Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 1-3] ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡ ‹‹ ሮሜ 1፡17 ››

‹‹ ሮሜ 1፡17 ››
‹‹ጻድቅ በእምነት ይራል ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና፡፡››
 
 
በእምነት መኖር አለብን፡፡
 
ጻድቅ የሚኖረው በምንድነው? በእምነት ነው፡፡ ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡ ‹‹እምነት›› የሚለው ቃል በጣም የተለመደ ቢሆንም የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መሰረት ነው፡፡ ጻድቅ የሚኖረው በእምነት ብቻ ነው፡፡ ጻድቅ በምን ይኖራል? በእግዚአብሄር በማመን ይኖራል፡፡ ከዚህ ክፍል መረዳትን እንደምናገኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ምክንያቱም ሥጋ አለን፤ መንፈስ ቅዱስም በውስጣችን ያድራልና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ቃል በቃል መረዳት ብንችልም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰወሩትን ፍቺዎች ባለማወቅ ብዙ ጥቅሶችን በራሳችን አስተሳሰቦች ለመተርጎም እናዘነብላለን፡፡ እኛ ሥጋም መንፈስም አለን፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እኛ ጻድቃን የሆንን ሰዎች በእምነት እንደምንኖር ይናገራል፡፡ ምክንያቱም የሐጢያቶች ስርየትን አግኝተናልና፡፡
 
 
ችግሩ ግን ሥጋ በጎ ነገርን አለማድረጉ ነው፡፡
 
ችግሩ ግን እኛ ሥጋ መሆናችንም ነው፡፡ ስለዚህ በብዙ ሁኔታዎች ብያኔችን ከስጋ የመነጨ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንድን ነገር ግትር በሆኑ አስተሳሰቦች በመመራት እንበይናለን፤ እናጤናለንም፡፡ ስለዚህ እምነትን በሚመለከት ቃሉን ሙሉ በሙሉ አናምነውም፡፡ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በአጭሩ ጻድቅ በእምነት ብቻ እንደሚኖር ይናገራል፡፡ ታዲያ ይህ ምን ማለት ነው? ‹‹በእምነት የማይኖር ጻድቅ የታለ? በዚህ ጥቅስ ላይ የምታተኩረው ለምንድነው? ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ጥቅሶች አንዱ ብቻ አይደለምን?›› ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡
 
ዛሬ ስለዚህ ጥቅስ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፡፡ በእምነት መኖር አለብን፡፡ ምንም እንኳን በሐሳባችን ስለ ጉዳዩ በሚገባ የምናውቅ ቢመስለንም አንድን ነገር ለማብራራት እስከምንሞክርበት ጊዜ ድረስ አለማወቃችንን አናውቅም፡፡ ሐጢያተኛ የሚታገለው ባለጋራ ምንድነው? ዳግም ያልተወለደ ሰው ከእርሱ/ከእርስዋ አስተሳሰቦች ጋር ይታገላል፡፡ ዳግም የተወለደ ሰው የሚታገለው ከማን ጋር ነው? በግለሰቡ ውስጥ ያሉት ሥጋና መንፈስ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ፡፡ ቀደም ብለን የምናውቀውን ለምን እንደምደጋግመው ተገርማችሁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህንን ደጋግሜ ማብራራት እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም መነገር ይገባዋልና፡፡
 
ዳግም በተወለደ ቅዱስ ውስጥ እንኳን ሥጋና መንፈስ እርስ በርሳቸው በተደጋጋሚ ይጣላሉ፡፡ ምክንያቱም እርሱ/እርስዋ ሥጋ አላቸውና፡፡ በሥጋ ውስጥ አንድ የደመ ነፍስ ክፍል አለ፡፡ እርሱም በእምነት ከመኖር ይልቅ ችግሮችን ሁሉ ለመቋቋም እየሞከረ በምቾት መኖርን ይመርጣል፡፡ በጻድቅ ሰው ሥጋ ውስጥም እንደዚሁ አንዳች ስህተት ሳይሰራ ፍጽምና ላይ ለመድረስ በመሞከር በምቾት መኖር የሚፈልግ የደመ ነፍስ ክፍል አለ፡፡ ይህ ደግሞ እግዚአብሄር ይኖር ዘንድ ከነገረው የእምነት ኑሮ በጣም የራቀ ነው፡፡
 
ስለዚህ የጻድቁም ሥጋ እያንዳንዱን መንፈሳዊ ችግር በተመሳሳይ ጊዜ ለማስተካከል በመሞከር በመንፈሳዊ ምግባሮች ፍጽምና ላይ ለመድረስ ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ሰው በሥጋ የእምነትን ኑሮ መኖር ይችላልን? ጳውሎስ እንደተናገረው ‹‹የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና፤ ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም›› (ሮሜ 7፡19) ሥጋ በጭራሽ ጥሩ ነገር አያደርግም፡፡ ሥጋ ክፉ ነገር ከማድረግ በቀር ሌላ ማድረግ ባይችልም በሥጋችን ውስጥ በእግዚአብሄር ፊት በኩራት መኖር የሚሻ ደመ ነፍስ አለ፡፡
 
 
በሥጋ የእምነትን ሕይወት መኖር አንችልም፡፡
 
ስለዚህ በግልጽ አነጋገር በሥጋ ቀና ሕይወትን ለመኖር መሞከር ትክክለኛ እምነትን ከመያዝ የራቀ ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር በእግዚአብሄር ዘንድ ተቃራኒ አስተሳሰቦችና ደመ ነፍሶች አሉን፡፡ በሥጋ ፍጹም መሆንና በሥጋ ያለ አንዳች ችግር የእምነትን ሕይወት መኖር የሚቻል አይደለም፡፡ የሰው ሥጋ አፈር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹አፈር እንደሆንን አስብ›› (መዝሙረ ዳዊት 103፡14) ይላል፡፡ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚጠፋ እንፋሎትም ነው፡፡ ምክንያቱም ጎዶሎ ነውና፡፡
 
