Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[22-2] ደስ ይበላችሁ፤ በክብር ተስፋም ጠንክሩ፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 22፡1-21 ››

ደስ ይበላችሁ፤ በክብር ተስፋም ጠንክሩ፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 22፡1-21 ››
 
ዮሐንስ ራዕይ 22፡6-21 የሰማይን ተስፋ ያሳየናል፡፡ የራዕይ መጽሐፍ የመደምደሚያ ምዕራፍ የሆነው ራዕይ 22 የቅዱሳን መጽሐፍቶችን ትንቢቶች ታማኝነትና እግዚአብሄር ወደ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ለመግባት ያቀረበውን ግብዣ ከማረጋገጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ አዲስቷ ኢየሩሳሌም እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግመኛ ለተወለዱት ቅዱሳን የሰጠው ስጦታ እንደሆነች ይነግረናል፡፡ 
 
እግዚአብሄር ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳን እርሱን በአምላክ ቤት ውስጥ እንዲያመሰግኑት አድርጎዋቸዋል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት በውሃውና በንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ይቅርታን ያገኘን ቅዱሳን እንድንሆን ስለፈቀደልን ምስጋናችንን የምንገልጥበት ቃላቶች የሉንም፡፡ በዚህ ምድር ላይ እኛ ከተቀበልነው የሚበልጥ የላቀ በረከት የሚቀበል ማነው? ማንም የለም! 
 
የዛሬው ዋናው ምንባብ የራዕይ የመጨረሻው ምዕራፍ ነው፡፡ በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሄር ለሰው የነደፋቸውን ንድፎች ሁሉ እናያለን፡፡ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥም ጌታችን እነዚህን ዕቅዶች በሙሉ ሲፈጽም እናየዋለን፡፡ የራዕይ ቃል እግዚአብሄር በዕቅዱ መሰረት ለሰው ዘር የሚሰራቸውን ሥራዎች በሙሉ ለማጠናቀቅ ሲል ይህንን ዓለም የሚያጠፋበት የጥፋት ሒደት ተብሎ ሊገለጥ ይችላል፡፡ በራዕይ ቃል አማካይነት እግዚአብሄር የገለጠውን መንግሥተ ሰማይ አስቀድሞ ማየት እንችላለን፡፡ 
 
 
የእግዚአብሄር ከተማ ቅርጽና የከተማይቱ ገነት፡፡ 
 
ምዕራፍ 21 ስለ እግዚአብሄር ከተማ ይናገራል፡- ቁጥር 17-21 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ቅጥርዋንም ለካ፤ መቶ አርባ አራት ክንድ በሰው ልክ እርሱም በመልአክ ልክ፡፡ ቅጥርዋም ከኢያስጲድ የተሰራ ነበረ፡፡ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች፡፡ የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጊጦ ነበር፤ ፊተኛው መሠረት ኢያስጲድ፣ ሁለተኛው ሰንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ፣ አምስተኛው ሰርዶንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ወራወሬ፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አስራ አንደኛው ያክንት፣ አስራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ፡፡ አስራ ሁለቱም ደጆች አስራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፤ እያንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቁ የተሰራ ነበረ፡፡ የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ፡፡›› 
 
ይህ የራዕይ ቃል እግዚአብሄር ዳግመኛ ለተወለዱት ሕዝቦቹ የሚሰጣቸውን አዲሲቷን ኢየሩሳሌም ያብራራል፡፡ በሰማይ ያለችው ይህች የኢየሩሳሌም ከተማ በአስራ ሁለት ዓይነት የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮችና ከዕንቁዎች በተሰሩ አስራ ሁለት ደጆች እንደተገነባች ተነግሮናል፡፡ 
 
ስለዚህ ምዕራፍ 22 በኢየሩሳሌም ከተማ ገነት ውስጥ ለሚገኘው ተፈጥሮ ይናገራል፡፡ ቁጥር 1 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሄርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ፡፡›› እግዚአብሄር በመጀመሪያ በኤድን ገነት የሚፈስሱ አራት ወንዞች እንደሰራ ሁሉ በእግዚአብሄር ከተማ ውስጥም በገነቶችዋ ውስጥ እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቅ ወንዝ ይፈስሳል፡፡ እግዚአብሄር ጻድቃን ወደፊት የሚደሰቱበት ገነት ይህ እንደሆነ ይነግረናል፡ 
 
ዋናውም ምንባብ እንደዚሁ በዚህ ገነት ውስጥ የሕይወት ዛፍ እንደተተከለ፣ አስራ ሁለት ዓይነት ፍሬዎችን እንደሚያፈራ፣ በየወሩም ፍሬውን እንደሚሰጥና ቅጠሎቹም ለአሕዛብ መፈወሻ እንደሚሆኑ ይነግረናል፡፡ የሰማይ ባህርይ ፍሬዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ቅጠሎቹም የሚበሉበት መስሎ ይታየኛል፡፡ ምክንያቱም ቅጠሎቹ የመፈወስ ሐይል አላቸውና፡፡ 
 
 
ጻድቃን የሚቀበሉዋቸው ባርኮቶች! 
 
መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሄር ከተማ ውስጥ ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም፡፡ የእግዚአብሄርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፡፡ ባሪያዎቹም ያመልኩታል›› ብሎ ይነግረናል፡፡ ይህም የሐጢያቶቻችንን ይቅርታ ያገኘን ሰዎች እኛን ካዳነን አምላክ ጋር ለዘላለም እንደሚኖር ይነግረናል፡፡ 
 
በዚህ ምድር ላይ ሲኖሩ ሳሉ በውሃወና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሐጠያቶቻቸው የተደመሰሱላቸው ሰዎች የሚቀበሉት ሐጢያቶቻቸው ሁሉ የተወገዱበትን በረከት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ልጆች የሚሆኑበትን በረከትም ነው፡፡ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሲገቡም ብዙ መላዕክቶች ያገለግሉዋቸዋል፡፡ ከጌታም ጋር ለዘላለም ይነግሳሉ፡፡ ምንባቡ ጻድቃን በሕይወት ወንዝ ላይ ቆመው የሕይወትን ፍሬዎች እየተመገቡ ከእግዚአብሄር ዘንድ እንዲህ ያለ ዘላለማዊ ባርኮቶችን እንደሚቀበሉ ይነግረናል፡፡ የእነዚህ በረከቶች ክፍል በመሆንም ከእንግዲህ ወዲህ በሽታ አይኖርም፡፡ 
 
ይህም እነርሱ የዚህ ምድር ብርሃንም ሆነ የፀሐይ ብርሃን እንደሚያስፈልጋቸው ይነግረናል፡፡ ምክንያቱም በከበረው የእግዚአብሄር መንግሥት ውስጥ እርሱ ራሱ ብርሃን ከሆነው አምላክ ጋር ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የሐጢያቶቻውን ስርየት የተቀበሉ የእግዚአብሄር ልጆች ልክ እንደ አምላክ ይኖራሉ፡፡ ጻድቃን የሚቀበሉት በረከት ይህ ነው፡፡ 
 
