Search

የመገናኛው ድንኳን ጥናት፤

የመገናኛው ድንኳን አደባባይ በር

የመገናኛው ድንኳን አደባባይ ምሰሶች
 
የአደባባዩ ደጅ
 
ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ ነበር፡፡ የመግቢያው በር ቁመት 2.25 ሜትር (7.4 ጫማ) ወርዱም 9 ሜትር (30 ጫማ) ነበር፡፡ ይህ በአራት ምሰሶዎች ላይ የተንጠለጠለ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይና ጥሩ በፍታ ሽፋን ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ለመግባት በሚሞክርበት ጊዜ የመግቢያውን በር በቀላሉ ሊያገኘው ይችላል፡፡
ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ እግዚአብሄር ልጁ ኢየሱስ በሰራቸው በአራቱ ሥራዎቹ አማካይነት ከሐጢያቶቻችን እንደሚያድነን ይገልጣል፡፡ 
በመጀመሪያ ሰማያዊው መጋረጃ ምንን ያሳየናል? የሐጢያተኞች እውነተኛ መሲህ የሆነውንና ወደዚህ ምድር በመምጣትና ከዮሐንስ ጥምቀቱን በመቀበል የዓለምን ሐጢያቶች የወሰደውን ኢየሱስን የእውነት ክፍል ያሳየናል፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ይህ ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ የመውሰዱ የኢየሱስ እውነት ነው፡፡ ኢየሱስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጫንቃው ላይ ተሸከመ፡፡ የሰዎች ሁሉ ሐጢያቶች እንዲህ ወደ ኢየሱስ ራስ ተላልፈው ስለነበር በዚህ እውነት የሚያምኑ ሰዎች በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት የለም፡፡
ሁለተኛ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ በር ላይ የተሸመነው ሐምራዊ ማግ ትክክለኛ ትርጉም ምንድነው? ይህ የሚነግረን ኢየሱስ ተጨባጩ የነገሥታት ንጉሥ መሆኑን ነው፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ ዩኒቨርስን ሰራ፡፡ ራሱም ፈጣሪ እንጂ ተፈጣሪ አይደለም፡፡ እርሱ ወደዚህ ምድር የመጣ ትክክለኛው መሲህ ነው፡፡ መሲህ የሆነው እርሱ በሰው ስጋ ምሳሌ በተጨባጭ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ሰውነት ላይ በመሸከም በመስዋዕታዊ ሞቱና ትንሳኤውም ኢየሱስ መሲሃቸውን ያወቁትን፣ የፈሩትንና ያመኑትን የራሱን ሕዝቦች በሙሉ ከሐጢያቶቻቸውና ከሐጢያት ፍርዳቸው በሙሉ አድኖዋቸዋል፡፡
ኢየሱስ በእርግጥም ፍጹም አምላካችንና ፍጹም መሲህ ነው፡፡ እርሱ ፍጹም የሆነ አዳኝ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውሰዱ፣ በመስቀል ላይ በመድማቱና በመሞቱ፣ ከሙታንም በመነሳቱ የእኛን ሐጢያቶች በሙሉ ከማንጻቱም በላይ በእኛ ፋንታም ይፋዊ የሆነውን የሐጢያት ፍርድ ደግሞ ተቀብሎዋል፡፡
ሶስተኛ ቀዩ ማግ የሚያመለከተው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደም ነው፡፡ ፍቺውም ኢየሱስ ለምናምነው ለእኛ አዲስ ሕይወትን የሰጠን መሆኑ ነው፡፡ ይህ የቀዩ ማግ እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በራሱ ላይ በመውሰድ ለሐጢያቶቻችን ፍርድን መቀበሉን ብቻ ሳይሆን ለሐጢያት ለሞቱ ሰዎች ሕይወት የሚሰጠውን እምነት በመለገስ ለአማኞች አዲስ ሕይወት መስጠቱንም ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና  ባፈሰሰው ደሙ ለሚያምኑ ሰዎች በእርግጥም አዲስ ሕይወትን ሰጥቷል፡፡
ታዲያ ነጩ በፍታ ምን ማለት ነው? ይህ የሚገልጠው እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን የተጻፈውን የደህንነት ተስፋውን  በአዲስ ኪዳን መፈጸሙን ነው፡፡ ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በወሰደና በመስቀል ላይ ለሐጢያቶቻችን በተፈረደበት ጊዜ እግዚአብሄር ለእሰራኤላውያንና ለእኛ ቃል የገባውን የኪዳን ቃል መፈጸሙንም ደግሞ ያሳያል፡፡    
ያህዌህ አምላክ በኢሳይያስ 1፡18 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሄር፤ ሐጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች፡፡›› እንደዚሁም የእስራኤል ሕዝብ ሐጢያቶች በእጆች መጫን ወደ መስዋዕቱ ጠቦት የሚተላለፉባቸውን በመገናኛው ድንኳን የሚቀርቡትን መስዋዕቶች አቀራረብ የሚመራው የብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓት እግዚአብሄር ለእስራኤሎችና ለእኛ ያበጀው ተስፋ ነበር፡፡ ይህም እግዚአብሄር ወደፊት በእግዚአብሄር በግ አማካይነት የዓለምን ሕዝብ ሁሉ ከዘወትር ሐጢያቶቻቸውና ከዓመታዊ ሐጢያቶቻቸው እንደሚያድን ተሰፋ የሰጠበት የእርሱ መገለጥ ነበር፡፡
ይህም እንደዚሁ ተስፋ የተሰጠው መሲህ መምጣት ምልክት ነበር፡፡ ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ  በብሉይ ኪዳን መንገድ መሠረት ጥምቀቱን በመቀበል የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ በወሰደ ጊዜ የእግዚአብሄር ኪዳን ክንዋኔ ነበር፡፡ እግዚአብሄር የተስፋ ቃሉን ሁሉ ከሰጠን በኋላ ተስፋ በሰጠው መሰረት በትክክል ሁሉንም በተጨባጭ እንደፈጸማቸው አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀት የኪዳኑ አምላክ የእርሱን ኪዳናቶች በሙሉ የመፈጸሙን ይህንን እውነት ይገልጣል፡፡