ዳግም የተወለደ ሰው የያዘው ሥጋና ዳግም ያልተወለደ የያዘው ሥጋ ተመሳሳይ ሐጢያት የመስራት አቅም አላቸውን? ዳግም የተወለደ ሰው ሐጢያት ማድረግን ማስወገድ ይችላልን? ሥጋ ሐጢያትን ሳይሰራ መኖር ቢችል ኖሮ በእምነት መኖር አያስፈልገንም ነበር፡፡ ታዲያ በሥጋ ብርታት መኖር እንችል ነበርን? ይህ እንደማይቻል በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ ችግሩ ዳግም የተወለድን ወይም ያልተወለድን ብንሆንም ሥጋ በጣም ደካማ በመሆኑ ሐጢያት መስራቱን የሚቀጥል መሆኑን ማወቅና መገንዘባችን ነው፡፡
 
ስለ ሥጋችን ምን ያህል እናውቃለን? ስለ ራሳችንስ ምን ያህል እናውቃለን? ራሳችሁን መቶ በመቶ እንደምታውቁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የራሳችሁ ማንነት ከእውነተኛ ባህሪያችሁ የራቀ ነው፡፡ ምክንያቱም ሐጢያተኞች እንደሆናችሁ በትክክል አታምኑምና፡፡ ስለ ራሳችሁ ምን ያህል በመቶኛ እንደምታውቁ ታስባላችሁ? 50% እንኳን በጣም ብዙ ነው፡፡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን የሚረዱት በአብዛኛው 10% ወይም 20% ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ራሳቸውን 100% እንደሚያውቁ ቢያስቡም ስለ ራሳቸው የሚያውቁት 10% ወይም 20% ነው፡፡ ብዙ መጥፎ ነገሮችን እንዳደረጉ ሲያስቡ ያዝኑና ጌታን መከተል ያቆማሉ፡፡ ከዚያም እምነታቸውን እስከ መጨረሻው ድረስ ጠብቀው ማቆየት ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይጠይቃሉ፡፡ ይህም የማይቻል ወደ መሆኑ ድምዳሜም ይደርሳሉ፡፡
 
ከሥጋ አእምሮ ቧንቧ ውስጥ ቆሻሻ ውሃና የማይረባ ነገር በብዛት ይወጣል፡፡፡ እነርሱ ያማረ የእምነት ሕይወት መኖር አዳጋች ይመስላቸዋል፡፡ ‹‹ኦ ከእንግዲህ ወዲህ ጌታን መከተል አይቻልም፡፡ ሐጢያቶቼ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከተደመሰሱ በኋላ ሥጋዬ የተሻለ ይሆናል ብዬ ባስብም ሥጋዬ ግን አሁንም ድረስ ደካማ ነው፡፡ ዳግም ከተወለድሁ ረጅም ጊዜ ባስቆጥርም ከፍጽምና ጎድያለሁ፡፡ ሥጋ አይረቤና አስቀያሚ ነው፡፡›› ስለ ራሳችን ፈጽሞ አናውቅም፡፡ በተለይም ደግሞ የሥጋችንን ስህተቶች ማመን አንፈልግም፡፡ ስለዚህ ውጤቱ ከሥጋ ብዙ ሥጋዊ አስተሳሰቦች ሲፈልቁ ስንመለከት ታማኝ ሕይወትን መኖር አለመቻላችን ነው፡፡ በሥጋ የእምነት ሕይወትን መኖር አንችልም፡፡ የሰብዓዊ ፍጡር ሥጋ ምንድነው? የሰብዓዊ ፍጡር ሥጋ በሚገጥሙት መከራዎች በሚገባ ቢሰለጥን በእግዚአብሄር ፊት በሂደት ሊቀደስና ፍጹም የሆነ ሕይወት ሊኖር ይቻለዋልን? ይህ ፈጽሞ የማይቻል ነው፡፡ ሥጋ የመጨረሻ እስትንፋሱ እስከሚወጣ ድረስ ሐጢያት መስራቱን አያቆምም፡፡
 


ታዲያ ጻድቅ እንዴት በእምነት ይኖራል?
 

‹‹ብትስቱም እግዚአብሄርም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትዕዛዛት ሁሉ ባታደርጉ እግዚአብሄር ካዘዘበት ከፊተኛው ቀን ጀምሮ ወደፊትም እስከ ልጅ ልጃችሁ እግዚአብሄር በሙሴ እጅ ያዘዛችሁን ሁሉ ባታደርጉ፤ ማህበሩ ሳያውቁ በስህተት ቢደረግ፤ ማህበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መስዋዕት ከእህሉ ቁርባንና ከመጠጡ ቁርባን ጋር እንደ ሕጉ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን አንድ ወይፈን፣ ለሐጢአትም መስዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ፡፡ ካህኑም ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ ያስተሰርይላቸዋል፡፡ ስህተትም ነበረና ይሰረይላቸዋል፡፡ ስለ ስህተታቸውም ለእግዚአብሄር ቁርባናቸውን በእሳት አቅርበዋል፡፡ ለእግዚአብሄርም የሐጢአታቸውን መስዋዕት አቅርበዋል፡፡ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ያለ እውቀት ተደርጎአልና ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ በመካከላቸውም ለሚኖሩት መጻተኞች ስርየት ይደረግላቸዋል፡፡ አንድ ሰው ሳያውቅ ሐጢያት ቢሰራ ለሐጢያት መስዋዕት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል፡፡ ሐጢያት ሰርቶ ሳያውቅ ለሳተ ለዚያ ሰው ካህኑ ያስተሰርይለታል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ ይሰረይለትማል፡፡ ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከልም ቢሆን ወይም በመካከላቸው የሚቀመጥ መጻተኛ ቢሆን ሳያውቅ ሐጢያትን ለሚሰራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆንለታል፡፡›› (ዘሁልቁ 15፡22-29)
 
