Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

አጋር ሠራተኛ ከሆንክና "መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች" በሚለው ላይ መልዕክትና ፎቶዎችን መለጠፍ የምትወድ ከሆነ "መልዕክት ለጥፍ" የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግና ግባ፡፡ ልጥፍህ የሚታየው የእኛን ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡

መልዕክት ለጥፍ
ጠቅላላ፤ 15
  • ቁ.5

    የእምነት ምስክርነት

    ሰላም ቅዱሳን ጸጋው የበዛላችሁ ከእግዚአብሔር የተሰጠን እውነተኛው ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን! ዛሬ ከእምነት ምስክርነታችን እንድንማማር የእምነት ምስክርነቴን ልጽፍላችሁ ወደድኩ! እግዚአብሔር ቢፈቅድ በእምነት ህይወቴ የሚገጥሙኝን መልካምና ክፉ ገጠመኞቼን እንድንማርባቸው በቀጣይ ጊዜያት ልጽፍ እመኛለው!!! ዳግም መቼ እንደተወለድኩ ትክክለኛ ቀኑን ወሩንና አመቱን አላስታውስም!  ግን ጻድቅ ያደረገኝ እግዚአብሔር ይመስገን! እንዴት ዳግም እንደተወለድኩ ማብራራት እችላለው!  ከ6 አመቴ ጀምሮ እስከ 14 አመቴ ድረስ ያደኩት በፕሮቴስታንት ሀይማኖት ውስጥ ነበር! የውሃውን እና የመንፈሱን ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ ከጎረቤት የሚኖር የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አርበኛ ስራውን ሊሰራ የመንደሩን ህጻናት ሰበሰበ በሰዓቱ እኔ የ10 አመት ልጅ ነበርኩ!  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ 14 አመቴ በመንደራችን ከህጻናቱ ጋር ከአርበኛው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እየሰማውና ቤተሰብ ከሚልከኝ ሀይማኖት ቤት በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉ ነብያት ታሪክ እየተማርኩ ቀጠልኩ በ11 እና 12 ዓመቴ፣ የክርስቶስን ጽድቅ መሰረታዊ የድነት እውቀት እየለየው መጣው!  ያም የክርስቶስ ጽድቅ በልቤ እንዲታተም አደረገ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ!!!  13 እና 14 አመት ሲሆነኝ የክርስቶስ ፅድቅ በልቤ ሲያብብ አየሁ!  ስለ ሰው ማንነት፣ ስለ ሕግ፣ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ስለ ብሉይ ኪዳንኑና ስለ አዲስ ኪዳኑ የስርየት ሥርየት፣ ስለ ውኃ ደም መንፈስ መሠረታዊ የደኅነት እውቀትና በአጠቃላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ወንጌል የበለጠ ተረዳው።  ሳላስበው ወንጌልን ስሰብክ እና ውሸታሞችን እየተቃወምኩ የሬቨረንድ ፓውልሲ ጆንግን መጽሃፍ የማሰራጭ ሆኜ እያገለገልኩ መጣው!  