Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 14] እርስ በርሳችሁ አትፈራረዱ፡፡

ሮሜ 14፡1 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእምነት የደከመውን ተቀበሉት፤ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ፡፡››
ጳውሎስ በሮሜ የሚገኙትን ቅዱሳን አንዳቸው የሌላቸውን እምነት እንዳይፈርዱ ወይም እንዳይነቅፉ አስጠንቅቆዋቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን በሮሜ ቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም ታማኝ የነበሩና ያን ያህል ታማኝ ያልነበሩ ሰዎች ስለነበሩ አንዳቸው የሌላቸውን እምነት ይነቅፉ ነበር፡፡ ይህ በእናንተ ላይ ደርሶ ከሆነ አንዱ የሌላውን እምነት ማክበር አለበት፡፡ በእግዚአብሄር ባሮች ላይ ያላችሁንም አንዳች ነቀፌታ ማስወገድ አለባችሁ፡፡ ባሮቹን የማስነሳትና የመገንባት ሥራ የእግዚአብሄር እንጂ የእኛ አይደለም፡፡
 
በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥም ቢሆን በምዕመናኖች መካከል ብዙ ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ እምነታቸውን ብንመለከት ሁሉንም ዓይነት እምነት ማግኘት እንችላለን፡፡ አንዳንዶች ከመዳናቸው በፊት በሕግ ታስረው ስለነበር አሁንም ድረስ የጥንቱ በሕግ ላይ የተመሰረተ እምነት ቅሪት ከእነርሱ ጋር አለ፡፡
 
አንዳንድ ክርስቲያኖች እየመረጡ መብላትን እንደ ታላቅ ጠቀሜታ ይቆጥሩታል፡፡ ለምሳሌ እነዚህ ሰዎች የአሳማ ሥጋ መብላት እንደሌለባቸው ያምኑ ይሆናል፡፡ ሌሎች ደግሞ በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ ሰንበትን መጠበቅ እንዳለባቸው ያምኑ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በእምነታችን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ልዩነቶች በእግዚአብሄር ጽድቅ መፍታት አለብን፡፡ በማይረቡ ጉዳዮችም እርስ በርሳችን መነቃቀፍ አይኖርብንም፡፡ የጳውሎስ አባባል መሰረተ አሳብ ይህ ነው፡፡
 
ጳውሎስ በምዕራፍ 14 ላይ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ከሆነ የወዳጅ ምዕመናኖቻችንን ድክመት መንቀፍ እንደማይገባን ተናግሮዋል፡፡ ለምን? ምክንያቱም ደካሞች ቢሆኑም በእግዚአብሄር ጽድቅ ያምናሉና፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ከሐጢያቶቻቸው የዳኑትን ሰዎች የእግዚአብሄር ክቡር ሕዝቦች አድርጎ ይቆጥራቸዋል፡፡ አንዳቸው በሌላቸው ዓይን ሲታዩ ብቃት ያላቸው ባይመስሉም እግዚአብሄር የሌሎች ምዕመናንን እምነት እንዳንነቅፍ አዞናል፡፡ ምክንያቱም እነርሱ በሥጋ ብቁዓን ባይሆኑም በእምነት የእግዚአብሄር ልጆች ናቸውና፡፡
          
 

የእያንዳንዱ ሰው እምነት አንዱ ከሌላው ይለያል፡፡ 

 
ቁጥር 2-3 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሚያምን አለ፡፡ ደካማው ግን አትክልት ይበላል፡፡ የሚበላ የማይበላውን አይናቀው፡፡ የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፡፡ እግዚአብሄር ተቀብሎታልና፡፡››
 
በእርሱ ጽድቅ በሚያምኑና እርሱን በሚከተሉ የእግዚአብሄር ባሮች መካከል ልዩነት ሊኖር ይችላል፡፡ በደህንነት ማመኑ ተመሳሳይ ነው፤ ነገር ግን በቃሉ ላይ ያለው የእምነት መጠን ሊለያይ ይችላል፡፡
 
አንድ ሰው በእግዚአብሄር የጽድቅ ወንጌል በማመን ዳግም ከመወለዱ በፊት ሕግ አጥባቂ ከነበረ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የራሱን ጽድቅ ለመተው ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ሰንበትን መጠበቅ ታላቅ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ልትነቅፉዋቸው አይገባም፡፡ ምክንያቱም እነርሱም በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ናቸውና፡፡
 
እግዚአብሄር የእርሱን ጽድቅ በሚያውቁና በሚያምኑ ሰዎች እምነት ይደሰታል፡፡ የራሱ ሕዝብ አድርጎም ይወስዳቸዋል፡፡ ስለዚህ በእርግጥ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች የእምነታቸውን ድክመት ከመንቀፍ ይልቅ ወዳጅ ምዕመናኖቻቸውን በእግዚአብሄር ጽድቅ ይመግቡዋቸው ዘንድ እያንዳንዱን ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡
 