‹‹ብትስቱም እግዚአብሄርም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትዕዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፡፡›› በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹መሳት›› የሚሉ ብዙ ማብራሪያዎች አሉ፡፡ ሥጋ ሳያስብ በስህተት ሐጢያቶችን ያደርጋል፡፡ መደረግ የሌለበትንም ነገር ያደርጋል፡፡ ሥጋ ፍጹም መሆን ይቻለው እንደሆነ ጠይቄያችሁ ነበር፡፡ ነገር ግን የሐጢያት ስርየትን ካገኘ በኋላ እንኳን ፍጹም ሊሆን አይችልም፡፡ ሥጋ መጀመሪያ መቤዠትን ካገኘን በኋላ ፍጹም ጻድቅ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ራሳችንን በማጋለጥ ረገድ እንደማያግዘን እርግጥ ነው፡፡ በፋንታው ይደብቀናል፡፡ ሥጋ ሁልጊዜም ቆሻሻ ነገሮችንና ሐጢያቶችን ይረጫል፡፡ ሥጋ ሁልጊዜም እግዚአብሄር የሚጠላቸውን ሐጢያቶች ይፈጽማል፡፡ ሥጋ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ጊዜያቶች ያህል ሐጢያት አልሰራምን? ሥጋ ሁልጊዜም እግዚአብሄር የማይፈልገውን ያደርጋል፡፡ ሥጋ ሁልጊዜም ያለ ቁጥጥር ሐጢያት ይሰራል፡፡
 
የእግዚአብሄር ሕግ አስርቱን ትዕዛዛት ይዞዋል፡፡ እነርሱም 613 ዝርዝር አንቀፆችን ይዘዋል፡፡ ‹‹በፊቴ ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፤ ለራስህ የተቀረጸ ምስል አታድርግ፤ የእግዚአብሄር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤ አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር፤ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፡፡›› የመጀመሪያዎቹ አራቱ ትዕዛዛቶች ከእግዚአብሄር ጋር ባሉን ግንኙነቶች ላይ ተመስርተው የሚጠበቁ ትዕዛዛቶች ናቸው፡፡ ከአምስተኛው እስከ አስረኛው ድረስ ያሉት የቀሩት ትዕዛዛቶች በሰብዓዊ ፍጡራን መካከል የሚጠበቁ ትዕዛዛቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ሥጋ ሕጉን በመታዘዝ ይደሰታልን?
 
እግረኞች መንገዱን በሰላም ያቋርጡ ዘንድ የተሰመሩ ነጫጭ መስመሮች (ዜብራዎች) አሉ፡፡ ሥጋ ግን ፈጽሞ የትራፊክ ሕጎችን መታዘዝ አይፈልግም፡፡ ሰዎች መስመሮቹን ጠብቀው የሚሻገሩት ሌሎች ሰዎች እያዩዋቸው መሆኑን ስለሚፈሩ ነው፡፡ እነርሱ ሕጉን መታዘዝ አይፈልጉም፡፡ በዙሪያቸው ሰው ከሌለ የትራፊክ ምልክቶችን ጥሰው መንገዱን ይሻገራሉ፡፡
 
ሥጋ ሐጢያቶችን ለማድረግ ፈጣን ነው፡፡ ምሁራን ከሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያዩዋቸው ወይም ባያዩዋቸውም የትራፊክ ምልክቶችን መጠበቅ አለባቸው፡፡ ነገር ግን በሥጋ ብቻ የሚታወቁ ናቸው፡፡ በትራፊክምልክቶች መሰረት መንገድ መሻገርን እንጠላለን፡፡ በተቻለ መጠንም እነዚያን ምልክቶች ላለመታዘዝ እንሞክራለን፡፡
 
ታዲያ እግዚአብሄር ሕጉን የሰጠን ለምን ዓላማ ነው? ሕግ የሐጢያትን እውቀት ይሰጠናል፡፡ (ሮሜ 3፡20) እኛ ሁልጊዜም አስርቱን ትዕዛዛት የምንተላለፍ ሐጢያተኞች መሆናችንን የምናውቀው በሕጉ ነው፡፡ ሕጉ ሁልጊዜም ጥሩ ነገርን እንጂ መጥፎ ነገርን እንድንሰራ አይጠይቀንም፡፡ ሆኖም ሥጋችን ሁልጊዜም ይበድላል፡፡ ምክንያቱም ሕጉን ይብቅ ዘንድ ሁልጊዜም በጣም ደካማ ነውና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቅ እንዴት በእምነት ይኖራል ይላል፡፡ ነገር ግን ይህንን ሥጋ የያዘ ጻድቅ እንዴት በእምነት ይኖራል? ጻድቅ በእግዚአብሄር እምነት ይኖራል፡፡
 
መንፈስ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መከተል ይፈልጋል፡፡ ሥጋ ግን የአስርቱን ትዕዛዛት አንቀጾች በሙሉ በመተላለፍ ሁልጊዜም ሐጢያቶችን ይሰራል፡፡ ሥጋ ዛሬ ይህንን ሐጢያት ነገ ደግሞ ያንን ሐጢያት በመስራት ይቀጥላል፡፡ ሥጋ ከሌሎች ሐጢያቶች የበለጠ ሊፈጽማቸው የሚመርጣቸው ሐጢያቶች አሉ፡፡ የሰብዓዊ ፍጡር ሥጋ ዕድሜ ዘመኑን ሁሉ ይበድላል፡፡ ይህ ትክክል ነው ወይስ አይደለም?
 