የራዕይን መጽሐፍ የጻፈው ከአስራ ሁለቱ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ዮሐንስ የዮሐንስን ወንጌል የአዲስ ኪዳንን ሦስቱ መልዕክቶች--መጀመሪያውን ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ዮሐንስ ጽፎዋል፡፡ የሮምን ንጉሠ ነገስት እንደ አምላክ ለመቀበል አሻፈረኝ በማለቱ ወደ ፍጥሞ ደሴት ተግዞ ነበር፡፡ በዚህ ግዞት ወቅት እግዚአብሄር መልአኩን ወደ ዮሐንስ ልኮ የዓለምን ጥፋትና ቅዱሳኖች ውሎ አድሮ የሚገቡበትንና የሚኖሩበትን ስፍራ በመግለጥ በዚህ ምድር ላይ የሚመጣውን አሳየው፡፡ 
 
የዘፍጥረትን መጽሐፍ የፍጥረት ንድፍ አድርገን የምንገልጠው ከሆነ የራዕይ መጽሐፍ ደግሞ የተጠናቀቀውን ትንሹን ንድፍ የሚያሳይ ነው ብለን ልንገልጠው እንችላለን፡፡ ጌታችን ለ4,000 ዓመታት ለሰው ዘር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሐጢያቶቹን በሙሉ እንዳስወገደ ነግሮታል፡፡ ዘመኑ በደረሰበት በአዲስ ኪዳን ዘመንም እግዚአብሄር አዳኙን ኢየሱስን ወደዚህ እንደሚልክ፣ በዮሐንስ ይጠመቅ ዘንድ እንደሚያደርግና በመስቀል ላይ በፈሰሰው የክርስቶስ ደም አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች እንደሚያስወግድ የሰጣቸውን ተስፋዎቹን በሙሉ ፈጸመ፡፡ 
 
የሰው ዘር በሰይጣን ተታልሎ በጥፋቱ ውስጥ በተጠመደ ጊዜ ጌታችን ከሐጢያቶቹ እንደሚያድነው ቃል ገብቷል፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው፡፡ እንዲጠመቅና ደሙን እንዲያፈስስ አደረገው፡፡ በዚህም የሰውን ዘረ ፈጽሞ ከሐጢያቶቹ አዳነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር በራዕይ ቃል አማካይነት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የተቀበሉ ሰዎች ምን ዓይነት ክብር እንደሚጠብቃቸውና በሌላ በኩል ደግሞ ሐጢያተኞችን ምን ዓይነት ፍርድ እንደሚጠብቃቸው በዘርዝር መዝግቦዋል፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር እርሱን በታማኝነት እንሚያምኑት ቢናገሩም መጨረሻቸው ሲዖል የሚሆን ብዙ ሰዎች አሉ፡ (ማቴዎስ 7፡21-23) 
 
ጌታችን ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው አድኖዋቸዋል፡፡ ለጻድቃን ያዘጋጀውንም የበረከቶች ቃል እንዳናትመው ነግሮናል፡፡ 
 
 
የማያምኑና ርኩሳን እነማን ናቸው? 
 
ቁጥር 11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ዓመጸኛው ወደፊት ያምጽ፤ ርኩሱም ወደፊት ይርከስ፤ ጻድቁም ወደፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ፡፡›› እዚህ ላይ ‹‹ዓመጸኛ›› እነማን ናቸው? ዓመጸኞች ጌታ በሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ፍቅር የማያምኑ ናቸው፡፡ ሰዎች ሁልጊዜም ሐጢያትን ስለሚሰሩ ጌታ በሰጣቸው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ማመንና እግዚአብሄርን እያከበሩ ሕይወታቸውን መኖር አለባቸው፡፡ ከሰው ዘር ክብርን መቀበል የሚኖርበት እግዚአብሄር ብቻ ስለሆነና የደህንነትን ጸጋ የሚያለብሰንም እርሱ ብቻ ስለሆነ ሁላችንም ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሄር የሚሰጥ ሕይወትን መኖር ይገባናል፡፡ እግዚአብሄርን የማይታዘዙ ሰዎች ርኩሳን ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜም በእርሱ ቃል አያምኑምና፡፡ 
 
በማቴዎስ 7፡23 ላይ ጌታችን በከንፈራቸው ብቻ በእርሱ ለሚያምኑት ሐይማኖተኞች እንዲህ ብሎዋቸዋል፡- ‹‹ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመጸኞች ከእኔ ራቁ፡፡›› ጌታችን ‹‹እናንተ ዓመጸኞች›› ብሎ ጠርቶዋቸዋል፡፡ የወቀሳቸው እነዚህ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከሙሉ ልባቸው በማመን ፋንታ በምግባሮቻቸው ብቻ በኢየሱስ በማመናቸው ነው፡፡ ዓመጸኝነትና የእግዚአብሄርን ቃል ከልብ አለማመን ሐጢያት ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ዓመጻን ሲያደርጉ እግዚአብሄር በሰጣቸው የውሃውና የመንፈሱ ፍቅርና ደህንነት አያምኑም ማለት ነው፡፡ ዓመጸኝነት የእግዚአብሄርን ቃል በራስ ስሜት መለወጥና ሰው በሚሰማው ስሜት መሰረት በማን አለብኝነት የተለወጠውን ቃል ማመን ማለት ነው፡፡ 
 
ከልባቸው በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሄር የመሰረተውን እንዳለ መቀበል አለባቸው፡፡ እኛ በኢየሱስ እናምናለን፡፡ ይህ ግን የእግዚአብሄርን ቃልና የደህንነቱን ፍጻሜ በምንም መንገድ እንድንለውጥ አይፈቅድልንም፡፡ የዋናው ምንባብ መልዕክት እግዚአብሄር በራሱ በቆመው የእርሱ ደህንነት ለሚያምኑ የዘላለምን ሕይወት እንደሚሰጥ የእግዚአብሄርን ሕግ የሚለውጡትንና ለራሳቸው በሚጥማቸው በማንኛውም መንገድ የሚያምኑትን ወደ ሲዖል እንደሚወረውራቸው የሚናገር ነው፡፡ 
 
‹‹ዓመፀኛውም ወደፊት ያምጽ፡፡›› ይህም እንዲህ ዓይነት ሰዎች ግትሮች ስለሆኑ እግዚአብሄር በወሰነው ደህንነት እንደሚያምኑ ይነግረናል፡፡ እነርሱ ዓመጸኞች ናቸው፡፡ ሐጢያተኞች ሁልጊዜም ዓመጸኞች የሚሆኑት ለዚህ ነው፡፡ 
 