 

በእግዚአብሄር ባሮች ላይ መፍረድ የለብንም፡፡ 

 
ቁጥር 4 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል፡፡››
 
እግዚአብሄር የተቀበላቸውን የእግዚአብሄር ባሮችና እምነታቸውን መደገፍ አለብን፡፡ የክርስትና ሕይወታችሁን እየኖራችሁ የእግዚአብሄርን ባሮች ትነቅፋላችሁ ትኮንናላችሁ? ስለማትወዱዋቸው ብቻ እግዚአብሄር የተቀበላቸውን የእግዚአብሄር ባሮች የምትኮንኑ ከሆናችሁ በእግዚአብሄር የፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጣችሁ የእርሱን ባሮች እየፈረዳችሁባቸው ነው፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ በፈንታው የማትወዱዋቸውን እነዚያን የአምላክ ባሮችም ቢሆን በምስጋና ልትቀበሉዋቸውና የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከፍ በማድረግ ምሪታቸውን ልትታዘዙ ይገባችኋል፡፡
 
እግዚአብሄር እምነታችንን መቀበል አለበት፡፡ የእግዚአብሄርን ምስጋናና ሽልማት የሚያስገኝ እውነተኛ እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡ እግዚአብሄር ሕይወታችንን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንድንቀድስ ስለፈቀደልን ስለ ጽድቁ እናመሰግነዋለን፡፡ እግዚአብሄር የተቀበላቸውን እንቀበላለን፤ እግዚአብሄር ያልተቀበላቸውን አንቀበልም፡፡ የራሳችሁን ጽድቅ ከፍ በማድረግ ፋንታ በእርሱ ጽድቅ በማመን እግዚአብሄርን እንደምታከብሩት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እግዚአብሄር እምነታችሁን እንደሚቀበል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ያን ጊዜ በእርሱ ጽድቅ ላይ ባላችሁ እምነት ከፍ ትላላችሁ፡፡
       
 
እነርሱም በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ከሆኑ…
 
‹‹ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፡፡ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደሆነ ያስባል፡፡ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ፡፡ ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፡፡ የሚበላም እግዚአብሄርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፡፡ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም፤ እግዚአብሄርንም ያመሰግናል፡፡›› (ሮሜ 14፡5-6)
በአይሁዶችም መካከል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ጌታችን በሆነው ክርስቶስ በማመን የዳኑ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ብዙዎቹ በኢየሱስ ያመኑ ቢሆኑም ገናም በሕግ የታሰሩ ነበሩ፡፡ ነገር ግን አስቀድመው የእግዚአብሄር ጽድቅ ባሮች ሆነው ነበር፡፡ ምክንያቱም ሕጉን ለመጠበቅ ያደረጉትን ነገር ሁሉ ያደረጉት የእግዚአብሄርን ሕግ ለማሰራጨት ነበርና፡፡
 
ጳውሎስ እንዲህ ያለው ለዚህ ነው፡- ‹‹አይሁድንም እጠቅም ዘንድ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ፡፡ ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ እኔ ራሴ ከሕግ በታች ሳልሆን ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ፡፡ ሕግ የሌላቸውን እጠቅም ዘንድ ያለ እግዚአብሄር ሕግ ሳልኖር ነገር ግን በክርስቶስ ሕግ በታች ሳለሁ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለኝ ሆንሁ፡፡›› (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡20-21)
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑትን ሰዎች እምነት ቸል ማለትም ሆነ መናቅ አይገባንም፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑና እርሱን የሚያገለግሉ ከሆኑ የእግዚአብሄር ባሮች አድርገን ልንቀበላቸው ይገባናል፡፡
   
 

ጻድቃን ለጌታ ይኖራሉ፡፡

 
ቁጥር 7-9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፤ ለራሱም የሚሞት የለም፡፡ በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፡፡ እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን፡፡››
 
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነን በወንጌል ውስጥ በተገለጠው የእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን አዲስ ሕይወትን ስለተቀበልን ከክርስቶስ ጋር እንኖራለን፤ እንሞትማለን፡፡ በክርስቶስ አሮጌው ሁሉ አልፎዋል፡፡ እኛም አዲስ ፍጥረቶች ሆነናል፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ በትክክል ማመን ማለት የክርስቶስ የመሆናችሁን እውነት ማወቅና ማመን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ከዚህ ዓለም ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም፡፡ በፈንታው የእግዚአብሄር ባሮች ሆነዋል፡፡
 