አምስተኛውን ትዕዛዝ እንመልከት፡- ‹‹አባትህንና እናትህን አክብር፡፡›› ይህ በጣም ተገቢ ነው፡፡ ሰዎች ይህንን ትዕዛዝ ሁልጊዜም ባይጠብቁትም ሊጠብቁት ግን ይሞክራሉ፡፡ ስለዚህ ባንወያይበት ጥሩ ነው፡፡ ቀጣዩ ‹‹አትግደል›› የሚለው ነው፡፡ ሁላችንም ሌሎችን በሐሳባችን እንገድላለን፡፡ በተጨባጭ በሥጋ የሚገድሉ ግን ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም መግደል ከባድ ሐጢያት ስለሆነ ይህንንም እንለፈው፡፡ ቀጣዮቹ ‹‹አታመንዝር›› እና ‹‹አትስረቅ›› የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ሐጢያቶች በቀን ተቀን ሕይወታችን በቀላሉ የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የመስረቅና የማመንዘር የተፈጥሮ ክህሎት አላቸው፡፡ ሐጢያቶችን መስራት ልማዳቸው አድርገውታል፡፡ አይመኙም? (መጽሐፍ ቅዱስ መመኘትም ሐጢያት እንደሆነ ይናገራል፡፡) የሌሎች ሰዎችን ንብረቶች ከተቀመጡባቸው ቦታዎች ላይ በማንሳት (በመስረቅ) ረገድ የተዋጣላቸው ናቸው፡፡ ሥጋ ማድረግ በሚፈልግበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን አይነት መጥፎ ምግባሮች ያደርጋል፡፡  
 
ከአስር አይነት ሐጢያቶች ውስጥ አንድ ወይም ሁለት አይነት ሐጢያቶችን ብቻ አደረግን ብለን እናስብ፡፡ ያ በእግዚአብሄር ፊት ጻድቃን ያደርገናልን? አያደርገንም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት በሥጋ ጻድቅ አንሆንም፡፡ ምክንያቱም በጣም ጥቃቅንዋ ሐጢያት እንኳን ሐጢያት ናትና፡፡ ሥጋ በተደጋጋሚ ይበድላል፡፡ እስክንሞት ድረስም ዛሬ ይህንን ነገ ደግሞ ያንን ሐጢያት ይሰራል፡፡ ሥጋ እስክንሞት ድረስ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት መስራቱን አያቆምም፡፡ ለአንድ ቀን እንኳን በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት መስራቱን አያቆምም፡፡ ለአንድ ቀን እንኳን በእግዚአብሄር ፊት ንጹህና ቅዱስ ሆናችሁ ታውቃላችሁን? ሥጋን ከመንፈስ ለይተን እንየው፡፡ በሥጋ ፍጹማን ሆናችሁ በእግዚአብሄር ፊት ፈጽሞ ሐጢያት አልሰራችሁምን? ሰው ተኝቶ እንኳን ሐጢያት ይሰራል፡፡ በሐሳቡ ውብ የሆኑ ሴቶችን እያሰበ እንኳን አይረቤ ምስሎችን እየተመለከተ ይደሰታል፡፡ ሁላችንም ሐጢያት እንሰራለን፡፡
 
ሥጋ እግዚአብሄር እንዳናደርገው የነገረንን ያደርጋል፤ እርሱ እንድናደርገው የነገረንን ደግሞ አያደርግም፡፡ ሐጢያቶቻችን ከተደመሰሱ በኋላ እንኳን ሥጋ ሁልጊዜም ያው ነው፡፡ ፍጹም መሆን የምንችለው እንዴት ነው? ሥጋችን ፍጹም መሆን የማይችል ከሆነ የቅድስናው መንገድ ምንድነው? ይህ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አይቻልምን?
 
እነዚያን ሐጢያቶች የሰራነው እኛ ነን፡፡ በኢየሱስ ፊት አልበደልንምን? አዎ በድለናል፡፡ ሐጢያት በመስራት አልቀጠልንምን? አዎ ቀጥለናል፡፡ በሥጋ እስከሆንን ድረስ እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ ሐጢያትን እንሰራለን፡፡ እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሳችን ድረስ ሐጢያትን በመስራት የምንቀጥል ሐጢያተኛ ፍጡራን ነን፡፡ ታዲያ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ነጻ የምንወጣው እንዴት ነው? በመጀመሪያ እስከ አሁን ዳግም ካልተወለዳችሁ ሐጢያቶቻችሁ ይደመሰሱ ዘንድ በጌታ ፊት ሐጢያተኞች መሆናችሁን ማመን አለባችሁ፡፡ ነጻ ከወጣን በኋላ ሐጢያተኞች መሆናችንን መናዘዝ አያስፈልገንም፡፡ ነገር ግን ሐጢያት እንደሰራን ማመን ያስፈልገናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጥሩ በመሆን ማስመሰያ በሥጋ በጎ ነገሮችን ብናደርግም ሐጢያት በሰራን ጊዜ በሕጉ አማካይነት ራሳችንን ከተመለከትን በኋላ ሐጢያቶቻችንን ማመን ያስፈልገናል፡፡
 
 

በእምነት ተቀድሰናል፡፡
 

ሐጢያታችንን ካመንን በኋላ የሐጢያትን ችግር የምንፈታው እንዴት ነው? ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና እኛንም ለመቤዠት በመስቀል ላይ በመኮነን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዳስወገደ በማመናችን አልተቀደስንምን? አዎ በሥጋ የተፈጸሙ ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ ወደ እርሱ እንደተሻገሩ በማመናችን ተቀድሰናል፡፡ ታዲያ ‹‹ጻድቅ በእምነት ይኖራል›› የሚለው ምንባብ ምን ማለት ነው?
 
