Search

በክርስቲያን እምነት ላይ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤

ርዕስ 1፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ፤

1-32. በአንተ አባባል መሰረት ኢየሱስ ያለፉትን አሁን ያሉትንና ወደፊት ሐጢያቶችን በሙሉ ቀድሞውኑም አስወግዶዋል ካልን በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል በማመን ቀድሞውኑም ሐጢያቶቹ ይቅር የተባሉ የመሆኑን እውነታ በማሰብ ያለ ማቋረጥ ሐጢያትን ቢሰራ የግለሰቡ ዕጣ ፈንታ እንዴት ይሆናል? ይህ ሰው ሌላ ሰው ቢገድል እንኳን በኢየሱስ አማካይነት በመስቀል ላይ ለዚህ አይነቱ ሐጢያትም እንኳን ይቅርታን እንዳገኘ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ወደፊት የሚሰራቸውን እነዚህን ሐጢያቶች ቀድሞውኑም እንዳስወገደለት በማመን ያለ ምንም ማመንታት ሐጢያት በመስራት ይቀጥላል፡፡ እባክህ እነዚህን ነገሮች አብራራልኝ፡፡ 

በመጀመሪያ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ጥያቄዎችን ስላነሳህ አመሰግንሃለሁ፡፡ ያነሳሃቸው ጥያቄዎች ብዙ ክርስቲያኖች ዳግም ከመወለዳቸው በፊት የጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ዳግም የተወለደ ሰው ፍጹም በሆነው ወንጌል ተመቻችቶ ያለማቋረጥ ሐጢያት ይሰራል ብለህ እንደምትጨነቅ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች አንተ የምትጨነቅለትን እንደዚህ ያለውን ሕይወት ወደ መኖር እንደማያዘነብሉ ነገር ግን በምትኩ የጽድቅ ሕይወትን እንደሚኖሩ ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡ 
በመጀመሪያ ስለዚህ ነገር ልታስብ ይገባሃል፡፡ በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ካለ እንደዚያ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን የተቀደሱ ፍሬዎችን ታፈራለህ፡፡ በሌላ በኩል መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ከሌለ ምንም ያህል ጠንክረህ ብትሞክርም አንዳች የመንፈስ ፍሬዎችን ማፍራት አትችልም፡፡ ሰው በኢየሱስ ቢያምንም እንኳን በልቡ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከሌለው እንዴት የመንፈስን ፍሬዎች ማፍራት ይቻለዋል? ይህ የማይቻል ነው፡፡ ጌታ ክፉ ዛፍ በፍጹም መልካም ፍሬዎችን ሊያፈራ እንደማይችል ተናግሮዋል፡፡ (ማቴዎስ 7፡17-18) 
አሁን ይህንን ጥያቄ ልጠይቅህና አንተም መልሱን ልትሰጠኝ እፈልጋለሁ፡፡ አንተ በኢየሱስ ታምናለህ፡፡ ነገር ግን ሕይወትህን የምትኖረው በእርግጥ አለማዊ ሐጢያቶችን አሸንፈህ ነው? አለማዊ ሐጢያቶችን እያሸነፍህ፣ ጌታን አብዝተህ እያገለገልህና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለእነርሱ በማቅረብ ሌሎች ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንዲድኑ በመፍቀድ ጻድቅ የእግዚአብሄር አገልጋይ ሆነህ እየኖርህ ነውን? ለዚህ ጥያቄ አዎ የሚል መልስ እንድትሰጥ የሚፈቅድልህ ብቸኛ እምነትና ወንጌል ጌታ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ውስጥ የመሰከረለት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ 
በኢየሱስ ካመንን በኋላ እንኳን በዓለም ላይ ሐጢያት መስራት እንቀጥላለን፡፡ ሆኖም ጌታችን ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ እኛን ለማዳን በዮሐንስ ተጠምቆ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶዋል፡፡ ስለዚህ ጌታ ለእኛ የጽድቅ ሥራን ሰርቶልናል፡፡ እኛም ሐጢያቶቻችንን ባስወገደው በእግዚአብሄር ጽድቅ፣ በጌታ ጥምቀትና ደም አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ድነናል፡፡ 