የእግዚአብሄር ባርያ ከሆናችሁ እርሱን ከፍ ታደርጉታላችሁ፤ ትወዱታላችሁ፡፡ ለክብሩም ትኖራላችሁ፡፡ ሕይወታችሁን በዚህ መንገድ እንድትኖሩ ስለፈቀደላችሁም ታመሰግኑታላችሁ፡፡
 
በእርግጥ የክርስቶስ ናችሁን? በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ተሰቅለዋል፡፡ እንደገናም ሕያው ሆነዋል፡፡ በሕይወት ብንኖር ብንኖር ወይም ብንሞት በእግዚአብሄር ጽድቅ የክርስቶስ ነን፡፡ ጌታም የዳኑት ጌታ ሆንዋል፡፡
 
 
ወዳጅ ምዕመናኖቻችንን ልንፈርድባቸው አይገባንም፡፡
 
በቁጥር 10-12 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹አንተም በወንድምህ ላይ ስለምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና፡፡ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ፤ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ መላስም ሁሉ እግዚአብሄርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሄር መልስ እንሰጣለን፡፡››
 
አምላካችን ክርስቶስ ሕያው ስለሆነ አንድ ቀን በፊቱ ተንበርክከን ሁሉን ነገር እንመሰክራለን፡፡ ስለዚህ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጠን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መኮነን የለብንም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት በጨዋነት ልንቆም ይገባናል፡፡ በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ እርስ በርስ ከመፈራረድና ከመኮናነን ለእግዚአብሄር ፈቃድ መኖር በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን ድክመቶች የምንፈርድና የምንኮንን ከሆንን እኛም በእግዚአብሄር ፊት በድክመቶቻችን እንኮነናለን፡፡ በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ላይ ሆኖ ለእግዚአብሄር ፈቃድ መኖር ምንኛ መልካም የሆነው ለዚህ ነው፡፡
እውነተኛ እምነት ወዳጅ ምዕመናኖችንና የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚከተሉትን ያንጻል፡፡ ሐሰተኛ እምነት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ትቶ የራሱን ጽድቅ ብቻ እንደሚገነባ ይታወስ፡፡ እናነተስ? የእግዚአብሄርን ጽድቅ በእምነት እየተከተላችሁ ነውን? ወይስ የራሳችሁን እምነት እየተከተላችሁ ነው?
የሌሎችን እምነት ማነጽ አለብን፡፡
 
ቁጥር 13-14፡- ‹‹እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፡፡ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቁረጡ፡፡ በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄያለሁ፤ ተረድቼአለሁም፡፡ ነገር ግን ምንም ርኩስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኩስ ነው፡፡››
በእግዚአብሄር ጽድቅ በሚያምኑ ሰዎች መካከል የእምነት መጠንን በሚመለከት ልዩነቶች ስላሉ አንዱ ሌላውን በማነጽ እርስ በርሳችን እምነታችንን ለመገንባት መስራት ይገባናል፡፡ ይህም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለሚያምኑ ምዕመናኖች ዕድገትን ያመጣላቸዋል፡፡ በእርግጥ ለእግዚአብሄርና ለጽድቁ የምንኖር ከሆንን ሁላችንም የእርሱ ሕዝብ ነን፡፡
በእግዚአብሄር ጽድቅ የምታምኑ ክርስቲያኖች ከሆናችሁ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ባላችሁ እምነት ማንኛውንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ የማትችሉ ከሆነ ምክንያቱ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከመከተል ይልቅ የራሳችሁን ጽድቅ መከተላችሁ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ውስጥ የራሳችሁን ጽድቅ መከተል ዓለምን እንደ መከተልና የተሳሳተ እምነት እንደ መያዝ ነው፡፡
የራሳቸውን ጽድቅ የሚከተሉ ሰዎች በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የዳኑ ቢሆኑም የእግዚአብሄር ጠላቶች ሆነው ይኖራሉ፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ ጽድቅ በማመን የዳኑ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው ሁሉ የእርሱን ጽድቅ መከተላቸውን እንዲቀጥሉ ይሻል፡፡
        