ሀዋሪያው ጳውሎስ "እኔ ከሰበኩላችሁ ወንጌል ውጭ ማንም በሰብካችሁ የተረገመ ይሁን" ገላቲያ 1፥7-9  እንዳለው እኔም ከአውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጭ ሌላ ወንጌል ሁሉ ከሰይጣን መሆኑን የውሃውንና የመንፈሱ ወንጌል በመስበክ አረጋግጣለው! ወንጌላችን ሌላ አደለም (ኢየሱስ እንደመስዎዕቱ በግ ያለነውር ከሰማይ መቷል በእጆች መጫን ስርዓት በጥምቀቱ የዓለምን ሁሉ ሀጢአት ወስዷል ሰለሀጢአትም ዋጋን ሁሉ ከፍሏል በእርግጥም ሞቷል በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነስቷል የሚል ነው ሀሌሉያ!) በሚገርም ሁኔታ እዚሁ 14ኛ አመቴ ላይ እያለው ጥምቀት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ከተረዳው በኋላ ፕሮቴስታንቶች እድሜክ 14 ደርሷል ብለው የጥምቀት ትምህርት እንድጀምር ተነገረኝ! መንፈስ ቅዱስ ወደ ውቡ ወንጌል (የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል) ጠቅልሎ ሊወስደኝ ሲወድ ያንን አደረገ! እኔ ባህሪዬ ዝምተኛና አይንአፋር ነኝ¡ የዛን ቀን ግን በሙሉ ድፍረት የተለያዩ ጥያቄዎችንና ንግግሮችን ሳደርግ እንደነበር አስታውሳለው ከጥያቄዎቼ አንዱ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? የሚል ነበር ምንም እንኳን ብዙ እና ከእኔ ትላልቅ ቢሆኑም ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀ አያውቁም ነበር በተዋቡ ቃላት የተሳሳቱ መልሶችን ብቻ ይመልሳሉ! በንግግራቸው ሁሉም እንደህጻናት ይታዩኝ ጀመር! ከዛን ጊዜ ጀምሮ በእኔ ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረስ ጀመሩ ለጓደኞቼ በሙሉ ተፈሪ የስዕተት አስተምህሮት ውስጥ ገብቷል እርሱን እንዳትሰሙት የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጡ! በዚህ ሁሉ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ድፍረት ሲሆነኝ እምነትን ሲሰጠኝ አንደበቶቼን ሲዳስስ እንደነበር አያለው፡ በመጨረሻም የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አሸንፎ ሙሉ እኔነቴን ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል አቅርብያለው በድጋሚ ምስጋን ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን!!! ከዛን ጌዜ ጀምሮ ሳልቀላቅል ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውሃ ጣፍጦኝ እየጠጣው ነው! ውቡ ወንጌላችን በዓለም ሁሉ ይድረስ!!! ሁላችንም እስከሞት ድረስ በእምነታችን እንድንጸና አባታችን ኢየሱስ በነገር ሁሉ ይርዳን! ወዳችኋለው ተባረኩ! ወንድማችሁ ተፈሪ ኦሺኔ ታንቶ Ethiopia/Hawassa