እንደገና አንዳንድ ጥያቄዎችን ልጠይቅህ እፈልጋለሁ፡፡ ከሕሊናህ ሐጢያቶች ነጻ ነህን? ከዚህ ቀደም በእርሱ ታምን እንደነበረው ሁሉ በኢየሱስ ካመንህ በኋላ እንኳን ሐጢያተኛ አልነበርክምን? ይህ እውነት ከሆነ ለዚህ ምክንያቱ ምናልባትም ስለ ውሃውና ስለ መንፈሱ ወንጌል አለማወቅህ ነው፡፡ ስለዚህ በልብህ ውስጥ መንፈስ ባለመኖሩ ከሥጋ በተወረሱ ችግሮችና ውዥንብሮች ውስጥ ወድቀሃል፡፡ ምንም ያህል የታመንህ ምዕመን ብትሆንም ከሥጋ አስተሳሰቦች ማምለጥ የምትችለው ልብህን ባዶ በማድረግና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመውሰድ ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነት የመሆኑን ሐቅ ለመረዳት ሥጋዊ አስተሳሰቦችን መጣልና ወደተጻፉት የእግዚአብሄር ቃሎች መመለስ ይገባሃል፡፡
በዚህ ዓለም ላይ ጌታን በአንደበታቸው ቢጠሩትም ጌታ የደነገገውን የደህንነት ሕግ በፈለጉት በማንኛውም መንገድ የሚለውጡ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ አንተ ከእነዚህ አይነት ሰዎች አንዱ ከሆንህ ጌታ በመጨረሻው ቀን ይተውሃል፡፡ አንተ ሊያድንህ የሚችለው ብቸኛው ነገር ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም እንደሆነ የማታምንና ጥያቄዎችንም የጠየቅኸው ቀሪ የሕይወት ዘመንህን ከሐጢያት ተላቀህ ለመኖር ካለህ ፍላጎት ከመነሳት ይሆን ዘንድ እጸልያለሁ፡፡
ሆኖም አስተሳሰቦችህ ‹‹ለእግዚአብሄር ሕግ የማይገዛ ሊገዛም የማይችል›› (ሮሜ 8፡8) የሥጋ አስተሳሰቦች ናቸው፡፡ በእርግጥ እግዚአብሄርን የሚያስደስት እምነት እንዲኖርህ ከፈለግህ ጌታ በድንግል ማርያም በኩል ወደዚህ ዓለም በመምጣት በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች እንደወሰደና በዚህም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ እንደፈጸመ በጌታ አስደናቂ ሥራ ማመን ይገባሃል፡፡ 
የእግዚአብሄርን የጽድቅ ሥራ ማከናወን የሚችለው ማን ይመስልሃል ጻድቅ ሰው ወይስ ሐጢያተኛ? ሐጢያተኛ በእግዚአብሄር ፊት የሐጢያቶችን ስርየት ስላልተቀበለ አሁንም ድረስ በሐጢያት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ሰው የሚጠብቀው ብቸኛው ነገር ለሐጢያቶቹ የሚቀበለው ፍርድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያተኞች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ አይፈቅድም፡፡ ምክንያቱም ‹‹አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፡፡›› (መዝሙረ ዳዊት 5፡4) እግዚአብሄር ሐጢያተኛ ወደ እርሱ መጥቶ ከእርሱ አንድ ነገር ቢጠይቀው የሐጢያተኛውን ጸሎቶች አይሰማም፡፡ ምክንያቱም ‹‹በደሎቻችሁ ከእግዚአብሄር ለይተዋችኋልና፡፡›› (ኢሳይያስ 59፡1-2) የሐጢያት ደመወዝ ሞት ስለሆነ ሐጢያተኛ ሲዖል መውረዱ የተረጋገጠ ነው፡፡ 
የጽድቅ ሥራዎችን መስራት የሚችሉት ቅዱስ የሆኑና በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት የሌለባቸው ጻድቃን ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ የሚኖረው የኢየሱስን ጥምቀትና መስቀል ካመኑ በኋላ ሐጢያት በሌለባቸው ሰዎች ልቦች ውስጥ ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ በበዓለ ሐምሳ ቀን እንዲህ አለ፡- ‹‹ንስሐ ግቡ፤ ሐጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፡፡ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡38) 
ይህ ምንባብ እያለ ያለው እውነተኛ እምነት እንዲኖርህና በእምነትም የሐጢያቶችህን ሁሉ ስርየት ማግኘት ከፈለግህ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ ማመን ይገባሃል ነው፡፡ እንዲህ ያለው እምነት ‹‹በኢየሱስ ስም እንድትጠመቅ›› ይፈቀድልሃል፡፡ ይህ ማለት በእርሱ የጽድቅ ምግባሮች በማመን የሐጢያቶችህን ስርየት ትቀበላለህ ማለት ነው፡፤ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በእርሱ ጥምቀትና መስቀል እምነት የነበራቸውን ዳግም የተወለዱ ምዕመናን እንዳጠመቁዋቸው የታወቀ ነው፡፡ ኢየሱስ ሰውን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ደቀ መዛሙርቱን አዞዋቸዋል፡፡ (ማቴዎስ 28፡19) 
