Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 4፡ የዘወትር ሐጢያቶችን መፍታት

[4-1] የተትረፈረፈው ስርየት ወንጌል ‹‹ ዮሐንስ 13፡1-17 ››

የተትረፈረፈው ስርየት ወንጌል
‹‹ ዮሐንስ 13፡1-17 ››
‹‹ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደደረሰ አውቆ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው፡፡ እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደሰጠው ከእግዚአብሄርም እንደወጣ ወደ እግዚአብሄርም እንዲሄድ አውቆ ከእራት ተነሳ፡፡ ልብሱንም አኖረ፡፡ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፡፡ በኋላም በመታጠቢያው ውሃ ጨመረ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግርን ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ፡፡ ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፡፡ እርሱም፡- ጌታ ሆይ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- እኔ የማደርገውን አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው፡፡ ጴጥሮስም፡- የእኔን እግር ለዘለዓለም አታጥብም አለው፡፡ ኢየሱስም፡- ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት፡፡ ስምዖን ጴጥሮስም፡- ጌታ ሆይ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው፡፡ ኢየሱስም፡- የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፤ ሁለንተናው ግን ንጹህ ነው፡፡ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፡፡ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው፡፡ አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና ስለዚህ ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለ፡፡
እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፡፡ እንዲህም አላቸው፡- ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላቸሁ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ፡፡ እንግዲህ እኔ መምህርና ጌታ ስሆን እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል፡፡ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ጌታ ከባርያው አይበልጥም፤ መልዕክተኛም ከላከው አይበልጥም፡፡ ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብጹዓን ናችሁ፡፡››
 

ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት ባለው ቀን የጴጥሮስን እግር ያጠበው ለምንድነው? እግሮቹን ከማጠቡ በፊት ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ የማደርገውን አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ፡፡›› ጴጥሮስ ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች ምርጥ የተባለ ሰው ነበር፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደነበር አምኖ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደነበርም መስክሮዋል፡፡ ኢየሱስ እግሩን ሲያጥበው ይህንን ያደረገበት ጥሩ ምክንያት ያለው መሆን አለበት፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ያለውን እምነት በመሰከረ ጊዜ ኢየሱስ እርሱን ከሐጢያቶቹ ሁሉ የሚያድነው አዳኝ መሆኑን እንዳመነ መናገሩ ነበር፡፡
 
ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበው ለምንድነው?
ምክንያቱም የእርሱን ፍጹም ደህንነት እንዲያስተውሉ ስለፈለገ ነበር፡፡
 
እርሱ የጴጥሮስን እግር ለምን አጠበ? ኢየሱስ ጴጥሮስ በቅርቡ ሦስት ጊዜ እንደሚክደውና ወደፊትም ሐጢያት መስራት እንደሚቀጥል ስላወቀ ነበር፡፡
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ጴጥሮስ በልቡ ውስጥ የቀረች አንዲት ሐጢያት ኖሮበት ቢሆን ኖሮ ከኢየሱስ ጋር ሊስማማ አይችልም ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን የደቀ መዛሙርቱን ድክመቶች በሙሉ ያውቅ ስለነበር ሐጢያቶቻቸው በእርሱና በደቀ መዛሙርቶቹ መካከል ጣልቃ እንዲገቡ አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ሐጢያቶቻቸው በሙሉ ቀድሞውኑም እንደነጹ ሊያስተምራቸው ፈለገ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበበት ምክንያቱ ያ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከመሞቱና ከእነርሱ ከመለየቱ በፊት በጥምቀቱ ወንጌልና በዕድሜ ዘመናቸው በሙሉ የሰሩዋቸው ሐጢያቶች ስርየትን በማግኘታቸው ላይ ጸንተው እንደሚቆሙ ማረጋገጥ ፈለገ፡፡
ዮሐንስ 13 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ስለፈጸመው ፍጹም ደህንነት ይናገራል፡፡ ኢየሱስ እግሮቻቸውን እያጠበ ሳለ ሰዎች ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ስለሚነጹበት የጥምቀቱ ወንጌል ጥበብ ነገራቸው፡፡
‹‹ወደፊት በዲያብሎስ አትታለሉ፡፡ በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበልሁት ጥምቀቴ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ወስጃለሁ፡፡ የእነርሱንም ፍርድ በመስቀል ላይ እቀበላለሁ፡፡ ከዚያም ከሙታን እነሳለሁ፡፡ ዳግም የመወለድን ደህንነት ለሁላችሁም እፈጽማለሁ፡፡ የወደፊት ሐጢያቶቻችሁንም አስቀድሜ እንዳነጻሁ ላስተምራችሁ፤ እውነተኛውን የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል ላስተምራችሁ ከመሰቀሌ በፊት እግሮቻችሁን እያጠብሁ ነው፡፡ ዳግም የመወለድ ምስጢሩ ይህ ነው፡፡ እናንተም ሁላችሁ በዚህ ማመን አለባችሁ፡፡››
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበበትንና ‹‹እኔ የማደርገውን አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ›› ያለበትን ምክንያት ሁላችንም መረዳት ይገባናል፡፡ ዳግም በመወለጃው ወንጌል ማመንና ራሳችንም ዳግም መወለድ የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡
 

እርሱ በዮሐንስ 13፡12 ላይ እንዲህ አለ፡-
 
መተላለፎች ምንድናቸው?
ከድክመታችን የተነሳ በየቀኑ የምንሰራቸው ሐጢያቶች ናቸው፡፡፡
 
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙር ጋር የፋሲካን በዓል በማክበር እግሮቻቸውን በራሱ እጆች በማጠብ ስለ ሐጢያቶች ስርየት ወንጌል አሳመናቸው፡፡::
‹‹ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደሰጠው ከእግዚአብሄርም እንደወጣ ወደ እግዚአብሄርም እንዲሄድ አውቆ ከእራት ተነሳ፡፡ ልብሱንም አኖረ፡፡ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፡፡ በኋላም በመታጠቢያው ውሃ ጨመረ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግርን ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ፡፡ ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፡፡ እርሱም፡- ጌታ ሆይ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- እኔ የማደርገውን አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው፡፡›› (ዮሐንስ 13፡3-7)
ለደቀ መዛሙርቱም በጥምቀቱ ውሃ አማካይነት የጥምቀትንና የሐጢያቶችን ስርየት ወንጌል አስተማራቸው፡፡ 
በወቅቱ ለኢየሱስ ታማኝ የሆነው ጴጥሮስ ጌታ ኢየሱስ ለምን እግሮቹን እንዳጠበው መረዳት አልቻለም ነበረ፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስ ለእርሱ ያደረገለትን በትክክል ከተረዳ በኋላ በኢየሱስ ያመነበት መንገድ ተለወጠ፡፡ ኢየሱስ ስለ ሐጢያቶች ስርየት፤ ስለ ጥምቀቱ ውሃ ወንጌል ሊያስተምረው ፈልጎ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ወደፊት ከሚሰራቸው ሐጢያቶቹ ሁሉ ማለትም ወደፊት በሥጋው ከሚሰራቸው ሐጢያቶች የተነሳ ወደ እርሱ ሊቀርብ እንደማይችል ተጨንቆ ነበር፡፡ ኢየሱስ እግሮቻቸውን ያጠበው ዲያብሎስ የደቀ መዛሙርትን እምነት እንዳይነጥቅ ነበር፡፡ በኋላም ጴጥሮስ ምክንያቱን ተረዳ፡፡
ኢየሱስ በእርሱ የጥምቀት ውሃና ደም ያመነ ማንኛውም ሰው ለዘላለም ከሐጢያቶቹ ሁሉ እንዲዋጅ መንገዱን አዘጋጀ፡፡
በዮሐንስ 13 ላይ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቶቹን እግሮች እያጠበ ሳለ የተናገራቸው ቃሎች ተጽፈዋል፡፡ እነዚህ ዳግም የተወለዱ ሰዎች ብቻ በትክክል ሊያስተውሉዋቸው የሚችሉዋቸው በጣም አስፈላጊ ቃሎች ናቸው፡፡
ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በኋላ የደቀ መዛሙርቶቹን እግሮች ያጠበበት ምክንያት አስቀድሞ የዕድሜ ዘመናቸውን ሐጢያቶች በሙሉ እንዳጠበላቸው እንዲረዱ ለመርዳት ነበር፡፡ ኢየሱስ ‹‹ለምን እግሮችህን እንደማጠብ አሁን አይገባህም፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ይገባሃል›› አለ፡፡ ለጴጥሮስ የተነገሩት እነዚህ ቃሎች በእርሱ ውስጥ ያለውን የዘላለም ቤዛነት እውነት ይዘዋል፡፡
ሐጢያቶቻችንንና በደሎቻችንን ሁሉ ያነጻውን የኢየሱስን ጥምቀት ሁላችንም ማወቅና ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ የተቀበለው ጥምቀት እጆችን በመጫን ሐጢያቶችን የማስተላለፍ ወንጌል ነበር፡፡ ሁላችንም በኢየሱስ ቃሎች ማመን አለብን፡፡ እርሱ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ በመኮነንና በመሰቀልም የሐጢያቶችን ስርየት አጠናቀቀ፡፡ ኢየሱስ የተጠመቀው ሰዎችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ለማላቀቅ ነበር፡፡
 


ዕድሜ ልካችንን የሰራናቸው መተላለፎች ሁሉ ስርየት በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ተፈጽመዋል፡፡

 
በጻድቃን ላይ የዲያብሎስ ‹ወጥመድ› ምንድነው?
ዲያብሎስ ጻድቃንን እንደገና ሐጢያተኞች ለማድረግ ሊያታልላቸው ይሞክራል፡፡
 
ኢየሱስ ከተሰቀለ፣ ከተነሳና ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ዲያብሎስና የውሸት እምነት አራማጆች መጥተው ደቀ መዛሙርትን ለማታለል እንደሚሞክሩ ያውቅ ነበር፡፡ ‹‹አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ነህ›› በሚለው የጴጥሮስ ምስክርነት እርሱ በኢየሱስ እንዳመነ ማየት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ያም ሆኖ ኢየሱስ ጴጥሮስን የሐጢያቶችን ስርየት ወንጌል በልቡናው ውስጥ ጠብቆ እንዲይዝ ዳግመኛ ሊያስታውሰው ፈለገ፡፡ ያ ወንጌል የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደበት የኢየሱስ ጥምቀት ነበር፡፡ ይህንንም እንደገና ለጴጥሮስ፣ ለደቀ መዛሙርትና ለእኛም በኋላ ለምንመጣው ማስተማር ፈለገ፡፡ ‹‹እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ፡፡››
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሐጢያት በሚሰሩበት ጊዜ ሁሉ ዲያብሎስ ‹‹ተመልከት! አሁንም ድረስ ሐጢያቶችን የምትሰራ ከሆንህ እንዴት ሐጢያት የለብኝም ማለት ትችላለህ? አንተ አልዳንክም፡፡ አንተ ሐጢያተኛ ነህ›› በማለት ይፈትናቸውና ይኮንናቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ የዚህ አይነቱን በሽታ ለመከላከል በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ያላቸው እምነት አስቀድሞ የዕድሜ ዘመን -- ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ እንዳነጻ ነገራቸው፡፡
‹‹ሁላችሁም እኔ እንደተጠመቅሁ ታውቃላችሁ! እኔ በዮርዳኖስ የተጠመቅሁበት ምክንያቱ የዕድሜ ዘመን ሐጢያቶቻችሁን እንደዚሁም የሰውን ዘር የአዳም ሐጢያት ለማስወገድ ነበር፡፡ አሁን ለምን እንደተጠመቅሁ፣ ለምን በመስቀል ላይ መሰቀልና መሞት እንደነበረብኝ መረዳት ትችላላችሁን?›› ኢየሱስ የደቀ መዛሙርትን እግር ያጠበው ዘወትር የሚሰሩዋቸውን ሐጢያቶች በጥምቀቱ አማካይነት እንደወሰደና የእነርሱንም ፍርድ በመስቀል ላይ እንደሚወስድ ሊያሳያቸው ነበር፡፡
አሁን እናንተና እኔ የሐጢያቶቻችንን ሁሉ ስርየት እንድንቀበል በሚያስችለን በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ወንጌል ባለን እምነታችን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ ኢየሱስ ስለ እኛ ተጠመቀ ተሰቀለም፡፡ በጥምቀቱና በደሙ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አነጻ፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት የሚያስገኘውን ወንጌል የሚያውቅ፣ የሚያምንና በእውነት የሚያምን ማንኛውም ሰው ከሐጢያቶቹ ሁሉ ይድናል፡፡
ታዲያ ዳግም የተወለዱ ሰዎች ከዳኑ በኋላ ምን ማድረግ አለባቸው? በየቀኑ ሐጢያቶቻቸውን አምነው መቀበልና ለሐጢያቶቻቸው ሁሉ የስርየት ወንጌል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ደህንነት ማመን ይኖርባቸዋል፡፡ እኛ ዳግም የተወለድን ሰዎች በአእምሮዋችን ውስጥ በጥልቀት ማተም ያለብን የሐጢያቶች ስርየት የሚገኝበትን ወንጌል ነው፡፡
ዳግመኛ ሐጢያት ስለሰራችሁ ያ ማለት እንደገና ሐጢያተኛ ናችሁ ማለት ነውን? አይደለም፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ እያወቅን እንዴት እንደገና ሐጢያተኞች ልንሆን እንችላለን? የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ስርየትን ያስገኘ ወንጌል ነበር፡፡ በዚህ በእውነተኛው የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል የሚያምን ማንኛውም ሰው ያለ ምንም መገለል ‹ጻድቅ ሰው› ሆኖ ዳግመኛ ሊወለድ ይችላል፡፡
 
 

ጻድቃን ዳግመኛ ፈጽሞ ሐጢያተኞች ሊሆኑ አይችሉም፡፡

 
ጻድቃን ፈጽሞ ዳግመኛ ሐጢያተኞች የማይሆኑት ለምንድነው?
ምክንያቱም ኢየሱስ የዕድሜ ልክ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ አስቀድሞ ስላስተሰረየላቸው ነው፡፡
 
የሐጢያቶችን ስርየት በሚያመጣው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እያመናችሁ ነገር ግን አሁንም ገና በየቀኑ በምትሰሩዋቸው መተላለፎች ምክንያት ሐጢያተኛ እንደሆናችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ወደተጠመቀበት ወደ ዮርዳኖስ መሄድ ይኖርባችኋል፡፡ የሐጢያቶቻችሁን ስርየት ከተቀበላችሁ በኋላ እንደገና ሐጢያተኞች ከሆናችሁ ኢየሱስ እንደገና መጠመቅ ሊኖርበት ነው፡፡ በኢየሱስ የጥምቀት ወንጌል ባገኛችሁት የሐጢያቶቻችሁ ስርየት እምነት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት በአንድ ጊዜ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ እንደወሰደ ማስታወስ ይኖርባችኋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችሁ ስለመሆኑ የማያወላውል እምነት ሊኖራችሁ ይገባል፡፡
ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ ማመን ማለት የዕድሜ ዘመናችሁን ሐጢያቶች በሙሉ በወሰደው የኢየሱስ ጥምቀት ማመን ማለት ነው፡፡ በእርግጥም በእርሱ ጥምቀት፣ መስቀል፣ ሞትና በኢየሱስ ትንሳኤ የምታምኑ ከሆነ ምንም ሐጢያት ብትሰሩም ዳግመኛ ፈጽሞ ሐጢያተኛ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ በሕይወት ዘመናችሁ ከምትሰሩዋቸው ሐጢያቶች በሙሉ በእምነት ተዋጅታችኋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የወደፊት ሐጢያቶችን፣ ከድክመቶቻችን የተነሳ የምንሰራቸውንም ሐጢያቶች ሳይቀር አነጻ፡፡ ኢየሱስ የጥምቀቱን ጠቀሜታ ማጉላት ስለነበረበት የሐጢያቶችን ስርየት ወንጌል ማለትም የእርሱን ጥምቀት ለማመልከት የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በውሃ አጠበ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ቃል የገባውን የተትረፈረፈ ስርየት ለመፈጸምና የሰውን ዘር ሁሉ ለማዳን ተጠመቀ፤ ተሰቀለ፤ ተነሳ፤ ወደ ሰማይም አረገ፡፡ ከዚህ የተነሳ የእርሱ ደቀ መዛሙርት የሐጢያቶችን ስርየት ወንጌል፤ የኢየሱስን ጥምቀት፣ መስቀሉንና ትንሳኤውን እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ መስበክ ችለው ነበር፡፡
 