    • Teferi Oshine
    • Ethiopia
    • 11/19/2021118
  • ቁ.4

    አሁን ግን ከዚህ የዲያብሎስ ሽንገላ ነጻ የሚያወጡበትና ከኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚድኑበት ዘመን መጥቷል። 

    አያሌ ክርስቲያኖች ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደሞተላቸው ቢያምኑም፣ ግን ኃጢአተኞች ናቸው። ኢየሱስ የአዳምን ወይም የውርስ ኃጢአት ብቻ እንዳስወገደ ስለሚያምኑ፣ በየዕለቱ ለሚሰሩት ኃጢአት ስርየትን ለማግኘት በእ/ር ፊት ያለቅሳሉ። በክርስቶስ ቢያምኑም ኃጢአተኞች እንደሆኑ ያስባሉ። አሁን ግን ከዚህ የዲያብሎስ ሽንገላ ነጻ የሚያወጡበትና ከኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚድኑበት ዘመን መጥቷል። Bereket Make Mara, Ethiopia

    • Bereket Make Mara
    • Ethiopia
    • 11/02/202162
  • ቁ.3

    የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ከሐጢያት አድኖኛል፡፡

    ከዓመታት በፊት በአንድ ቢሮ ውስጥ እየሰራሁ አንድ ወጣት ባለ ጉዳይ ወደ ቢሮዬ መጣ፡፡ በእጁ ‹‹Have You Truly Been Born Again of Water and The Spirit?›› የሚል በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሐፍ ይዞ ነበር፡፡ ርዕሱ ትንሽ እንግዳ ስለሆነብኝ ወጣቱ የሚፈልገውን ካሰተናገድሁት በኋላ መጽሐፉን አየው ዘንድ ቢፈቅድልኝ ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ወጣቱም ‹‹እንዲያውም ትርፍ ስላለኝ ውሰደውና አንብበው›› በማለት ሰጠኝ፡፡ በአክብሮት ተቀበልኩት፡፡ ወደ ቤት ከተመለስሁ በኋላ በመደርደሪያዬ ላይ አስቀመጥሁት፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል አላየሁትም፡፡    አንድ ቀን ሌላ መጽሐፍ ስፈልግ ዓይኖቼ በዚህ መጽሐፍ ላይ አረፉ፡፡ የምፈልገውን መጽሐፍ ትቼ ይህንን መጽሐፍ ከመደርደሪያው ላይ ሳብ አድርጌ እንደ ነገሩ ማገላበጥ ጀመርሁ፡፡ የአንድ መጽሐፍ ምንነት የሚታወቀው መቅድሙን በማንበብ እንደሆነ ስለማውቅ የዚህን መጽሐፍ መቅድም ማንበብ ጀመርሁ፡፡ ምንም እንኳን በሃይማኖት ቤት ለረጅም ጊዜ ባሳልፍም የኢየሱስ ጥምቀት ከደህንነቴ ጋር ይገናኛል ብዬ አንዴም እንኳን አስቤ አላውቅም ነበር፡፡  በእጄ ላይ ያለው መጽሐፍ ፈጽሞ አዲስ የደህንነት እሳቤን አሳየኝ፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስ መወለድ ለእኔ ፈጽሞ አዲስ መገለጦች ነበሩ፡፡ ይህንን መጽሐፍ በታላቅ ጉጉትና አውቆ ለመዳን በተከፈተ ልብ ማንበቤን ተያያዘሁት፡፡ የብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዓት፤ የእጆች መጫን፤ የመሥዋዕቶችን ደም የማፍሰስ ስርዓት በአዲስ ኪዳን ከኢየሱስ ጥምቀትና ሞት ጋር ያላቸውን ቁርኝት በሰፋት በተረዳሁ ጊዜ፤ ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን የእግዚአብሄር በግ ሆኖ ወደዚሀ ምድር በመምጣት የሰው ዘር ወኪል (ዮሐንስ 11፡11) በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ አማካይነት ሐጢያቶቼን በሙሉ በራሱ ላይ በጥምቀቱ መወሰዱን ሳውቅና ይህም በጥላው ለመስዋዕቶች በሚቀርቡት እንስሶች ላይ በሚደረገው የእጆች መጫን ስርዓት አማካይነት ከሚተላለፉት የሐጢያተኛው ሐጢያቶች ጋር መሳ ለመሳ እንደሚመሳሰል ስረዳ ለዚህ ትልቅ የመዳን ዕውቀት እጄን ወደላይ አንስቼ ከመማረክ በቀር ላደርገው የምችለው ነገር አልነበረም፡፡ ይህ የእውነት ብርሃን በልቤ ላይ በራ፡፡ ሐጢያት አልባ ያደረገኝ የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱ ነፍሴን በሐሴት ሞላት፡፡ ኢየሱስ ተጠምቆ ‹‹ጽድቅን ሁሉ በመፈጸም›› (ማቴዎስ 3፡15) የዘላለም ጽድቁን ስላወረሰኝ አሁን ጻድቅ ነኝ፡፡ ዳግመኛ ከተወለድሁም 18 ዓመት አልፎኛል፡፡ አሁን የ18 ዓመት መንፈሳዊ ወጣት ነኝ፡፡ ይህንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ገናም በሐጢያት እስራት ውስጥ ላሉና በጨለማ ውስጥ ለሚዳክሩ መስበኬን አላቋረጥሁም፡፡ ክብር በውሃ፣ በደምና በመንፈስ (1ኛ ዮሐንስ 5፡6) ለመጣው፣ ሐጢያቴን ከላዬ ላይ እንዳረጀ  ልብስ ገፎ ለጣለውና አዲሱን የጽድቅ ልብስ ላለበሰኝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን! አሜን!! ካሳሁን አየለ, Ethiopia

    • Kassahun Ayele
    • Ethiopia
    • 10/31/202145
  • ቁ.2

    ከእኔ ሕይወት ትማሩ ዘንድ የደህንነት ምስክርነቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።

