስርቱን ትዕዛዛትህንና የሕግህን 613 አንቀጾች በሙሉ ተላለፉ፡፡ እስራኤላውያንም ሐጢያተኞች ሆኑ፡፡ እኔ አሁን አመታዊ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወደዚህ ፍየል ለማስተላለፍ እጆቼን በዚህ ፍየል ላይ እጭናለሁ፡፡ ብሎ ተናዘዘ፡፡     
ከዚያም የፍየሉን ጉሮሮ በመቁረጥ ደሙን ይዞ ወደ መገናኛው ድንኳን ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፡፡ ከዚያም የተወሰነውን ደም በስርየት መክደኛው ላይና ፊት ለፊት  ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ 
በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የቃል ኪዳኑ ታቦት ይቀመጣል፡፡ መሸፈኛው የስርየት መክደኛ ተብሎ ይጠራል፡፡ በእርሱ ውስጥ ሁለት የኪዳን ድንጋይ ጽላቶች፣ መና የሚቀመጥበት የወርቅ ማሰሮና የለመለመችው የአሮን በትር ይገኙበታል፡፡    
የአሮን በትር ትንሳኤን ስታመላክት ሁለቱ የኪዳን ድንጋይ ጽላቶች ደግሞ የእግዚአብሄርን ፍትህ ያሳያሉ፡፡ የመናው የወርቅ ማሰሮ ደግሞ የእርሱን የሕይወት ቃል ያመላክታል፡ 
በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ መሸፈኛ አለ፡፡ ደሙ በስርየት መክደኛው ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡ በሊቀ ካህኑ መጎናጸፊያ ዘርፍ ላይ የወርቅ ቃጭሎች ተንጠልጥለው ስለነበር እርሱ ደሙን በሚረጭበት ጊዜ ያንቃጭሉ ነበር፡፡ 
በዘሌዋውያን 16፡14-15 እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ከወይፈኑም ደም ወስዶ በስርየቱ መክደኛ ላይ ወደ ምሥራቅ በጣቱ ይረጨዋል፡፡ ከደሙም በመክደኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡ ስለ ሕዝቡም ሐጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፡፡ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፡፡ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ በፍየሉ ደም ያደርጋል፡፡ በመክደኛውም ላይና በመክደኛው ፊት ይረጨዋል፡፡››    
እርሱ ከፍየሉ ደም የተወሰነውን በረጨ በእያንዳንዱ ጊዜ ቃጭሎቹ ድምጽ ሰጡ፡፡ ከውጭ የተሰበሰቡት እስራኤላውያን በሙሉ ድምጹን ይሰሙታል፡፡ ለሐጢያቶቻቸው የሚደረገው ስርየት የሚከናወነው በሊቀ ካህኑ በመሆኑ የቃጭሎቹ ድምጾች ሐጢያቶቻቸው ይቅር መባላቸውን የሚያበስሩ ናቸው፡፡ ይህ ለእስራኤል ሕዝቦች የበረከት ድምጽ ነው፡፡  
ቃጭሎቹ ለሰባት ጊዜ ያህል በጮሁ ጊዜ ‹‹አሁን ቀልሎልኛል፡፡ በዓመቱ ውስጥ ለሰራሁት ሐጢያት ስጸጸት ነበር፡፡ አሁን ግን ነጻ ነኝ›› ይላሉ፡፡ ሕዝቡ ከጥፋተኝነት ነጻ ሆነው ወደ ኑሮዋቸው ተመለሱ፡፡ የዚያን ዘመን የቃጭሎቹ ድምጽ በአሁኑ ጊዜ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ዳግም የመወለድ የምስራች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡   
የውሃውንና የመንፈሱን የቤዛነት ወንጌል ስንሰማ፣ ከልባችን ስናምንበትና በአፋችን ስንመሰክር ይህ በትክክል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ማለት ይህ ነው፡፡ ቃጭሉ ሰባት ጊዜ ሲጮህ የእስራኤል ልጆች ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ ነጽተዋል፡፡ ሐጢያቶቻቸውም በሙሉ በእግዚአብሄር ፊት ታጥበዋል፡፡   
ሊቀ ካህኑ አንድ ፍየል ለእስራኤላውያን ካቀረበ በኋላ ሌለውን ፍየል ያዘና ከድንኳኑ ውጭ ወደሚጠብቁት ሕዝብ ሄደ፡፡ እነርሱ እየተመለከቱ ሊቀ ካህኑ አሮን እጆቹን በሌላው ፍየል ራስ ላይ ጫነ፡፡   
በዘሌዋውያን 16፡21-22 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፡፡ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፣ መተላለፋቸውንም ሁሉ፣ ሐጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፡፡ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፡፡ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል፡፡ ፍየሉም ሐጢአታቸውን ሁሉ ወደ በርሀ ይሸከማል፡፡ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል፡፡›› 
ሊቀ ካህኑ አሮን በሌላው ፍየል (አዛዜል) ላይ እጆቹን ጫነና የእስራኤላውያንን አመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ በእግዚአብሄር ፊት ተናዘዘ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር ሆይ እስራኤላውያን በፊትህ ሐጢያትን ሰሩ፡፡ እኛ አስርቱን ትዕዛዛትህንና የሕግህን 613ቱን አንቀጾች ጣስን፡፡ አቤቱ የእስራኤሎችን አመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ ወደዚህ ፍየል ራስ ላይ አሻግራለሁ፡፡››   
በኤርምያስ 17፡1 መሰረት ሐጢያቶች የተጻፉት ሁለት ቦታዎች ላይ ነው፡፡ አንዱ በሥራዎች መጽሐፍ ላይ ሲሆን ሌላው በልቦቻቸው ጽላቶች ላይ ነው፡፡  
ስለዚህ ሰዎች ለሐጢያቶቻቸው ስርየትን የሚያገኙ ከሆነ ሐጢያቶቻቸው ከሥራዎች መጽሐፍና ከልቦቻቸው ጽላቶች ላይ መፋቅ አለባቸው፡፡ በስርየት ቀን አንዱ ፍየል በፍርድ መጽሐፍ ላይ ለተጻፉት ሐጢያቶች ሲሆን ሌላው ፍየል ደግሞ በልቦቻቸው ጽላቶች ላይ ለተጻፉት ሐጢያቶች ነበር፡፡ 
 
እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን  የመስዋዕት ስርዓት አማካይነት ለእስራኤላውያን ምን አሳየ?
አዳኝ እንደሚመጣና ሐጢያቶቻቸውን እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደሚደመስስ ነው፡፡ 

ሊቀ ካህኑ እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ በመጫን ዓመታዊዎቹ ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ፍየሉ መተላለፋቸውን አሳያቸው፡፡ ሐጢያቶቹ ወደ ፍየሉ ራስ ላይ በተጫኑ ጊዜ የተመረጠው ሰው  ምድረ በዳ ሰደደው፡፡ 
ፓለስቲን ምድረ በዳ አገር ነች፡፡ የእስራኤላውያንን ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደው ፍየል ለዚህ ሥራ በተመደበው ሰው አማካይነት ውሃም ሆነ ሣር ወደማይኖርበት ምድረ በዳ ተወሰደ፡፡ ፍየሉ ወደ ምድረ በዳው ሲሄድ ሕዝቡ ቆመው ተመለከቱ፡፡  
ለራሳቸውም እንዲህ አሉ፡- ‹‹እኔ መሞት ሲገባኝ በእኔ ፋንታ ይህ ፍየል ሞተ፡፡ የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ ነገር ግን በእኔ ፋንታ ፍየሉ ሞተ፡፡ አንተ ፍየሉ አመሰግንሃለሁ፡፡ የአንተ መሞት ማለት ለእኔ መኖር ነው፡፡›› ፍየሉ ወደ ምድረ በዳ ርቆ ተወሰደና እስራኤሎችም የአመቱን ሐጢያት ይቅርታ አገኙ፡፡ 
በልባችሁ ውስጥ ያለው ሐጢያት ወደ ቁርባኑ ከተላለፈ እናንተ ከሐጢያት ነጽታችኋል፡፡ ይህንን ያህል ቀላል ነው፡፡ እውነትን አንድ ጊዜ ካስተዋልነው ሁልጊዜም ቀላል ነው፡፡  
ፍየሉ ከአድማሱ ባሻገር ተሰወረ፡፡ ሰውየው ፍየሉን ከለቀቀው በኋላ ብቻውን ተመለሰ፡፡ የእስራኤላውያን ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ አከተሙ፡፡ ፍየሉ ውሃና ሣር በሌለበት ምድረ በዳ ተቅበዘበዘና ውሎ አድሮም እስራኤሎች ዓመቱን ሙሉ የሰሩዋቸውን ሐጢያቶች ይዞ ሞተ፡፡   
የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ የእግዚአብሄርም ፍትህ ተከናወነ፡፡ እስራኤሎች በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሄር ፍየሉን መስዋዕት አደረገው፡፡ እስራኤሎችም ዓመቱን በሙሉ የፈጸሙዋቸው መተላለፎች በሙሉ ነጽተዋል፡፡  
በብሉይ ኪዳን የቀኑ ሐጢያትና የዓመቱ ሐጢያት በዚያ መልኩ ይቅር እንደተባሉ ሁሉ የእኛም ሐጢያቶች እንደዚሁ ለአንዴና ለሁሌም ይቅርታን ያገኙ ዘንድ የእግዚአብሄር ኪዳን ነው፡፡ መሲሁን ለእኛ መላኩና ከዕድሜ ልክ ሐጢያቶቻችን በሙሉ እኛን ማዳኑ የእርሱ ኪዳን ነበር፡፡   
 
 
በአዲስ ኪዳን ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም መወለድ፡፡ 
 
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ ለምን ተጠመቀ? 
የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ያለው የኢየሱስ ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ካለው እጆችን መጫን ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ 

ማቴዎስ 3፡13-15ን እናንብብ፡- ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡››  
ኢየሱስ ወደ ዮርዳኖስ ሄደና በአጥማቂው ዮሐንስ  ተጠመቀ፡፡ እንዲህ በማድረግም ጽድቅን ሁሉ ፈጸመ፡፡ እርሱ  በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ ዮሐንስ ከሴት ከተወለዱት ሁሉ እጅግ ትልቁ ሰው ነበር፡፡ 
ማቴዎስ 11፡11-12 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እውነት እላችኋለሁ፡- ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፡፡ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል፡፡ ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፡፡ ግፈኞችም ይናጠቋታል፡፡›› 