ምንባቡ ይቀጥላል፡- ‹‹ርኩሱም ወደፊት ይርከስ፡፡›› ይህም ሐጢያተኞች ቢሆኑም ኢየሱስም በውሃውና በመንፈሱ ሐጢያቶቻቸውን ያስወገደ ቢሆንም ሐጢያቶቻቸውን በእምነት ለማንጻት ምንም አሳብ የሌላቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እነዚህን እምነተ ጎዶሎ ሰዎች ባሉበት ብቻቸውን ይተዋቸውና ይፈርድባቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ለሰዎች ሕሊናን በመስጠት በልባቸው ውስጥ ያለውን ሐጢያት በግልጽ እንዲያውቁ አስችሎዋቸዋል፡፡ ያም ሆኖ በልባቸው ውስጥ ያለውን ሐጢያት የማጽዳትም ሆነ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማወቅ አሳብ የላቸውም፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ሰዎች በማንነታቸው እንዲቀጥሉ እንደሚፈቅድላቸው ነግሮናል፡፡ 
 
ምሳሌ 30፡12 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለራሱ ንፁህ የሆነ የሚመስለው ከርኩሰቱ ያልጠራ ትውልድ አለ፡፡›› ዛሬ ሐይማኖተኛ የሆኑ ክርስቲያኖች ከሐጢያቶቻቸው መንጻት እንኳን የማይፈልጉ ሰዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ራሱ አምላክ የሆነው ኢየሱስ ሐጢያተኞችን ለማዳን ወደዚህ ምድር መጥቶ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ በጥምቀቱ በራሱ ላይ በመውሰድ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ አንጽቶ በስቅለት ለእነዚህ ሁሉ ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ ተኮነነ፡፡ በዚህም የምናምነውን ሰዎች በእርግጥም ከሐጢያት አዳነን፡፡ 
 
ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያተኞችን ያዳነበትን የውሃውንና የመንፈሱ ን ወንጌል ቃል የሚያውቅ ሁሉ ምንም ዓይነት ሐጢያተኛ ቢሆንም ጌታችን የሐጢያቶቹን ይቅርታ እንዲያገኝ ፈቅዶለታል፡፡ ሆኖም በእምነት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያላገኙ ሰዎች አሁንም ድረስ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሐጢያቶቻቸው ይነጹላቸው ዘንድ ሙከራ ላለማድረግ በራሳቸው የወሰኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሄርም ባሉበት እንዲሆኑ ይፈቅድላቸዋል፡፡ 
 
ይህም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለመፈጸም ነው፡፡ ይህም እግዚአብሄር የጽድቅ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ለዘላለም በዲን ወደሚቃጠል እሳት ይጣላሉ፡፡ ያን ጊዜ የጽድቅ አምላክ በትክክል ማን እንደሆነ ይገዘባሉ፡፡ እነርሱ ኢየሱስ አዳኛቸው እንደሆነ ቢናገሩም ሕሊናቸውን እያሳቱ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ሕሊና እያረከሱ ናቸው፡፡ እነርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስለናቁ እግዚአብሄርም እንደ ሥራቸው መጠን ይከፍላቸዋል፡፡ ቀኑ ሲመጣ እግዚአብሄር ቁጣው ለሚገባቸው ሰዎች ቁጣውን ያወረድባቸዋል፡፡ 
 
 
ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን መስጠት፡፡ 
 
በዚህ ምድር ላይ ሁለት ዓይነት ሰዎች ያሉ ሲሆን እነርሱም ጌታን የተገናኙና ያልተገናኙ ናቸው፡፡ ጌታችን ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን ይከፍለዋል፡፡ 
 
ማንም ሰው በራሱ ጥረት መጽደቅ አይችልም፡፡ ጽድቅ የሚመጣው ከኢየሱስ ነው፡፡ እርሱ በጥምቀቱ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በመስቀል ላይ ተሸክሞዋል፡፡ በመስቀል ላይም የሰው ዘር ሊጋፈጠው የሚገባውን የሐጢያት ፍርድ በሙሉ ተቀብሎዋል፡፡ የሰው ዘር በዚህ እውነት በማመን መጽደቅ ይችላል፡፡ በዚህ እውነት የሚያምኑ ጌታን የተገናኙ ሰዎች ናቸው፡፡ 
 
እግዚአብሄር ሐጢያት አልባ የሆኑትንና ይህንን እውነት አውቀው የሚያምኑትን ሰዎች በዚህ ምድር ላይ ወንጌልን እንዲሰብኩና በኑሮዋቸውም ቅዱስ ቃሉን እንዲጠብቁ ይጠይቃቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ‹‹ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ›› ይላል፡፡ ይህንን ትዕዛዝ በልባችን ውስጥ ማኖር፣ እምነታችንን መጠበቅና ሁልጊዜም እንከን የሌለበትን ወንጌል መስበክ አለብን፡፡ ለምን? ምክንያቱም በዚህ ዓለም ላይ የሚኖሩ እጅግ ብዙ ሰዎች ይህንን እውነተኛ ወንጌል ባለማወቃቸው እምነታቸው ተሳስቶዋልና፡፡ 
 
በዚህ ምድር ላይ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሒደት የሚሆነውን የቅድስና ትምህርት የሚደግፉ ሰዎች አሉ፡፡ ጌታችን ቀድሞውንም የሰውን ዘር ሐጢያቶች ያስወገደ ቢሆንም እነዚህ ሰዎች አሁንም ድረሰ በየቀኑ ለሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች ይቅርታን ለማግኘት ይፀልያሉ፡፡ በየቀኑም የንስሐ ፀሎቶቻቸውን በማቅረብ በመጨረሻ ዳግመኛ ምንም ሐጢያት የማይሰሩና ኢየሱስን የሚመስሉ ጻድቃን ይሆኑ ዘንድ ቀስ በቀስ እንዲቀደሱ ሐጢያቶቻቸውን ለማንጻት ይሞክራሉ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ንጉሥ፣ ነቢይና ካህን ነው፡፡ 
 
የእግዚአብሄር እውነተኛ ባሪያዎች እያንዳንዱ ሰው በእርግጥም የሐጢያት ይቅርታን አግኝቶ የመሆኑን ተግባራቸውን የሚፈጽሙ ብቻ ሳይሆኑ እያንዳንዱን ሰውም ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ ሰራተኛ ይሆን ዘንድ ወደ እውነት ይመሩታል፡፡ የእግዚአብሄር ባሮች በተጻፈው ቃል አማካይነት ሊመጡ ስላሉት ነገሮች ትክክለኛ እውቀት አላቸው፡፡
 
ቁጥር 12-13 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እነሆም በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ፡፡›› ጌታችን በእርግጥም አልፋና ዖሜጋ፣ መጀመሪያውና መጨረሻው፣ ፊተኛና ኋለኛ ነው፡፡ ጌታ የነገረንን ነገር ሁሉ በፍርሃት ማመን አለብን፡፡ 
 