የጴጥሮስ ሥጋዊ ድክመት፡፡
 
ጴጥሮስ ኢየሱስን የካደው ለምንድነው?
ምክንያቱም ደካማ ስለነበረ ነው፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ ጴጥሮስ ከሊቀ ካህኑ ከቀያፋ ባሪያዎች ጋር በተገናኘና ከኢየሱስ ተከታዮች አንዱ እንደነበር በተከሰሰ ጊዜ ‹‹ይህን ሰው አላውቀውም›› በማለት ሁለት ጊዜ ካደ፡፡ ከዚያም ይህንኑ እየማለና እየተገዘተ ለሦስተኛ ጊዜ ተናገረ፡፡
ምንባቡን ከማቴዎስ 26፡69 እናንብበው፡- ‹‹ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፡፡ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው፡፡ እርሱ ግን፡- የምትይውን አላውቅም ብሎ በሁሉ ፊት ካደ፡፡ ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና፡- ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበረ አለች፡፡ ዳግመኛም ሲምል ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ካደ፡፡ ጥቂትም ቆይቶ በዚያ የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፡- አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእርሱ ወገን ነህ አሉት፡፡ በዚያን ጊዜ ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ሊራገምና ሊምል ጀመረ፡፡ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ፡፡ ጴጥሮስም፡- ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፡፡ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ፡፡›› (ማቴዎስ 26፡69-75)
ጴጥሮስ በኢየሱስ ማመኑ እርግጥ ነው፡፡ በታማኝነትም ተከትሎታል፡፡ ጌታ ኢየሱስ አዳኙና የሚመጣው ‹ነቢይ› እንደነበርም አምኖዋል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ጲላጦስ ችሎት በተወሰደና ከኢየሱስ ጋር ያለውን ግንኙነት ለባለሥልጣናቱ መግለጡ ለእርሱ አደገኛ ሲሆንበት በእነርሱ ፊት እየተራገመ ካደው፡፡
ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደሚክደው አላወቀም ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን እንደሚክደው አውቆ ነበር፡፡ ኢየሱስ የጴጥሮስን ድክመት በሚገባ አውቆታል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ የጴጥሮስን እግሮች አጠበ፡፡ በዮሐንስ 13 ላይ እንደተጻፈው ‹‹አንተ ወደፊትም ሐጢያት ትሰራለህ፡፡ እኔ ግን አስቀድሜ የወደፊት ሐጢያቶችህንም እንኳን ሳይቀር አስወግጄልሃለሁ›› በማለት በትውስታው ውስጥ የደህንነትን ወንጌል ቀረጸ፡፡  : 
ጴጥሮስ ሕይወቱ አደጋ ላይ ሲወድቅ በእርግጥም ኢየሱስን ካደው፡፡ ይህንን እንዲያደርግ ያደረገው ግን የሥጋው ድካም ነበር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶቹን ከወደፊት በደሎች ሁሉ ለማዳን ሲል አስቀድሞ እግሮቻቸውን አጠበ፡፡ 
‹‹እኔ የወደፊት ሐጢያቶቻችሁንም በሙሉ አስወግዳለሁ፡፡ ስለተጠመቅሁና ሐጢያቶቻችሁን ስለወሰድሁ እሰቀላለሁ፡፡ ለሁላችሁም እውነተኛ አዳኝ ለመሆንም የሁሉንም ሐጢያቶች ዋጋ እከፍላለሁ፡፡ በጥምቀቴና በደሜም እረኛችሁ እሆናለሁ፡፡ እኔ የደህንነታችሁ እረኛ ነኝ፡፡››
ኢየሱስ ይህንን እውነት በልቦቻቸው ውስጥ በጽኑ ለመትከል ሲል ከፋሲካ በዓል በኋላ እግሮቻቸውን አጠበ፡፡ የወንጌል እውነት ይህ ነው፡፡
ዳግም ከተወለድን በኋላም ቢሆን ሥጋችን ደካማ ስለሆነ እንደገና ሐጢያት እንሰራለን፡፡ በእርግጥ ሐጢያት መስራት አይገባንም ነበር፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ እንደገጠመው አይነት ከበድ ያሉ ችግሮች በሚገጥሙን ጊዜ እንደዚያ ለማድረግ ባናስብም ሐጢያትን ወደ መስራት እናዘነብላለን፡፡ የምንኖረው በሥጋ ነው፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ በሐጢያቶቻችን ወደ ጥፋት እንገሰግሳለን፡፡ በዚህ ሥጋዊ ዓለም ላይ እስከኖርን ድረስ ሥጋ ሐጢያትን ይሰራል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ እነዚያን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አስወግዶዋቸዋል፡፡
ኢየሱስ አዳኛችን እንደሆነ አንክድም፡፡ ነገር ግን በሥጋ ስንኖር ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር የሚቃረኑ ሐጢያቶችን በመስራት እንቀጥላለን፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ከሥጋ ስለተወለድን ነው፡፡
ኢየሱስ በሥጋ ስንኖር ሐጢያቶችን እንደምንሰራ በሚገባ ስላወቀ በጥምቀቱና በደሙ የሐጢያቶቻችንን ዋጋ በመክፈል አዳኛችን ሆነ፡፡ እርሱ በደህንነቱና በትንሳኤው የሚያምኑ ሰዎችን ሁሉ ሐጢያቶች አስወግዶዋል፡፡
አራቱም ወንጌሎች በሙሉ በአጥማቂው ዮሐንስ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀት የሚጀምሩት ለዚህ ነው፡፡ የእርሱ ሰብአዊ ሕይወት አላማ የደህንነት ወንጌል የሆነውን ዳግም የመወለድ ወንጌል መፈጸም ነው፡፡
 
በሥጋ ሐጢያትን የምንሰራው እስከ መቼ ነው?
እስከምንሞትበት ቀን ድረስ በሕይወታችን ሁሉ ሐጢያትን እንሰራለን፡፡
 
ጴጥሮስ ዶሮ ሳይጮህ በፊት እርሱን አንድ ጊዜ ሳይሆን፣ ሁለት ጊዜም ሳይሆን፣ ሦስት ጊዜ በካደው ጊዜ ልቡ ምኛ ተሰብሮ ነበር! ምንኛስ አፍሮ ነበር? በኢየሱስ ፊት ፈጽሞ እንደማይክደው ምሎ ነበር፡፡ ሐጢያት የሰራው ከሥጋው ድካም የተነሳ ነው፡፡ በድካሙ ተሸንፎ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሦስት ጊዜ በመካዱ ምንኛ የጎስቋላነት ስሜት ተሰምቶት ነበር? ኢየሱስ እንደገና በርህራሄ በተመለከተው ጊዜ ምንኛ የሐዘን ስሜት ተሰምቶት ነበር?
ኢየሱስ ግን እነዚህንና ሌሎችንም ነገሮች አውቆ ነበር፡፡ ስለዚህ እንዲህ አለ፡- ‹‹ደጋግመህ ሐጢያት እንደምትሰራ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ሐጢያቶችህ እንዳያሰናክሉህና ሐጢያተኛ እንዳያደርጉህ ወደ እኔ መመለስም እንዳያስቸግርህ እነዚያን ሐጢያቶች በሙሉ አስቀድሜ በጥምቀቴ ወስጃለሁ፡፡ በመጠመቅና ለሐጢያቶችህ ሁሉ በመኮነን ፍጹም አዳኝህ ሆኛለሁ፡፡ አምላክህና እረኛህ ሆኛለሁ፡፡ በሐጢያቶችህ ስርየት ወንጌል እመን፤ የሥጋ ሐጢያቶችን በተደጋጋሚ ብትሰራም አንተን መውደዴን እቀጥላለሁ፡፡ ቀድሞውኑም በደሎችህን ሁሉ አንጽቻለሁ፡፡ የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል ለዘላለም ውጤታማ ነው፡፡ እኔ ለአንተ ያለኝ ፍቅርም እንደዚሁ ዘላለማዊ ነው፡፡››
ኢየሱስ ለጴጥሮስና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡፡ ‹‹ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም፡፡›› እርሱ በዮሐንስ 13 ላይ ስለሚገኘው ስለዚህ ወንጌል የተናገረበት ምክንያት ሰዎች ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም መወለዳቸው አስፈላጊ ስለሆነ ነበር፡፡ በዚህ ታምናላችሁን?
በቁጥር 9 ላይ ደግሞ ‹‹ስምዖን ጴጥሮስም፡- ጌታ ሆይ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው፡፡ ኢየሱስም፡- የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፤ ሁለንተናው ግን ንጹህ ነው፡፡ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው፡፡››
ውድ ወዳጆች ወደፊት ‹የሥጋ› ሐጢያቶችን ትሰራላችሁን ወይስ አትሰሩም? በእርግጥም ትሰራላችሁ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ቀድሞውኑም የወደፊት ሐጢያቶችን፤ የሥጋችንን በደሎች ሁሉ ሳይቀር በጥምቀቱና በደሙ እንዳነጻ ተናግሮዋል፡፡ ከመስቀሉ በፊትም ለደቀ መዛሙርቱ የእውነትን ቃል፤ የስርየትን ወንጌል በግልጽ ነግሮዋቸዋል፡፡
እኛ ከድክመቶቻችን ሁሉ ጋር በሥጋችን ስለምንኖር ሐጢያት እንሰራለን፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አንጽቷል፡፡ እርሱ ያጠበው ራሶቻችንንና ሰውነቶቻችንንን ብቻ ሳይሆን እግሮቻችንንም ማለትም የወደፊት ሐጢያቶቻችንንም ሁሉ ነው፡፡ ዳግም የመወለድ የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል ይህ ነው፡፡
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ አጥማቂው ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፡- ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡29) እኛም የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ ወቅት ወደ ኢየሱስ ተላልፈው እንደነጹ ማመን አለብን፡፡
በዚህ ሐጢያተኛ ዓለም ላይ ስንኖር ሐጢያት እንሰራለን፡፡ ያ ግልጽ ሐቅ ነው፡፡ የሥጋ ድክመቶቻችን በሚገለጡበት ጊዜ ሁሉ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉና የዓለምን ሐጢያቶችም በሙሉ በስርየት ወንጌል እንዳነጻና በደሙም ዋጋቸውን እንደከፈለ ራሳችንን ማስታወስ ይኖርብናል፡፡ ከልባችን ለእርሱ ምስጋናን ማቅረብ ይገባናል፡፡ ኢየሱስ አዳኛችንና እግዚአብሄር እንደሆነ በእምነት እንናዘዝ፡፡ ጌታ ይመስገን፡፡
በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር እያንዳንዱ ሰው በሥጋው ሐጢያቶችን ከመስራት በቀር ሊያደርገው የሚችለው ነገር የለም፡፡ ሰዎች በሥጋቸው ያለ ማቋረጥ ሐጢያት ይሰሩና በዕድሜ ዘመናቸው በሰሩዋቸው ሐጢያቶች ይሞታሉ፡፡
 

በሰዎች ልቦች ውስጥ ያሉ ክፉ አሳቦች፡፡ 
 
ሰውን የሚያረክሰው ምንድነው?
የተለያዩ ሐጢያቶችና ክፉ አሳቦች ናቸው፡፡
 
ኢየሱስ በማቴዎስ 15፡19-20 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ከልብ ክፉ አሳብ፣ መግደል፣ ዝሙት፣ ምንዝርነት፣ መስረቅ፣ በውሸት መመስከር፣ ስድብ ይወጣልና፡፡ ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ ባልታጠበ እጅ መብላት ሰውን አያረክሰውም፡፡›› በሰው ልብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የሐጢያት አይነቶች እርሱን ያረክሱታል፡፡ ንጹህ እንዳይሆንም ያደርገዋል፡፡ 
 

አንድ ሰው የራሱን ክፉ ተፈጥሮ ማወቅ አለበት፡፡
 
በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ምንድነው? 
አስራ ሁለት አይነት ሐጢያቶች ናቸው፡፡ (ማርቆስ 7፡21-23)
 
እኛ ‹‹እነዚህ አስራ ሁለት አይነት ሐጢያቶች በሰዎች ልቦች ውስጥ አሉ፡፡ በእኔም ልብ ውስጥ ሁሉም አሉ፡፡ በውስጤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉት አስራ ሁለት አይነት ሐጢያቶች አሉብኝ›› ማለት መቻል ይኖርብናል፡፡ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም ከመወለዳችን በፊት ቀድሞውኑም ሐጢያቶች በልቦቻችን ውስጥ እንዳሉ ማመን ይኖርብናል፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ፊት ሙሉ ሐጢያተኞች እንደሆንን መቀበል ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ያንን አናደርግም፡፡ ብዙዎቻችን ‹‹በልቤ ውስጥ እነዚያ አሳቦች ፈጽሞ አልነበሩም፤ ለጊዜው ተሳስቼ ነበር››  በማለት ለሐጢያቶቻችን ምክንያቶችን እናቀርባለን፡፡
ኢየሱስ ግን ስለ ሰዎች ምን አለ? እርሱ ከሰው ልብ የሚወጣው እርሱን ‹እንደሚያረክሰው› በግልጽ ተናገረ፡፡ ሰዎች በውስጣቸው ክፉ አሳቦች እንዳላቸው ነገረን፡፡ ምን ይመስላችኋል? እናንተ ጥሩ ናችሁ ወይስ ክፉ? እያንዳንዱ ሰው ክፉ አሳቦች እንዳለው ታውቃላችሁን? አዎ የእያንዳንዱ ሰው አሳቦች ክፉ ናቸው፡፡
ከጥቂት አመታቶች በፊት በሴዑል ያለ አንድ ግዙፍ መጋዘን በድንገት ተደረመሰ፡፡ ውዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ሐዘናቸው ጥልቅ ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች አሳዛኝ በሆነው ትዕይንት ለመደሰት ወደዚያ ሄደው ነበር፡፡
አንዳንዶች ‹‹ምን ያህል ሰዎች ሞቱ? 200? አይደለም፤ ያ ቁጥር ትንሽ ነው፡፡ ምናልባት 300? የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ አንድ ሺህ ቢሆን በጣም የሚያስደስትና የሚያስደንቅ በሆነ ነበር፡፡…›› ብለው አሰቡ፡፡ የሰዎች ልቦች እንደዚህ ክፉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህንን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ይህ ለሙታን እንዴት ያለ ንቀት ነበር! ለቤተሰቦቻቸውም እንዴት ያለ ዱብ ዕዳ ነበር! አንዳንዶቹ በገንዘብ አቅምም ፈራርሰዋል፡፡
ከተመልካቾቹ አንዳንዶቹ በጣም አስተዛዛኞች አልነበሩም፡፡ ‹‹ብዙ ሞተው ቢሆን ኖሮ ይበልጥ ያስደስት ነበር! እንዴት ያለ ትዕይንት ነው! በሰዎች በተሞላው ቦልፓርክ ላይ ተመሳሳይ ነገር ቢከሰትስ? በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከፍርስራሽ በታች ይቀበሩ ነበር አይደል? አዎ! ያ በእርግጥ ከዚህም የበለጠ አስደሳች በሆነ ነበር!›› ምናልባት አንዳንዶች እንዲህ አይነት አሳቦች ነበሩዋቸው፡፡ ስለ መኪና አደጋዎችም ተመሳሳይ ነገር ሊሰማ ይችላል፡፡ የጓጉ ተመልካቾች በትናንሽ ግጭቶች ወደ አለመደሰቱ ያዘነብላሉ፡፡
ሁላችንም አንዳንድ ጊዜ ምን ያህል ክፉዎች እንደምንሆን እናውቃለን፡፡ እነዚህን ክፉ አሳቦች ፈጽሞ ጮክ ብለን እንደማንናገራቸው የታወቀ ነው፡፡ በአጋጣሚ አንድ አደጋ ስንመለከት ከንፈሮቻችንን እንመጥና ሐዘኔታችንን እንገልጥ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በድብቅ በልቦቻችን ውስጥ አደጋው ይበልጥ አስገራሚ እንዲሆን እንናፍቃለን፡፡ ከእኛ ፍላጎቶች ጋር እስካልተቃረነ ድረስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚገደሉባቸው አሰቃቂ አደጋዎችን ማየት እንፈልጋለን፡፡ የሰዎች ልቦች የሚሰሩበት መንገድ ይህ ነው፡፡ አብዛኞቻችን ዳግም ከመወለዳችን በፊት እንደዚህ ነበርን፡፡
 

በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለ ነፍስ መግደል፡፡ 
 
ሐጢያት ለምን እንሰራለን? 
ምክንያቱም በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦች ስላሉ ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ነፍስ መግደል እንዳለ ነገረን፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ‹‹እንዴት እንደዚያ ትላለህ! በልቤ ውስጥ ምንም ነፍስ የማጥፋት አሳብ የለም! እንዴት እንደዚያ አይነት ሰው አድርገህ ትመለከተኛለህ!›› በማለት ይህንን በእግዚአብሄር ፊት ይክዳሉ፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ ነፍስ መግደል እንዳለ በጭራሽ አያምኑም፡፡ ነፍሰ ገዳዮች ከእነርሱ የተለዩ ዘሮች እንደሆኑ ያስባሉ፡፡
‹‹በሌላ ቀንና በዜና የተነገረው ክፉ ነፍሰ ገዳይ፣ ከመሬት በታች ባሉት ቤቶቻቸው ውስጥ ሳሉ ሰዎችን የገደሉትና ያቃጠሉት ወሮበሎች በልቦቻቸው ውስጥ ነፍስ ማጥፋት ያላባቸው ሰዎች ናቸው! እነርሱ ልዩ ዲቃላ ናቸው፡፡ እኔ በፍጹም እነርሱን አልመስልም! እነርሱ አረመኔዎች ናቸው! ነፍሰ ገዳዮች ናቸው!›› እነርሱ በወንጀለኞች ላይ ተቆጥተው ‹‹ከክፉ ዘር የተወለዱ ሰዎች ከዚህ ምድር ላይ ተጠርገው መወገድ አለባቸው! ሁሉም ሞት ሊፈረድባቸው ይገባል!›› በማለት ይጮሃሉ፡፡
ነገር ግን የመግደል አሳብ በእነዚያ የተቆጡ ሰዎች ልቦች፣ እንደዚሁም አረመኔ በሆኑ ገዳዮችና ነፍስ አጥፊዎች ልቦች ውስጥ አሉ፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ሁሉ ልቦች ውስጥ መግደል እንዳለ ነገረን፡፡ እኛ በልቦቻችን ውስጥ የተደበቁትን ነገሮች እንኳን የሚያውቀውን የእግዚአብሄር ቃል መቀበል አለብን፡፡ ስለዚህ ‹‹እኔ በልቤ ውስጥ የመግደል ሐጢያት ያለብኝ ሰው ነኝ›› በማለት ማመን ይኖርብናል፡፡
አዎ እግዚአብሄር በሰዎች ሁሉ ልቦች ውስጥ ነፍስን መግደል ጨምሮ ክፉ አሳቦች እንዳሉ ነገረን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል እንቀበል፡፡ የሰዎች ትውልዶች ይበልጥ ክፉ ሲሆኑ ሁሉም አይነት ራስን የመጠበቂያ መሳሪያዎች፤ የግድያ መሳሪያዎች ይሆናሉ፡፡ ይህም በልቦቻችን ውስጥ ያለው ነፍስ ማጥፋት ውጤት ነው፡፡ በቁጣ ወይም በፍርሃት ነፍስ ልታጠፉ ትችላላችሁ፡፡ እያንዳንዳችን በእርግጥም ሌሎችን እንገድላለን ማለቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን በልቦቻችን ስለ ግድያ እናስባለን፡፡
ሁላችንም በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦችን ይዘን የተወለድን ነን፡፡ አንዳንዶች በእርግጥም ይገድላሉ፡፡ ይህንን የሚያደርጉት በተለየ ሁኔታ ነፍሰ ገዳዮች ሆነው ስለተወለዱ ሳይሆን ሁላችንም ነፍሰ ገዳዮች ሆነው ስለተወለዱ ሳይሆን ሁላችንም ነፍሰ ገዳዮች የመሆን አቅም ስላለን ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛ በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦችና ነፍስን መግደል እንዳለ ነግሮናል፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ ማናችንም ከዚህ እውነት ውጪ አይደለንም፡፡
ስለዚህ እኛ ልንወስደው የሚገባን ትክክለኛው መንገድ የእግዚአብሄርን ቃል መቀበልና መታዘዝ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ሐጢያትን የምንሰራው በልቦቻችን ውስጥ ክፉ አሳቦች ስላሉ ነው፡፡
 

በልቦቻችን ውስጥ ያለ አመንዝራነት፡፡ 
 
እግዚአብሄር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምንዝርነት እንዳለ ተናገረ፡፡ ትስማማላችሁን? በልባችሁ ውስጥ ምንዝርነት እንዳለ ታምናላችሁን? አዎ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምንዝርነት አለ፡፡
በማህበረሰባችን ውስጥ ሴተኛ አዳሪነትና ሌሎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ግድፈቶች የበዙት ለዚህ ነው፡፡ ይህ በሰው ታሪክ በእያንዳንዱ ዘመን ውስጥ ገንዘብ ከሚገኝባቸው እጅግ አስተማማኝ መንገዶች አንዱ ነው፡፡ ሌሎች የንግድ ሥራዎች በኢኮኖሚ ችግር ሊመቱ ይችሉ ይሆናል፡፡ እነዚህ የረከሱ የንግድ ሥራዎች ግን ብዙም አይጎዱም፡፡ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምንዝርነት አለና፡፡
 