እምነት ያለን መሆን ማለት በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ማመን ማለት ነው፡፡ ሊቀድሰን የሚችለው በእግዚአብሄር፣ በቃሉ፣ በሕጉና በቤዛነቱ ማመን ብቻ ነው፡፡ በእርሱ አምነን ከጸደቅን በኋላ ፍጹማን መሆን እንችላለን፡፡ ይህ እውነት ነው ወይስ አይደለም? እውነት ነው፡፡ እኛ የሐጢያቶችን ስርየት ተቀብለን ጻድቃን ብንሆንም ሥጋ አሁንም ደካማና ከፍጽምና የራቀ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፤ በአፉም መስክሮ ይድናልና፡፡›› (ሮሜ 10፡10) ነገር ግን የሐዋርያው ጳውሎስ ሥጋ ደካማ የነበረውን ያህል ሥጋ ሁልጊዜም ደካማና እንከን ያለበት ነው፡፡ ስለዚህ በሥጋ ቀስ በቀስ ጻድቃን መሆንም ሆነ ጽድቅ ላይ መድረስ አንችልም፡፡ ሥጋ የጽድቅ ሕይወትን መኖር አይችልም፡፡
 
ጻድቅ ሊኖር የሚችልበት ብቸኛው መንገድ እግዚአብሄርን በማመን ማለትም እግዚአብሄር የሰጠንን የሐጢያቶች ስርየትና ባርኮቶች በመቀበል ነው፡፡ ከእግዚአብሄር በተቀበልነው የእርሱ ጽድቅ ላይ ለዘላለም በመደገፍ ቅዱሳንና ጻድቃን መሆንና በእርሱ ላይ ባለን እምነትም የዘላለም ሕይወትን መኖር እንችላለን፡፡ ሕይወታችን በእግዚአብሄር ላይ ባለን እምነት ላይ ጥገኛ ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ይላል፡፡ በእምነት ተቀድሰናል፡፡ እምነትን በመያዝና በእርሱም በመኖር የእግዚአብሄርን ጽድቅ አቆይተናል፡፡ ሥጋ ጻድቅ ባይሆንም በሒደት ለመቀደስ መሞከር ሞኝነት ነው፡፡ ምክንያቱም የማይቻል ነውና፡፡ መኖር የምንችለው እርሱ አምላካችን፣ ጌታችንና እረኛችን መሆኑን በማመን የእግዚአብሄርን እርዳታ ስንቀበል ብቻ ነው፡፡
 
ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስ ከብሉይ ኪዳኑ ዕንባቆም በመጥቀስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡›› ደግሞም እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ (በወንጌል) ይገለጣልና፡፡›› የእግዚአብሄር ጽድቅ ምንድነው? ከሰብዓዊ ፍጡራን ጽድቅ ጋር ተመሳሳይ ነውን? ሐጢያትን በጥቂት በጥቂቱ መቀነስ ይቀድሰናልን? ኢየሱስን ካመንን ወይም እምነት ከያዝን በኋላ ዳግመኛ ሐጢያት ስለማንሰራ ፍጹማን ነን?
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ የተገለጠው በወንጌል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ እርሱ ፈጽሞ ሊቀድሰን የሚችለው በሐጢያቶች ስርየት አማካይነት ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም በሥጋ ፈጽሞ ጻድቃን መሆን አንችልምና፡፡ ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና፡፡›› ይህ ማለት ጻድቃን መሆን የምንችለው በእምነት ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ጻድቅ ከጸደቀ በኋላ በእግዚአብሄር ላይ ባለው እምነት ይኖራል፡፡ ጻድቅ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በማቆየትና በእምነት አማካይነትም የእርሱን በረከቶች በሙሉ በመቀበል ይጸድቃል፡፡
 
 
በእምነት መኖር አለብን፡፡
 
በእምነት መኖር ማለት እንደዚያ ነው፡፡ የሰብዓዊ ፍጡራን ፈቃድ ምንም ያህል ጠንካራ ቢሆንም በአሸዋ ከተሰራ ግምብ የበለጠ በቀላሉ ይፈረካከሳል፡፡ እርሱ/እርስዋ ‹‹አቤቱ ይህንና ያንን አደርጋለሁ›› ይላሉ፡፡ ነገር ግን ሥጋ ያንን ማድረግ አይችልም፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት ከተቀበልን በኋላ በጌታ ከሐጢያትና ከሕግ መቤዠት በተገኘበት ቃል በእምነት እንኖራለን፡፡ ለረጅም ጊዜ የእምነት ሕይወትን ብንኖር ሥጋ ጥሩ ባህርይ ያለው፣ የተዋበና የሚያምር ወደ መሆን ይለወጣልን? በፍጹም! ስለዚህ በእምነት መኖር ማለት ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ማመን ማለት ነው፡፡ ጻድቃን የምንሆነው በወንጌል ፍጹም የሆነ እምነት ሲኖረንና በእርሱ ላይ ባለን እምነት አማካይነት የእግዚአብሄርን በረከቶች ሁሉ በመቀበል ስንኖር ነው፡፡
 
ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡ ያም ማለት በእግዚአብሄር ላይ ባለን እምነት እንኖራለን ማለት ነው፡፡ ይህንን ታምናላችሁን? አዎ ከሥጋችሁ ብዙ ተስፋ የምታደርጉዋቸው ነገሮች ገጥመዋችሁ ያውቃሉን? ‹‹20% ብቻ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሥጋዬ በሌሎች ረገዶች ትክክል ባይሆንም በዚህ ረገድ አሁንም ድረስ ጥሩ ነው›› ብላችሁ አስባችሁ ይሆን? ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ይላል፡፡ እግዚአብሄር ሰው በሥጋ ሊኖር አይችልም ይላል፡፡ 0.1% እንኳን አይችልም፡፡ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሐጢያት ባለመስራትና ከሥጋ ጥቂት ነገር እንኳን ተስፋ ሳታደርጉ እምነትን የምትጠብቁበት አሳብ አላችሁን?
 
ምንም ያህል ብዙ ሐጢያቶችን ብንሰራም በኢየሱስ ላይ ባለን እምነት ጻድቃን ነን፡፡ 100% በኢየሱስ ስናምን እንቀደሳለን፡፡ ነገር ግን በእርሱ 100% ካላመንን ሐጢያተኞች እንሆናለን፡፡ የምንሰራቸው ሐጢያቶች ምንም ያህል ጥቂቶች ቢሆኑም እርሱ ይደሰታልን? በሥጋ በኩል ጻድቃን ብንሆን ይህ እግዚአብሄርን ያስደስተዋልን?
 
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ጻድቃን አድርጎናል፡፡
 
ሮሜ 3፡1-8ን እንመልከት፡- ‹‹እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው፡፡ አስቀድሞ የእግዚአብሄር ቃላት አደራ ተሰጡዋቸው፡፡ ታዲያ ምንድነው? የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን? እንዲህ አይሁን፤ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደተጻፈ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሄር እውነተኛ ይሁን፡፡ ነገር ግን አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን? ቁጣን የሚያመጣ እግዚአብሄር አመጸኛ ነውን? እንደ ሰው ልማድ እላለሁ እንዲህ አይሁን፡፡ እንዲህ ቢሆን እግዚአብሄር በዓለም እንዴት ይፈርዳል? በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሄር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ሐጢያተኛ ገና ይፈረድብኛል? ስለምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና፤ አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና፡፡ የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው፡፡›› (ሮሜ 3፡1-8)
 
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- ‹‹አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን? ቁጣን የሚያመጣ እግዚአብሄር አመጸኛ ነውን?›› እግዚአብሄር እርሱ/እርስዋ እስከሚሞቱ ድረስ ሥጋቸው የሚበድለውን ሰብዓዊ ፍጡራን በጸጋው ቢያድን አመጸኛና የተሳሳተ ነውን? ሐዋርያው ጰውሎስ ላላገጡበት በምላሹ የጠየቀው ጥያቄ ‹‹ድካማችን አብዝቶ በተገለጠ ቁጥር እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ የሚያድነን የእግዚአብሄር ጽድቅ የላቀ ይሆናል›› የማለት ያህል ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሐጢያት ሲሰራ የነበረ ሰብዓዊ ፍጡር እንዴት ሊቀደስ ይችላል ብለው ለተገረሙ ሰዎች ተናገረ፡፡ የሰው ድካም የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚገልጥ መሆኑን ተናገረ፡፡ ሥጋቸው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ሐጢያት ከመስራት በቀር ሌላ ማድረግ የማይችል ሰብዓዊ ፍጡራን በድካማቸው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ታላቅነት ያሳያሉ፡፡
 
ሰው በራሱ ጽድቅ፤ በጥረቶቹ ጻድቅ መሆን የሚችል ቢሆን ኖሮ፣ 97% በእግዚአብሄር እርዳታ 3% ደግሞ በገዛ ራሱ ጥረቶች የሚድን ቢሆን ኖሮ የእግዚአብሄር ጽድቅ ምንም ማለት በሆነ ነበር፡፡ ጳውሎስ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ሐጢያት በመስራት የሚቀጥሉትን በኢየሱስ አማካይነት ፈጽሞ ማዳን የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ እንደሆነ ተናግሮዋል፡፡ ስለዚህ አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ባለጠግነት ይገልጣል፡፡ ሥጋ እስኪሞት ድረስ ሐጢያት መስራቱን ሊያቆም አይችልም፡፡ ለአንድ ቀን እንኳን ፍጹም መሆን አይችልም፡፡ ኢየሱስ እነዚህን እንከን የሞላባቸውን ሐጢያተኞች ከሐጢያቶቻቸው ፈጽሞ የማዳኑ እውነታ የእግዚአብሄርን ጽድቅ አብዝቶ ይገልጣል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ስለምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና፤ አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና፡፡ የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው፡፡›› (ሮሜ 3፡8)  
በሥጋ ጻድቃን መሆን እንችላለንን? ሥጋችን የሐጢያቶችን ይቅርታ ከተቀበለ በኋላ ፍጹም መሆን ይችላልን? ሥጋ አይችልም፡፡ ሌሎች የዓለም ሕዝቦችን ሁሉ ከጥያቄው ውጪ አድርገን እናንተና እኔ በሥጋ ጻድቃን መሆን እንችላለንን? አንችልም፡፡ ነገር ግን ጌታ ፈጽሞ አድኖናል ወይስ አላዳነንም? አድኖናል፡፡ ጌታ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ፈጽሞ አድኖናል፡፡ ኢየሱስን በልባችን ብናምን ሐጢያት ይኖርብናልን? አይኖርብንም፡፡ አመጸኞች ብንሆንም ሐጢያት የለብንም፡፡
 