አጥማቂው ዮሐንስ የሰው ዘር ወኪል ይሆን ዘንድ በእግዚአብሄር ተመረጠና ከክርስቶስ 6 ወራቶች በፊት ተላከ፡፡ እርሱም የአሮን ዝርያና የመጨረሻው ሊቀ ካህን ነበር፡፡ 
አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ ‹‹እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?›› አለው፡፡ 
‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› የእርሱ ዓላማ የሰውን ዘር ሁሉ ከሐጢያት ነጻ በማድረግ የእግዚአብሄር ልጆች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ኢየሱስ ለዮሐንስ ሲናገር ‹‹ከውሃውና ከመንፈሱ ዳግም የመወለድን ወንጌል መፈጸም አለብን፡፡ ስለዚህ አሁን አጥምቀኝ›› አለው፡፡   
ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ኢየሱስ መጠመቁ ተገቢ ነበር፡፡ ኢየሱስ እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ ስለተጠመቀ እኛ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ በተገቢው መንገድ ድነናል፡፡ ኢየሱስ የተጠመቀው ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ ይተላለፉ ዘንድ ነው፡፡
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጣና 30 ዓመት ሲሆነው ተጠመቀ፡፡ ይህ የመጀመሪያ አገልግሎቱ ነበር፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመደምሰስ ጽድቅን ሁሉ ፈጸመና በዚህም ሰዎችን ሁሉ ቀደሰ፡፡  
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣና ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ሊያድነን እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ ተጠመቀ፡፡ ‹‹በዚህም›› ጽድቅ ሁሉ ተፈጸመ፡፡  
እግዚአብሄር ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› (ማቴዎስ 3፡17) አለ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ሁሉ ሐጢያት በሙሉ እንደሚወስድና በመስቀል ላይ እንደሚደማ ያውቅ ነበር፡፡ ሆኖም ‹‹አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን›› (ማቴዎስ 26፡39) በማለት የአባቱን ፈቃድ ታዘዘ፡፡ የአብ ፈቃድ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ማስወገድና ለዓለም ሕዝብ ደህንነትን መስጠት ነበር፡፡ 
ስለዚህ ታዛዡ ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ 
1ኛ ዮሐንስ 1፡29 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በነገውም ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ፡- እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ አለ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡29) ኢየሱስ ሐጢያትን በሙሉ ወሰደና በጎልጎታ በመስቀል ላይ ደማ፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› በማለት መሰከረ፡፡ 
ሐጢአት አለባችሁ ወይስ የለባችሁም? ጻድቅ ሰው ናችሁ ወይስ ሐጢያተኞች? እውነቱ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያት በሙሉ መውሰዱና ለሁላችንም በመስቀል ላይ መሰቀሉ ነበር፡፡  
 