የሐጢያተኞች ፍሬ ሐጢያት ነው፡፡ 
 
የሰው ልጅ የሚነጻጸረው ከምን ጋር ነው? 
የሐጢያት ፍሬዎችን ብቻ ከሚያፈራ ዛፍ ጋር ነው፡፡
 
የአፕል ዛፎች አፕልን፣ የፒር ዛፎች ፒርን፣ የቴምር ዛፎች ቴምርን፣ የፐርሲሞን ዛፎችም ፐርሲሞንን ብቻ እንደሚያፈሩ ሁሉ በልቦቻችን ውስጥ 12 ሐጢያቶችን ይዘን ዳግም የተወለድነው እኛም ማፍራት የምንችለው የሐጢያት ፍሬዎችን ነው፡፡
ኢየሱስ ከሰው ልብ የሚወጣው እርሱን እንደሚያረክሰው ይናገራል፡፡ ትስማማላችሁን? እኛ ከኢየሱስ ቃሎች ጋር ብቻ በመስማማት ‹‹አዎ እኛ የሐጢያተኞች ዘሮች፣ ክፉ አድራጊዎች ነን፡፡ አዎ ጌታ ሆይ አንተ ትክክል ነህ›› ማለት እንችላለን፡፡ አዎ ክፋቶቻችንን አምነን መቀበል አለብን፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እውነቱን ለራሳችን መቀበል ይኖርብናል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንደታዘዘ እኛም የእግዚአብሄርን ቃል መቀበልና እርሱን መታዘዝ ይኖርብናል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡ እነዚህ ከእግዚአብሄር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡
አገሬ በአራት ውብ ወቅቶች የተባረከች ነች፡፡ ወቅቶች ሲለዋወጡም የተለያዩ አይነት ዛፎች ፍሬዎቻቸውን ያፈራሉ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በልቦቻችን ውስጥ ያሉት አስራ ሁለት ሐጢያቶች እኛን አጥብቀው ይይዙናል፡፡ ያለ ማቋረጥም ወደ ሐጢያት ይነዱናል፡፡ ዛሬ ልቦቻችንን ጨብጦ የያዘው ነፍስ ማጥፋት ይሆናል፡፡ ነገ ደግሞ ምንዝርና ይሆናል፡፡
ከዚያም በቀጣዩ ቀን ክፉ አሳቦች፣ ከዚያም ስርቆት፣ ከዚያም ዝሙት፣ ስርቆት፣ በሐሰት መመስከርና…ወ.ዘ.ተ ይሆናል፡፡ ዓመቱን ሙሉ በየወሩ፣ በየቀኑ፣ በየሰዓቱ ሐጢያት መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡ አንዳች ሐጢያት ሳንሰራ ቀኑ አያልፍብንም፡፡ ሐጢያት እንደማንሰራ ለራሳችን እንምላለን፡፡ ነገር ግን ልንዘልቅበት አንችልም፡፡ ምክንያቱም የተወለድነው በዚህ መንገድ ነውና፡፡
አንድ የአፕል ዛፍ ማፍራት ስላልፈለገ የአፕል ፍሬዎችን ማፍራት እምቢ ሲል አይታችሁ ታውቃላችሁን? ‹‹አፕሎችን ማፍራት አልፈልግም!›› ፍሬ ማፍራቱን እምቢ ቢል እንኳን እንዴት አፕሎችን ማፍራት አይቻለውም? በጸደይ አበቦች ማበባቸው፤ አፕሎችም ማደጋቸውና በበጋም ማፍራታቸው አይቀርም፡፡ በበልግም ፍሬዎቹ ተለቅመው ለመበላት ዝግጁ ይሆናሉ፡፡   : 
ይህ የተፈጥሮ ችሮታ ነው፡፡ የሐጢያተኞችም ሕይወት እንደዚሁ ተመሳሳይ የሆነ የተፈጥሮ ሕግን መከተል አለበት፡፡ ሐጢያተኞች የሐጢያትን ፍሬዎች ከማፍራት በቀር ምንም ነገር ማድረግ አይችሉም፡፡
 


‹የኢየሱስ ጥምቀትና መስቀሉ› ሐጢያቶቻችን ማስተሰረይ ነበረባቸው፡፡

 
የኢየሱስ ‹ስርየት› ማለት ምን ማለት ነው? 
ይህ በኢየሱስ ጥምቀትና (በእጆች መጫን) በመስቀሉ ላይ ደሙ የሐጢያትን ደመወዝ መክፈል ነው፡፡
 
የክፉ አድራጊዎች ዘር የሆኑት ሐጢያተኞች በእግዚአብሄር ፊት እንዴት ሐጢያቶቻቸውን ማስተሰረይ እንደሚችሉና ሕይወታቸውንም በደስታ እንደሚኖሩ ለማወቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ምንባብ እናንብብ፡፡ ይህ የሐጢያቶች ስርየት የሚገኝበት ወንጌል ነው፡፡
በዘሌዋውያን 4 ላይ እንዲህ ተብሎዋል፡- ‹‹ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ሐጢአትን ሳያውቅ ቢሰራ እግዚአብሄርም አትስራ ያለውን ትዕዛዝ ቢተላለፍ ቢበድልም ለእርሱም የሰራው ሐጢአት ቢታወቀው ስለ ሰራው ሐጢአት ነውር የሌለባትን ፍየል ለቁርባኑ ያመጣል፡፡ እጁንም በሐጢአት መስዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ የሚቃጠልም መስዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የሐጢአትን መስዋዕት ያርዳል፡፡ ካህኑም ከደምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መስዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፡፡ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈሰዋል፡፡ ስቡም ከደህንነት መሥዋዕት ላይ እንደሚወስድ ስብዋን ሁሉ ይወስዳል፡፡ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፤ እርሱም ይቅር ይባላል፡፡›› (ዘሌዋውያን 4፡27-31)
የብሉይ ኪዳን ሰዎች ለሐጢያቶቻቸው ስርየትን የሚያገኙት እንዴት ነበር? በመጀመሪያ እጆቻቸውን በሐጢያት ቁርባኑ ራስ ላይ ይጭኑና ሐጢያቶቻቸውን ወደ እርሱ ያስተላልፋሉ፡፡
በዘሌዋውያን ላይ እንዲህ ተጻፈ፡- ‹‹ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሄር መባን ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ፡፡ መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል፡፡ እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ ያስተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆንለታል፡፡›› (ዘሌዋውያን 1፡2-4)
በዚያ ዘመን የሚኖር አንድ ሰው በልቡ ውስጥ ሐጢያት እንዳለ ካወቀ ለሐጢያት ስርየት ጥቅም ላይ የሚውሉ የሐጢያት ቁርባኖችን ማዘጋጀት ነበረበት፡፡ የሰራቸውን ሐጢያቶች ለማስተላለፍም በሐጢያት መስዋዕቱ ራስ ላይ ‹እጆቹን መጫን› ነበረበት፡፡ በቅዱሱ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ የሚቃጠል መስዋዕት መሰውያ ነበር፡፡ ይህም ሳጥን የሚመስል ከአንድ የምስባክ ጠረጴዛ ትንሽ የሚተልቅ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ማዕዘን ላይም ቀንዶች ነበሩት፡፡ የእስራኤል ሕዝብ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የሚያገኙት ሐጢያቶቻቸውን ወደ ሐጢያት መስዋዕቱ ራስ ላይ በማስተላለፍና ሥጋውን በሚቃጠለው መስዋዕት መሰዊያ ላይ በማቃጠል ነበር፡፡
እግዚአብሄር በዘሌዋውያን ውስጥ ለሕዝቡ ‹‹በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል›› ሲል ተናገረ፡፡ እጆቻቸውን በራሱ ላይ በሚጭኑበት ጊዜ የእነርሱ ሐጢያቶች ወደ ሐጢያት ቁርባኑ ይተላለፉ ነበር፡፡ ከዚያም ሐጢያተኛው የቁርባኑን ጉሮሮ ይቆርጥና ደሙን በሚቃጠለው መስዋዕት መሰዊያ ቀንዶች ላይ ይቀባል፡፡
ከዚያ በኋላ የቁርባኑ በድን በውስጡ ካሉት ብልቶቹ ይጸዳና ሥጋው ተቆራርጦ በሚቃጠለው መስዋዕት መሰዊያ ላይ አመድ እስኪሆን ድረስ ይቃጠላል፡፡ ከዚያም የሥጋው ጣፋጭ ሽታ ለስርየታቸው ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሄር ይቀርባል፡፡ የዘወትር ሐጢያቶቻቸውን የሚያስተሰርዩት እንዲህ ነበር፡፡
እግዚአብሄር ለዓመታዊ ሐጢያቶቻቸው ሌላ የስርየት መስዋዕትን ፈቀደ፡፡ ይህ ለዘወትር ሐጢያቶች ከሚቀርበው የስርየት መስዋዕት ይለያል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ወክሎ እጆቹን በሐጢያት ቁርባኑ ላይ ይጭንና በስርየት መክደኛው በስተ ምሥራቅ ደሙን ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ እንደዚሁም ሕያው በሆነው ፍየል ራስ ላይ እጆቹን መጫኑ በየአመቱ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን በእስራኤል ሕዝብ ፊት ይደረጋል፡፡ (ዘሌዋውያን 16፡5-27)
 
የብሉይ ኪዳን የሐጢያት ቁርባን የሚያመለክተው ማንን ነው?  
ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡
 
አሁን የመስዋዕቱ ስርየት በአዲስ ኪዳን እንዴት እንደተለወጠና የእግዚአብሄር ዘላለማዊ ስርዓትም በዓመታት ውስጥ እንዴት እንደተለወጠና የእግዚአብሄር ዘላለማዊ ስርዓትም በአመታት ውስጥ እንዴት እንደተለወጠ እንመልከት፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት የነበረበት ለምንድነው? እግዚአብሄር ልጁ በመስቀል ላይ ይሞት ዘንድ የፈቀደው እርሱ በምድር ላይ ምን ስህተት ስለሰራ ነበር? በመስቀል ላይ እንዲሞትስ ማን አስገደደው? የዓለም ሐጢያተኞች ማለትም ሁላችንም በሐጢያት ውስጥ ሳለን፣ ወድቀን ሳለን ኢየሱስ ሊያድነን ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ ተጠመቀ፤ በሰው ዘር ፋንታም ለሐጢያቶች ሁሉ በመስቀል ላይ ቅጣትን ተቀበለ፡፡ ኢየሱስ የተጠመቀበትና በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰበት መንገድ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካለው የስርየት መስዋዕት በሐጢያት ቁርባን ላይ ከሚደረገው እጆች መጫንና ከመስዋዕቱ ደም መፍሰስ ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡
በብሉይ ኪዳን ሲደረግ የነበረው እንደዚህ ነበር፡፡ ሐጢያተኛ በሐጢያት ቁርባን ራስ ላይ እጆቹን  ይጭንና ‹‹ጌታ ሆይ ሐጢያትን ሰርቻለሁ፡፡ ነፍስ አጥፍቻለሁ፤ አመንዝሬያለሁ›› በማለት ሐጢያቶችን ይናዘዛል፡፡ ከዚያም ሐጢያቶቹ ወደ ሐጢያት ቁርባን ይተላለፋሉ፡፡
ሐጢያተኛው ለሐጢያት የቀረበውን ቁርባን እንደሚያርድና በእግዚአብሄር ፊት እንደሚያቀርበው ሁሉ ኢየሱስም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለማስተሰረይ በተመሳሳይ መንገድ ቀረበ፡፡ ኢየሱስ እኛን ለማዳንና በመስዋዕቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለማስተሰረይ ተጠመቀ፡፡ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡
እንዲያውም ኢየሱስ የሞተው በእኛ ምክንያት ነው፡፤ ስለዚህ ነገር ስናስብ እንከን የሌለባቸውን እነዚያን እንስሶች ለሕዝቡ ሁሉ ሐጢያቶች ቁርባን አድርጎ የማቅረቡ ትርጉም ምንድነው? እነዚያ እንስሶች በሙሉ ሐጢያት ምን እንደሆነ ያውቁ ነበርን? እንስሶች ሐጢያትን አያውቁም፡፡ እነርሱ እንከን የሌለባቸው መሆን ነበረባቸው፡፡
እነዚያ እንስሶች ሙሉ በሙሉ ያለ እንከን ስለነበሩ ኢየሱስም እንደዚሁ ሐጢያት የሌለበት መሆን ነበረበት፡፡ እርሱ ቅዱስ አምላክ የእግዚአብሄር ልጅ ነው፡፡ እርሱ ፈጽሞ ሐጢያት አልሰራም፡፡ ስለዚህ 30 ዓመት ሲሆነው በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀው ጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ 
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሞተው ከእኛ በወሰዳቸው ሐጢያቶች ምክንያት ነው፡፡ የሰውን ዘረ ሐጢያቶች በሙሉ ያነጻው የእርሱ የደህንነት አገልግሎት ነበር፡፡ 
 

የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል መጀመሪያ፡፡ 
 
ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀው ለምን ነበር? 
ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ነበር፡፡
 
በማቴዎስ 3 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡›› (ማቴዎስ 3፡13-15)
ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሆነው ለምን እንደተጠመቀ ማወቅና ማስተዋል ይኖርብናል፡፡ እርሱ የተጠመቀው የሕዝቡን ሁሉ ሐጢያቶች ለማስተሰረይና የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ ለመፈጸም ነበር፡፡ እንከን የሌለበት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት፡፡
በዚህም የዓለምን ሐጢያቶች ወሰደ፡፡ የሰዎችን ሁሉ ሐጢያቶች ለማስተሰረይም ራሱን አቀረበ፡፡ እኛም ከሐጢያት ለመዳን ምሉዕ የሆነውን እውነት ማወቅና በእርሱ ማመን አለብን፡፡ በእርሱ ደህንነት ማመንና መዳን የእኛ ፋንታ ነው፡፡
የኢየሱስ ጥምቀት ምን ማለት ነው? ይህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚደረገው እጆችን መጫን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የሕዝቡ ሁሉ ሐጢያቶች በሊቀ ካህኑ እጆች መጫን ለሐጢያት ወደቀረበው መስዋዕት ራስ ላይ ይተላለፍ ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳንም እንደዚሁ ኢየሱስ ራሱን ለሐጢያት መስዋዕት አድርጎ በማቅረብና በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች ወስዶዋል፡፡
አጥማቂው ዮሐንስ ከሰዎች መካከል እጅግ ታላቁ ሰውና በእግዚአብሄርም የተሾመ የሰው ዘር ወኪል ነበር፡፡ እርሱ የሰው ዘር ወኪል የሰብአዊ ፍጡራን ሊቀ ካህን በመሆኑ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ ጭኖ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ አስተላለፈ፡፡ ‹ጥምቀት› የሚየመላክተው ‹ማስተላለፍን፣ መቀበርንና መታጠብን› ነው፡፡
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ለምን በአጥማቂው ዮሐንስ እንደተጠመቀ ታውቃላችሁን? የእርሱን ጥምቀት አውቃችሁ በኢየሱስ ታምናላችሁን? ኢየሱስ ተጠመቀው ሐጢያቶቻችንን በሙሉ፣ እኛ የክፉ አድራጊ ዘሮች በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የሰራናቸውን ሐጢያቶች ለመውሰድ ነበር፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ለሐጢያቶቻችን የሚሆነውን እውነተኛ ወንጌል ለመፈጸም ኢየሱስን አጠመቀው፡፡
ማቴዎስ 3፡13-17 የሚጀምረው ‹ያን ጊዜ› በሚል ቃል ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ የተጠመቀበትን ጊዜ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ የተላለፉበትን ጊዜ ነው፡፡
‹ያን ጊዜ› ኢየሱስ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በመሉ ወሰደ፡፡ ከሦስት ዓመት በኋላም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ በሦስተኛው ቀን ተነሳ፡፡ እርሱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለማንጻት ለአንዴና ለመጨረሸ ተጠመቀ፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ከሙታንም ለአንዴና ለመጨረሻ ተነሳ፡፡ እርሱ በእግዚአብሄር ፊት ከሐጢያቶቻቸው መዳን ለሚፈልጉ ሰዎች የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻም አዳናቸው፡፡
ኢየሱስ ለምን መጠመቅ አስፈለገው? እንደ አንድ ተራ ወንጀለኛ የእሾህ አክሊልን የደፋውና በጲላጦስ ችሎት የተፈረደበት ለምንድነው? በመስቀል ላይ መሰቀልና እስከ ሞት ድረስ መድማት ያስፈለገውስ ለምን ነበር? ከላይ ለተጠቀሱት ሁሉ ምክንያቱ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ስለወሰደ ነው፡፡ እርሱ ስለ ሐጢያቶቻችን በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት፡፡
እግዚአብሄር እንዳዳነን በሚናገረው የደህንነት ቃል ማመንና እርሱን ማመስገን ይኖርብናል፡፡ ያለ ኢየሱስ ጥምቀት፣ ያለ መስቀሉና ትንሳኤው ደህንነት አናገኝም፡፡
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ በዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን ወስዶ በደህንነት ወንጌሉ የምናምነውን አዳነን፡፡ ‹‹ኢየሱስ ወሰደው የአዳምን ሐጢያት ብቻ ነው አይደል?›› ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ተሳስተዋል፡፡
ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደወሰደ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተጽፎዋል፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የአዳምንም ሐጢያት ጨምሮ ነጽተዋል፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ማለት ሁሉም ሐጢያቶች አንዳችም ሳይቀሩ ከእኛ ተወስደዋል ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ የዕድሜ ዘመን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አንጽቷልን? አዎ አንጽቷል፡፡ በቅድሚያ የዚህን መረጃ በዘሌዋውያን ውስጥ እናግኝ፡፡ ይህም ስለ ሊቀ ካህኑና ስለ ስርየት ቀን መስዋዕት ይነግረናል፡፡
 