ጌታችን ለቅዱሳን ከሥራቸው በሚልቁ ባርኮቶች ይባርካቸዋል፡፡ እርሱ የከበረና መሐሪ ነውና፡፡ እርሱ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነን ርህሩህና መሐሪ አምላክ ነው፡፡ የራዕይ ቃል እንደሚነግረንም የሐይልና የፍትህ አምላክ የደህንነት ሥራውን ይፈጽማል፡፡ ይህ በቅርቡ የሚሆነው የደህንነት ፍጻሜ ቅዱሳን ወደ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከተማ በክብር እንዲገቡ የሚፈቅድላቸውና ጌታችን ለሰሩዋቸው ሥራዎች በልግስናና በበቂ ሁኔታ የሚሰጣቸው ሽልማት ነው፡፡ 
 
 

ትዕዛዛቱን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፡፡ 

 
ቁጥር 14ን ስንቀጥል ዋናው ምንባብ እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው፡፡›› በዚህ ጥቅስ ላይ በመመርኮዝ ደህንነት የሚገኘው በምግባሮች ማለትም የእርሱን ትዕዛዛቶች በመጠበቅ ነው የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ 
 
ነገር ግን ‹‹የእርሱን ትዕዛዛት ማድረግ›› ማለት የተጻፈውን የእግዚአብሄር ቃል ሁሉ በእምነት ማመንና መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ ጽዋፎዋል፡- ‹‹ትዕዛዚቱም ይህች ናት፤ እርሱ ትዕዛዝን እንደሰጠን በልጁ በኢየሱስ ስም ልናምንና እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 3፡23) ስለዚህ በእውነተኛው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ስናምንና በመላው ዓለም ላይ ያሉትን የጠፉ ነፍሳቶች ሁሉ ለመስበክ ራሳችንን ለወንጌል ስብከት ቀድሰን ስንሰጥ በፊቱ ትዕዛዙን እያደረግን ነው፡፡ 
እውነቱ በሕይወት ዘመናችን የምንፈጽማቸው ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ቀድሞውኑም የተደመሰሱ መሆናቸው ነው፡፡ ከዚህ ጥምቀት በኋላ ጌታችን በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ፣ ትንሳኤውና ዕርገቱ ዳግመኛ እንድንወለድ አድርጎናል፡፡ በእርሱ እውነትም አዲስ ሕይወትን እንድንኖር ፈቅዶልናል፡፡ 
 
ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ በሐጢያት በምንወድቀበት ጊዜ ሁሉ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ወዳነጻን የእውነት ቃል መመለስ፣ የዘር ግንዶቻችንም ሐጢያተኞች በመሆናቸው ሐጢያት መስራትን ማቆም እንደማንችል መገንዘብና ጌታችን ድክመቶቻችንን፣ ጉድለቶቻችንንና ሐጢያቶቻችንን ወደወሰደበት፣ ከኢየሱስ ጥምቀት ጋር አብረን ወደተጠመቅንበት፣ በመስቀል ላይ ከሞተው ከክርስቶስ ጋርም አብረን ወደተቀበርንበት የዮርዳኖስ ወንዝ በእምነት መመለስ አለብን፡፡ ይህንን ስናደርግ በመጨረሻ ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ ከሰራናቸው ሐጢያቶች ነጻ መውጣትና ንፁህ መሆን አንችላለን፡፡ ዘላለማዊ የሆነውን የስርየት ደህንነታችንን ደግመን በማጽናትና ዘላቂና ፍጹም ስለሆነው ደህንነቱም እርሱን በማመስገን የእግዚአብሄርን ጽድቅ አጥብቀን እንያዝ፡፡ 
 
ኢየሱስ ቀድሞውኑም የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ አንጽቶዋል፡፡ ችግሩ ያለው ሕሊናችን ውስጥ ነው፡፡ ጌታችን የዓለምን ሐጢያቶች አስቀድሞ በጥምቀቱ ቢወስድም እኛ ሰዎች ጌታ በጥምቀቱና በስቅለቱ ሐጢያቶቸችንን በሙሉ መወሰዱን ባለመገንዘባችን፣ ሐጢያተኞች በመሆናችን ሕሊናችን ይታወካል፡፡ ስለዚህ በውስጣችን የቀረ ሐጢያት እንዳለ ወደ ማሰቡ እናዘነብላለን፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን እኛ ማድረግ የሚኖርብን ነገር ቢኖር ሐጢያቶቻችን በሙሉ ቀድሞውኑም ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል አማካይነት በተጨባጭ መወገዳቸውን ማመን ብቻ ነው፡፡ 
 
ልባችን በሐጢያቶቻችን ከተጎዳ የእነዚህን ሐጢያቶች ቁስሎች መፈወስ የምንችለው በየትኛው እውነት ነው? 
 
እነዚህ ቁስሎች ሊፈወሱ የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ማለትም ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች እንደወሰደ፣ እነዚህን ሐጢያቶችም በቀራንዮ መስቀል ላይ በመሸከም እንዳስወገዳቸውና በዚያም ደሙን እንዳፈሰሰ በማመን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የሐጢያት ስርየትን ከተቀበልን በኋላ የምንፈጽማቸው የምግባር ሐጢያቶቻችን ሊነጹ የሚችሉት ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን የምግባር ሐጢያቶቻችንን ጨምሮ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አስቀድሞ ባነጻበት ወንጌል ያለንን እምነታችንን ደግመን በማረጋገጥ ነው፡፡ 
ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀና በተሰቀለ ጊዜ የዚህ ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ ተወግደዋል፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓለም ሐጢያቶችም ሆኑ በግል የምንሰራቸው ሐጢያቶች በየጊዜው መንጻት ያለባቸው ይመስል ሁለቴ ወይም ሦስቴ መንጻት አያስፈልጋቸውም፡፡ የሐጢያት ስርየት የሚገኘው ጥቂት በጥቂት ነው ብሎ የሚያስተምር ሰው ካለ የሚሰብከው ወንጌል የሐሰት ወንጌል ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ አስወግዶዋል፡፡ ዕብራውያን 9፡27 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ለሰዎች አንድ ጊዜ ሞት ከዚያ በኋላም ፍርድ እንደተመደበባቸው፡፡›› በሐጢያት ምክንያት እንደምንሞት ሁሉ የሐጢያትንም ስርየት አንድ ጊዜ እንቀበል ዘንድ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ በአንድ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ አንድ ጊዜም ሞተ፡፡ በእኛ ምትክም አንድ ጊዜ ሞተ፡፡ እነዚህን ነገሮች ብዙ ጊዜ አላደረገም፡፡ 
 
ከልባችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሐጢያት ስርየትን ስንቀበል በአንድ ጊዜ ማመንና የሐጢያቶቻችንን ዘላለማዊ ስርየት መቀበላችን ትክክል ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የምንሰራቸው ሐጢያቶች በየጊዜው ልባችንን ስለሚያቆስሉት ማድረግ የሚኖርብን ነገር ቢኖር ጌታችን ሐጢያቶችንን በሙሉ በአንድ ጊዜ እንዳስወገደ፣ በእምነትም የረከሰውን ልባችንን እንዳነጻና እንደፈወሰ ወደሚናገረው የደህንነት ቃል መቅረብ ነው፡፡ ‹‹አቤቱ እኔ በጉድለቶች የተሞላሁ ነኝ፡፡ ደግሜ ሐጢያት ሰርቻለሁ፡፡ እንደ ፈቃድህ የጽድቅ ሕይወትን መኖር አልቻልሁም፡፡ ነገር ግን በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ በተጠመቅህና በመስቀል ላይ በደማህ ጊዜ እነዚህን የእኔን ሐጢያቶች በሙሉ አላስወገድህምን? ሐሌሉያ! ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ!›› 
 
በዚህ ዓይነት እምነት የሐጢያት ስርየታችንን እንደገና ማረጋገጥና ጌታን ሁልጊዜ ማመስገን እንችላለን፡፡ ይህ የመጨረሻው የራዕይ ምዕራፍ የሕይወት ዛፍ ወደሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅረብና ጌታም አስቀድሞ የዓለምን ሐጢያቶች እንዳነጻ በማመን የሐጢያት ስርየትን ያገኙ ሰዎች በእምነታቸው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ወደ ቅድስት ከተማ የመግባትን መብት እንዳገኙ ይነግረናል፡፡ 
 
ወደ እግዚአብሄር ከተማ መግባት የሚፈልግ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ የሰውን ዘር ሐጢያቶች ለዘላለም እንዳስተሰረየ ማመን አለበት፡፡ ሁላችንም ብዙ ጉድለቶች ቢኖሩብንም በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና ደም በማመን እምነታችን በእግዚአብሄር ዘንድ እውነተኛ መሆኑ ይረጋገጣል፡፡ እኛም ሁላችን ወደ ሕይወት ዛፍ መድረስ እንችላለን፡፡ 
 
በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ከሚፈስሰው የሕይወት ውሃ የመጠጣትና ወደ ሕይወት ዛፍ ፍሬዎች የመድረስ መብት ሊኖረን የሚችለው በክርስቶስ ጥምቀትና ደም በማመን ብቻ ነው፡፡ በማንም ሰው ሊወሰድ ከቶ የማይፈቀደው ወደ አዲስ ሰማይና ምድር የመግባት መስፈርት የሚመጣው ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ብቻ በመሆኑ እምነታችንን መጠበቅና ለብዙ ሌሎች ሰዎችም ይህንኑ መስበክ አለብን፡፡ ‹‹ትዕዛዛቱን የሚያደርጉ›› የሚለው ሐረግ ዓለምን በእምነት ማሸነፍ አለብን ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመንና እርሱን መጠበቅ እውነተኛውንም ወንጌል ለመላው ዓለም ለመስበክ ራሳችንን ቀድሰን መስጠት ማለት ነው፡፡
 
በማቴዎስ 22 ላይ ኢየሱስ ‹‹የሰርጉን ድግስ ምሳሌ›› ነገሮናል፡፡ የዚህ ምሳሌ ድምዳሜ የሰርግ ልብሳቸውን ያልለበሱ በውጭ ወዳለው ጨለማ መጣል የሚገባቸው መሆኑ ነው፡፡ (ማቴዎስ 22፡11-13) በበጉ ሰርግ እራት ላይ ለመገኘት የሰርግ ልብሳችንን መልበስ የምንችለው እንዴት ነው? የሰርጉስ ልብስ ምንድነው? ወደ በጉ ሰርግ እራት እንድንገባ የሚያስችለን የሰርጉ ልብስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የተሰጠን የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ታምናላችሁን? እንደዚያ ከሆነ ያን ጊዜ የልጁ ሐጢያት አልባ ሙሽሪት ሆናችሁ ሰማይ መግባት ትችሉ ዘንድ ያማረውን የእርሱን ጽድቅ ትለብሳላችሁ፡፡ 
 
እኛመ ዳግመኛ የተወለድን በየቀኑ ሐጢያትን እንሰራለን፡፡ ነገር ግን በየቀኑ የሚሰሩዋቸውን ሐጢያቶች በእምነት ከጽድቅ ልብሳቸው ላይ ለማንጻት ብቃት ያላቸው በእግዚአብሄር ፊት የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ያገኙና ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ያላገኙ ሰዎች ሐጢያቶቻቸውን ለማንጻት ብቃት ስለሌላቸው በሚያቀርቡዋቸው የንስሐ ጸሎቶች ራሳቸውን ከሐጢያቶቻቸው ፈጸሞ ማንጻት አይችሉም፡፡ ጌታን በማመን ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ መዳን የቻልነው ጌታ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በመጠመቅና ደሙን በማፍሰስ የዓለም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በማንጻቱ ነው፡፡ 
 
በሌላ አነጋገር በየቀኑ የምንሰራቸው ሐጢያቶቻችን ቀድሞውኑም በእርሱ እውነተኛ ወንጌል ብቻ እንደነጹ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ በውሃውና በደሙ ቃል አማካይነት ከጌታ ዘንድ የሐጢያት ስርየትን ያገኙ በሕይወት መኖራቸውን እየቀጠሉ ሲሄዱ ከሚፈጽሙዋቸው ሐጢያቶች ለመዳናቸው ማረጋገጫ ይኖራቸዋል፡፡ 
 
እኛ በዚህ የዘላለም ስርየት ደህንነት በማመን በድርጊቶቻችን የምንፈጽማቸውን ሐጢያቶች በሙሉ ማንጻት የምንችለው ጌታችን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በአንድ ጊዜ ባያስወግድ ኖሮ እንዴት ሐጢያት አልባ መሆን እንችል ነበር? 
 