የሐጢያተኞች ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ የተላለፉት መቼ ነበር?
ኢየሱስ በዮርዳኖስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን ወሰደ፡፡ 

እኛ በዚህ ዓለም ላይ ከተወለድንበት ጊዜ አንስቶ ከ1 እስከ 10 ዓመት ድረስ ባለው ዕድሜያችንም እንኳን ሐጢያትን እንሰራለን፡፡ ኢየሱስ እነዚያን ሐጢያቶች ወሰደ፡፡ እንዲሁም በ11 እና በ20 ዓመታችን መካከል ሐጢያት እንሰራለን፡፡ በልቦቻችንና በምግባሮቻችን የምንሰራቸውን ሐጢያቶች በሙሉ እርሱ ወሰደ፡፡   
በ21 እና በ45 ዓመታችን መካከልም እንደዚሁ ሐጢያት እንሰራለን፡፡ እነዚህን ሁሉ ደግሞ ወሰደ፡፡ እኛ ከተወለደንበት ቀን አንስቶ እስከምንሞትበት ቀን ድረስ ሐጢያትን እንሰራለን፡፡ ነገር ግን እርሱ ሁሉንም ወሰዳቸው፡፡  
‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም አንስቶ በዚህ ዓለም ላይ እስከሚወለደው የመጨረሻ ሰው ድረስ--ያ ሰው የትም ይሁን--ያለውን ሐጢያት በሙሉ ወሰደ፡፡ የማንን ሐጢያቶች  መውሰድ እንዳለበት ለቅሞ አልመረጠም፡፡   
እርሱ አንዳንዶቻችንን ብቻ ለመውደድ አልወሰነም፡፡ እርሱ ሥጋን ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደና በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ ለሁላችንም ፍርድን ተቀበለና የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለዘላለም ደመሰሰ፡፡ 
ከእርሱ ደህንነት የተገለለ ሰው የለም፡፡ ‹‹የዓለም ሐጢያት ሁሉ›› የእኛንም ሐጢያቶች በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ ኢየሱስ ሁሉንም ወሰደ፡፡  
እርሱ በጥምቀቱና በደሙ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ አነጻ፡፡ በጥምቀቱ አማካይነት ሁሉንም ወሰደና በመስቀል ላይ ለሐጢያቶቻችን ተፈረደበት፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከመሞቱ በፊት ‹‹ተፈጸመ›› (ዮሐንስ 19፡30) አለ፡፡ ይህ ማለት የሰው ዘር ደህንነት ተጠናቋል ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ ለምን በመስቀል ላይ ተሰቀለ? የሥጋ ሕይወት ያለው በደም ውስጥ ስለሆነና ለአንድ ሰው ሕይወትም ደሙ  ስርየት ስለሆነ ነው፡፡ (ዘሌዋውያን 17፡11) ኢየሱስ መጠመቅ ያስፈለገው ለምንድነው? የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ መውሰድ ስለፈለገ ነው፡፡ 
‹‹ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፡›› (ዮሐንስ 19፡28) ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉት የእግዚአብሄር ኪዳናት በሙሉ በዮርዳኖስ ባደረገው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ መፈጸማቸውን በማወቅ ሞተ፡፡ 
ኢየሱስ ቤዛነት በእርሱ በኩል እንደተፈጸመ አወቀና ‹‹ተፈጸመ›› ብሎ ተናገረ፡፡ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ቀደሰን፡፡ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳና አሁን በእግዚአብሄር ቀኝ ወደተቀመጠበት ወደ ሰማይ አረገ፡፡ 
ሐጢያቶች በሙሉ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ አማካይነት መንጻታቸው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድ ወንጌል በረከት ነበር፡፡ ይህንን እመኑት፡፡ ለሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ይቅርታን ታገኛላችሁ፡፡   
በየቀኑ ስለ ንስሐ በመጸለይ ከሐጢያቶቻችን መንጻት አንችልም፡፡ ቤዛነት ለአንዴና ለመጨረሻ የተለገሰው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› (ዕብራውያን 10፡18)    
አሁን እኛ ሁላችን ማድረግ ያለብን በኢየሱስ ጥምቀትና ስቅለት ማመን ነው፡፡ በዚህ እመኑ ትድናላችሁ፡፡ 
ሮሜ 5፡1-2 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሄር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፡፡ በእርሱም ደግሞ ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፡፡ በእግዚአብሄር ክብርም ተስፋ እንመካለን፡፡›› 
ለመጽደቅ ከውሃና ከመንፈስ የሆነውን ዳግም የመወለድ የተባረከ ወንጌል ከማመን ውጪ ሌላ መንገድ የለም፡፡   
 
