Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

አጋር ሠራተኛ ከሆንክና "መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች" በሚለው ላይ መልዕክትና ፎቶዎችን መለጠፍ የምትወድ ከሆነ "መልዕክት ለጥፍ" የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግና ግባ፡፡ ልጥፍህ የሚታየው የእኛን ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡

መልዕክት ለጥፍ
ጠቅላላ፤ 15
  • ቁ.10

    የእግዚአብሔር ዕቅዱ ሲደርስ (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)

      የእግዚአብሔር ዕቅዱ ሲደርስ  ምድራዊ ድንኳኑ ሲፈርስ ጻድቃን ለሕይወት ትንሣኤ ኃጢአተኖች ለፍርድ ትንሣኤ  ይነሳሉ ይፈጸማል /ይሄ አይቀርም(3*) በእግዚአብሔር ዘንድ ውሸት የለም(3*)   (1) ስጋና ደም ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከቶ አይገቡም የሰው አለማመን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ከቶ አያስቀርም   የዓለም ኃጢአት ሁሉ ተወግዷል ይሄን አምናለው  የማይታየውን ተስፋ በማድረግ በእምነት ኖራለው   (2) ቃሉ ከሚያልፍ ሰማይና ምድር /ቢያልፍ ይቀላል(2*) ጌታ ያለው ሁሉ የተስፋው ቃል /ሁሉ ይፈጸማል(2*) አያለሁ እኔ በዓይኔ ቅድስቲቱን ውቡ ከተማ ከላይ ስትወርድ ኢየሩሳሌም የጻድቃን ቤት ተሸላልማ   (3) ዛሬ በለቅሶ እዘራለው  ነገ በደስታ አጭዳለው ዛሬ በምሞት አካል አለው ተስፋዬንም እጠብቃለው ማይሞተውን አካል ይዤ በትንሣኤ እነሳለው የጠበቅኩትን ጌታ ፊት ለፊት በዓይኔ አያለው።   (4) ኃጢአት በጽድቅ ተዋጠ ሞት በሕይወት ተለወጠ ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ? የኃጢአት ኃይል ሕግ ሆኗል የሕግ ፈጻሜ ኢየሱስ ሆኗል።

    • Mesfin Berhanu Ubba
    • Ethiopia
    • 12/12/202248
  • ቁ.9

    ለመዳን አስቀድመን (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ)

      ርዕስ፦ ለመዳን አስቀድመን (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ) ለመዳን አስቀድመን ኃጢአቶችንንማወቅ አለብንለመዳን አስቀድመን ክፋቶቻችንንመገንዘብ አለብን።   (1)   ኃጢአት ሰሪ መሆናችንን ሁል ጊዜ አመንዛሪ መሆናችንን ሁል ጊዜ ሰራቂ መሆናችንን እንድናውቅ ይፈልጋል እግዚአብሔር ራሳችንን። (2)  ይፈልቃል ከእኛ ልብ በየቀኑ የኃጢአት ዓይነትዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነትመጎምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራትስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና፣ ምቀኝነትእነዚህ ኃጢአት ይፈልቃሉ  ዘውትር ከእርኩስ ልባችንመዳን ከቶ አንችልም ካላወቅን ራሳችንን። (3)   አውቃለሁ ኃጢአቴን፣ የኃጢአቴንም ደመወዝ አመለጥኩኝ ባንተ ኢየሱስ ፣ ዳንኩኝ እኔ ከሞት መዘዝበውኃና በደም መጥተህ በአንዴ እኔን አጸደቅከኝ በዘላለም ቤዛነትህ በአዲስ ኪዳን ምህረት ማርከኝ።በዓመፃዬ ጽድቅህን  አይቻለሁናአመሰግናለሁ ኢየሱስ ይድረስ ለአንተ ምስጋና። (4) ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርግርነቱንይለውጥ ዘንድ ይችላል ወይ የተፈጥሮ ማንነቱንምንም ያህል ብንለፋ ከሰል አጥበን አናነጣምበሕግ ኑሮ ብንታገል የልብ ኃጢአት ከቶ አይጠራም ከቶም አንጸድቅም በጽድቃችንበትንቢት ቃል ተጽፎ አለ የክፉ ዘር መሆናችን። (5)መዳኛችን የእኛ ቤዛ አዲስ ፍጥረት ምንሆንበትበኢየሱስ ጥምቀትና በሞቱ ላይ ያለን እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ ትምክታችን የሚያቆመን የቆምንበትየዘላለም ተስፋችን ነው ብድራቱን ምናይበት።