    ሰላም!ዳንኤል ተስፋዬ እባላለሁ።ከእኔ ሕይወት ትማሩ ዘንድ የደህንነት ምስክርነቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ። ተወልጄ ያደኩት  በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥነው።አባቴ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ሲሆን ከአንድም ሁለት ቦታየመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ በሌሉባቸው ቦታዎች ቤ/ክ በመትከልብዙ ሰዎችን ጴንጤ አድርጉዋል።በቤተሰባችን ውስጥም ቋሚ የሆነየማለዳ ፣የቀትርና የማታ ፕሮግራሞች ይደረጋሉ።ራሴን ወደማወቅ ደረጃ ላይ ስደርስ (የ7ተኛ ክፍል ተማሪ እያለው ነው)አንድ ቀን የምሽት ፕሮግራማችን ላይ አባቴ "ዳንኤል" ብሎሲጠራኝ "አቤት አባባ" አልኩኝ።"ጌታን መቀበል ትፈልጋለህ?"ሲለኝ ፣ ጥያቄው እንግዳ ስለነበረብኝና እኔ ጌታን ተቀብያለው ብዬአስብ ስለነበር ፈራ ተባ እያልኩ "እንዴ አባባ እስከዛሬ ጌታንአልተቀበልኩም ማለት ነው? ለማለት አስቤ ፊት ፊቱን ሳየው"ሃሳቤ ገባው መሰለኝ ሳልጠይቀው እንዲህ አለኝ።ይኸውልህ ልጄ ክርስትና የሚወረስ ነገር አይደለም።ወደህአምነህ የምትከተለው ነገር ነው።ሲለኝ እንዴ አባባ እኔ እኮክርስቶስን የምከተለው ወድጄ ነው አልኩት።ከዛም በልእንግዲህ ወደህ የምትከተል ከሆነ ተነስና እጆችህን ወደላይበማንሳት እኔ የምለውን ደግመህ በማለት ጌታን ተቀበል አለኝእኔም በደስታ እጄን አንስቼ አባቴ የሚለውን በመከተል"አለምንናሴጣንን ክጃለው፤ኃጢያትን ክጃለው፤ጌታ ሆይ ስሜን በህይወትመዝገብ ላይ ፃፈው..." ስል ጌታን ተቀበልኩ።ከዛም የተለያዩትምህርቶችን በመከታተል ተጠመኩ ፣ወደ አገልግሎት ውስጥተሰማራው።እያደኩ ስመጣም የታዋቂ ፓስተሮችንናወንጌላውያንን አገልግሎት በሬድዮ (በተለይ የምስራች ድምጽን)፣በመፅሄት፣እንዲሁምስብከቶቻቸውን በካሴት አጥብቄ እከታተል ነበር፤ የሃይስኩልተማሪ እያለው ትዝ ይለኛል፤ሃጢያት ያስጨንቀኝ፤ቅጀትያስጨንቀኝ ጀመረ።የምሰማቸው ስብከቾች ሁሉ ተቀደስ፤ኃጢያትአትስራ ነው፤የምሰማቸው መገለጦች ያሳቅቁኝ ነበሩ" አንድ ሴትአለሽ/አንድ ሰው አለህ በቅርቡ ይሄንና ያንን ሃጢያትሰርተሃል..." የሚሉ አሳቃቂ መገለጦች።እኔ በወቅቱ በአፍላ እድሜዬ ላይ እንደመገኘቴ በየቀኑ በተግባርባላመነዝርም ባሳብ ግን የምዳራቸው ሴቶች ነበሩ፤እናም "አንድሰው አለህ አመንዝረህ የመጣህ"የሚሉ መገለጦችን በሰማውቁጥር በጣም እሳቀቅ ነበር፤ከዛም ያው አንድ በተግባርየሚያመነዝር ሰው ስለማይጠፋ ያ ሰው ብድግ ሲል ሁፈይ እኔንአደለም ማለት ነው ብዬ እፅናናለው።