 
የእግዚአብሄር ሕግ ዓላማ፡፡ 
 
በሕጉ መቀደስ እንችላለን? 
የለም አንችልም፡፡ ሕጉሐጢያቶቻችንን እንድናውቅ ብቻ ያደርጋል፡፡ 

በዕብራውያን 10፡9 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ቀጥሎ እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል፡፡ ሁለተኛውን ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል፡፡›› በሕጉ አማካይነት ልንቀደስ አንችልም፡፡ ሕጉ የሚያደርገን ሐጢያተኞች ብቻ ነው፡፡ ሕጉን እንታዘዝ ዘንድ የእግዚአብሄር ዓላማ አይደለም፡፡ 
ሮሜ 3፡20 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም የሕግን ሥራ በመስራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፡፡ ሐጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡›› እግዚአብሄር አብርሃም ኪዳኑን ከተቀበለ ከ430 ዓመታት በኋላ በሙሴ በኩል ሕጉን ለእስራኤሎች ሰጠ፡፡ ሕጉን የሰጣቸው በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት መስራት ምን ማለት እንደሆነ ያውቁ ዘንድ ነበር፡፡ የእግዚአብሄር ሕግ በሌለበት የሰው ዘር የሐጢያት እውቀት አይኖረውም ነበር፡፡ ሐጢያትን ወደ መረዳት እንድንመጣ እግዚአብሄር ሕጉን ሰጠን፡፡   
የሕጉ ዓላማ በእግዚአብሄር ፊት ሁላችንም ሐጢያተኞች መሆናችንን ማሳወቅ ነው፡፡ በዚህ ዕውቀት አማካይነት በተባረከው የውሃና የመንፈስ ዳግም የመወለድ ወንጌል በማመን ወደ ኢየሱስ እንድንጠጋ ይጠበቅብናል፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን ሕግ ዓላማው ይህ ነው፡፡  
 