    • Mesfin Berhanu Ubba
    • Ethiopia
    • 12/12/202245
  • ቁ.8

    አሁን ኃጢአተኛ አይደለሁም።

    እኔ ኃጢአተኛ የነበርኩት የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባላመንኩ ሰዓት ብቻ ነበረ፤ አሁን ኃጢአተኛ አይደለሁም።ደካማ ሥጋ ስለለበስኩ በሥጋዬ ስበት ኃጢአትን ልሰራ እችላለሁ፤ ነገር ግን የሚያጸድቀኝን የእግዚአብሔር ጽድቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እስካልጣልኩ ድረስ ለዘላለሙን ጻድቅ ነኝ እንጂ ዳግመኛ ኃጢአተኛ አልሆንም። ሃሌሉያ!!! ኃይማኖት ሰዎችን አጠፋ! እንዴት ያሳዝናል የኃጢአትን ስርየት የተቀበለ ማንም የለም። ምክንያቱም የኃጢአት ስርየት ወንጌል የሆነው የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል አይሰበክምና!Mesfin Berhanu Ubba, Ethiopia

    • Mesfin Berhanu Ubba
    • Ethiopia
    • 10/23/202244
  • ቁ.7

    ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ተመለሱ

    ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት አንድ ብቸኛ መንገድ አለ! እንዲሁም እውነተኛ ያልሆኑ ግን እውነትኛ የሚመስሉ የሀሰት መንገዶችም አሉ! ታዲያ የሰው ልጅ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚወስደውን እውነተኛውን መንገድ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ማግኘትና በዛም ማመን አለበት! መጽሀፍ ቅዱስ በዩሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3፥5 ላይ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደማይገባ ተጽፏል! ስለዚህ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ከውሃና ከመንፈስ መወለድ አለበት! ይህ መጽሀፍ ስለውሃና መንፈስ ወንጌል መንፈሳዊ ትርጉም እንዲሁም የዘመኑን የሀሰት ወንጌልና እውነተኛውን ወንጌል  በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በግልጽ የሚዳስስ የቄስ ፓውል ሲ ጆንግ ሁለተኛ እትም መጽሀፍ ነው!መጽሀፉ ስምንት ስብከቶች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ስብከት  በዩሐንስ 3፥1-6 መሰረት እውነተኛ ዳግም የመወለድ ወንጌል ትርጉምን ያስረዳል!  ዳግመኛ ስለመወለድ መንፈሳዊ ሚስጢር ስንገነዘብ የሰው ልጅ ሁሉ ከእድሜ ልክ ኅጢአቱ የሚነጻበትን እውነታ እናገኛለን፡ ያም እውነት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ማለት ነው። ውሃ ማለት የኢየሱስ ጥምቀት ሲሆን መንፈስ ማለት የእርሱ አምላክነት ማለት ነው። ስለዚህ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ለመወለድ ማናችንም ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ የዓለምን ኅጢአት ሁሉ መሸከሙን ስለዛም ኅጢአት ዋጋን ሁሉ እስከሞት ድረስ መክፈሉን ከሞትም መነሳቱን እንዲሁም ይህን ታላቅ ስራ ለሰው ልጅ ሁሉ በእኩል ያደረገው ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ማመን አለብን!በሁለተኛው ስብከት በኢሳያስ 28፥13-14 መሰረት በክርስትና ውስጥ ስላሉ አስመሳይ ክርስቲያኖችና መናፍቃን በስፋት ተብራርቷል! ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ያልተወለደ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መናፍቅ ነው! በሌላ አነጋገር በክርስቶስ አምናለው እያለ በልቡ ኅጢአት ያለበት ሰው ሁሉ እርሱ መናፍቅና አስመሳይ ክርስቲያን ነው! እነዚህ አስመሳይ ክርስቲያኖች ለሰዎች በትክክል ዳግም የሚወለዱበትን ወንጌል ሊሰብኩ አይችሉም! ስብከታቸው ሁሌም ስለቁሳዊ ነገሮችና ስለሰው ልጅ አስተሳሰብ ብቻ ነው! እነዚህ መናፍቃን በእርግጥም የእግዚአብሔር ፍርድ ይጠብቃቸዋል! እውነተኛ ክርስቲያኖች የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አማኞች ብቻ ናቸው! እነርሱም ስለኢየሱስ አምላክነት፡ ጥምቀት፡ ሞትና ትንሳኤ በግልጽ የሚሰብኩ ሁሉም ሰው ከሀሰተኛ ነብያቶች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስተምሩ ድንቅ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸው!በሶስተኛው ስብከት በዘጸአት 12፥43-49 መሰረት ስለእውነተኛው መንፈሳዊ ግርዘት በስፋት ተብራርቷል! በብሉይ ኪዳን ፋሲካን ማክበር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መገረዝ አለበት! ፋሲካ ማለት እስራኤለውያን ከግብጽ የባርነት ህይወት ነጻ የወጡበትን ጊዜ የሚያስታውሱበት እና እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት በዓል ሲሆን በዓሉንም ለማክበር የመገረዝ ግዴታ ነበረባቸው! በአዲስ ኪዳን ስንመጣ ማንም በክርስቶስ ማመንና የእርሱ ልጅ መሆን የሚችለው በልቡ ሲገረዝ ነው፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ በሮሜ 2፥29 ላይ መገረዝ የልብ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ያም ማለት እስራኤልቅውያን ሸለፈታቸውን ቆርጠው በመጣል የእግዚአብሔር ህዝብ እንደሚሆኑት ሁሉ እኛም በክርስቶስ ጥምቀት ስናምን ወይም ኅጢአቶቻችንን ሁሉ በእምነት ወደ ኢየሱስ ስናሻግር የእርሱ እውነተኛ ልጆች እንሆናለን ማለት ነው!አራተኛው ስብከት በ1ኛ ዩሐንስ 1፥9 በኩል እውነተኛውና ትክክለኛው ኑዛዜ እንዴት እንደሚደረግ ይነግረናል! ይህን ክፍል ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ይረዱትና በንስሀ ጸሎቶቻቸው ከኅጢአቶቻቸው ለመንጻት ይሞክራሉ! እውነታው ግን ማንም ሰው በንስሀ ጸሎት ኅጢአትን የማስወገድ ስልጣን የለውም የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ኅጢአትን የማስውውገድ ስልጣን ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ በልባችሁ ኅጢአት ያለባችሁ ማናችሁም ለመዳን ብትወዱ የሚከተልውን ኑዛዜ ማድረግ ይኖርባችኋል! ጌታ ሆይ እኔ ኅጢአቶቼ በዝተዋል ሞትም ይገባኛል፡፡ አንተ ካላዳንከኝ በእርግም እሞታለው! ዘወትር ይቅር በለኝ በማለት እጸልያለው ነገር ግን ከኅጢአቶቼ ሁሉ መንጻት አልቻልኩም እባክህ አባት ሆይ አድነኝ እራራልኝም! በንጹህ ልብ ይህን ካደረጋችሁ እግዚአብሔር በአግልጋዮቹ አማካኝነት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይገልጥላችኋል! የክርስቶስ ልጅ ከሆንን በኋላ እንደሚከተለው እንናዘዛለን ጌታሆይ ስጋዬን የመከተል ኅጢአት ሰርቻለው፡፡ አንተ በአጥማቂው ዩሐንስ ስትጠመቅ ያለፈውን አሁን የፈጸምኩትን እና የወደፊቱንም ኅጢአቴን ሁሉ እንዳስወገድክልኝ አምናለው! ያ ባይሆን እሞት ነበር! በጥምቀትህ በሞትህና በትንሳኤክ ስላዳንከኝ አመሰግናለው! ዘወትር እንዲህ በመናዘዝ ጻድቃን ህይወታቸውን ይቀጥላሉ! የጻድቃን እና የኅጢአተኞች ኑዛዜ ይለያያል፡፡አምስተኛው ስብከት በሮሜ 8፥28-30 መሰረት አስከድሞ በመወሰንና በመልኮት ምርጫ ጽንስ ሀሳብ ውስጥ ስላለው ስዕተት ያብራራል! በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ መረዳት ከሌለን በክርስቶስ ለማመን እንቸገራለን እንዲሁም ተመርጬ ይሁን ወይስ አይሁን በማለት ግራ መጋባት ውስጥ እንወድቃለን! እግዚአብሔር አስቀድሞ ከአዳም ጀምሮ የሰው ልጅ ሁሉ በኅጢአት እንደሚወድቅና ለዛም ቅጣት ፍርዱ ሞት ስለሆነ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሊያድነን ወደደ ሁላችንም ማወቅ ያለብን እውነት እግዚአብሔር ያለምንም አድሎ ሁላችንንም በእኩል እንደወደደን መገንዘብ አለብን! ስለዚህ ሁላችንም ያለምንም አድሎ የወደደንን ጌታ በንጹህ ልባችን ማመን አለብን! ይህን በማድረግ ሃሰተኛ ሰባኪዎች በሚያስፋፉት የአስቅድሞ መወሰንና የመለኮት ምርጫ የተሳሳቱ አስተምህሮቶች ላይ እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ይኖርብናል!