ለእስራኤል ሕዝቦች ዓመታዊ ሐጢያቶች የሚቀርበው የስርየት መስዋዕት፡፡
 
እስራኤላውያን በዚህ ምድር ላይ በሚቀርበው የሐጢያት መስዋዕት ለአንዴና ለመጨረሻ መቀደስ ይችላሉን? 
በፍጹም፡፡
 
‹‹አሮንም ለእርሱ ያለውን የሐጢአቱን መስዋዕት ወይፈን ያቀርባል፡፡ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፡፡ ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሄር ፊት ያቆማቸዋል፡፡ አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፡፡ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሄር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ፡፡ አሮንም የእግዚአብሄር ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያቀርባል፡፡ ስለ ሐጢአትም መስዋዕት ያደርገዋል፡፡ የመለቀቅም ዕጣ የሖነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሄር ፊት ያቆመዋል፡፡›› (ዘሌዋውያን 16፡6-10) እዚህ ላይ አሮን የእስራኤሎችን ዓመታዊ ሐጢያቶች ለማንጻት በመገናኛው ድንኳን በራፍ ላይ ሁለት ፍየሎችን አቀረበ፡፡
 ‹‹አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፡፡ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሄር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ፡፡››
የሐጢያተኛውን ሐጢያት ለቁርባን በቀረበው እንስሳ ራስ ላይ እጆቹን በመጫን ወደ እርሱ ለማስተላለፍ ዘወትር ለሚሰሩት ሐጢያቶች ሕጋዊ ስርየትን ለማድረግ አንድ የመስዋዕት እንስሳ አስፈለገ፡፡ ነገር ግን በየዓመቱ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን እስራኤሎች አመቱን በሙሉ ለሰሩዋቸው ሐጢያቶች ሕዝቡን ሁሉ ወክሎ የዓመቱን ሐጢያቶች ለሐጢያት በቀረበው መስዋዕት ላይ የሚያስተላልፈው ሊቀ ካህኑ ነበር፡፡
በዘሌዋውያን 16፡29-31 ላይ እንዲህ ተጻፈ፡- ‹‹በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፡፡ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሰሩበት፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ከሐጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፡፡ ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፡፡ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፡፡ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፡፡›› (ዘሌዋውያን 16፡29-31)
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የእስራኤል ሕዝብ ዘወትር ለሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች ስርየትን ለማግኘትና ‹‹ጌታ ሆይ እንዲህና እንዲህ ያሉ ሐጢያቶችን ሰርቻለሁ፤ እባክህ ይቅር በለኝ›› ብለው በመናዘዝ ሐጢያቶቻቸውን ወደ ቁርባኑ እንስሳ ራስ ለማስተላለፍ የሐጢያት ቁርባንን አቀረቡ፡፡ ከዚያም ለሐጢያት ቁርባን ሆኖ የቀረበውን እንስሳ በማረድ ደሙን ለካህኑ ይሰጠውና አሁን ከሐጢያቶቹ ነጻ እንደሆነ አምኖ ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡ በዚህም ለሐጢያት የቀረበው ቁርባን ሐጢያቱን በራሱ ላይ ተሸክሞ ለሐጢያተኛው ይሞታል፡፡ ለመስዋዕት የቀረበው እንስሳ በሐጢያተኛው ፋንታ ይገደላል፡፡ በብሉይ ኪዳን የሐጢያት ቁርባኑ ፍየል፣ ጠቦት፣ ጥጃ ወይም ወይፈን ማለትም እግዚአብሄር ከለያቸው የተቀደሱ እንስሶች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
እግዚአብሄር ወሰን በሌለው ምህረቱ በሐጢያተኛው ፋንታ ለሐጢያቶቹ እንዲሞትለት የእንስሳ ሕይወት እንዲቀርብ ፈቀደ፡፡
በብሉይ ኪዳን ሐጢያተኞች በዚህ መንገድ በስርየቱ መስዋዕት አማካይነት ሐጢያቶቻቸውን ማስተሰረይ ቻሉ፡፡ የሐጢያተኛው መተላለፍ በእጆች መጫን ወደ ሐጢያት መስዋዕቱ ተላልፈዋል፡፡ ደሙም የሐጢያተኛውን ሐጢያት ለማስተሰረይ ለካህኑ ይሰጥ ነበር፡፡ 
ሆኖም በየቀኑ ሐጢያቶችን ማስተሰረይ አዳጋች ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ እግዚአብሄር ሊቀ ካህኑ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፋንታ በየዓመቱ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የዓመቱን ሁሉ ሐጢያቶች እንዲያስተሰርይ ፈቀደለት፡፡
ታዲያ በስርየት ቀን የሊቀ ካህኑ ሚና ምን ነበር? በመጀመሪያ ሊቀ ካህኑ አሮን በሐጢያት መስዋዕቱ ላይ እጆቹን በመጫን ‹‹ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህና እንዲህ ያሉትን ሐጢያቶች ነፍስ መግደልን፣ ምንዝርናን፣ ዝሙትን፣ ስርቆትን፣ በሐሰት መመስከርን ስድብን…ፈጽመዋል›› ብሎ የሕዝቡን ሐጢያቶች ይናዘዛል፡፡
ከዚያም የሐጢያት መስዋዕቱን ያርድና ደሙን ወስዶ ያንን ደም በቅዱሱ መቅደስ ውስጥ ባለው የስርየት መክደኛ ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ (በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 7 ቁጥር ፍጹም ቁጥር ተብሎ ይቆጠራል፡፡)
የሕዝቡን ዓመታዊ ሐጢያቶች በእነርሱ ፋንታ ለሐጢያት በቀረበው መስዋዕት ራስ ላይ ማስተላለፍ የእርሱ ተግባር ነበር፡፡ የሐጢያት መስዋዕቱም በይፋ ይሰዋል፡፡
እግዚአብሄር ጻድቅ ስለሆነ ሰዎችን ሁሉ ከሐጢያቶቸቸው ለማዳን ለሐጢያት የሚቀርበው መስዋዕት በሕዝቡ ፋንታ እንዲሞት ፈቀደ፡፡ እግዚአብሄር በእውነት መሐሪ ስለሆነ ሕዝቡ በእነርሱ ምትክ የመስዋዕቱን እንስሳ ሕይወት እንዲያቀርቡ ፈቀደላቸው፡፡ ከዚያም ሊቀ ካህኑ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን በሚውለው የስርየት ቀን ደሙን በስርየት መክደኛው በስተ ምስራቅ በመርጨት ሕዝቡ ባለፈው ዓመት የሰሩዋቸውን ሐጢያቶች በሙሉ ያስተሰርያል፡፡ 
 
በብሉይ ኪዳን መሰረት መስዋዕቱ ማነው? 
ሐጢያት የሌለበት ኢየሱስ ነው፡፡
 
ሊቀ ካህኑ በስርየት ቀን ለእስራኤል ሕዝብ ሁለት ፍየሎችን ማቅረብ ነበረበት፡፡ ከእነርሱ አንዱ የሚለቀቅ ፍየል ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም ‹ማውጣት› ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የአዲስ ኪዳን የሚለቀቅ ፍየል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡›› (ዮሐንስ 3፡16)
እግዚአብሄር አንድያ ልጁን የመስዋዕት በግ አድርጎ ሰጠን፡፡ እርሱ ለሰው ዘር የመስዋዕት በግ በመሆኑ በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠምቆ አዳኝ የዓለም መሲህ ሆነ፡፡ ኢየሱስ ማለት ‹አዳኝ› ማለት ሲሆን ክርስቶስ ማለት ደግሞ ‹የተቀባው ንጉሥ› ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ‹ሁላችንንም ለማዳን የመጣ የእግዚአብሄር ልጅ› ማለት ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን በስርየት ቀን የሕዝቡ አመታዊ ሐጢያቶች ስርየትን እንዳገኙ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስም ከ2,000 አመታት በፊት ለሐጢያቶቻችን ሁሉ የሚሆነውን የስርየት ወንጌል ለማጠናቀቅ ሊጠመቅና በመስቀል ላይ ደሙን ሊያፈስስ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡
እዚህ ላይ በዘሌዋውያን ላይ የሚገኝ አንድ ምንባብ እናንብብ፡፡ ‹‹አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፡፡ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ሐጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፡፡ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፡፡
ጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል፡፡ ፍየሉም ሐጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሃ ይሸከማል፡፡ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል፡፡ (ዘሌዋውያን 16፡21-22)
በዘሌዋውያን 1 ላይ እንደተጠቀሰው የእስራኤሎች ሁሉ ሐጢያቶች በፍየሉ ራስ ላይ እንደተላለፉ ተጽፎዋል፡፡ ‹መተላለፎቻቸውን ሁሉ› በሊቀ ካህኑ እጆች መጫን ለሐጢያት በቀረበው መስዋዕት ራስ ላይ ተጭኖዋል፡፡
 

በእግዚአብሄር ሕግ መሰረት ሁላችንም ስለ ሐጢያቶቻችን እውነተኛ እውቀት ሊኖረን ይገባል፡፡
 
እግዚአብሄር ሕግን የሰጠን ለምንድነው? 
የሐጢያትን እውቀት ሊሰጠን ነው፡፡
 
የእግዚአብሄር ሕግ 613 ትዕዛዛትን ይዞዋል፡፡ እንዲያውም ስለዚህ ስናስብ እርሱ አታድርጉ ያለንን እናደርጋለን፤ እንድናደርግም የነገረንንም አናደርግም፡፡
ስለዚህ እኛ ሐጢያተኞች ነን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄር እነዚያን ትዕዛዛቶች የሰጠን ሐጢያቶቻችንን እንድናውቅ እንደሆነ ተጽፎዋል፡፡ (ሮሜ 3፡20) ይህ ማለት የትዕዛዛት ሕጉን የሰጠን ሐጢያተኞች እንደሆንን ሊያስተምረን ነው ማለት ነው፡፡ እነርሱን የሰጠን በእነርሱ መኖር ስለምንችል ሳይሆን ሐጢያቶቻችንን እንድናውቅ ነው፡፡
እርሱ ትዕዛዛቱን የሰጠን እንድንጠብቃቸው አይደለም፡፡ ውሻ እንደ ሰው ይኖር ዘንድ አትጠብቁም፡፡ እኛም ፈጽሞ የእግዚአብሄርን ሕግ በመጠበቅ አንኖርም፡፡ ነገር ግን በትዕዛዛት ሕጉ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን ብቻ ማወቅ እንችላለን፡፡
እግዚአብሄር እነርሱን የሰጠን የሐጢያት ክምችቶች ስለሆንን ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን በትክክል አልተረዳንም፡፡ ‹‹እናንተ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝራዎችና ክፉ አድራጊዎች ናችሁ፡፡›› እግዚአብሄር በትዕዛዛቱ አማካይነት ውስጠ ወይራ ነገር ነግሮናል፡፡ እንዳንገድል ነግሮናል፡፡ እኛ ግን በልቦቻችን አንዳንድ ጊዜም በሥጋችን እንገድላለን፡፡
ነገር ግን መግደል እንደማይገባን በሕጉ ውስጥ ስለተጻፈ ‹‹አሃ ተሳስቼ ነበር፡፡ እኔ ማድረግ ማይገባኝን ነገር በማድረጌ ሐጢያትን የሰራሁ ሐጢያተኛ ነኝ›› በማለት ነፍሰ ገዳዮች መሆናችንን እናውቃለን፡፡
እግዚአብሄር የእስራኤልን ሕዝብ ከሐጢያት ለማዳን በብሉይ ኪዳን የስርየት መስዋዕት እንዲቀርብ ፈቀደ፡፡ በዓመት አንድ ጊዜም ለሕዝቡ የሚያስተሰርየው አሮን ነበር፡፡
በብሉይ ኪዳን በስርየት ቀን ሁለት የሐጢያት መስዋዕቶች ለእግዚአብሄር መቅረብ ነበረባቸው፡፡ አንዱ በእግዚአብሄር ፊት ሲቀርብ ሌላው እጆች ተጭነውበት የሕዝቡን ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ ከወሰደ በኋላ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዳል፡፡ ፍየሉ በተመረጠው ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ከመሰደዱ በፊት ሊቀ ካህኑ እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ጭኖ የእስራኤልን ሐጢያቶች በሙሉ ይናዘዛል፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ሕዝቡ ገድሎዋል፤ አመንዝሮዋል፤ ሰርቋል፤ ጣዖታትን አምልከዋል፡፡…በፊትህ በድለናል፡፡››
የፓለስቲን ምድር በረሃማ ምድረ በዳ ነው፡፡ የሚለቀቀው ፍየል ማለቂያ ወደሌለው ምድረ በዳ ይሰደድና ውሎ አድሮ ይሞታል፡፡ ሲሰደድ የእስራኤል ሕዝብ ርቆ እስኪሰወር ድረስ ይመለከቱታል፡፡ ሐጢያቶቻቸውም ከሚለቀቀው ፍየል ጋር አብሮ እንደተወሰደ ያምናሉ፡፡ በዚህም ሕዝቡ የአእምሮ ሰላም ያገኛል፡፡ የሚለቀቀው ፍየልም የሕዝቡን አመታዊ ሐጢያቶች ተሸክሞ በምድረ በዳ ይሞታል፡፡
በዚህ ሁኔታ እግዚአብሄር የአምላክ በግ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ይቅር ብሎዋል፡፡ ሐጢያቶቻችን በሙሉ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት ፈጽመው ነጽተዋል፡፡
ኢየሱስ አምላክና አዳኛችን ነው፡፡ እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከሐጢያት ለማዳን የመጣ የእግዚአብሄር ልጅ ነው፡፡ እርሱ በአምሳሉ የሰራንና ከሐጢያት ሊያድነን ወደዚህ ምድር የወረደ ፈጣሪ ነው፡፡
ወደ ኢየሱስ የተላለፉት በሥጋችን የምንሰራቸው የዘወትር ሐጢያቶች ብቻ ሳይሆኑ የወደፊት ሐጢያቶቻችንንና የአእምሮዋችንና የሥጋችንም ሐጢያቶች ጭምር ናቸው፡፡ ስለዚህ እርሱ ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ የተሟላ ስርየት የሆነውን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ ይፈጽም ዘንድ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት፡፡
ኢየሱስ ከመሰቀሉ ከሦስት ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አገልግሎቱን ሲጀምር በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በማስተሰረይ ለሰው ዘር ደህንነቱን የጀመረው በጥምቀቱ ነው፡፡
እስከ ወገብ ድረስ በሚያጠልቀው በዮርዳኖስ ወንዝ አጥማቂው ዮሐንስ እጆቹን ጭኖ በውሃው ውስጥ አጠለመው፡፡ ይህ ጥምቀት ከብሉይ ኪዳኑ እጆችን መጫን ጋር ተመሳሳይና ሐጢያቶችን ሁሉ የማስተላለፍ ያው አይነት ብቃት የነበረው ነው፡፡
በውሃ ውስጥ መጥለም ማለት ሞት ማለት ነው፡፡ ከውሃ ውስጥ መውጣት ማለት ደግሞ ትንሳኤ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የተልዕኮውን ሦስቱንም ደረጃዎች ማለትም ሐጢያቶችን በሙሉ መውሰድ፣ ስቅለትንና ትንሳኤን ፈጸመ፤ ገለጠም፡፡
እኛ መዳን የምንችለው ኢየሱስ እኛን ከሐጢያት ያነጻባቸውን ቃሎች ስንታዘዝ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በኢየሱስ በኩል ሊያድነን ወሰነ፡፡ በብሉይ ኪዳን የገባው ኪዳንም በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ድርጊት አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ተሸክሞ ወደ መስቀል ሄደ፡፡ 
 
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ ለእኛ የቀረው ሥራ ምንድነው?
እኛ ማድረግ የሚኖርብን በእግዚአብሄር ቃሎች ላይ እምነት እንዲኖረን ነው፡፡
 
በዮሐንስ 1፡29 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹በነገውም ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፡- እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› አጥማቂው ዮሐንስ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› በማለት መሰከረ፡፡ የሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ወደ እርሱ ተላልፈዋል፡፡ ይህንን እመኑ! ያን ጊዜ የሐጢያቶቻችሁን ሁሉ ስርየት በማግኘት ትባረካላችሁ፡፡
በእግዚአብሄር ቃል ላይ እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡ የራሳችንን አስተሳሰቦችና ግትርነት ትተን ተጻፈውን የእግዚአብሄር ቃል መታዘዝ ይኖርብናል፡፡ በአጭሩ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደ የመሆኑን እውነት ማመን አለብን፡፡
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወስዶዋል ማለትና ሐጢያቶቻችን በማስተሰረይም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ፈጽሞዋል ማለት በትክክል ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ‹እጆችን መጫን› እና ‹ጥምቀትም› እንደዚሁ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡
‹ሁሉም› ‹እያንዳንዱ ነገር› ወይም ‹ሙሉ› ብንልም ትርጉሙ ያው ተመሳሳይ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ‹እጆችን መጫን› የሚለው ቃል ትርጉም በምትኩ ‹ጥምቀት› የሚለው ቃል ቃል ጥቅም ላይ ከመዋሉ በቀር በአዲስ ኪዳንም ያው ተመሳሳይ ነው፡፡
ይህም ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለማሰተሰረይ የተጠመቀና በመስቀል ላይ የተኮነነ ወደመሆኑ ቀላል እውነት ይደርሳል፡፡ በዚህ እውነተኛ ወንጌል ስናምን መዳን እንችላለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ‹የዓለምን ሐጢያት› በሙሉ (ዮሐንስ 1፡29) እንደወሰደ ሲናገር የዓለም ሐጢያት ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ይዘናቸው የተወለድናቸው ሐጢያቶች በሙሉ ማለትም በአእምሮዋችን ውስጥ ያሉ ክፉ አሳቦች፣ ስርቆት፣ ምንዝርና፣ መመኘት፣ ክፋት፣ ስድብ፣ ትዕቢትና ስንፍና ማለት ነው፡፡ ይህ በሥጋና በልብ የምንሰራቸውን መተላለፎችና በደሎች በሙሉ ይጨምራል፡፡
‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡›› (ሮሜ 6፡23) ‹‹ደም ሳይፈስ ስርየት የለም፡፡›› (ዕብራውያን 9፡22) በእነዚህ ቁጥሮች ውሰጥ እንደተባለው ሐጢያቶች በሙሉ ደመወዛቸው መከፈል ይኖርበታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር በሙሉ ከሐጢያት ለማዳን የራሱን ሕይወት አቀረበና ለአንዴና ለመጨረሻ ስለ እኛ የሐጢያትን ደመወዝ ከፈለ፡፡
ስለዚህ ከሐጢያቶቻችን ለመላቀቅ እኛ ማድረግ የሚኖርብን በእውነተኛው ወንጌል--በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ እንደዚሁም በመለኮታዊነቱ ማመን ነው፡፡
 