 
ጌታ የመጣው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈጸም ነው፡፡ 
 
በእግዚአብሄር ፊት ማድረግ ያለብን ምንድነው?
በኢየሱስ በኩል በሆነው የእግዚአብሄር ቤዛነት ማመን ይኖርብናል፡፡ 

‹‹እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል፡፡ ሁለተኛውን ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል፡፡›› (ዕብራውያን 10፡9) እኛ በሕጉ ልንቀደስ ስለማንችል እግዚአብሄርም ፍጹም በሆነው ቤዛነቱ እንጂ በሕጉ አልታደገንም፡፡ እግዚአብሄር በፍቅሩና በምህረቱ አዳነን፡፡  
‹‹በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል፡፡ ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ሐጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡›› (ዕብራውያን 10፡10-12)
እርሱ የቤዛነት ሥራው ስለተጠናቀቀና ሌላ የሚሰራው ነገር ስላልነበረው በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ከዚህ በኋላም እኛን ለማዳን ዳግመኛ አይጠመቅም፤ ራሱም መስዋዕት አያደርግም፡፡ 
አሁን የዓለም ሐጢያት በሙሉ ስለነጻ እርሱ ከዚህ በኋላ የሚያደርገው ነገር ቢኖር በእርሱ ለሚያምኑት የዘላለም ሕይወትን መስጠት ብቻ ነው፡፡ አሁን እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ደህንነት ያመኑትን በመንፈሱ አትሞዋቸዋል፡፡
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፤ በመስቀል ላይ በመሞትም ሥራውን አጠናቀቀ፡፡ አሁን የጌታ ስራ በመጠናቀቁ እርሱ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡  
ኢየሱስ ለዘላለም ከሐጢያት እንዳዳነን ማመን አለብን፡፡ እርሱ በጥምቀቱና በደሙ ለዘላለም ፍጹማን አደረገን፡፡ 
 
 
የእግዚአብሄር ጠላቶች የሚሆኑ፡፡ 
 
የእግዚአብሄር ጠላቶች እነማን ናቸው?
በኢየሱስ እያመኑ በውስጣቸው ሐጢያት ያለባቸው ናቸው፡፡ 

በዕብራውያን 10፡12-13 ላይ ጌታ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መሥዋዕት አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል፡፡ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡›› የመጨረሻው ፍርድ ዕጣ ፈንታቸውን እስከሚወስን ድረስም እንደሚጠብቃቸው ተናግሮዋል፡፡   
የእርሱ ጠላቶች አሁንም ድረስ ‹‹እግዚአብሄር ሆይ ሐጢያቴን ይቅር በለኝ›› ይላሉ፡፡ ሰይጣንና ተከታዮቹ በእርሱ የውሃና የመንፈስ ወንጌል አያምኑምና የእርሱን ይቅርታ መለመናቸውን ይቀጥላሉ፡፡ 
ጌታ አምላካችን አሁንም በእነርሱ ላይ አይፈርድም፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ዳግም ምጽአት ቀን ለዘላለም ይፈርድባቸውና ለሲዖል ይኮነናሉ፡፡ እግዚአብሄር በቤዛነት አማካይነት ንስሐ ይገቡና ጻድቃን ይሆናሉ በሚል ተስፋ እስከዚያን ቀን ድረስ ይታገሳቸዋል፡፡ 
ጌታችን ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደና በእርሱ ለምናምነው ሞተልን፡፡ ኢየሱስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ለመታደግ አንድ ቀን ለሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል፡፡ ‹‹አቤቱ ፈጥነህ ናልን፡፡›› ሐጢያት አልባ የሆኑት በመንግሥተ ሰማይ ለዘላለም አብረውት ይኖሩ ዘንድ ሊወስዳቸው ዳግመኛ ይመጣል፡፡  
ሐጢያተኞች ነን ብለው ድርቅ የሚሉ ጌታ በሚመለስበት ጊዜ በሰማይ ቦታ አያገኙም፡፡ በመጨረሻው ቀን ይፈረድባቸውና ወደ ሲዖል እሳት ይወረወራሉ፡፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም መወለድን ለማመን እምቢተኞች የሚሆኑ የሚጠብቃቸው ቅጣት ይህ ነው፡፡ 
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ባልሆነ ነገር የሚያምኑትን እንደ ጠላቶቹ አድርጎ ይመለከታቸዋል፡፡ ይህንን እውነት ያልሆነ ነገር መዋጋት ያለብን ለዚህ ነው፡፡ በተባረከው ዳግም ከውሃና ከመንፈስ የመወለድ ወንጌል ማመን ያለብን ለዚህ ነው፡፡ 
 