 
በፍቅር መመላለስ፡፡
 
ቁጥር 15-18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ወንድምህንም በመብል ምክንያት የምታሳዝን ከሆንህ እንግዲህ በፍቅር አልተመላለስህም፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለትን እርሱን በመብልህ አታጥፋው፡፡ እንግዲህ ለእናንተ ያለው መልካም ነገር አይሰደብ፡፡ የእግዚአብሄር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና፡፡ እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚአብሄርን ደስ ያሰኛልና፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነውና፡፡››
የእግዚአብሄርን ጽድቅ በማመን ድነው ይህንን ጽድቅ ለማሰራጨት የሚኖሩ ሰዎች ለመብል ብለው የእግዚአብሄርን ሕዝብ አይንቁም፡፡ አንዳንድ ጊዜ መብል እናመጣና በፍቅር እንጋራለን፡፡ ጳውሎስ ግን በሐብታሞች መካከል እየተካፈልን ድሃ የሆኑ ወንድሞችንና እህቶችን እንዳናገል ያስጠነቅቀናል፡፡ ምክንያቱም የዚህ ዓይነቱ ድርጊት አብረውን ያሉትን ክርስቲያኖች ሊያሰናክላቸው ይችላልና፡፡
እግዚአብሄር በእርሱ ጽድቅ ለሚያምኑ ሰዎች የለገሳቸው በረከቶች የእግዚአብሄርን ጽድቅ፣ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የተሰጠንን የአእምሮ ሰላም እንድንከተል፣ ጌታን አብረን ማገልገል እንድንችልና እርሱ የሰጠንን ደስታ እርስ በርሳችን እንድጋራ ፈቅደውልናል፡፡ ስለዚህ ባለጠጋ የሆኑ ሰዎች ብልጥግናቸው ሁሉ ከእግዚአብሄር የተሰጠ ስለሆነ ወንጌልን ለማገልገልና የእግዚአብሄርንም ጽድቅ በጋራ ለመከተል ከሌሎች ጋር መጋራት እንዳለባቸው መንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ እግዚአብሄር የዚህ ዓይነት ሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ይደሰታል፤ ይወዳቸውማል፡፡
     
 
ሌሎችን ለማነጽ ፈልጉ፡፡
 
ቁጥር 19-21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን፣ እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል፡፡ በመብል ምክንያት የእግዚአብሄርን ሥራ አታፍርስ፡፡ ሁሉ ንጹህ ነው፡፡ በመጠራጠር የተበላ እንደሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው፡፡ ሥጋን አለመብላት፣ ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው፡፡››
ጥንት እንደ ሮሜና ቆሮንቶስ ባሉ ጥንታዊ ከተሞች ውስጥ በአንድ ወቅት ለጣዖታት መስዋዕት የሆኑ ምግቦችን ይሸጡ ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ አንዳንድ ምዕመናኖች ይህንን ሥጋ ገዝተው መመገብ ለምደው ነበር፡፡ ያን ጊዜ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ በእምነታቸው የደከሙ አንዳንድ ወዳጅ ምዕመናኖች እንዲህ ያለውን ሥጋ መብላት ሐጢያት እንደሆነ አስቡ፡፡ ጳውሎስ ‹‹በመብል ምክንያት የእግዚአብሄርን ሥራ አታፍርስ›› (ቁጥር 20) ያለው ለዚህ ነው፡፡
ለወይንም እንደዚሁ ነው፡፡ ስለ መጠጥ ብዙ የማይጨነቁ የአንዳንድ ምዕመናን ነበሩ፡፡ ጳውሎስ ግን እነዚህ ባህሪዎች አብረዋቸው ያሉትን ምዕመናኖች ከማሰናከል ቢቆጠቡ መልካም እንደሆነ መከራቸው፡፡ ስለዚህ የክርስትና ሕይወታችንን ሌሎችን በሚያንጽ መልኩ መኖርና የእግዚአብሄርን ጽድቅ መሻት አለብን፡፡ ዛሬም ለቅድመ አያቶች የሚቀርቡ መብሎችን በሚመለከት አንዳንድ ጉዳዮች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በእምነታቸው ደካማ ስለሆኑት ሲባል እንደዚህ ያለውን መብል አለመብላት ይሻላል፡፡
 
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ እምነት ይኑራችሁ፡፡
 
ቁጥር 22-23 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሄር ፊት ለራስህ ይሁንልህ፤ ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቆጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብጹዕ ነው፡፡ የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፡፡ በእምነትም ያለሆነ ሁሉ ሐጢአት ነው፡፡››
ትክክለኛ እምነት ያላቸው ሰዎች በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን እምነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የሚያነጻ ከእግዚአብሄር የተሰጠ እምነት ነው፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመንና በእርሱ ጽድቅም እምነታቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በእርሱ ጽድቅ ሳያምኑ እግዚአብሄርን መከተል ሐጢያት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ያለ እምነት የተደረገ ማንኛውም ነገር ሐጢያት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ሳያምኑ የተደረገ ማንኛውም ነገር ሐጢያት መሆኑ ከታወቀ በእርሱ ጽድቅ ይበልጥ የሚያምን እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የሚጠራጠረው ግን ቢበላ ተኮንኖዋል›› ይላል፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ አምናችሁ ብትበሉ ሁሉም ንጹህ ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር እያንዳንዱን ተክልና እንስሳ ፈጥሮዋልና፡፡
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማወቃችንና ማመናችን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ አብረውን ያሉትን ዳግም የተወለዱ ምዕመናን ማነጽና እምነታቸውንም ማክበር ይገባናል፡፡