ነገ ለሚሰሩ ሐጢያቶች የሚሆን ስርየት፡፡
 
ዳግመኛ ለሐጢያቶቻችን መስዋዕት ማቅረብ ያስፈልገናልን? 
ዳግመኛ በፍጹም፡፡
 
የነገ፣ የከነገ በስቲያ ሐጢያቶችና እስከ ዕለተ ሞታችን የምንሰራቸው ሐጢያቶችም እንደዚሁ ‹በአለም ሐጢያት ውስጥ› ተጨምረዋል፡፡ የዛሬው የትናንትናውና ከትናትና በፊት ተሰሩት ሐጠያቶችም እንደዚሁ ‹በዓለም ሐጢያት ውስጥ› ተጨምረዋል፡፡ ሰዎች ከውልደት እስከ ሞት ድረስ ሰዎች የሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች ሁሉም ‹የዓለም ሐጢያት› ክፍል ናቸው፡፡ የዓለም ሐጢያቶችም በጥምቀቱ አማካይነት ፈጽመው ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡ እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ የምንሰራቸው ሐጢያቶች በሙሉ አስቀድመው ከእኛ ተወስደዋል፡፡
ለመዳን የሚያስፈልገን በዚህ እውነተኛ ወንጌል በተጻፉት የእግዚአብሄር ቃሎች ማመንና እውነትን መታዘዝ ብቻ ነው፡፡ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለመዋጀት የራሳችንን አስተሳሰቦች ማስወገድ ይገባናል፡፡ ‹‹ገና ያልተሰሩትን ሐጢያቶች እንዴት ሊወስድ ይችላል?›› ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል፡፡ እኔም ደግሞ መልሼ እጠይቃችኋለሁ፡፡ ‹‹ሐጢያት በሰራን ጊዜ ሁሉ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ተመልሶ መምጣትና ደሙን ደጋግሞ ማፍሰስ ይገባዋልን?››
ዳግም በመወለድ ወንጌል ውስጥ ለሐጢያቶቻችን ስርየት የሚሆን ሕግ አለ፡፡ ‹‹ደም ሳይፈስ ስርየት የለም፡፡›› (ዕብራውያን 9፡22) በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ሰው ከሐጢያቶቹ ለመዳን በፈለገ ጊዜ እጆቹን በሐጢያት መስዋዕቱ ላይ በመጫን ሐጢያቶቹን ማስተላለፍ ነበረበት፡፡ ለሐጢያት የቀረበውም መስዋዕት ለሐጢያቶቹ መሞት ነበረበት፡፡
በዚሁ ተመሳሳይ መንገድ የእግዚአብሄር ልጅ የሰውን ዘር ሁሉ ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድም ተጠመቀ፡፡ የሐጢያቶቻችንን ደመወዝ ለመክፈልም በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ ‹‹ተፈጸመ!›› በማለትም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሳ፡፡ አሁን በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጦዋል፡፡ በዚህም ለዘላለም አዳኛችን ሆነ፡፡
ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ነጻ ለመውጣት ግትር አሳቦቻችንን መጣልና በየቀኑ በምናቀርባቸው የንስሐ ጸሎቶች ራሳችንን ዘወትር ከምንሰራቸው ሐጢያቶች እንድንዋጅ የሚነግረንን የሐይማኖት ትምህርት መተው ይኖርብናል፡፡ የሰው ዘር ሐጢያቶች ስርየትን ያገኙ ዘንድ ሕጋዊው መስዋዕት ለአንዴና ለመጨረሻ መቅረብ ነበረበት፡፡ በሰማይ ያለው አምላክ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ገዛ ልጁ በማስተላለፍ ስለ እኛ እንዲሰቀል አደረገው፡፡ እርሱ ከሙታን በመነሳቱም ደህንነታችን ተጠናቋል፡፡
‹‹እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፡፡ የደህንነታችንም ተግሳጽ በእርሱ ላይ ነበረ፡፡ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፡፡ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፡፡…እግዚአብሄርም የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡›› በኢሳይያስ 53 ላይ የዓለምና የሰው ዘር መተላለፎችና በደሎች ሁሉ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተላለፉ ተነግሮዋል፡፡
በአዲስ ኪዳን ውስጥ በኤፌሶን 1፡4 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፡፡›› ይህ እርሱ ከዓለም ፍጥረት በፊት በእርሱ በኩል እንደመረጠን ይነግረናል፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንኳን እግዚአብሄር በክርስቶስ የእርሱ ሕዝብ፤ እንከን የሌለብን ጻድቃን ሊያደርገን ወሰነ፡፡ ከዚህ በፊት ያሰብነው ምንም ነገር ቢኖር አሁን የእግዚአብሄር ቃል የሆኑትን የውሃውን፣ የደሙንና የመንፈሱን ቃሎች ማመንና መታዘዝ ይገባናል፡፡
እግዚአብሄር የእርሱ በግ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች እንደወሰደና ለሰው ዘር ሁሉ ስርየትን እንደሰጠ ነግሮናል፡፡ በዕብራውያን 10 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፡፡ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መስዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም፡፡›› (ዕብራውያን 10፡1)
እዚህ ላይ ቃሉ በየዓመቱ የሚያቀርቡዋቸው እነዚያው መስዋዕቶች እነርሱን በጭራሽ ፍጹማን ሊያደርጉዋቸው እንደማይችሉ ይናገራል፡፡ ሕጉ ሊመጣ ያለው በጎ ነገር ጥላ እንጂ የእውነተኛው ነገር ትክክለኛ አምሳል አይደለም፡፡ የሚመጣው መሲህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለማስተሰረይ በመጠመቅና በመሰቀል ለአንዴና ለመጨረሻ (የእስራኤል አመታዊ ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ እንደሚሰረዩ ሁሉ) ፍጹማን አደረገን፡፡
ስለዚህ ኢየሱስ በዕብራውያን 10 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ቀጥሎ፡- እነሆ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ላደርግ መጥቻለሁ ብሎአል፡፡ ሁለተኛውን ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል፡፡ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል፡፡ ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ሐጢያትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መስዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደፊት ይጠብቃል፡፡ አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡ መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናልና፡፡ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ ሐጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል፡፡ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› (ዕብራውያን 10፡9-18)
ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ እንዳዳነን እናምናለን፡፡
 

በልቦቻችንና በልቡናዎቻችን ላይ የተጻፈው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድ ደህንነት፡፡
 
ዳግመኛ ሐጢያትን ስለማንሰራ ብቻ ጻድቃን ነን?  
አይደለንም፡፡ እኛ ጻድቃን የሆንነው ኢየሱስ ሐጢያታችንን በሙሉ ስለወሰደና እኛም በእርሱ ስለምናምን ነው፡፡
 
ሁላችሁም በእርሱ ፍጹም ደህንነት ታምናላችሁን? --አሜን-- ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እኛን ለማዳን እንደተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰ የሚናገሩትን የእግዚአብሄር ቃሎች በእምነት ትታዘዛላችሁን? ዳግም ለመወለድ በእርሱ ቃል ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በስርየት ወንጌል አማካይነት ከዓለም ሐጢያት ጋር አብሮ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዳነጻ ስናምን መዳን እንችላለን፡፡
የእግዚአብሄርን ሕግ በመጠበቅ ፈጽሞ ሐጢያት አልባ መሆን አንችልም፡፡ ነገር ግን በእርሱ ሥራዎች ላይ ባለን እምነት ፍጹማን ልንሆን እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደና ተፈረደበት፡፡ በመስቀል ላይም ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ቅጣትን ተቀበለ፡፡ ይህንን ወንጌል ከሙሉ ልባችን በማመን ከሐጢያቶቻችን ልንድንና ጻድቃን ልንሆን እንችላለን፡፡ ይህንን ታምናላችሁን?
 የኢየሱስ ጥምቀት፣ ስቅለቱና ትንሳኤው ለሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ስርየትን የሚያመጡና ወሰን በሌለውና በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የእግዚአብሄር ፍቅር ላይ የተመሰረቱ የደህንነት ሕግ ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ባለንበት ሁኔታ ወዶናል፡፡ እርሱ ጻድቅ ነው፡፡ ስለዚህ አስቀድሞ ጻድቃን አደረገን፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በእርሱ ጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ በማስተላለፍም ጻድቃን አደረገን፡፡
ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለማንጻት አንድያ ልጁን ኢየሱስን ስለ እኛ ወደዚህ ዓለም ላከው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንዲወስድ ፈቀደ፡፡ ከዚያም የሐጢያቶቻችንን ፍርድ በሙሉ ወደ ልጁ አስተላለፈ፡፡ የእግዚአብሄር አጋፔ በሆነው የውሃና የደም ደህንነት አማካይነት ጻድቅ ልጆቹ አደረገን፡፡
በዕብራውያን 10፡16 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡፡ ‹‹በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፡፡››
እኛ በልቦቻችንና በአእምሮዋችን በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች ነን ወይስ ጻድቃን ነን? በእግዚአብሄር ቃል ላይ እምነት ካለን ጻድቃን እንሆናለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰዶ ለእነርሱ ተኮንኖዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን ነው፡፡ ‹‹እኛ በየቀኑ ሐጢያት ስለምንሰራ እንዴት ጻድቃን ልንሆን እንችላለን? እኛ በእርግጥም ሐጢያተኞች ነን›› ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ አባቱን እንደታዘዘ በእግዚአብሄር ቃል ስናምን ጻድቃን እንሆናለን፡፡
በእርግጥ ቀደም ብዬ እንዳልሁት ዳግም ከመወለዳችን በፊት በልቦቻችን ውስጥ ሐጢያት ነበረብን፡፡ የሐጢያቶቻችን ስርየት የሆነውን ወንጌል ከወሰድን በኋላ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ዳንን፡፡ ወንጌልን ሳናውቅ በነበርንበት ጊዜ ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ በኢየሱስ ደህንነት ማመን ስንጀምር ጻድቃንና የእግዚአብሄር ጻድቅ ልጆች ሆነን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረለት ጻድቃን የመሆን እምነት ይህ ነው፡፡ የሐጢያት ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ያለን እምነት ‹ጻድቃን› አደረገን፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ፣ አብርሃም፣ የእምነት አባቶችም ጭምር ጻድቃን የሆኑት የሐጢያቶች ስርየት በእርሱ የበረከት ቃሎች፤ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ባላቸው እምነት እንጂ በሥራዎቻቸው አይደለም፡፡
ዕብራውያን 10፡18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ ከዚህ ወዲህ ስለ ሐጢአት ማቅረብ የለም፡፡›› እንደተጻፈው በሐጢያቶቻችን እንዳንሞት እግዚአብሄር አዳነን፡፡ በዚህ ታምናላችሁን?--አሜን፡፡--
በፊልጵስዩስ 2 ላይ ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በአናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን፡፡ እርሱ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሄር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም፡፡ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፡፡ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፡፡ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ፡፡ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሄር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፡፡ ከስምም በላይ ያለውን ስም ሰጠው፡፡ ይህም በሰማይና በምድር ከምድር በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሄር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው፡፡›› (ፊልጵስዩስ 2፡5-11)
የክብሩ መንጸባረቅና የባህሪው ትክክለኛ መገለጫ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ (ዕብራውያን 1፡3) ለራሱ አንዳች ትልቅ ክብርን አልወሰደም፡፡ በፋንታው ለራሱ የባሪያን መልክ ወሰደ፡፡ በሰው አምሳልም መጣ፡፡ እርሱ ራሱን አዋረደ፡፡ እኛን ለማዳንም እስከ ሞት ድረስ ታዘዘ፡፡
ስለዚህ ኢየሱስን እናመሰግነዋለን፡፡ ‹‹እርሱ አምላካችን አዳኝና ንጉሥ ነው፡፡›› እግዚአብሄርን የምናከብረውና ኢየሱስን የምናመሰግነው ኢየሱስ እስከ መጨረሻው ድረስ የአባቱን ፈቃድ ስለታዘዘ ነው፡፡ እርሱ ባይታዘዝ ኖሮ አሁን የእግዚአብሄርን ልጅ ባላከበርነውም ነበር፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ልጅ የአባቱን ፈቃድ እስከ ሞት ድረስ ስለታዘዘ በዚህ ምድር ላይ ያለ ፍጥረትና ሕዝብ ሁሉ ያከብረዋል፡፡ ይህንኑም ለዘላለም ያደርገዋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደ የእግዚአብሄር በግ ነው፡፡ እርሱ እነዚህን ሐጢያቶች በጥምቀቱ አማካይነት እንደወሰዳቸውም ተጽፎዋል፡፡ እርሱ የዓለምን ሐጢያቶች ከወሰደ 2,000 አመታት ያህል አልፎዋል፡፡ እናንተና እኔ ከውልደታችን ጀምሮ በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ነበርን፡፡ ሐጢያቶቻችንም ሁሉ በዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡

ነገ ሐጢያትን ብንሰራ ሐጢያተኞች እንሆናለን? 
አንሆንም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱንም ሐጢያት ሁሉ ወስዶዋል፡፡
 
የአዳምን ሐጢያት በዕድሜ ዘመናችን ከሰራናቸው ሐጢያቶች ሳንለይ ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ሐጢያት አልሰራንምን? -- አዎ ሰርተናል፡፡-- 
ኢየሱስ ከተወለድንበት ቀን እስከምንሞትበት ቀን ድረስ ሐጢያት እንደምንሰራ ስላወቀ አስቀድሞ ሐጢያቶቸችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ አሁንን ይህንን ማየት ትችላላችሁን? እስከ 70 አመት ድረስ ብንኖር ሐጢያቶቻችን ከመቶ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ የጭነት መኪናዎች በላይ ይሞሉ ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ በአንድ ጊዜ ወሰደ፡፡ ከእርሱም ጋር በመስቀል ላይ ተሸከማቸው፡፡
ኢየሱስ የአዳምን ሐጢያት ብቻ ወስዶ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም ሞተን ሲዖል እንወርድ ነበር፡፡ እርሱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ መውሰድ እንዳልቻለ ቢሰማን እንኳን ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የመደምሰሱን ሐቅ ፈጽሞ አይለውጠውም፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ምን ያህል ሐጢያት መስራት እንችላለን? የምንሰራቸው ሐጢያቶች በሙሉ በዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡
ኢየሱስ ዮሐንስን እንዲያጠምቀው በነገረው ጊዜ በትክክል የተናገረውን ማለቱ ነበር፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ ራሱ መሰከረ፡፡ እግዚአብሄር ከኢየሱስ በፊት ባርያውን ልኮ በእርሱ እንዲጠመቅ አደረገው፡፡ ኢየሱስ የሰው ዘር ወኪል በሆነው በዮሐንስ በመጠመቅና ለመጠመቅም በፊቱ ራሱን ዝቅ በማድረግ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡
ከ20 እስከ 30፤ ከ30 እስከ 40፤ እና ወ.ዘ.ተ ዕድሜ ድረስ የሰራናቸው ሐጢያቶችና የልጆቻችንም ሐጢያቶች እንኳን ሳይቀሩ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት በወሰዳቸው የዓለም ሐጢያቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ሐጢያት አለ ብሎ መናገር የሚችል ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች ወስዶዋል፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ለማስተሰረይ ባደረገው ነገር ማለትም በጥምቀቱና ባፈሰሰው ክቡር ደሙ ያለ አንዳች ጥርጥር በልቦቻችን ስናምን ሁላችንም መዳን እንችላለን፡፡
ብዙ ሰዎች ሕይወታቸው በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ስለ ሕይወታቸው በመናገር በራሳቸው አስተሳሰቦች ውስጥ ተጠቅልለው ያልተረጋጋ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪ ሕይወት የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ያልተረጋጋ ሕይወትን ኖረዋል፡፡ እኔም ዳግም ከመወለዴ በፊት እንዲህ አይነት ሕይወት ኖሬአለሁ፡፡ የስርየትን፣ የኢየሱስን ጥምቀትና የደሙን ወንጌል መረዳት ወይም መቀበል እንዴት አትችሉም?
 
 
የሐጢያተኞች ደህንነት ተፈጽሞዋል፡፡
 
ኢየሱስ የጴጥሮስን እግር ያጠበው ለምንድነው? 
ለዚህ ምክንያቱ እርሱ በጥምቀቱ አማካይነት የጴጥሮስን የወደፊት ሐጢያትም ጭምር እንዳነጻለት ጠንካራ እምነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡
 
ዮሐንስ 19ን እናንብብ፡- ‹‹ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፡፡ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ፡፡ በዚያም ሰቀሉት፡፡ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉት፡፡ ጲላጦስም ደግሞ ጽህፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፡፡ ጽህፈቱም የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበር፡፡ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበርና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽህፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር፡፡›› (ዮሐንስ 19፡17-20)
ውድ ወዳጆች ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደና በጲላጦስ ችሎት እንዲሰቀል ተፈረደበት፡፡ አሁን ስለዚህ ትዕይንት አብረን እናስብ፡፡
ከቁጥር 28 ጀምሮ ‹‹ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፡›› ኢየሱስ መጽሐፍ የሚለውን ለመፈጸም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ ‹‹ተጠማሁ አለ፡፡ በዚያም ሆምጣቴ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፡፡ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት፡፡ ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ተፈጸመ አለ፡፡ ራሱን አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡›› (ዮሐንስ 19፡28-30)
ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ተፈጸመ!›› ከዚያም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላም ከሙታን ተነሳና ወደ ሰማይ አረገ፡፡
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቁና በመስቀል ላይ መሞቱ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር ሳይነጣጠሉ የተያያዙ ናቸው፡፡ አንዱ ከሌላው ተነጥሎ መኖር የሚችልበት ምክንያት የለውም፡፡ ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በስርየት ወንጌሉ ስላዳነን እናመስግነው፡፡ 
የሰው ዘር ሥጋ ሁልጊዜም የሚከተለው የስጋን ፍላጎቶች ስለሆነ በሥጋችን ሐጢያት ከመስራት ማምለጥ አንችልም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋችን ሐጢያቶች ሊያድነን ጥምቀቱንና ደሙን ሰጠን፡፡ በወንጌሉም ከሥጋ ሐጢያቶቻችን አዳነን፡፡
ሙሉ የሐጢያቶች ስርየት ያገኙ ሰዎች በቤተልሄም በተወለደው፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀው፣ በመስቀል ላይ በሞተውና በሦስተኛው ቀን በተነሳው ኢየሱስ በማመን በማንኛውም ጊዜ መንግሥተ ሰማይ መግባት ይችላሉ፡፡ ጌታን እናመሰግነዋለን፤ ስሙንም ለዘላለም እናከብራለን፡፡
በመጨረሻው የዮሐንስ ምዕራፍ ውስጥ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ ወደ ገሊላ ሄዶ ነበር፡፡ ወደ ጴጥሮስም ሄደና እንዲህ አለው፡- ‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ከእነዚዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? ጴጥሮስም፡- አዎ ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ›› በማለት መለሰለት፡፡ ያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፡- ‹‹ግልገሎቼን አሰማራ፡፡››
ጴጥሮስ ሁሉን ነገር ማለትም የኢየሱስን ጥምቀትና የደሙን፤ የሐጢያቶች ስርየትንም ወንጌል ተረዳ፡፡ አሁን የሐጢያቶቹን ሁሉ ስርየት በሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በማመኑና ኢየሱስም ለምን እግሮቹን እንዳጠበለት በመረዳቱ በኢየሱስ ላይ ያለው እምነቱ ይበልጥ ብርቱ ሆነ፡፡
እንደገና ዮሐንስ 21፡15ን እናንብብ፡- ‹‹ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፡- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው፡፡ አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው፡፡ እርሱም፡- ግልገሎቼን አሰማራ አለው፡፡›› እርሱ ግልገሎቹን ለጴጥሮስ በአደራ መስጠት የቻለው ጴጥሮስ ሙሉ በሙሉ የዳነ የእርሱ ደቀ መዝሙር ስለነበርና ጴጥሮስ ጻድቅና ፍጹም የሆነ የእግዚአብሄር አገልጋይ ስለነበር ነው፡፡
ጴጥሮስ በየቀኑ በሚሰራቸው ሐጢያቶቹ ዳግመኛ ሐጢያተኛ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ የሐጢያቶች ስርየት የሚገኝበትን ወንጌል እንዲሰብክ ባልነገረውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ሌሎች ደቀ መዛሙርቶችን ጨምሮ እርሱም በሥጋ በየቀኑ ሐጢያት ከመስራት ማምለጥ ስለማይችል ነበር፡፡ ነገር ግን ለሐጢያቶች ስርየት በሆነው ወንጌለ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመናቸው ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ የደመሰሰውን ወንጌል እንዲሰብኩ ነገራቸው፡፡
 

ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ፡፡
 
ዳግመኛ ሐጢያትን ስትሰሩ ዳግመኛ ‹ሐጢያተኞች› ትሆናላችሁን? 
አንሆንም፤ ኢየሱስ በዮርዳኖስ የወደፊት ሐጢያቶቼን ቀድሞውኑም ወስዶዋል፡፡
 