ስድስተኛ ሰብከት በዕብራውያን 7፥1-28 መሰረት ስለተለወጠው ክዕነት ያስረዳል! የተለወጠውን ክዕነት በአግባቡ ለይተን ካላወቅን እምነታችን ሙሉ አይሆንም! ብዙዎች ይህን ባለማወቅ በብዙ ውንዥንብር ውስጥ ወድቀዋል! የተለወጠው ክዕነት ማለት በአጭሩ ሲገልጽ በብሉይ ኪዳን የነበረውን የስርየት ስርዓትን በመሻር በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ሁሉ በእኩል የሰራው ጽድቅ ማለት ነው! በብሉይ ኪዳን ለስርየት የሚቀርበው መስዋዕት እለት እለት ወይም በቀጣይነት በአመት አንድ ጊዜ  የእስራኤለውያንን ኅጢአት በእጆች መጫን ስርዓት ይቀበላል ስለዛም ኅጢአት መስዋዕቱ ይሞታል! ነገር ግን ያ የስርየት የስርዓት ስርዓት ከእድሜ ልክ ኅጢአቶቻቸው አያነጻቸውም ነበር! የብሉይ ኪዳኑ መስዋዕት በአዲስ ኪዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያመለክት ሲሆን ኢየሱስ ያለነውርና እንከን ወደ ምድር በመምጣት በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ በእጆች መጫን ስርዓት አማካኝነት የዓለምን ኅጢአት ሁሉ ተሸከመ ሰለዛም ኅጢአት በመስቀል ላይ ዋጋን ከፈለ! ሞተም በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነሳም! ሀሌሉያ!!!ሰባተኛው ስብከት ማቲዮስ 3፥13-17ን በመዳሰስ የኢየሱስ ጥምቀት ለቤዛነት አስፈላጊ የመሆኑን ሂደት ያብራራል! ማናችንም ከዕድሜ ልክ ኅጢአቶቻችን በመንጻት ከዘላለም ሞት መንዳን ብንወድ የግዴት በክርስቶስ ጥምቀት በኩል ማመን አለበን!!! (በዩሐንስ 1፡29) የዓለምን ኅጢአት የሚያስውግድ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጆች መጫን ስርዓት በጥምቀቱ የእድሜ ልክ ኅጢአቶቻችንን ሁሉ በስጋው ተሸከመ! ስለበደላችንም በመስቀል ላይ ሞተ በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነሳ ሃሌሉያ! ለቤዛነታችን ከዚህ ውጭ ወንጌል የለም!!!በመጨረሻው ስብከት ማቲዮስ 7፡21-23ን እናገኛለን በዚህም ስብከት የአብን ፈቃድ በእምነት ስለመፈጸም እንማራለን! ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚል ሁሉ መአንግስተ ሰማያት የሚገቡ አይደሉም፡፡ ክፍሉ የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚያደርጉ ብቻ ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደሚገቡ ይናገራል! ስልዚህ የእግዚአብሔር ፍቃድ ምን እንደሆነ ሁሉም ሰው ማወቅ እና ማመን አለበት! ያም ፈቃድ ማለት እግዚአብሔር እኛን የሰው ልጆችን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ከኅጢአቶቻችን ሁሉ በማንጻት የራሱ ልጆች ማድረጉ ነው! እግዚአብሔር ይመስገን ከውሃውና ከምንፈስ ዳግም በመወለዴ የክርስቶስ ልጅ ሆኛለው! ይህን ወንጌል በመስበክ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእምነት እየፈጸምኩ ነው!ማናችሁም በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ያሉትን መልዕክቶች በልባችሁ ብትቀበሏቸው ከሀሰተኛ ንብያት በመጠንቀቅ እውነተኛውን የወንጌል በር ታገኛላችሁ የክርስቶስ ደቀመዝሙርም ትሆናላችሁ!Teferi Oshine, Ethiopia