እንዴትስ በሰማይ ወዳለችው ቅድስት ከተማ መግባት እንችል ነበር? የሕይወት ዛፍ ወደሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት መቅረብ ይቻለን ነበር? ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ባስወገደው በጌታችን በማመን ንፁህና ነቁጥ የሌለብን ሰዎች ሆነን መንግሥተ ሰማይ መግባት እንችላለን፡፡ በሕይወታችን ሐጢያት ስንሰራም በጌታችን ፊት ቀርበን እርሱ እነዚህን ሐጢያቶች እንዳስወገደ በማረጋገጥ ከእነዚህ ሐጢያቶች ሁሉ ነጻ መውጣት እንችላለን፡፡ በየቀኑ የሚሰሩዋቸው ሐጢያቶች በእምነት ይቅርታን ለማግኘት የታደሉት ጻድቃን ብቻ እንደሆኑ የምንግራችሁ ለዚህ ነው፡፡ 
 
ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሄር ባርያ ቢሆንም በእግዚአብሄር ፊት ታላላቅ ሐጢያቶችን ፈጽሞዋል፡፡ ትዳር ከነበራት ሴት ጋር አመንዝሮዋል፡፡ የእርሱ ታማኝ አገልጋይ የነበረውን ባልዋንም ገድሎዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን በምህረት ስለተሞላው ይቅርታው እንዲህ በማለት አመሰገነው፡- 
‹‹መተላለፉ የቀረችለት
ሐጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው፡፡
እግዚአብሄር በደልን የማይቆጥርበት
በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው
ምስጉን ነው፡፡›› (መዝሙረ ዳዊት 32፡1-2) 
 
በዚህ ዓለም ላይና በእግዚአብሄር ፊት እጅግ ምስጉን ማነው? ምስጉኖቹ ሌሎች ሳይሆኑ ዳግመኛ የተወለድነው፣ የዳንነውና በሕይወታችን ሐጢያት በምንሰራበት ጊዜ ጌታ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የማስወገዱን እውነታ የምንመለከት፣ በየቀኑም ወደ ሕይወት ምንጭ የምንሄድና በየቀኑም የረከሰውን ልባችንን የምናነጻ ነን፡፡ ይህም ደህንነታችንን ማሰብና የጌታችንን ታላቅ የደህንነት ጸጋ ማረጋገጥ ነው፡፡ 
 
የሐጢያት ስርየትን ተቀብለው ጉድለቶቻቸውን በሙሉ የሚያስወግዱ ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ ምግባሮቻቸው ምሉዕ ናቸው፡፡ ልባቸውም እንደዚሁ ምሉዕ ነው፡፡ እንዲህ ነቁጥ የሌለብን ጻድቃን ከሆንን በኋላ እግዚአብሄር ወዳዘጋጀልን መንግስት ሰማይ መግባት እንችላለን፡፡ የደህንነት በርና የሕይወት ዛፍ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ያደረገውን ነገር ብቻ ብንቀበል ሐይሉ ይገለጣል፡፡ ስለዚህ እኛም የሐጢያት ስርየትን አግኝተን ሰማይ እንገባለን፡፡ 
 
 

ወደ ሕይወት ዛፍ የሚደርሱ፡፡ 

 
የሐጢያት ስርየትን የተቀበልን ሰዎች ሁልጊዜ በጌታ ፊት የምንቀርበው ሁላችንም ወደ እርሱ መንግሥት መግባት እንችል ዘንድ ጌታችን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዳስወገደ ለማረጋገጥ፣ እንደገና የደህንነትን ጸጋ ለማሰላሰል፣ ለማስታወስና ለዚህም ደግሞ እግዚአብሄርን ለማመስገን ነው፡፡ ወንጌልን የምንሰብከው ለዚህ ነው፡፡ 
 
በርካታ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል በማስተማር ሊመሩዋቸው የሚችሉትን የእግዚአብሄር አገልጋዮች ማግኘት ባለመቻላቸው ቃሉን በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል፡፡ የተሳሳቱ እምነቶችም ይዘዋል፡፡ አሁንም እንኳን በምግባሮቻቸው ተጠፍረው በየማለዳውና በየምሽቱ የንስሐ ጸሎቶችን የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት ለምንድነው? እንዲህ በማድረግ ሐጢያቶቻቸው ይቅር እንደሚባሉ ስለሚያምኑ ነው፡፡ እንዲህ የሚያምኑትም የተሳሳቱ ትምህርቶችን ስለተማሩ ነው፡፡ እነዚህ ግን በእግዚአብሄር ፊት የዓመጽ ምግባሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅም ሆነ የእርሱን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ፍቅር የማያውቁ ምስኪኖች ናቸው፡፡ 
 
መጽሐፍ ቅዱስ ማንም ሰው እንደፈለገው በፈለገው መንገድ ሊተረጉመው የሚችል በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ ሆኖም ሰዎች በራሳቸው ሰው ሰራሽ አስተሳሰቦች ላይ ተመርኩዘው ስለተረጎሙት፣ ስላስተማሩትና ስላመኑት ውጤቱ ከላይ የተጠቀሰው ሆንዋል ማለትም እነርሱ የእግዚብሄርን ጽድቅና ፍቅር የማያውቁ ሰዎች ሆኑ፡፡ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ትክክለኛ ፍቺ አለው፡፡ ይህም በትክክል ሊተረጎም የሚችለው የሐጢያቶችን ስርየት ባገኙ የእግዚአብሄር ነቢያት ብቻ ነው፡፡ 
 
ለእኛ ወደ ሕይወት ዛፍ መድረስ ማለት በዚህ ምድር ላይ ሳለን በጌታ ማመን ጌታችን ሐጢያቶቻችንን እንዳስወገደ በየቀኑ ማስታወስ፣ እርሱን ማመስገንና ይህንን ወንጌል መስበክ ነው፡፡ እኛ ዳግመኛ የተወለድን፣ እርሱ በራሱ ላይ ሐጢያቶቻችንን መውሰዱን ማስታወስ፣ ይህንን እውነትም በየቀኑ ማረጋገጥ፣ በምስጋና ደስታም ለእርሱ መስገድና በጌታችን ለእርሱ መስገድና ጌታችን ፊት መቅረብ ይኖርብናል፡፡
 
በመላው ዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ይህንን ምንባብ በተሳሳተ መንገድ እንደተረጎሙትና በየቀኑ በሚያቀርቡዋቸው የንስሐ ጸሎቶችም ሐጢያቶቻቸውን በማንጻት ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንደሚገቡ በተሳሳተ መንገድ እንዳመኑ መናገሩ ማጋነን አይደለም፡፡ ምንባቡ ግን ይህንን አይልም፡፡ 
 
የሐጢያት ስርየትን ከተቀበልን በኋላ ልባችን ሰላም የሚሆነው ጌታችን በምግባሮቻችን የሰራናቸውን ሐጢያቶች በሙሉ እንዳስወገዳቸው ስናረጋግጥ ነው፡፡ የሐጢያቶቻችንን ሁሉ ስርየት ስናረጋግጥ ከእንግዲህ ወዲያ በሐጢያት አንታሰረም፡፡ በሰማይ ወዳለው የሕይወት ዛፍ ለመድረስ መንገዱ ይህ ነው፡፡ 
 
መጽሐፍ ቅዱስ ከሰው ሰራሽ አስተሳሰቦች ሙሉ በሙሉ የተለየ ደርዝ አለው፡፡ ስለዚህ እውነትን ለማወቅ በመጀመሪያ ዳግመኛ ከተወለዱ የእግዚአብሄር አገልጋዮች እውነቱን መማርና መስማት ይገባናል፡፡ 
 