ኢየሱስ ለጴጥሮስ ስለተናገራቸው ቃሎች እናስብ፡፡ :: ‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?›› ‹‹አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ፡፡›› የእርሱ የፍቅር ኑዛዜ የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ላይ ካለው እምነት የመነጨ እውነተኛ ኑዛዜ ነበር፡፡
ኢየሱስ እግሮቻቸውን በማጠብ ጴጥሮስንና ሌሎቹን ደቀ መዛሙርት የሐጢያቶች ስርየት የሚገኝበትን ወንጌል አስተምሮዋቸው ባይሆን ኖሮ ፍቅራቸውን በዚያ መንገድ መመስከር ባልቻሉም ነበር፡፡
በምትኩ ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ ‹‹ከእነዚህ አብልጣችሁ ትወዱኛላችሁ?›› ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ‹‹ጌታ ሆይ እኔ ጎዶሎ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ እኔ ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች በላይ ይበልጥ ልወድህ የማልችል ሐጢያተኛ ነኝ፡፡ እባክህ ተወኝ›› ማለት ይችል ነበር፡፡ ጴጥሮስ ራሱን ከኢየሱስ ለመደበቅም ሮጦ በሸሸ ነበር፡፡
ነገር ግን እስቲ የጴጥሮስን መልሶች እናንብብ፡፡ እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ባዳነው የሐጢያቶች ስርየት ማለትም የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ወንጌል ተባርኮ ነበር፡፡
ስለዚህ ጴጥሮስ ‹‹አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ›› ማለት ችሎ ነበር፡፡ ይህ የፍቅር ኑዛዜ የመነጨው በኢየሱስ ስርየት ወንጌል ላይ ካለው እምነቱ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በወሰደበት እውነተኛ የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል አምኖዋል፡፡ ይህም ሰዎች ከጉድለቶቻቸውና ከሥጋ ድክመቶቻቸው የተነሳ የሚፈጸሙዋቸውን የወደፊት ሐጢያቶች በሙሉ አካተተ፡፡
ጴጥሮስ የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል በጽናት አመነ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር በግ እንደነበረም ስላመነ ያለ ምንም ማመንታት ለጌታ መልስ መስጠት ቻለ፡፡ የኢየሱስ ደህንነት የመጣው የሐጢያቶችን ስርየት ከሚያስገኘው ወንጌል ነው፡፡ በዚህም ጴጥሮስ የዓለምን ሐጢያቶች ሁሉ በሚያስተሰርየው ወንጌል አማካይነት በደህንነት አመነ፡፡
እናንተም ደግሞ እንደ ጴጥሮስ ናችሁን? ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በስርየቱ፣ በጥምቀቱና በደሙ ወንጌል የወሰደውን ኢየሱስን መውደድና ማመን ትችላላችሁን? እንዴት እርሱን ላታምኑትም ሆነ ላትወዱት ትችላላችሁ? ሌላ መንገድ የለም፡፡ 
ኢየሱስ የወሰደው ያለፉትን ወይም አሁኖቹን ሐጢያቶች ብቻ ከሆነና የወደፊት ሐጢያቶችን ለእኛ ከተወልን አሁን እንደምናመሰግነው ልናመሰግነው ባልቻልንም ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሁላችንም ሲዖል እንደምንወርድ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ማመናችን እንዳዳነን መመስከር አለብን፡፡
ሥጋ ሁልጊዜም ሐጢያትን ለመስራት ያዘነብላል፡፡ ስለዚህ እኛም ሁልጊዜ ሐጢያትን እንሰራለን፡፡ ከዚህ የተነሳ ኢየሱስ በሰጠን የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው የተትረፈረፈ ወንጌል፤ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ወንጌል ማመናችን እንዳዳነን መመስከር አለብን፡፡
የኢየሱስ ጥምቀትና ደም በሆነው የስርየት ወንጌል ባናምን ኖሮ ማንም አማኝ ከዕድሜ ልክ ሐጢያቶቹ ባልዳነም ነበር፡፡ በተጨማሪም በየጊዜው በመናዘዝና ንስሐ በመግባት ከዕድሜ ልክ ሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነን ቢሆን ኖሮ ምናልባትም ጻድቃን ሆነን ለመቆየት በጣም ሰነፎችና ሁልጊዜም በልቦቻችን ውስጥ ሐጢያት ያለብን ሰዎች እንሆን ነበር፡፡
ይህ ቢሆን ኖሮ ሐጢያተኛ ወደ መሆን እንመለስና ኢየሱስን አንወደውም ወይም ወደ እርሱ አንቀርብም ነበር፡፡ በኢየሱስ ደህንነትም ማመንና እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስም እርሱን መከተል አንችልም ነበር፡፡ 
ኢየሱስ የሐጢያቶች ስርየት የሚገኝበትን ወንጌል ሰጠንና የምናምነውን ሰዎች አዳነን፡፡ እርሱ ፍጹም የሆነ አዳኝ በመሆን በእውነት እንወደው ዘንድ የዘወትር መተላለፎቻችንን ሁሉ አነጻ፡፡  
እኛ ምዕመናኖች የሐጢያቶቻችንን ስርየት ያስገኘውን የኢየሱስን ጥምቀትና ደም ወንጌል ከመውደድ ማምለጥ አንችልም፡፡ ምዕመናኖች ሁሉ ኢየሱስ በሰጠን የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል አማካይነት ኢየሱስን ለዘላለም መውደድና የደህንነት ፍቅር ምርኮኞች መሆን እንችላለን፡፡    
ውዶች! ኢየሱስ ኢምንት ሐጢያትን እንኳን ትቶ ቢሆን ኖሮ በኢየሱስ ማመንና የሐጢያቶችን ስርየት ለሚያስገኘው ወንጌልም ምስክር መሆን ባልቻላችሁ ነበር፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋይ ሆናችሁም መስራት ባልቻላችሁ ነበር፡፡  
ነገር ግን የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ብታምኑ ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ መዳን ትችላላችሁ፡፡ በኢየሱስ ቃል ውስጥ የተጻፈውን እውነተኛውን የስርየት ወንጌል ስትገነዘቡ ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ እንድትድኑ ይፈቅድላችኋል፡፡
 

‹‹ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?›› 
 
ኢየሱስን ከማንኛውም ሌላ ነገር ይበልጥ እንድንወደው ያደረገን ምንድነው? 
ሐጢያቶቻችን በሙሉ የወደፊት ሐጢያቶቻችንም ሁሉ ሳይቀሩ ባነጻልን በጥምቀቱ አማካይነት ለእኛ ያለው ፍቅር ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር ሙሉ በሙሉ የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ለሚያምኑ አገልጋዮቹ ጠቦቶቹን በአደራ ሰጠ፡፡ ኢየሱስ ሦስት ጊዜ ‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?›› በማለት ሲጠይቀው ጴጥሮስ በእያንዳንዱ ጊዜ ‹‹አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ›› በማለት መለሰ፡፡ አሁን ስለ ጴጥሮስ መልሶች እናስብ፡፡ ይህ የፈቃዱ መገለጫ ሳይሆን የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ላይ ያለው እምነቱ እንደነበር ማየት እንችላለን፡፡
አንድን ሰው ስንወድና ያም ፍቅር በፈቃዳችን ላይ የተመሰረተ ሲሆን ስንደክም ሊንገዳገድ ይችላል፡፡ ነገር ግን ያ በእግዚአብሄር ፍቅር ጉልበት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ለዘላለም ይኖራል፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር ማለትም ለሐጢያቶቻችን የሆነው የተትረፈረፈ ስርየት የኢየሱስ ጥምቀት ውሃና መንፈስ ደህንነት ልክ እንደዚያ ነው፡፡
የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ላይ ያለን እምነታችን ለጌታ ላለን ፍቅርና ሥራዎች መሰረት መሆን አለበት፡፡ እርሱን የወደድነው በልባችን ብቻ ከሆነ ነገ ተሰናክለን እንወድቃለን፡፡ መጨረሻችንም ስለ በደሎቻችን ራሳችንን መጥላት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ፣ የአዳምን ሐጢያት፣ ያለፉትን፣ የቀን ተቀን ሐጢያቶቻችንን፣ የዛሬውንና የወደፊቱን ሐጢያቶቻችንን፣ እንደዚሁም የሕይወት ዘመን ሐጢያቶቻችንን አነጻ፡፡ እርሱ ከደህንነቱ ማንንም አላስቀረም፡፡
ይህ ሁሉ እውነት ነው፡፡ ፍቅራችንና እምነታችን የተመሰረቱት በፈቃዳችንና በጽናታችን ላይ ቢሆን ኖሮ በእምነታችን እንወድቅ ነበር፡፡ ነገር ግን ፍቅራችንና እምነታችን ኢየሱስ በሰጠን የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ቀድሞውኑም የእግዚአብሄር ልጆችና ጻድቃን ሆነናል፡፡ እኛ በውሃውና በመንፈሱ ደህንነት ስለምናምን ሐጢያት የለብንም፡፡
ደህንነታችን የመጣው በእኛ ዘንድ መልካምነት ስላለ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ፍቅርና በሐጢያቶች ስርየት አማካይነት ከእውነተኛው የደህንነት ሕጉ ከመሆኑ እውነታ የተነሳ በሕይወታችን ምንም ያህል ጎዶሎዎች ወይም ደካሞች ብንሆንም ጻድቃን ነን፡፡ መንግሥተ ሰማይ ገብተንም ጌታን ለዘላለም እናመሰግነዋለን፡፡ ይህንን ታምናላችሁን?
1ኛ ዮሐንስ 4፡10 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄር እርሱ ራሱ እንደወደደን ስለ ሐጢአታችንም ማስተሰርያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደላከ እንጂ እኛ እግዚአብሄርን እንደወደድነው አይደለም፡፡›› በስርየት ወንጌል ማለትም በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ወንጌል ላይ እምነት ይኖረን ዘንድ ኢየሱስ በውሃና በመንፈስ አዳነን፡፡
እግዚአብሄር የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል ባያድነን ኖሮ ምንም ያህል በግለት ብናምንም መዳን ባልቻልንም ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን በልቦቻችንና በሥጋችን የምንሰራቸውን ሐጢያቶች በሙሉ አጠበልን፡፡
እኛ ጻድቃን እንሆን ዘንድ የስርየት ወንጌል በሆኑት የውሃውና የመንፈሱ ቃሎች ላይ ባለን እምነት አማካይነት ስለ ደህንነታችን እርግጠኞች መሆን አለብን፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ያስተሰረየው ወንጌል ከኢየሱስ ጥምቀትና ከደሙ የተዋቀረ ነው፡፡ የስርየት ወንጌል የእውነተኛ እምነት ይዘት፣ እውነተኛ የደህንነት መሰረትና ወደ እግዚአብሄር መንግሥት የመግቢያውም ቁልፍ ነው፡፡
 

የራሳችንን የፈቃድ እምነት መተው አለብን፡፡
 
እውነተኛ እምነት የሚመጣው ከየት ነው? 
ይህ የሚመጣው ቀድሞውኑም የወደፊት ሐጢያቶቻችንን ካነጻው ከጌታ ፍቅር ነው፡፡
 
በአንድ ሰው ፈቃድ የተያዘ እምነት ወይም ፍቅር እውነተኛ ፍቅርም ሆነ እውነተኛ እምነት አይደለም፡፡ በዚህ ላይ መጀመሪያ በበጎ ፈቃድ በኢየሱስ ያመኑ ብዙዎች አሉ፡፡ በኋላ ግን በልቦቻቸው ውስጥ ካለው የሐጢያት ስቃይ የተነሳ እምነታቸውን ፈጽመው ትተውታል፡፡
ነገር ግን ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ፤ ኢምንት የሆኑ በደሎችን ብቻ ሳይሆን ከእውቀት ማነስ የተነሳ የተሰሩ ታላላቅ ሐጢያቶችንም እንዳነጻ መገንዘብ አለብን፡፡
ኢየሱስ በዮሐንስ 13 ላይ የእርሱ ደህንነት ምን ያህል ሁሉን አቀፍና ለዘለቄታውም ውጤታማ እንደሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ለማስተማር ከመሰቀሉ በፊት ደቀ መዛሙርቱን ሰበሰባቸው፡፡ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እራት ከበላ በኋላም የተትረፈረፈውን ደህንነቱን እውነት በልቦቻቸው ላይ ለመቅረጽ ተነስቶ እግሮቻቸውን አጠበ፡፡ ሁላችንም ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በማጠብ ያስተማራቸውን የስርየት ወንጌል ማወቅና ማመን ይኖርብናል፡፡
ጴጥሮስ ግን መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ እግሮቹን እንዳያጥበው በጽኑ ተቃውሞ ነበር፡፡ ‹‹የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም፡፡›› ይህ በራሱ ፈቃድ የያዘው እምነት መግለጫ ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል ተናገረው፡- ‹‹እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታሰተውለዋለህ፡፡››
አሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከአስተውሎታችን በላይ የነበሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች መረዳት እንችላለን፡፡ ሐጢያተኛው በሙሉ ልቡ በማመን ጻድቅ ይሆን ዘንድ የሚፈቅድለት የእውነት ቃል ማለትም የውሃውና የመንፈሱ የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል ይህ ነው፡፡
ጴጥሮስ ኢየሱስን ከማግኘታቸው በፊት ያደርጉ እንደነበረው ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር ዓሳ ለማጥመድ ሄደ፡፡ ያን ጊዜ ኢየሱስ በፊታቸው ተገለጠና ጠራቸው፡፡ ኢየሱስ ቁርስ አዘጋጅቶላቸው ነበር፡፡ ቁርስ እየበሉ ሳለ ጴጥሮስ ኢየሱስ ቀደም ብሎ የተናገራቸውን ቃሎች ትርጉም ተረዳ፡፡ ‹‹እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ፡፡›› በመጨረሻ ከዚህ በፊት እግሮቹን ባጠበው ጊዜ ኢየሱስ በእርግጥም ምን ማለቱ እንደነበር ተገነዘበ፡፡
‹‹ጌታ ሐጢያቶቼን በሙሉ እጠብልኝ፡፡ ከድክመቶቼ የተነሳ የሰራኋቸው ሐጢያቶች በሙሉ ወደፊት የምሰራቸውንም ሐጢያቶች በሙሉ ጨምሮ ነጽተዋል፡፡›› ጴጥሮስ በራሱ ፈቃድና ውሳኔ የያዘውን እምነት ትቶ የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል በሆነው በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ላይ ጸንቶ መቆም ጀመረ፡፡
ከቁርስ በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡፡ ‹‹ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?›› አሁን ጴጥሮስ በኢየሱስ ፍቅር በእምነት ተጠናክሮ ‹‹አዎን እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ›› በማለት መሰከረ፡፡ ጴጥሮስ መመስከር የቻለው ኢየሱስ ‹‹ከዚህ በኋላ ታስተውለዋለህ›› ሲል ምን ማለቱ እንደነበር ስለተገነዘበ ነበር፡፡ እርሱ የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል የሆነውን የኢየሱስ ጥምቀትና ደም እምነት እውነተኛ እምነቱን መመስከር ችሎ ነበር፡፡
 

ከዚያም በኋላ እርሱ እውነተኛ የእግዚአብሄር አገልጋይ ሆነ፡፡
 
የእግዚአብሄር እውነተኛ አገልጋይ የምትሆኑት እንዴት ነው?
ለሐጢያቶቼ ሁሉ በሆነው ዘላለማዊ ስርየቱ በማመን ነው፡፡ 
 
ከዚያ ልምምድ በኋላ ጰጥሮስና ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት እስከ መጨረሻው እስትንፋሳቸው ድረስ ወንጌልን ሰበኩ፡፡ ክርስቲያኖችን ያለ ምሕረት ሲያሳድድ የነበረው ጳውሎስም እንኳን በእነዚያ የሮም ንጉሠ ነገሥት ክፉ ቀናቶች ወቅት ወንጌልን መስክሮዋል፡፡
ከአስራ ሁለቱ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መካከል ይሁዳ ኢየሱስን ሸጠው፡፡ በኋላም ራሱን ሰቀለ፡፡ የእርሱን ቦታ የወሰደው ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርት በመካከላቸው ማትያስን መርጠው ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የመረጠው ጳውሎስን ነበር፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር የሐጢያቶችን ስርየት የሚያስገኘውን ወንጌል ሰበከ፡፡
አብዛኞቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሞቱት ሰማዕታት ሆነው ነው፡፡ የሞት ዛቻ ሲደርስባቸው እንኳን እምነታቸውን አልካዱም፡፡ እውነተኛውን ወንጌል መስበካቸውን ቀጠሉ፡፡
እንዲህ በማለት ሰብከው ይሆናል፡፡ ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋችሁን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱና በደሙ ማለትም የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው ወንጌሉ አነጻ፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ጥምቀቱ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ወሰደና ስለ እናንተ በመስቀል ላይ ፍርድን ተቀበለ፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ወንጌል ደም እመኑና ዳኑ፡፡››
እውነተኛውን ወንጌል መስማትና በእርሱ ማመን በእርግጥም ብዙዎችን አዳነ፡፡ ይህ በኢየሱስ ጥምቀት፣ በደሙና በመንፈስ ወንጌል ላይ ያለ የእምነት ሐይል ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርት ‹‹ኢየሱስ አምላክና አዳኝ ነው›› በማለት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰበኩ፡፡ እናንተና እኔ አሁን የኢየሱስን ጥምቀትና ደም ወንጌል ደህንነታችን አድርገን መስማት የቻልነውና ከሐጢያት የዳንነው እነርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስለመሰከሩ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ወሰን የለሽ ፍቅርና ከኢየሱስ የተሟላ ደህንነት የተነሳ ሁላችንም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆነናል፡፡
ሁላችሁም ታምናላችሁን? ኢየሱስ አብዝቶ ስለወደደን የሐጢያቶች ስርየት የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰጠን፡፡ እኛም ጻድቃን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆንን፡፡ ኢየሱስ እውነተኛውን የስርየት ወንጌል ለማስተማር የደቀ መዛሙርቱን እግሮች አጠበ፡፡ 
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበው የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የምንሰራቸውን ሐጢያቶች ጨምሮ እርሱ በተጠመቀና በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንደነጹ እነርሱንና እኛን ለማስተማር ነው፡፡ ለፍቅሩና ለስርየት ወንጌሉ እናመሰግነዋለን፡፡
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግሮች በማጠብ ሁለት ነገሮችን አስተምሮናል፡፡ የመጀመሪያው ‹‹እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ›› ብሎ በተናገረው መሰረት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የስርየት ወንጌል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ መንጻታቸውን ለማስተማር ነበር፡፡
ሁለተኛው ትምህርት ኢየሱስ ሐጢያተኞችን ለማዳንና ጻድቃን ለማድረግ ራሱን ዝቅ እንዳደረገ እኛ ዳግም የተወለድን ሰዎች የስርየትን ወንጌል በመስበክ ሌሎችን ማዳን የሚገባን መሆኑ ነው፡፡ መጀመሪያ የመጣነው እኛ በኋላ የሚመጡትን እነርሱን ማገልገላችን ተገቢ ነው፡፡
ኢየሱስ በፋሲካው በዓል ቀን የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ያጠበባቸው ሁለቱ ምክንያቶች ግልጽ ናቸው፡፡ እነርሱ አሁንም በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ደቀ መዝሙር በፍጹም ከመምህሩ አይበልጥም፡፡ ስለዚህ እኛም ወንጌልን ለዓለም እንሰብካለን፡፡ ኢየሱስን እንደምናገልል ሆነንም እናገለግለዋለን፡፡ ቀደም ብለን የዳንን ሰዎች ከእኛ በኋላ የሚመጡትን ልናገለግላቸው ይገባናል፡፡ ኢየሱስ ይህንን ለማስተማር የደቀ መዛሙርቱን እግሮች አጠበ፡፡ በተጨማሪም የጴጥሮስን እግሮች በማጠብ ዳግመኛ በፍጹም በዲያብሎስ እንዳንሳሳት እርሱ ፍጹም አዳኝ እንደሆነ አሳየን፡፡
ሁላችሁም የሐጢያቶችን ስርየት በሚያስገኘው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን መዳን ትችላላችሁ፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ፣ በስቅለቱና በትንሳኤው ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አንጽቷል፡፡ ለዘላለም ከዓለም ሐጢያቶች መዳን የሚችሉት በእርሱ ወንጌል የሚያምኑ ብቻ ነው፡፡ 
 

