Search

የመገናኛው ድንኳን ጥናት፤

የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ

የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ
 
የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ ዕቃዎች
 
የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበት መሰውያ ስፋቱና ወርዱ 2.25 ሜትር ሜትር (7.4 ጫማ) ሲሆን ቁመቱ ደግሞ 1.35 ሜትር (4.5 ጫማ) ሆኖ ከግራር እንጨት የተሰራና በናስ የተለበጠ ነበር፡፡ እስራኤሎች ይህንን የሚቃጠል መስዋዕት መሰውያ በሚመለከቱበት ጊዜ ሁሉ በፍርድ የተከረቸሙትና ኩነኔያቸውን ማስወገድ የማይችሉት እነርሱ እንደሆኑ ይገነዘባሉ፡፡ የመስዋዕቱ እንሰሳ እንደሚሞት ሁሉ እነርሱም ደግሞ በሐጢያቶቸቸው ምክንያት መሞት እንደነበረባቸው ተገነዘቡ፡፡ ነገር ግን መሲሁ ወደዚህ ምድር መጥቶ በመኮነንና ልክ ለመስዋዕት እንደቀረበው ጠቦት በሐጢያቶቻቸው ምክንያት በመሞት ሐጢያቶቻቸውን እንደሚደመስስላቸውም አምነዋል፡፡  
የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ ነበር፡፡ ነውር የሌለባቸው እንስሶች በእጆች መጫንና ደማቸውን በማፍሰስ እንደሚሰዉ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስም የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ ወደ እኛ በመምጣት የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ ሁሉ ተሸከመ፡፡ በብሉይ ኪዳን ይቀርቡ የነበሩት የመስዋዕት ጠቦቶች በእጆች መጫን አማካይነት ሐጢያቶችን በሙሉ መቀበልና ደማቸውን ማፍሰስ እንደነበረባቸው ሁሉ ኢየሱስም በዮሐንስ በመጠመቅ ወደ እርሱ የተሻገሩትን ሐጢያቶች በሙሉ ተቀብሎ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ የእነዚህን ሐጢያቶች ኩነኔ ተሸከመ፡፡ 
በዚህ መንገድ የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ ኢየሱስ ክርሰቶስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውሰድ በመስቀል ላይ እንደሞተ፣ ዳግመኛም ከሙታን እንደተነሳና እንዳዳነን ያሳየናል፡፡