 
ከከተማይቱ ውጭ ያሉ፡፡ 
 
ቁጥር 15 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ውሻዎችና አስማተኞች፣ ሴሰኛዎችም፣ ነፍሰ ገዳዮችም፣ ጣዖትንም የሚያመልኩት፣ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ፡፡›› ይህ ቃል በመጨረሻው ዘመን ላይ ዳግመኛ ያልተወለዱትን ሁሉ ይመለከታል፡፡ ጌታችን እነዚህን ሰዎች እንዲህ ባለ ትክክለኛነት መግለጡ በአጭሩ አስገራሚ ነው፡፡ 
 
ከውሾች ባህርይ አንዱ ትውከታቸው ነው፡፡ የበሉትን ያስታውካሉ፡፡ እንደገናም ይበሉታል፡፡ ደግመውም ይተፉታል፡፡ ከዚያም ያስታወኩትን መልሰው ይበሉታል፡፡ ጌታችን እዚህ ላይ እነዚህ ‹‹ውሾች›› ወደ ከተማይቱ መግባት እንደማይችሉ ይናገራል፡፡ 
 
ታዲያ እነዚህ ውሾች የሚያመለክቱት ማንን ነው? ‹‹አቤቱ እኔ ሐጢያተኛ ነኝ፤ እባክህ ሐጢያቶቼን አንጻቸው›› ብለው የሚጮሁና ከዚያም ‹‹እኔ ይቅር ተብያለሁ፤ አንተም ይቅር ተብለሃል፤ ሁላችንም ይቅር ተብለናል!›› እያሉ በመዘመር እግዚአብሄርን የሚመሰግኑ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን በቀጣዩ ቅጽበት እነዚሁ ሰዎች እንደገና ‹‹አቤቱ እኔ ሐጢያተኛ ነኝ፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ ይቅር ብትለኝ ዳግመኛ ፈጽሞ አልሰራም›› ብለው ይጮሃሉ፡፡ ከዚያም እንደገና ‹‹በቀራንዮ ደም ይቅር ተብያለሁ›› ብለው ይዘምራሉ፡፡ 
 
እነዚህ ሰዎች አብዝተው ስለሚንቀዠቀዡ ይቅርታን አግኝተው ይሁን ወይም አይሁን ማንም እርግጠኛ አይሆንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ውሾች›› የሚላቸው እነዚህን ዓይነት ሰዎች ነው፡፡ ውሾች ሁልጊዜም ይጮሃሉ፡፡ በማለዳ ይጮሃሉ፡፡ በቀትር ይጮሃሉ፡፡ በምሽትም ይጮሃሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በትክክል በዚህ መንገድ ባይጮሁም የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ አግኝተውም እንኳን ሐጢያተኞች ስለመሆናቸው ይጮሃሉ፡፡ አንዴ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ወዲያው ደግሞ ሐጢያተኞች ይሆናሉ፡፡ 
 
በዚህ ሁኔታ ከውስጥ ያለውን የሚያስታውኩና ያንኑ ደግመው የሚውጡ ከዚያም እንደገና ያንኑ የሚያስታውኩና ያንኑ ደግመው የሚውጡ ውሾችን ይመስላሉ፡፡ በአጭሩ መጽሐፍ ቅዱስ ገናም በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸው ክርስቲያኖች ‹‹ውሾች›› መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ እነዚህ ውሾች ከከተማይቱ በስተ ውጭ ይቀራሉ እንጂ ፈጽሞ ሰማይ መግባት አይችሉም፡፡ 
 
ቀጥሎ ‹‹አስማተኞች›› እነማን ናቸው? እነዚህ ምስኪን የሆኑ የቤተክርስቲያን አዘውታሪዎችን ስሜቶች በመጠቀም በጣፋጭ ንግግራቸው ገንዘባቸውን የሚዘርፉና በሽታዎቻቸውን እንደሚፈውሱ በመናገር ሰዎችን በሐሰት ምልክቶችና ተዓምራቶች የሚያስቱ ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ የእግዚአብሄርን ስም በከንቱ ስለሚጠሩ ወደ ቅድስት ከተማ ሊገቡ አይችሉም፡፡ 
 
ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎችና ውሸትን የሚወድና የሚያደርግ ማንኛውም ሰው ወደ ከተማይቱ መግባት አይችሉም፡፡ የመጨረሻው ዘመን ሲመጣ ውሾችና አስማተኞች ሰዎችን ያስታሉ፡፡ ጸረ ክርስቶስም ይገለጣል፡፡ በሐሰት ምልክቶችና ተዓምራቶች ብዙ ሰዎችን የሚያስተው፣ ነፍሳቸውን የሚሰርቀው፣ እግዚአብሄርን የሚቃወመውና ራሱን ከእግዚአብሄር በላይ ከፍ ለማድረግና ለመመለክ የሚሻው ጸረ ክርስቶስና የእርሱ ተከታዮች በሙሉ ፈጽሞ ወደ ከተማይቱ መግባት አይችሉም፡፡ 
 
ስለዚህ አሁንም ድረስ ሐጢያት እንዳለብን በሚናገሩ ሰዎች ማታለያ ውስጥ ከወደቅን ወይም ስሜቶቻችንን በሚያነሳሱ የምልክቶችና የተዓምራቶች ማታለያ ውስጥ ከወደቅን የሁላችንም መጨረሻ ከጸረ ክርስቶስና ከሰይጣን ጋር ከከተማይቱ ውጭ ሆኖ ቃሉ እንደሚያስጠንቀን ልቅሶና ጥርሳችንን ማፋጨት ይሆናል፡፡ 
 
ቁጥር 16-17 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ፡፡ እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፡፡ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ፡፡ መንፈሱና ሙሽራይቱም ና ይላሉ፡፡ የሚሰማም ና ይበል፡፡ የተጠማም ይምጣ፤ የወደደም የሕይወትን ውሃ እንዲያው ይወስድ፡፡›› 
 
የሐጢያት ስርየታችሁን በነጻ ተቀብላችኋልን? ጌታችን በመንፈስ ቅዱስና በአምላክ ቤተክርስቲያን አማካይነት የሕይወትን ውሃ እንድንጠጣ የሚያስችለንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚራብ፣ የእውነትን ቃል የሚጠማና የሐጢያትን ስርየት ፈጽሞ መቀበል የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እግዚአብሄር ምህረቱን ያለብሰዋል፡፡ ደህንነት የሚሰጠውን የሕይወት ውሃ ቃሉን እንዲቀበሉ ግብዣውን አቅርቦዋል፡፡ የሕይወት ውሃ ወደሚፈስስበት አዲስ ሰማይና ምድር ለመግባት ለቀረበው ግብዣ ምላሽ የሚሰጥበት ብቸኛው መንገድ የሐጢያትን ስርየት መቀበል ነው፡፡ 
 
 
አሜን ጌታ ኢየሱስ ና! 
 