 
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለብን፡፡ 
 
ዕዳዎቻችን (ሐጢያቶቻችን) በሙሉ ተከፍለው ሳሉ ለሐጢያቶቻችን ስርየት ማግኘት ያስፈልገናልን?
በፍጹም አይገባንም፡፡ 

ዕብራውያን 10፡15-16 እንዲህ ይላል፡- ‹‹መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፡፡ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፡፡ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፡፡ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፡፡››
ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ከደመሰሰልን በኋላ ‹‹ይህ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ነው›› አለ፡፡ ይህ ኪዳን ምንድነው? ‹‹ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፡፡›› በመጀመሪያ እኛም በሕጉ መሰረት ሕግ አክባሪ ሕይወትን ለመኖር ሞክረን ነበር፡፡ ነገር ግን በእውነት በሕጉ መዳን አልቻልንም፡፡ 
በኋላም ኢየሱስ ከውሃና ከመንፈሱ ዳግም የመወለድን የተባረከ ወንጌል በልቦቻቸው ያመኑትን እንዳዳናቸው አወቅን፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የሚያምን ማንኛውም ሰው ይድናል፡፡  
ኢየሱስ የደህንነት ጌታ ነው፡፡ ‹‹መዳንም በሌላ በማንም የለም፡፡ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው አዳኛችን ሆኖ ነው፡፡ እኛ በሥራዎቻችን መዳን ስለማንችል ኢየሱስ አዳነንና በፍቅርና በደህንነት ሕጉ እንዳዳነንም በልባችን ጽላቶች ላይ ጻፈልን፡፡ 
‹‹ሐጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል፡፡ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢያት ማቅረብ የለም፡፡›› (ዕብራውያን 10፡17-18) አሁን ሕግ አልባ ምግባሮቻችንን ዳግመኛ አያስታውስም፡፡ አሁን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በማስወገዱ እኛ ምዕመናን ይቅር የሚባሉ ሐጢያቶች የሉብንም፡፡ ዕዳዎቻችን ሙሉ በሙሉ ተከፍለዋል፡፡ ሳይከፈል የቀረ ምንም ነገር የለም፡፡ ሰዎች በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙ አማካይነት ባዳነን የኢየሱስ አገልግሎት በእምነት ድነዋል፡፡
አሁን እኛ ሁላችን ማድረግ ያለብን ብቸኛው ነገር በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማመን ነው፡፡ ‹‹እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› (ዮሐንስ 8፡32) በኢየሱስ በኩል በተገኘው ደህንነት እመኑ፡፡ ቤዛነትን ማግኘት ከመተንፈስም ይቀላል፡፡ እናንተ ማድረግ የሚኖርባችሁ ነገሮችን እንዳሉ ማመን ነው፡፡ መዳን በእግዚአብሄር ቃል ማመን ነው፡፡  
ኢየሱስ (በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ) አዳኛችን እንደሆነ እመኑ፡፡ ደህንነት የእናንተ እንደሆነ እመኑ፡፡ እርሱ እንዳዳናችሁ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ፡፡ አስተሳሰቦቻችሁን ካዱና በኢየሱስ ደህንነት እመኑ፡፡ በኢየሱስ በተጨባጭ እንድታምኑና ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለም ሕይወት ለመግባት እንድትዘጋጁ እጸልያለሁ፡፡