Search

የመገናኛው ድንኳን ጥናት፤

የወርቁ መቅረዝ

የወርቁ መቅረዝ
 
የወርቁ መቅረዝ ከአንድ መክሊት ንጹህ ወርቅ የተሰራ ነበር፡፡ አገዳው ከተቀጠቀጠ አንድ መክሊት ንጹህ ወርቅ የተሰራ ነበር፡፡ በሁለቱ ጎን በእያንዳንዳቸው ሦስት ቅርንጫፎች ወጥተውለታል፡፡ በአገዳውና በስድስቱ ቅርንጫፎቹ ጫፍ ላይም ሰባት መብራቶች ተደርገውበታል፡፡ የወርቁ መቅረዝ ከአንድ መክሊት ንጹህ ወርቅ የተሰራ ስለነበር መስህብነት ያለውና የሚያምር ነበር፡፡ 
በወርቁ መቅረዝ ጫፍ ላይ ቅድስቱን ስፍራ ሁልጊዜም የሚያበሩና ዘይትን የሚይዙ ሰባት መብራቶች ነበሩ፡፡ 
በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ ያለው የወርቅ መቅረዝ ሁልጊዜም ብሩህ ብርሃኑን እንደሚያበራ ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የእግዚአብሄር ልጆች የሆኑትም ሰዎችን ከሐጢያቶቻቸው በሚያድን የደህንነት ብርሃን ይህንን ዓለም ማብራት ይችላሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ሌሎች ይህንን እውነት ያውቁና የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ይቀበሉ ዘንድ የደህንነትን ብርሃን የሚሰጠውን የመቅረዝ ሚና መጫወት የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የሐጢያት ስርየትን የተቀበሉ ብቻ ናቸው፡፡  
የወርቁ መቅረዝ አበቦች፣ ጉብጉቦችና ጽዋዎች ነበሩ፡፡ በመቅረዙ ላይ ሰባት መብራቶች ሊደረጉ እንደሚገባቸው እግዚአብሄር ስላዘዘ መቅረዙ ሲበራ ሁልጊዜም ጨለማ ከቅድስቱ ስፍራ ይገፈፋል፡፡ ይህ ማለት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው የነጹ ጻድቃን አብረው በመሰባሰብ የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን ገንብተው ይህንን ዓለም ያበራሉ ማለት ነው፡፡ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ የሚያበራው የመቅረዙ ብርሃን የዚህን ዓለም ጨለማ የሚገፍፈው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