ጌታ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ደግሞ ለቀደሙት በውሸት አትማል፤ ነገር ግን መሃላዎችህን ለጌታ ስጥ እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ ከቶ አትማሉ፡፡ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሄር ዙፋን ነውና፤ በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፡፡ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፡፡ በራስህም አትማል አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና፡፡ ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፡፡ ከእነዚህም የወጣ ከክፉው ነው፡፡›› (ማቴዎስ 5፡33-37) መማል በራሱ ሐጢያት ነው፡፡ ምክንያቱም መሃላችሁን ልትጠብቁ አትችሉምና፡፡ ስለዚህ በኋላ አንድ ነገር ለማድረግ ብላችሁ አትማሉ ወይም ቃል አትግቡ፡፡ በእርሱ ቃሎች ብቻ ታመኑ፡፡ ያን ጊዜ በሕይወት ትኖራላችሁ፡፡ በእርሱ ጽድቅ ብታምኑ ጻድቅ መሆን ትችላላችሁ፡፡ በእርሱ ብታምኑ ጌታ ይረዳችኋል፡፡
 
እጅግ ብዙ ቅዠቶች አሉ፡፡ የሥጋ መስፈርት አለን፡፡ ሥጋ ስለሆንን በዚያ መሰረት እንበይናለን፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የማይስማማ ዳኛ በውስጣችን አለ፡፡ በውስጣችን ሁለት ዳኞች አሉ፡፡ አንዱ እኔነት ሲሆን ሌላው ኢየሱስ ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም በውስጣችን ሊነግሱ ይሞክራሉ፡፡ የሥጋ ሕጎችን ደንግገን በእነዚያ ሕጎች ለመፍረድ እናዘነብላለን፡፡ ምክንያቱም ሥጋ ነንና፡፡ ሥጋ ‹‹ሐጢያት መስራትህን ብትቀጥልም ጥሩ ሰው ነህ፡፡ ሥጋህ 100% ጻድቅ ባይሆንም ጻድቅ መሆንህን አረጋግጥልሃለሁ›› በማለት ይነግረናል፡፡ የሥጋው ዳኛ ሁልጊዜም ጥሩ ማርኮችን ይሰጣል፡፡
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ዳኛ ግን 100% ሐጢያት አልባ እንድንሆን ይጠይቀናል፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡ ጻድቃን መሆን የምንችለው የሐጢያቶችን ስርየት በእምነት ስንቀበል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በእርሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናን ቀድሞውኑ ወደ እግዚአብሄር ጽድቅ ደርሰዋል፡፡ ቀድሞውኑም ጻድቃን ሆነናል፡፡ በእግዚአብሄር የሚያምኑ ሰዎች በእርግጥም በሕይወት ይኖራሉ፡፡ እነርሱ በእግዚአብሄር እርዳታ ተባርከዋል፡፡ ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡ ይህ ማለት የማያምኑና በሥጋ የሚኖሩ በሕይወት ሊኖሩ አይችሉም ማለት ነው፡፡ እየነገርኋችሁ ያለሁት የትልቁን ስዕል ጥቂት ክፍል ብቻ ነው፡፡ ሾርባው ነጭ እስኪሆን ድረስ አጥንቶችን ደጋግመን እንደምንቀቅል ሁሉ ደጋግሜ እየነገርኋችሁና ፍቺውንም በዝርዝር እያብራራሁላችሁ ነው፡፡
 
 
እምነት ያስፈልገናል፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ በጣም አስፈላጊው ነገር ግን ምን ያህል በእርሱ እንደምናምን ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለው የእግዚአብሄር ፍጥረት ብቻ ያምናሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሄር ሰማያትንና ምድርን እንደፈጠረና የአዳምን ሐጢያት ያነጻው ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ በየቀኑ የሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች በየቀኑ መንጻት እንዳለባቸውም ያምናሉ፡፡ በሥጋ ሕግ መሰረትም የራሳቸውን ብያኔ ይሰጣሉ፡፡ ምን ያህል እናምናለን? ጻድቅ በእምነት ይኖራል፡፡ ጻድቅ መሆንና በሕይወት መኖር የሚቻለው በእምነት ብቻ ነው፡፡ ከጅማሬው እስከ ፍጻሜው ድረስ በእግዚአብሄር ላይ እምነት ያስፈልገናል፡፡
 
ታዲያ ምን ያህል ታምናላችሁ? በሥጋ አስተሳሰቦች ተይዛችሁ ‹‹እኔ ደህና ነኝ፤ ሥጋዬም ጥሩ ነው፡፡›› ወይም ‹‹እኔ በእግዚአብሄር ለማመን በጣም ደካማ ነኝ›› ብላችሁ በማሰብ ራሳችሁን እንደወደዳችሁት መርምራችሁ ታውቃላችሁን? ዛሬ ለራሳችሁ 80%፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ 95%፤ በተወሰኑ ቀናቶች 5% በመስጠት ‹‹ባልወለድ ይሻል ነበር›› ብላችሁ አስባችሁ ለራሳችሁ ዋጋ ሰጥታችሁ ታውቃላችሁን? እንደዚያ ታስባላችሁን? አዎ እኔም አስባለሁ፡፡
 