ከዚህም በላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም፡፡ (ሮሜ 8፡9) እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን ለጻድቃን የሰጠው የእርሱ ልጆች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በፍጹም በሐጢያተኞች ውስጥ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ሐጢያት አለባቸውና፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሐጢያትን አይወድም፡፡ የሚመርጠው ቅድስናን (ከሐጢያት መለየትን) ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በጽድቅ መንገድ ይመራቸዋል፡፡ የአብንም ፈቃድ እንዲከተሉ ይመራቸዋል፡፡ ታዲያ የእግዚአብሄር ፈቃድ ምንድነው? የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በየአገሩ ላሉ ሰዎች ማሰራጨትና በታላቁ ተልዕኮ መሰረትም እነርሱን ማጥመቅ ነው፡፡ 
የጻድቃንና የሐጢያተኞች ሥጋ እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ ሐጢያትን ይሰራል፡፡ ሆኖም ጌታ በጥምቀቱና በደሙ ሰዎች በሥጋቸውና በልባቸው የሚሰሩትን ሐጢያቶች በሙሉ የማስወገዱን የጽድቅ ሥራ ሰርቷል፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ጻድቅ በእምነት (በእውነተኛው ወንጌል) ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና፡፡›› (ሮሜ 1፡17) በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ያገኘ ሰው ‹‹የሐጢአትና የሞት ሕግ›› አሸንፎ የእርሱን ጽድቅ ይከተላል፡፡ ይህ የሚቻለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑ ሰዎች ላይ ቢወርደውና በሚያድረው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ 
የጻድቅ ሰው ያለፉት፣ አሁን ያሉትና የወደፊት ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀበት ጊዜ ወደ እርሱ ተላልፈዋል፡፡ የጻድቃን ሥጋም እንደዚሁ ከኢየሱስ ጋር ሞቷል፡፡ አንድ ሰው በዚህ ሲያምን ከኢየሱስና ከሞቱ ምሳሌ ጋር ይተባበራል፡፡ ይህም ለሐጢያቶቹ ሁሉ ፍርድ ይሆናል፡፡ (ሮሜ ምዕራፍ 6) 
ስለዚህ የአንድ ጻድቅ ሰው ሥጋ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ያለ ማቋረጥ ሐጢያት ቢሰራም መንፈስን መከተል ይችል ዘንድ በልቡ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል፡፡ አንድ ጻድቅ ሰው መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ስለሚኖር መንፈስ ቅዱስን ይከተላል፡፡ የእግዚአብሄርንም ሥራ ይሰራል፡፡ 
በሐዋርያት ዘመንም እንኳን ብዙ ሰዎች ዳግም የተወለዱ ሰዎችን ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ መውቀስ ያዘወትሩ ነበር፡፤ ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ይመሩ የነበሩት ዳግም የተወለዱ ሰዎች በሚኖሩት ሕይወት ይጨነቁ ነበርና፡፡ ነገር ግን የዚህ አይነት ሰዎች ሐዋርያት የሰበኩትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከሥጋ የመነጩ ግብታዊ እሳቤዎች አድርገው በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጰውሎስ ለእነዚህ ሰዎች እንዲህ አለ፡- ‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በሐጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም፡፡ ለሐጢአት የሞትን እኛ ወደፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?›› (ሮሜ 6፡1-2) ጨምሮም ‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ ለጌታችን ምስጋና ይሁን፤ እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሄር ሕግ በሥጋዬ ግን ለሐጢአት ሕግ እገዛለሁ፡፡›› (ሮሜ 7፡25) 