የየዕለቱን ሐጢያቶቻችን በሙሉ ባጠበልን ወንጌል እምነት ይኑራችሁ፡፡
 
የስርየት ወንጌል በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ቃሎች በማመን የዲያብሎስን ማታለያዎች በሙሉ መቁረጥ እንችላለን፡፡ ሰዎች በቀላሉ በዲያብሎስ ይታለላሉ፡፡ ዲያብሎስም ሁልጊዜ በጆሮዎቻቸው ያንሾካሹካል፡፡ የሰዎች ሥጋ በዓለም ላይ ያለ ማቋረጥ ሐጢያቶችን እንደሚሰራ ከታወቀ እንዴት ያለ ሐጢያት ሊሆኑ ይችላሉ? ሰዎች ሁሉ ሐጢያተኞች ናቸው፡፡
እኛ ግን መልሱን እናውቃለን፡፡ ‹‹ኢየሱስ በጥምቀቱ የሥጋችንን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደ ካወቅን በኋላ አንድ አማኝ እንዴት ሐጢያት ሊኖርበት ይችላል? ኢየሱስ የሐጢያትን ደመወዝ ሙሉ በሙሉ ከፈለ፡፡ ስለዚህ ለእኛ የቀረልን ምን የምንከፍለው ደመወዝ አለ?››
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማናምን ከሆንን የዲያብሎስ ቃሎች ምክንያታዊ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን ወንጌል ከእኛ ወገን ከሆነ በእግዚአብሄር ቃል እውነት ላይ የማይናወጥ እምነት ሊኖረን ይችላል፡፡፡
ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም የመወለድ ወንጌል እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡ እውነተኛ እምነት በኢየሱስ ጥምቀት፣ በመስቀል ላይ ደሙ፣ በሞቱና በትንሳኤው ወንጌል ማመን ነው፡፡
የተቀደሰውን የመገናኛ ድንኳን ሞዴል ስዕል አይታችሁ ታውቃላችሁን? ይህ ትንሽዬ የድንኳን ቤት ነው፡፡ ቤቱ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ውጭኛው ክፍል ቅድስት ስፍራ፣ ውስጠኛው ክፍል ደግሞ የስርየት መክደኛው ያለበት ቅድስተ ቅዱሳን የተባለው መቅደስ ነው፡፡
በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ውጫዊ አደባባይ ላይ የቆሙ በአጠቃላይ 60 ምሰሶች አሉ፡፡ ቅድስቱ ስፍራ 48 ሳንቃዎች አሉት፡፡ የእግዚአብሄርን ቃሎች ትርጉም ለመረዳት የተቀደሰውን የመገናኛውን ድንኳን በአእምሮዋችን መሳል ይገባናል፡፡
 

የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያው በር የተሰራው ከምንድነው? 
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር የተሰራው ከምንድነው? 
የተሰራው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ መጋረጃ ነው፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደበባይ የመግቢያ በር በዘጸአት 27፡16 ላይ ተገልጦዋል፡፡ ‹‹ለአደባባዩም ደጅ ከሰማያዊ ከሐምራዊ፣ ከቀይም ግምጃ፣ ከጥሩ በፍታም፣ በጥልፍ አሰራር የተሰራ ሃያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፡፡ ምሰሶዎቹም አራት፣ እግሮቹም አራት ይሆናሉ፡፡›› ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሶች ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ እንደዚሁም ጥሩ በፍታ ነበሩ፡፡ ይህም በደምብ የተፈተለና በጣም ውብ ነበር፡፡
 እግዚአብሄር እያንዳንዱ ሰው የመግቢያውን በር ለማግኘት ቀላል እንዲሆንለት የመግቢያውን በር በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃ በቀለም አሸብርቆ እንዲፈትል ሙሴን አዘዘው፡፡ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተሰራው የመግቢያው በር በአራት ምሰሶች ላይ ተንጠልጥሎ ነበር፡፡
እነዚህ አራቱ ቁሳቁሶች እግዚአብሄር በኢየሱስ ጥምቀትና ደም አማካይነትና እርሱ አምላክ ስለመሆኑ በልጁ ያመኑትን ሰዎች ሁሉ የሚያድንበትን የእግዚአብሄርን የደህንነት ንድፍ ያመላክታሉ፡፡
የተቀደሰውን የመገናኛ ድንኳን ለመስራት ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች እያንዳንዳቸው የተለየ ትርጉም አላቸው፡፡ የሰውን ዘርም በኢየሱስ አማካይነት ለማዳን ያለውን የእግዚአብሄር ቃልና የእርሱን እቅዶች ያመላክታሉ፡፡
ለተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ምን ያህል የተለያዩ ቁሳቁሶች ነበሩ? አራት የተለያዩ ቁሳቁሶች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነርሱም ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ ነበሩ፡፡ እነዚህ አራቱ ዳግም በምንወለድበት ወንጌል ላይ ያለንን እምነት በማጠንከር ረገድ በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ አስፈላጊ ባይሆኑ ኖሮ ይህ መረጃ እንዲህ ባለ ዝርዝር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፈ ነበር፡፡ ለተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች በሙሉ የደህንነታችንን አቢይ ትርጉሞች ያመላክታሉ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እነዚህን ነገሮች ለሙሴ ገለጠለትና በትክክል እንደተነገረው እንዲያደርግ ነገረው፡፡
 

ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ በእግዚአብሄር ወንጌል ውስጥ ምን ማለት ናቸው? 
 
ለመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሶች የሚያመላክቱት ምንድነው?
በጥምቀቱና በደሙ አማካይነት የሆነውን የኢየሱስን ደህንነት ነው፡፡
 
በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን ውስጥ በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል ለተንጠለጠለው መጋረጃ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ ዳግም ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚገባው ሊቀ ካህን የሚለብሳቸው ልብሶችም ከተመሳሳይ ቁሳቁሶች የተሰሩ ነበሩ፡፡
ሰማያዊው ግምጃ የኢየሱስን ጥምቀት ያመለክታል፡፡ በ1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡›› ጴጥሮስ በዚህ ቁጥር ላይ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደበት የኢየሱስ ጥምቀት የስርየት ደህንነት ምሳሌ እንደሆነ አረጋገጠ፡፡ ሐጢያቶቻችን በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡ ስለዚህ የኢየሱስን ጥምቀት የሚያመላክተው ሰማያዊ ግምጃ የደህንነት ቃል እጅግ አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡
ቀዩ ግምጃ የኢየሱስን ደም ያመለክታል፡፡ ሐምራዊው ግምጃም የእርሱን መለኮታዊነት-- ኢየሱስ ንጉሥና አምላክ የመሆኑን ማዕረግ ያመላክታል፡፡ የግምጃው ሦስቱ ቀለማት በኢየሱስና በደህንነቱ ላይ ላለን እምነታችን አስፈላጊ ነበሩ፡፡ ሊቀ ካህኑ ከውጭ የሚለብሰው ያማረ መጎናጸፊያ ኤፉድ ተብሎ ይጠራል፡፡ የኤፉዱ ቀሚስም እንደዚሁ ሰማያዊ ነበር፡፡ ሊቀ ካህኑ በንጹህ የወርቅ ምልክት ላይ ‹ቅድስና ለእግዚአብሄር› የሚል የተቀረጸበት ጥምጣም በራሱ ላይ አድርጎዋል፡፡ ምልክቱ በሰማያዊ ፈትል ከጥምጣሙ ጋር ተያይዞዋል፡፡
 

በሰማያዊው ግምጃ የተገለጠው እውነት፡፡
 
ሰማያዊው ግምጃ ምንን ያመለክታል?
የኢየሱስን ጥምቀት፡፡
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰማያዊውን ግምጃ ትርጉም ተመለከትሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰማያዊ ምን ይላል? በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃዎች መካከል ያለውን ሰማያዊውን ግምጃ ማስተዋል ይኖርብናል፡፡
ሰማያዊ ግምጃ ‹ውሃውን› ማለትም የኢየሱስን ጥምቀት ያመላክታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠምቆዋል፡፡ (ማቴዎስ 3፡15)
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በጥምቀቱ ባይወስድ ኖሮ በእግዚአብሄር ፊት መቀደስ ባልቻልንም ነበር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ወደዚህ ዓለም መምጣትና በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት፡፡
በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ ሰማያዊ ግምጃ የተደረገበት ምክንያት ያለ ኢየሱስ ጥምቀት መቀደስ ስለማንችል ነው፡፡
ቀዩ ግምጃ የእርሱን ደም ማለትም የኢየሱስን ሞት ያመላክታል፡፡ ሐምራዊው የኢየሱስን አምላክነት ማለትም ‹‹ብጹዕና ብቻውን የሆነ ገዥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ›› (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡15) የተባለውን የኢየሱስን ማዕረግ ያመለክታል፡፡
እውነቱ ቀዩ ግምጃ ለሰው ዘር ሁሉ የሐጢያትን ደመወዝ ለመክፈል በመስቀል ላይ የደማውን የክርስቶስ ደም የሚያመላክት መሆኑ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ በሥጋ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ራሱን በመስቀል ላይ መስዋዕት በማድረግም የሐጢያትን ደመወዝ በሙሉ ከፈለ፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና ደም በብሉይ ኪዳን በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ በዋሉት ግምጃዎች ቀለማት አማካይነት የተተነበየ እውነተኛ የስርየት ወንጌል ነው፡፡
የመገናኛው ድንኳን ምሰሶዎች ከግራር እንጨት፤ መያዣዎቹም ከናስ የተሰሩ ነበሩ፡፡ የናሱ መያዣዎች በብር ማሰሪያዎች ተሸፍነው ነበር፡፡
ሐጢያተኞች በሙሉ ለሐጢያቶቻቸው የተፈረደባቸው የሐጢያት ደመወዝ ሞት ስለሆነ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ሰው አዲስ ሕይወት ለማግኘት በእግዚአብሄር መባረክ ከመቻሉ በፊት ለሐጢያቶቹ መስዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡
ነገር ግን በአዲስ ኪዳን በተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን በሰማያዊ ግምጃ የተመሰለው የኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወስዶዋል፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ወደ መስቀል ወሰደና ደማ፡፡ ለእነርሱም ተፈረደበት፡፡ እንዲህ በማድረጉም በስርየት ወንጌል እምነት ያለንን ሰዎች ሁሉ አዳነን፡፡ እርሱ የነገሥታት ንጉሥና ቅዱስ አምላክ ነው፡፡
የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች የኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውሰድ ያዳነን የኢየሱስ ማዳን ነው፡፡ አምላክ የሆነው ኢየሱስ በሥጋ ወደ ዓለም መጣ፡፡ (ሐምራዊ ግምጃ፡፡) የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድም ተጠመቀ፡፡ (ሰማያዊ ግምጃ፡፡) በእኛ ፋንታ ፍርድን ለመቀበልም በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፡፡ (ቀዩ ግምጃ፡፡) የኢየሱስ ጥምቀት እርሱ ለሰው ዘር ሁሉ እውነተኛ አዳኝ እንደሆነ ያለ ጥርጥር ያስተምረናል፡፡
ይህንን ለተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ በዋሉት ቀለማቶች ውስጥም ማየት እንችላለን፡፡
ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተፈተለው የመግቢያው በር መጋረጃ የእግዚአብሄርን ደህንነት እውነት በግልጽ የሚነግረን ነበር፡፡ እዚህ ላይ ጥሩው በፍታ የሚያሳየው ሁላችንንም ያለ ምንም አድልዎ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን ነው፡፡  ይህ ለስርየት ደህንነት ፈጽሞ አስፈላጊ ነበር፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ሐጢያተኞችን ያለ እቅድ እንዲያው በዘፈቀደ እንዳላዳነን ለተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ ከዋሉት ተመሳሳይ ቁሳቁሶች ማየት እንችላለን፡፡ እርሱ የእግዚአብሄርን ዝርዝር እቅድ በጥንቃቄ በመታዘዝ የሰውን ዘር ደህንነት ለመፈጸም ተጠመቀ፤ ተሰቀለ፤ ከሙታንም ተነሳ፡፡ ኢየሱስ የስርየት ወንጌል ቁሳቁሶች በሆኑት በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ግምጃ በእርሱ ማዳን ያመኑትን ሁሉ አዳናቸው፡፡
 

የብሉይ ኪዳኑ የናስ መታጠቢያ ሰን በአዲስ ኪዳን የጥምቀት ጥላ ነበር፡፡
 
ካህናቱ ወደ ቅድስቱ ክፍል ከመግባታቸው በፊት እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ለምን ይታጠባሉ?
ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፊት ያለ ምንም ሐጢያት መቆም ስለነበረባቸው ነው፡፡
 
የመታጠቢያውም ሰን የተሰራው ከናስ ነበር፡፡ ናስ የሚያመላክተው ኢየሱስ የተሰቃየበትን ፍርድ ነው፡፡ የውሃ መያዣው ሐጢያቶቻችን በሙሉ እንደነጹ የሚነግረንን የወንጌል ቃል ያመላክታል፡፡
ይህም በየቀኑ የምንሰራቸው ሐጢያቶች እንዴት እንደተወገዱ ያሳየናል፡፡ የሰው ዘር በየቀኑ የሚሰራቸው ሐጢያቶች በኢየሱስ ጥምቀት ቃሎች እምነት አማካይነት መንጻት ይችላሉ፡፡
የሚቃጠል መስዋዕት መሰውያ ፍርድን ያመላክታል፡፡ በሌላ አነጋገር ሰማያዊ የሆነው የኢየሱስ ውሃ፣ የሐጢያቶች ስርየት ማለትም በአጥማቂው ዮሐንስ የሆነው የኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል ነው፡፡ (ማቴዎስ 3፡15፤ 1ኛ ዮሐንስ 5፡5-10) ይህም በስርየት አማካይነት የደህንነትን ወንጌል የሚመሰክር የምስክርነት ቃል ነው፡፡ 
በ1ኛ ዮሐንስ 5 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ከእግዚአብሄር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው፡፡ የሚመሰክሩት መንፈሱ፣ ደሙና ውሃው ሶስት ናቸውና ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ፡፡›› እርሱ በእግዚአብሄር ልጅ የሚያምን ሰው በውስጡ የውሃው፣ የደሙና የመንፈሱ ምስክርነት እንዳለው ይነግረናል፡፡
ግዚአብሄር በስርየቱ ወንጌል እምነት አማካይነት እንድንቀደስና ወደተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን እንድንገባ ፈቀደልን፡፡ ስለዚህ አሁን በእምነት መኖር፣ የእግዚአብሄርን ቃሎች መመገብ፣ በእርሱ መባረክና የጻድቃን ሕይወትን መኖር እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝብ መሆን ማለት በስርየት ወንጌል እምነት አማካይነት መዳንና በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ መኖር ማለት ነው፡፡
ዛሬ ብዙ ሰዎች በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ ስላለው ስለ ሰማያዊው፣ ሐምራዊውና ቀዩ ግምጃ ትርጉም ሳያስቡ ማመን ብቻ በቂ ነው ይላሉ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ነገሮች ሳያውቅ በኢየሱስ አምኖ ከሆነ በልቡ ውስጥ አሁንም ገና ሐጢያት ስላለ እምነቱ እውነተኛ አይሆንም፡፡ ይህ ሰው በስርየት፣ በውሃ፣ በደምና በመንፈስ ወንጌል አማካይነት ዳግም የመወለድን እውነት ባለማመኑ አሁንም ድረስ በልቡ ውስጥ ሐጢያት አለበት፡፡
አንድ ሰው የማያውቀውን ሰው እንዲመዝን ቢጠየቅ አድማጩን ለማስደሰት ሲል ‹‹አዎ ይህንን ሰው አምነዋለሁ፡፡ በእርግጥ ፈጽሞ አግኝቼው አላውቅም፤ ነገር ግን አምነዋለሁ›› ይላል፡፡ አድማጩ ይህንን በመስማት የሚደሰት ይመስላችኋልን? ምናልባት አንዳንዶቻችሁ በሰዎች ጉዳዮች ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ይሆናል፡፡ ይህ ግን እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገው መታመን አይደለም፡፡ 
እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) በሐምራዊው፣ (የኢየሱስ መለኮታዊነት) እና በቀዩ (የኢየሱስ ደም) ግምጃ አማካይነት የኢየሱስ ደህንነት በሆነው የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል እንድናምን ይፈልግብናል፡፡ በኢየሱስ ከማመናችን በፊት እኛን ከሐጢያቶች ሁሉ እንዴት እንዳዳነን ማወቅ ይገባናል፡፡
በኢየሱስ ስናምን እንዴት በውሃ፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) በደም፣ (ሞቱ) እና በመንፈስ (ኢየሱስ አምላክ መሆኑ) ከሐጢያቶቻችን ሁሉ እንዳዳነን ማወቅ ይገባናል፡፡
በትክክል ስንረዳ እውነተኛና ሙሉ እምነት መለማመድ እንችላለን፡፡ እውነተኛ እምነት የሚመጣው የኢየሱስን ደህንነት፣ የስርየትን ወንጌልና ኢየሱስ እውነተኛ የሰው ዘር አዳኝ የመሆኑን ምስክርነት በመረዳት ብቻ ነው፡፡
በኢየሱስ ላይ የሚያላግጥ እምነትስ ምን ይመስላል? እስቲ እንመልከት፡፡
 