ቁጥር 19 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ማንም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት መጽሐፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሄርን ዕድሉን ያጎድልበታል፡፡›› በእግዚአብሄር ፊት በራሳችን አስተሳሰቦች ላይ ተመስርተን የምንሻወን ማንኛውንም ነገር ማመን አንችልም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ተጽፎ ከሆነ እኛ ማለት የሚኖርብን ነገር ‹‹አዎ›› ነው፡፡ ምክንያቱም ለቃሉ ‹‹አይሆንም›› የሚል ሰው ቢኖር ጌታችንም ‹‹አንተ ልጄ አይደለህም›› በማለት ያገልለዋል፡፡ በቃሉ መሰረት በእርሱ ማመን የሚገባን ለዚህ ነው፡፡ በማናቸውም የእግዚአብሄር ቃል ላይ መጨመርም ሆነ ከእርሱ መቀነስ አንችልም፡፡ ነገር ግን ልክ እንደተጻፈው ማመን አለብን፡፡ 
 
እውነተኛ እምነት የእግዚአብሄርን አገልጋዮች ማክበርና መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በኩል የሚናገረውን ማመን ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከእምነታቸው ስላስወገዱ አሁንም ድረስ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት አለ፡፡ ቃሉ ወደ እግዚአብሄር ቅድስት ከተማ መግባት የሚችሉት ሐጢያ አልባ የሆኑት ብቻ እንደሆኑ በተደጋጋሚ ቢነግራቸውም አሁንም ድረስ የኢየሱስን ጥምቀት ከእምነታቸው አስወግደው በቃሉ ላይ የንስሐ ጸሎቶችንና ቁሳዊ ስጦታዎችን የመሳሰሉ ምግባሮች በመጨመር ከርረዋል፡፡ 
 
ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው የሚያምኑ ሰዎች የሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ በእምነታቸው መመስከር መቻል አለባቸው፡፡ የኢየሱስን ጥምቀት ከገደፋችሁ በመሰረታዊነት እምነታችሁን እየተዋችሁ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማታምኑ ከሆናችሁ የመስቀሉ ላይ ደም እንኳን ትርጉም የለውም፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤም እንደዚሁ ዋጋ የለውም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ትርጉም ያለው የሚሆንላቸው እግዚአብሄር ሐጢያቶቻቸውን እንዲያው እንዳስወገደላቸው የሚያምኑ ብቻ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ በቁጥር 20 ላይ እንዳደረገው የጌታ ኢየሱስን ምጽዓት ጮክ ብለው ማወጅ የሚችሉት እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ 
 
ቁጥር 20 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህን የሚመሰክር አዎን በቶሎ እመጣለሁ ይላል፡፡ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና፡፡›› ይህንን ማለት የሚችሉት ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ ጌታችን በጻድቃን ጸሎት መሰረት ፈጥኖ ወደዚህ ምድር ይመጣል፡፡ ፈጥኖ በሚመጣው በጌታ የሚደሰቱና ያንንም በጉጉት የሚጠብቁ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ፍጹም የሆነውን የሐጢያት ስርየት የተቀበሉ ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ጌታን ለመቀበል የተዘጋጁት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ልብስ የለበሱ ማለትም ሐጢያት የሌለባቸው ብቻ ስለሆኑ ነው፡፡ 
 
ጌታችን ለጻድቃን ጥበቃ ምላሽ የሚሰጥበትን፣ ወደዚህ ምድር የሚመጣበትን ቀን እየጠበቀ ነው፡፡ እርሱ የሺህ ዓመት መንግስቱን ይሰጠናል፡፡ ጻድቃን የሆንነውንም የሕይወት ውሃ ወደሚፈስስበት አዲስ ሰማይና ምድር የምንገባባቸውን ታላላቅ በረከቶች በመስጠት ያለብሰናል፡፡ ጌታችን ለረጅም ጊዜ አይቆይም፡፡ ስለዚህ እኛ ማድረግ የምንችለው ነገር ‹‹አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና›› ማለት ብቻ ነው፡፡ የጌታችንን መምጣትም በእምነትና በምስጋና ከልባችን እንናፍቃለን፡፡ 
 
በመጨረሻም ቁጥር 21 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን፡፡›› ሐዋርያው ዮሐንስ የራዕይን መጽሐፍ ያጠናቀቀው ለእያንዳንዱ ሰው የመጨረሻውን የቡራኬ ጸሎት በማቅረብ ነው፡፡ እርሱ በልቡ እያንዳንዱ ሰው በኢየሱስ አምኖ በመዳን ወደ እግዚአብሄር ከተማ እንዲገባ ተስፋ በማድረግ መጨረሻ ላይ የቡራኬ ጸሎቱን አሳረገ፡፡ 
 
ውድ ቅዱሳኖቼ እግዚአብሄር ስለወደደን አዳነን፡፡ ከሐጢያቶቻችንም ሁሉ ነጻ አወጣን፡፡ የራሱ ሕዝብም አደረገን፡፡ እግዚአብሄር ወደ መንግሥቱ እንገባ ዘንድ እኛን ጻድቃን ማድረጉ ድንቅና የሚወደስ ነው፡፡ 
 
መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ የነገረን መሰረታዊ ነገር ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛን በመንግሥቱ ውስጥ ለዘላለም ሊያኖረን ይህንን እውነተኛ ወንጌል በመስማት ዳግመኛ እንድንወለድ ፈቀደልን፡፡ ከሐጢያቶቻችንና ከፍርድ ሁሉም ነጻ አወጣን፡፡ ስለ ማዳኑ ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ አወድሰውማለሁ፡፡ 
 
የሐጢያቶቻችንን ስርየት በሰላም መቀበላችን አስደሳች ነው፡፡ እኛ ሁላችን በአያሌው በእግዚአብሄር የተባረክን ሰዎች ነን፡፡ የእርሱ ነቢያቶችም ነን፡፡ ስለዚህ የሐጢያት ስርየት የሚያስገኘውን ወንጌል ገና ይህንን ወንጌል ላልሰሙት ሁሉ ማሰራጨትና የወንጌል ፍጻሜ የሆነውንም የራዕይን ቃል ልንሰብክላቸው ይገባናል፡፡ 
 
ሁሉም ፈጣሪ፣ አዳኝና ፈራጅ በሆነው በኢየሱስ እንዲያምንና የመጨረሻው ዘመን ሲመጣም ጌታ ወደሰጠው የአዲስ ሰማይና ምድር የተቀደሰ ስፍራ እንዲገባ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እጸልያለሁም፡፡ የጌታችን የኢየሡስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