በመጨረሻ የጻድቃን ሥጋ አሁንም ድረስ ጎዶሎ ነው፡፡ በየጊዜው ሐጢያት ከመስራት በቀር ምርጫ የለውም፡፡ ነገር ግን እነርሱ አሁንም ወንጌልን በመላው አለም በመስበክ መንፈስ ቅዱስን ይከተላሉ፡፡ ጻድቃን ልቦቻቸው በጸጋው ዕርፍ ስላሉ በመንፈስ ይመላለሳሉ፡፡ ‹‹እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ሐጢአትን እንስራን? አይደለም፡፡ ለመታዘዝ ባርያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የሐጢአት ባርያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባርያዎች ናችሁ፡፡›› (ሮሜ 6፡15-16) 
እውነተኛ አበቦች ከሰው ሰራሽ አበቦች በጣም የተለዩ እንደሆኑ ሁሉ በጻድቅ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ጌታና በሐጢያተኛ ልብ ውስጥ ያለው ጌታ እርስ በርሳቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ በጻድቅ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ጌታ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ሰውየው በመንፈስ መመላለስና በሕይወቱ ውስጥም እግዚአብሄርን የሚያስደስተውን የጽድቅን እውነት መከተል ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ሐጢያተኛ በውስጡ ያለው ጌታ ራሱ ስለሆነ ሐጢያትን ከመከተል ውጪ ምርጫ የለውም፡፡ ሐጢያተኛ በብዙ ሐጢያቶቹ ምክንያት መንፈስ ስለሌለው የተቀደሰ ሕይወትን መኖር አይችልም፡፡
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች የተቀደሰ ሕይወትን መኖር አይችሉም የሚለው ግምት ከሥጋ ግብታዊ እሳቤዎች የመነጨ ስህተት ነው፡፡ እግዚአብሄር እነርሱን እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃቸዋል፡፡ ‹‹እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፡፡ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ፡፡›› (ይሁዳ 1፡10) ዛሬ ብዙዎች የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነተኛ ወንጌል መሆኑን ቢያውቁም የጻድቃኖችን ሕይወት አይረዱም፡፡ ምክንያቱም ወንጌሉን ሙሉ በሙሉ ስላላወቁትና በልባቸው ስላልተቀበሉት ነው፡፡ 
ዳግም የተወለዱ ቅዱሳን የሚሰሩትን የጽድቅ ሥራዎች በሚመለከት ምን ታስባለህ? እነርሱ ወንጌልን በመላው ዓለም ለማስፋፋት በጎ ሥራ ያላቸውን ክቡር ነገሮች ራሳቸውንም ጭምር ሕያው መስዋዕቶች አድርገው አቅርበዋል፡፡ በአንተ እሳቤዎች መሰረት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናኖች ሆነ ብለው በወንጌል ሽፋን ሐጢያት እንደሚሰሩ የምታስበው ለምንድነው? 
ጻድቃን በእውነት ብርሃንና በእግዚአብሄር ጽድቅ መካከል በጎ ሥራዎችን ይሰራሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያደርጉ ሰዎች ከእግዚአብሄር ተወልደዋል፡፡ ሐጢያተኞች በሙሉ ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ሐጢያቶቻቸውን ወዳስወገደበት ወንጌል እንዲመለሱ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ 
አዎ ልባዊ ምኞታችን አንተም በእውነት ከልብህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት እንድትቀበልና እስከ መጨረሻው ቀን ድረስም ያለ ሐጢያት ሆነህ ጌታን እንድትጠብቅ ነው፡፡