    • Teferi Oshine
    • Ethiopia
    • 08/04/202253
  • ቁ.6

    ወንጌልን ስንሰብክ በጥበብ ይሁን!

    ወንጌልን ስንሰብክ በጥበብ መስበክ እንዳለብን የእምነት አባቶቻችን ይመክሩናል! ያ እጅግ በጣም ድንቅ ምክር ነው! ወንጌልን በጥበብ መስበክ ማለት ከዕለት ዕለት ህይወትችን ስንነሳ ዳግም ካልተወለዱ ሰዎች ጋር በሚኖሩን የተለያዩ ግንኙነቶቻችን መልካም ግንኙነቶችን ማድረግ ይኖርብናል! ያም ወንጌልን በምንሰብካቸው ሰዓት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል! ሌላው ለዓለም ህጎችም መገዛት ይኖርብናል ምክንያቱም የዓለም ህጎችን ተላልፈን ወንጌልን መስበክ አይቻልምና! የዓለም ህጎችን መታዘዝ ስንል ግን ሁሉንም ህጎች መቀበል ማለት አይደለም! መታዘዝ ያለብን እምነታችንን የማይነኩ ሲሆኑ ብቻና ብቻ መሆን አለበት! የእምነት አባቶቻችን እምነታቸውን የሚነኩ የዓለም ህጎችን አንቀበልም በማለት ሰማዕት ሆነዋል! እኛም የዛሬዎቹ ጻድቃን በእምነታችን የሚመጣብንን ማንኛውንም ነገር መታዘዝም ሆነ መቀበል የለብንም! በሌላ በኩል ወንጌልን በጥበብ መስበክ ማለት ባገኘናቸው የወንጌል በሮች ሁሉ በመጠቀም ወንጌልን መስበክ አለብን ማለት ነው! በሌላ አነጋገር አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ወንጌልን መስበክ አለብን ማለትም ነው! ሁላችንም እዚጋ አንድ ማስታዋል ያለብን ነገር ወንጌልን በየትኛው ዘርፍ መስበክ እንዳለብን ማወቅ አለብን ያም ማለት የትኛው ዘርፍ ወንጌልን ለመስበክ እንደሚቀርበን መገንዘብ ማለት ነው! በቸርች ውስጥ ወንጌልን በማሰራጨት ሂደት ላይ ከትናንሽ ሀላፊነቶች ጀምሮ እስከ ትላልቅ ሀላፊነቶች አሉ! ለምሳሌ ቤ/ክንን ማጽዳት, ለወንጌል ስርጭት መውጣት, የተለያዩ የጉልበት ስራዎችን መስራት, ለቅዱሳን ምግብ ማብሰል, ስብከቶችን መስበክ, ዝማሬዎችን ማዘጋጀት ሌሎችም የመሳሰሉ ስራዎች ይኖራሉ! አንድ ጻድቅ ሁሉንም ሀላፊነቶች ብቻውን መወጣት በፍጽም አይችልም ሁላችንም ግን የየራሳችንን ሀላፊነቶች ስናውቅ ሀላፊነቶቻችንን በአግባቡ መወጣት እንችላለን እዚጋ ዋናው መልዕክት አንዳችን ያለአንዳችን በጋራ ካልሆነ በቀር በግላችን በፍጥነት መራመድ አለመቻላችን ነው! እኛ ቅዱሳን ባለንበት ውስብስብ ዓለም ውስጥ የውሀውንና የመንፈሱን ወንጌልን በአራቱም ማዕዘናት የማሰራጨት ሃላፊነት አለብን ይሄን ስል የእኔ ሃላፊነት ምንድነው በየትኛውስ ዘርፍ ነው ማገልገል ምችለው? ጥያቄውን ለራሳችን እየመልስን በምንችለው ሁሉ ወንጌልን መስበክ ይኖርብናል! ሁላችንም ባለን አቅም በትጋት ወንጌልን የምንሰብክ ከሆነ በዛም ድንቅ ስራ እስከመጨረሻው የምንጸና ከሆነ ወንጌላችን በመላው ዓለም ይደረሳል ከዛም በእርግጥም ኢየሱስ ይመጣል የተስፋውንም ቃል ይጠብቃል! ከበደላችን ሁሉ ያነጻን እስካለንበት ጊዜ ድረስ በእምነት ያቆመን እግዚአብሔር ይመስገን እስከሞት ድረስት በሚታመን እምነትም ይባርከን! ወንድማችሁ Teferi Oshine Tanto Ethiopia/Hawassa

    • Teferi Oshine
    • Ethiopia
    • 05/10/2022102