በኢየሱስ የሚያላግጥ እምነት፡፡
 
ለእምነት እጅግ የሚያስፈልገው ምንድነው? 
ትክክለኛ የሆነ የኢየሱስ ጥምቀት እውቀት፡፡
 
ኢየሱስን በዘፈቀደ ማመን በእርሱ ማላገጥ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርባችኋል፡፡ ‹‹ማመን አስቸግሮኛል፡፡ ነገር ግን እርሱ አምላክና የእግዚአብሄር ልጅ ስለሆነ የሆኖ ሆኖ በእርሱ ማመን ይኖርብኛል›› ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ በኢየሱስ ላይ እያላገጣችሁ ነው፡፡ በእርግጥ ዳግም መወለድ የምትፈልጉ ከሆነ የስርየት ወንጌል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማመን አለባችሁ፡፡
የስርየትን ወንጌል ሳያውቁ በኢየሱስ ማመን ጨርሶ በኢየሱስ ከአለማመንም የከፋ ነው፡፡ የኢየሱስን ደም ወንጌል ብቻ መስበክ እውነትን ሳያውቁ በከንቱ መልፋት ነው፡፡
ኢየሱስ ማንም ተነስቶ በዘፈቀደ ያምን ዘንድ ወይም ያለ ምክንያት በእርሱ እምነት እንዲኖረው አይፈልግም፡፡ እርሱ የስርየትን ወንጌል አውቀን በእርሱ እንድናምን ይፈልግብናል፡፡ በኢየሱስ ስናምን የኢየሱስ ጥምቀትና ደም የስርየት ወንጌል እንደሆነ ማመን ይኖርብናል፡፡ በኢየሱስ ስናምን በቃሉ አማካይነት የስርየትን ወንጌል መረዳትና ሐጢያቶቻችንንም ሁሉ እንዴት እንዳነጻልን በግልጽ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ 
በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ ያሉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ የሚያመላክቱት ምን እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ያን ጊዜ ለዘላለም የሚኖር እውተነኛ እምነት ሊኖረን ይችላል፡፡
 

የሰማያዊው የሐምራዊውና የቀዩ ግምጃ መገለጫ በሆነው በኢየሱስ ሳናምን ፈጽሞ ዳግም መወለድ አንችልም፡፡
ወደ ቅድስቱ ስፍራ ከመግባታቸው በፊት ካህናቱ ምን ያደርጋሉ? 
በናሱ የመታጠቢያ ሰን ውስጥ ባለው ውሃ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠባሉ፡፡ 
 
ጌታችን ኢየሱስ አዳነን፡፡ እንዴት ፈጽሞ እንዳዳነን ስንመለከት ጌታን እናመሰግናለን፡፡ የተቀደሰውን የመገናኛውን ድንኳን መመልከት ይገባናል፡፡ እርሱ በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ አማካይነት የስርየትን ወንጌል ቃሎች ሰጠን፡፡ ጌታን እናመሰግነዋለን፤ እናወድሰዋለንም፡፡
ሐጢያተኞች አስፈሪ በሆነ ፍርድ ውስጥ ሳያልፉ ወደ ቅድስቱ መግባት አይችሉም፡፡ በሐጢያቶቹ ሳይፈረድበት ቅድስቱ ክፍል ውስጥ መግባት የሚችል ማነው? ይህ የማይቻል ነው፡፡ ይህ ሰው ወደተከለከለው ስፍራ ከገባ እዚያው ይሞታል፡፡ ሐጢያተኛ ቅድስቱ ስፍራ ሊገባና ፈጽሞ በሕይወት መኖር ሊጠብቅ አይችልም፡፡
ጌታችን በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ውስጥ በተሰወረው ምስጢር በኩል አዳነን፡፡ እርሱ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃዎች እንደዚሁም በጥሩ በፍታ አዳነን፡፡ በእነዚህ ነገሮች አማካይነትም የማዳኑን ምስጢር ነገረን፡፡
እናንተና እኔ የዳንነው በዚያ መንገድ አይደለምን? በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ግምጃ ቃሎች ካላመናችሁ በስርየቱ ወንጌል አማካይነት ደህንነት ሊኖር አይችልም፡፡ ሰማያዊው ቀለም እግዚአብሄርን አያመላክትም፡፡ የሚያመለክተው ሌላ ምንም ሳይሆን የኢየሱስን ጥምቀት ነው፡፡ ይህም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የወሰደ የኢየሱስ ጥምቀት ነው፡፡
አንድ ሰው በሰማያዊው ግምጃ ሳያምን የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ እስካለበት ስፍራ ድረስ መሄድ ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ወደሚኖርበት ቅድስት ስፍራ መግባት አይችልም፡፡ 
ስለዚህ በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን በር ውስጥ ከመግባታችን በፊት በሰማያዊው ግምጃ፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) በቀዩ ግምጃ (በመስቀሉ ደም) እና በሐምራዊው ግምጃ (ኢየሱስ አምላክና የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑ) ማመን ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሄር የሚቀበለንና የቅድስተ ቅዱሳኑን መጋረጃ አልፈን እንድንገባ የሚፈቅድልን ስናምን ብቻ ነው፡፡
አንዳንዶች ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ገብተው ውስጥ እንዳሉ ያስባሉ፡፡ ይህ ግን ደህንነት አይደለም፡፡ ለመዳን ምን ያህል ርቀን መሄድ ይኖርብናል? ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት መቻል አለብን፡፡
ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የናሱን የመታጠቢያ ሰን ማለፍ ይኖርብናል፡፡ የናሱ የመታጠቢያ ሰን የሚያመላክተው የኢየሱስን ጥምቀት ነው፡፡ በኢየሱስ ጥምቀት በየቀኑ ከምንሰራቸው ሐጢያቶች በሙሉ መንጻትና ወደ ቅድስቱ ስፍራ በመግባት መቀደስ ይኖርብናል፡፡
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካህናት ከመግባታቸው በፊት  መታጠብ ነበረባቸው፡፡ በአዲስ ኪዳንም ኢየሱስ የዕድሜ ዘመናቸውን ሐጢያቶች ማንጻቱን ለማመላከት የደቀ መዛሙርቱን እግሮች አጠበ፡፡
የእግዚአብሄር ሕግ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው፤ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡›› (ሮሜ 6፡23) እግዚአብሄር ምንም ሳያስቀር የሰዎችን ሐጢያቶች ኮነነ፡፡ ነገር ግን እነርሱን ወደ ልጁ አስተላልፎ እርሱ ላይ ፈረደበት፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ፍቅር የእርሱ ደህንነት ነው፡፡ እውነተኛ ደህንነት የሚገኘው የኢየሱስን ጥምቀት፣ ደም፣ ሞትና ትንሳኤ የያዘውን የስርየት ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡
 
 
አንድ ሰው ዳግም ይወለድ ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሆነው የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል ላይ በጭራሽ ማላገጥ የለበትም፡፡  
 
እኛ እንድናደርገው የተተወልን ብቸኛው ነገር ምንድው? 
በተጻፉት የእግዚአብሄር ቃሎች በወንጌሉ ማመን ነው፡፡
 
እኔ ፈጽሞ በሌሎች ሰዎች አላላግጥም፡፡ አንድ ሰው እኔ የማላውቀውን አንዳች ነገር ሲናገር እንዲያብራራልኝ በትህትና እጠይቀዋለሁ፡፡ ነገር ግን ስለ ተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን አንደምታዎች በጠየቅሁ ጊዜ ማንም ሊነግረኝ አልቻለም፡፡ 
ታዲያ ምን አደረግሁ? ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መመለስ ነበረብኝ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን የተነገረው የት ቦታ ላይ ነው? በዝርዝር የተብራራው በዘጸአት ውስጥ ነው፡፡ አንድ ሰው ይህንን መጽሐፍ በጥንቃቄ ቢያነብ በተጻፉት የእግዚአብሄር ቃሎች አማካይነት ትርጉሙን መረዳት ይችላል፡፡
ውድ ወዳዶች በደፈናው በኢየሱስ በማመን መዳን አትችሉም፡፡ በየጊዜው ቤተክርስቲያን በመሄድም ዳግም ልትወለዱ አትችሉም፡፡ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ምን እንደነገረው እናውቃለን፡፡ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡…አንተስ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?›› (ዮሐንስ 3፡5,10)
በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በሰማያዊው ግምጃ፣ (ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ተላልፈዋል) ቀይ ግምጃ፣ (ለሐጢያቶቻችን ሁሉ የሆነው የኢየሱስ ሞት) እና ሐምራዊ ግምጃ (ኢየሱስ አዳኝ አምላክና የእግዚአብሄር ልጅ ነው) ማመን አለባቸው፡፡
ኢየሱስ የዓለም ሐጢያተኞች ሁሉ አዳኝ እንደሆነ ማመን ይኖርብናል፡፡ ከዚህ እምነት ውጭ ሰው ፈጽሞ ዳግም ሊወለድ አይችልም፡፡ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ቅዱስ ስፍራም መግባት አይችልም፡፡ ያለዚህ ማንም ሰው በዚህ ዓለም ላይ በታማኝነት መኖር እንኳን አይችልም፡፡
ሰው በኢየሱስ በማመን ብቻ ዳግም መወለድ ቢችል በጣም ቀላል አይሆንም ነበርን? --አዎ-- ‹‹♫ድነሃል፤ ድኛለሁ፤ ሁላችንም ድነናል♫›› እንዴት ግሩም ነው! ነገር ግን በእውነት ‹ዳግም ሳይወለዱ› በኢየሱስ የሚያምኑ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን እውነት ልናውቅና በኢየሱስም ላይ እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡ ወደተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለመግባትና በእምነት ግዛት ውስጥ ከእግዚአብሄር ጋር ለመሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የሐጢያት ስርየት ወንጌልና የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ግምጃ ትርጉም መረዳት አለብን፡፡ በእምነት ድንኳን ውስጥ ኢየሱስ ወደ መንግሥቱ ሊወስደን ዳግመኛ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ አብረን በደስታ መኖር እንችላለን፡፡ በትክክለኛው መንገድ በኢየሱስ ማመን ለእኛ አስፈላጊ ነው፡፡
 

እውነተኛው ወንጌል በሰማያዊው ግምጃ ቅድስናን ይወልዳል፡፡
 
ከኢየሱስ መስቀል ሌላ ለደህንነታችን ወሳኙ ሁኔታ ምንድነው? 
የኢየሱስ ጥምቀት፡፡ 
 
ሰዎች ስህተቶችን ሳይሰሩ ፍጹም ሆነው መኖር እንደሚችሉ ወደ ማሰብ ያዘነብላሉ፡፡ ነገር ግን አብዝተው መልካም ነገር ለማድረግ በሞከሩ ቁጥር ወዲያው ጉድለቶቻቸውን አብልጠው ይገነዘባሉ፡፡ ስለዚህ ሐጢያት አለመስራት አይቻላቸውም፡፡ ኢየሱስ የስርየት ወንጌል በሆነው ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ ስላዳነን መቀደስና ወደ እግዚአብሄር ቅዱስ ስፍራ መግባት እንችላለን፡፡
እግዚአብሄር በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ግምጃ ባያድነን ኖሮ በራሳችን ፈጽሞ ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት ባልቻልን ነበር፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት የሚችሉት በሥጋቸው ፍጹማን ሆነው የሚኖሩ ሰዎች ብቻ ቢሆኑ ኖሮ ብቁ የሚሆን ማንም ባልኖረ ነበር፡፡ አንድ ሰው እውነተኛውን ወንጌል ሳያውቅ በኢየሱስ ቢያምን የሚጨምረው ነገር በልቡ ላይ ተጨማሪ ሐጢያቶችን መጨመር ብቻ ነው፡፡
ኢየሱስ ያዳነን በጥንቃቄ ባቀደው ደህንነቱ ነው፡፡ ይህም የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ግምጃና ጥሩ በፍታ ደህንነት ነው፡፡ እርሱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አነጻ፡፡ በዚህ ታምናላችሁን?--አዎ--፡፡
‹ቅድስና ለእግዚአብሄር› የሚለውን ምልክት ማድረግ የምትችሉትና ‹የንጉሥ ካህን› (1ኛ ጴጥሮስ 2፡9) ከሆኑት ጋር የምትቀላቀሉት ወንጌልን ስትመሰክሩ ብቻ ነው፡፡ በሰዎች ፊት ቆማችሁ የንጉሥ ካህን በመሆን የምትሰሩ የእግዚአብሄር ባርያ እንደሆናችሁ ልትነግሩዋቸው የምትችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡
የሊቀ ካህኑ ጥምጣም የወርቅ ምልክት አለው፡፡ ምልክቱም በሰማያዊ ፈትል ተያይዞዋል፡፡ ለምን ሰማያዊ? ምክንያቱም ኢየሱስ በስርየት ወንጌል አዳነን፡፡ በጥምቀቱ አማካይነትም ሐጢያቶቻችንን ወሰደና ሐጢያት አልባ አደረገን፡፡ በአዲስ ኪዳን ያለው ጥምቀት ከብሉይ ኪዳን እጆችን መጫን ጋር እኩል ነው፡፡
ምንም ያህል በትጋትና በታማኝነት በኢየሱስ ብናምንም የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ግምጃ የምስጢር ቃሎች ሳናውቅ ‹ቅድስና ለእግዚአብሄር› የሚለው ጽሁፍ የተቀረጸበትን ምልክት ማግኘት አንችልም፡፡
ጻድቃን የሆንነው እንዴት ነው? በማቴዎስ 3፡15 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› ኢየሱስ ተጠምቆ ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ አድኖናል፡፡ እርሱ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ እኛ ምዕመናኖችም ጻድቃን ሆነናል፡፡
የኢየሱስ ጥምቀት ባይኖር ኖሮ እንዴት ያለ ሐጢያት ነን ማለት እንችል ነበር? በኢየሱስ ብናምንና የመስቀሉን ሞት በማሰብ ብናለቅስም በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ዕንባዎች በሙሉ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ማንጻት አይችሉም፡፡ ምንም ያህል አብዝተን ብናለቅስና ንስሐ ብንገባ ሐጢያቶቻችን በውስጣችን ይቀራሉ፡፡
‹ቅድስና ለእግዚአብሄር፡፡› እርሱ በጥምቀቱና በደሙ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስለወሰደ ጌታ የእኛ የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ እንዲተላለፉ ፈቀደ፡፡ የደህንነት ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈ ሐጢያቶችና ድክመቶች ቢኖሩብንም በእምነታችን ጻድቃን ሆነናል፡፡
ስለዚህ አሁን በእግዚአብሄር ፊት መቆም እንችላለን፡፡ አሁን ጻድቃን ሆነን መኖርና ወንጌልን ለዓለም ሁሉ መስበክ እንችላለን፡፡ ‹‹♪ድኛለሁ፤ ድነሃል፤ ሁላችንም ድነናል♪፡፡›› በእግዚአብሄር የምሕረት እቅድ መሰረት ድነናል፡፡
በልባችሁ ውስጥ የስርየት ወንጌል ቃል ከሌለ ምንም ያህል በርትታችሁ ብትሞክሩም ደህንነት የለም፡፡ ይህ ምላሽ ስለማይሰጥ ፍቅር ከሚዘመረው ታዋቂ የኮርያ መዝሙር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ‹‹♫ኦ እርስዋን ባየኋት ጊዜ ሁሉ፤ በቀረብሁዋት ጊዜ ሁሉ፤ ልቤ ያለ ምክንያት በፍጥነት ይደልቃል፡፡ ምላሽ በማይሰጥ ፍቅር ውስጥ ያለሁ መሆን አለብኝ♫›› ልቤ በፍጥነት ይደልቃል፡፡ የእርስዋ ግን አይደልቅም፡፡ ፍቅሬ ፈጽሞ ምላሽ አላገኘም፡፡ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች አሁንም ድረስ ለእግዚአብሄር ያላቸው ፍቅር ምላሽ የማይሰጥ ፍቅር መሆኑ ያሳዝናል፡፡
ሰዎች ደህንነት በብዙ የተለያዩ መንገዶች ይመጣል ብለው ለማሰብ ያዘነብላሉ፡፡ ‹‹በጥምቀት ወንጌል አማካይነት ብቻ መምጣት ያለበት ለምንድነው?›› በማለትም ይጠይቃሉ፡፡ ነገር ግን ደህንነት በኢየሱስ የጥምቀት ወንጌል በኩል ካልሆነ በቀር ፈጽሞ የተሟላ ደህንነት መሆን ባልቻለም ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ጻድቃን መሆን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መንጻት የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነውና፡፡ 
 

ኢየሱስ የሰጠን የሰማያዊው ግምጃ ደህንነት ምንድነው?
 
ጻድቃን ያደረገን ምንድነው? 
የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ግምጃ ወንጌል ነው፡፡ 
 
በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ግምጃ አማካይነት የመጣው ደህንነት እግዚአብሄር ለሰው ዘር ሁሉ የሰጠው ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ ወደተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን እንድንገባና በሰላም እንድንኖር አስችሎናል፡፡ ጻድቃንም አድርጎናል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንድንኖርና በቤተክርስቲያን አማካይነትም በቅዱሳት መጻህፍት እንድንሰለጥን አስችሎናል፡፡
በእግዚአብሄር ፊት ለመጸለይ በምንቀርብበት ጊዜ ሁሉ ወንጌል በእርሱ ፍቅር ይባርከናል፡፡ ደህንነት ለእኛ እንዲህ ክቡር የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ የእምነትን ቤት ‹በዓለት› ላይ እንድንገባ ነግሮናል፡፡ ዓለቱ የጥምቀቱ ወንጌል ነው፡፡ ሁላችንም መዳን፣ በደህንነት መኖር፣ ሰማይ መሄድ፣ የዘላለምን ሕይወት ማግኘትና የእግዚአብሄር ልጆች መሆን ይገባናል፡፡
ውድ ወዳጆች ከስርየት ወንጌል የተነሳ በእምነት ወደተቀደሰው የመገናኛ ድንኳን መግባት እንችላለን፡፡ ከሐጢያቶቻችን መንጻትና (የኢየሱስ ጥምቀት) በመስቀል ላይ ከሆነው ፍርድ የተነሳ በኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል ላይ ባለን እምነት ድነናል፡፡
ለሐጢያቶቻችን ሁሉ የሆነው የትተረፈረፈ ስርየት የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ያነጻ ወንጌል ነው፡፡ ይህንን ታምናላችሁን? እውነተኛው ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ፈጽሞ ያነጻ ሰማያዊ ወንጌል ነው፡፡
በስርየት ወንጌል በማመን ዳግም ተወልደናል፡፡ ኢየሱስ የዘወትር ሐጢያቶቻችንንና የወደፊት ሐጢያቶቻችንንም ሁሉ ሳይቀር ያነጻውን የስርየት ወንጌል ሰጥቶናል፡፡ ጌታ ይመስገን ሐሌሉያ!
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል (የውሃውና የደሙ ወንጌል) በኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጸመና የተሰበከ እውነተኛ ወንጌል ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የተጻፈው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሆነውን የኢየሱስን ወንጌል ምስጢር ለመግለጥ ነበር፡፡
ብዙ ሰዎች ሙሉ የሆነውን እውነት ሳያውቁ በኢየሱስ ስለሚያምኑ አሁን በክርስቲያን የስነ መለኮት ዓለም (ፍልስፍናዊ ስነ መለኮት ተብሎ የሚጠራ) ውስጥ ወግ አጥባቂዎች ወይም ሐይማኖተኛ ብዙሃኖች እንደሆኑ አድርገው ይመጻደቃሉ፡፡ በአጭሩ በመናፍቅነትና በውዥንብር ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ ወደኋላ ተመልሰን በእውነተኛው ወንጌል ማመን አለብን፡፡ ገና በጣም አልረፈደም፡፡
ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ስለ መወለድ ወንጌል ጥያቄዎች ላሉዋቸው ሰዎች በሁለተኛው መጽሐፍ ላይ ይበልጥ በዝርዝር እገባለሁ፡፡