እኔ አንዳንድ ጊዜ የምር እንደዚያ እሆናለሁ፡፡ እረፍት ስወስድ እንኳን ‹‹ጌታን ባላምንና እርሱን ባላውቅ ኖሮ የተሻልሁ እሆን ነበር፡፡ በእምነት የጽድቅን ሕይወት መኖር እየከበደ የመጣ ይመስላል፡፡ እስከ አሁን ድረስ አስቸጋሪ ነው፡፡ የወደፊቱን ለማየትና ያለፈውን ለማስታወስ እንቆቅልሽ ውስጥ ገብቻለሁ፡፡ እስከ አሁን ድረስ ቢያንስ የእምነትን ሕይወት በመኖሬ ተመስጋኝ ነኝ፡፡ ነገር ግን አቤቱ ከአሁን በኋላ ከአንተ ጋር መጓዝ አልችልም፡፡ አንተን ካወቅሁ ጀምሮ ከውስጤ ብዙ አሳቦችና መስፈርቶች ፈልቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ አንተን በትክክል ሳላውቅ በደፈናው ተከትዬሃለሁ፡፡ አሁን ግን ዳግመኛ አንተን ለመከተል ድፍረት የለኝም፡፡ ለምን? እግዚአብሄር ቅዱስና ፍጹም እንደሆነ አውቃለሁና፡፡ አሃ! አቤቱ ከእንግዲህ ልከተልህ አልችልም፡፡ ድፍረት የለኝም›› በማለት አስባለሁ፡፡
 
ስለዚህ እግዚአብሄር በሚገባ ስለሚያውቀን በእምነት እንድንኖር ነገረን፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ጻድቅ በመሆን መቆየትና በእምነት ተባርካችሁ መቅረት አለባችሁ፡፡ ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሻግረዋል፡፡ ሥጋችሁን በሕጉ በኩል ስመለከተው ሁልጊዜም ትበድላላችሁ፡፡ ስለዚህ ሐጢያት መስራትን ማቆም እንደማትችሉ እመኑ፡፡ አዳኛችሁ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ወስዶዋል ወይስ አልወሰደም? አዎ ወስዶዋል፡፡ ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ ወደ አዳኛችሁ ተሻግረዋል ወይስ አልተሻገሩም? አዎ ተሻግረዋል፡፡ ታዲያ ሐጢያት አለባችሁ ወይስ የለባችሁም? የለብንም፡፡ ጌታ አድኖዋችኋል ወይስ አላዳናችሁም? አድኖናል፡፡ እንግዲያውስ ‹‹ዛሬ በነፍሴ ውስጥ ጸሐይ በርታለች›› እንደሚሉት የዝማሬ ቃሎች ጭጋጋማዎቹና ጨለማዎቹ ቀኖች ወደ ጸሐያማ ቀኖች ተቀይረዋል፡፡
 

 
ዳግመኛ ሐጢያተኞች ልንሆን አንችልም፡፡
 

ስለ ወደፊቱ ስናስብ ተስፋ ቢስ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በእምነት ጌታን ስንመለከት ጸሐያማና ብሩህ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ጻድቅ በእምነት ይኖራል ይላል፡፡ ይህንን ታምናላችሁን? -- አዎ-- በእምነት ድነናል፡፡ በእምነትም በሕይወት እንኖራለን፡፡ የምናምነው በማን ነው? በእግዚአብሄር በማመን በሕይወት እንኖራለን፡፡ በእምነት መኖር የሚችለው ጻድቅ ብቻ ነው፡፡ ያንን ታምናላችሁን? --አዎ-- ሥጋን በሚገባ በማሰልጠን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማቆየት ትችላላችሁን? አንችልም፡፡ ሥጋ ክፉ ነገር ሲያደርግ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሽባ ይሆናልን? ዳግመኛ ሐጢያተኞች እንሆናለንን? አንሆንም፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ 2፡18 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ያፈረስሁትን ይህን እንደገና የማንጽ ከሆንሁ ራሴ ሕግ ተላላፊ እንድሆን አስረዳለሁና፡፡›› ሐጢያቶቹ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሻገረና ለእርሱ ሲልም በመስቀል ላይ እንደተኮነነ የሚያምን ሰው ዳግመኛ ፈጽሞ ሐጢያተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢየሱስን የማይክድ ሰው በአንድ ጊዜ ይቀደሳል፡፡ ሐጢያት አልባም ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ሐጢያቶቹ በሙሉ ወደ እርሱ ተሻግረዋል፡፡ ዳግመኛም በፍጹም ሐጢያተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህንን ተረድታችኋልን? --አዎ--
 
ያዳነን አምላክ ሁልጊዜም ጌታችንና አባታችን ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜም ይረዳናል፡፡ እስከ ዓለም ፍጻሜም ድረስ ከእኛ ጋር ነው፡፡ ‹‹በእምነት ኑሩ፡፡ በእኔ የምታምኑ ከሆናችሁ እረዳችኋለሁ፡፡ ዳግም የተወለዳችሁትንም መላዕክቶች ያገለግሉዋችኋል›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ መላዕክቶች በእግዚአብሄርና በእኛ መካከል አገልጋዮች ናቸው፡፡ ለእግዚአብሄርም ስለ እኛ ሁሉንም ነገር ይነግሩታል፡፡ እግዚአብሄር ልጆቹ አድርጎናል፡፡ በፍጥረታችን ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ በሥጋ ምግባሮች ፈጽሞ ጻድቃን ልንሆን አንችልም፡፡ በእምነት ግን ጻድቃን እንሆናለን፡፡
 
ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ጌታ በእምነት እረኛችንና አባታችን ሆንዋል፡፡