ነገር ግን ለጊዜውነው፤ወዲያው ሃጢያቴ እንደጭጋግ ይከበኝና እጨነቃለው።በዛላይ ለሊት በጣም ያቃዠኛል።እፀልያለው።አፀልያለው። ነገር ግንሁሌም ኃጢያት ያስጨንቀኛል።ስለ ኃጢያቶቼ የንስሃ ፀሎትፀልያለው።ደስ ይለኛል።ግን ደሞ ወዲያው ተመልሼ ራሴንኃጢያት ስሰራ አገኘዋለው።ያኔ በቃ እኔ መቀደስ የማልችል ሰውመሆኔ ገባኝ።ባህሪዬ ጥሩ ስላልሆነ መፅሀፍ ቅዱስ መያዝ ራሱአፍራለው።የማፍረው በመፅሀፍ ቅዱስ ሳይሆን በራሴ ባህሪ ነው።አንዳንድ እኔ በደንብ የማውቃቸው ሴትና ወንድ ጓደኞቼ መፅሀፍቅዱስ ይዘው ሽር ብትን እያሉ ቸርች ሲሄዱ ሳይ በድፍረታቸውእደነቃለው።እኔ ግን ማስመሰልን እንደነሱ ስላልተካንኩበት ነውመሰለኝ የሃጢያቴን ብዛት ሳስብ ራሴን ለጌታ ያልተገባው አድርጌ አስብ ነበር።የ10ኛ ክፍል ውጤት መቶልኝ የፕሪፕ ተማሪ ስሆን፤የተለያዩጥያቄዎችን በማንሳት ስለ እምነቴ ራሴንና የተለያዩ አገልጋዮችንመጠየቅ ጀመርኩ።ከዛም ማቴ7:21-23ን አንድ ቀን ሳነብ አንድነገር ግልፅ ሆነልኝ።ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ስም አጋንንትአውጥተው፣በሽተኛ ፈውሰው፣ትንቢት ተናግረውና ብዙተሃምራትን አድርገ ገሃነም የሚገቡ ከሆነ እኔማ ብዬመዳኔን100% እርግጠኛ ሆኜ መናገር እንደማልችልገባኝ፤ከነዚህ ሰዎች አንዱ አለመሆኔን ማረጋግጥበት ነገርአልነበረም።በዛ ላይ ኃጢያት ያለበት ሰው በኢየሱስ ቢያምንምእንኳ መንግስተሰማይ መግባት እንደማይችል አውቃለው።የሚገርመው አንድ እንግዳ ሰው አግኝቶኝ በጌታ ነህ? ብሎቢጠይቀኝ "አዎ፤ተጠምቄያለው፤በክርስቶስ ፀድቂያለው" ብዬመልሳለው።አዬ መፅደቅ እቴ?! ኃጢያት በሰራው ሰሃት ሁሉ ግንአለመፅደቄ ኃጢያት ያለብኝ ሰው መሆኔ ቁልጭ ብሎይታየኛል።ሰዎች ድኛለው በጌታ ነኝ የሚሉት ቃላት ሁሉ ባዶ ይሆንብኛል።ከዛም በቃ አምሮዬ ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረመፅደቅ ማለት ምን ማለት ነው? በአዳም የገባው ኃጢያት ሚባለው የትኛው ነው? እኔ ብቻ ነኝ አጢያት መስራት ማቆምያቃተኝ ወይስ ሁሉም ሰው እንደኔ ነው?....ብዙጥያቄዎች።በዚህ መሃል ኢንትራንስ ውጤት መጥቶልኝ አ.አ.ዩገባው።እውነት እኔ ድኛለው?የሚለው ጥያቄዬ ተጠናክሮ ከኔ ጋር ካንፓስ ገባ።ትንሽ ግን "ፌሎ አቴንድ" ሳደርግ፤በለስላሳ ሙዙቃ ታጅበንስናመልክ ምናምን በቃ ሁሉን እረሳለው።ደስ ይለኛል።በእንባታጅቤ ያመለኳቸው ጊዜያቶችን አልረሳቸውም።የማልዋሻቹ ነገርግን ከፌሎ እንደወጣው ሁሉን እረሳለው።"የኔን አምልኮበእርግጥ እ/ር ይቀበለዋል?" ስል አስባለው።እንደ አብዛኞቹየፌሎ ጓደኞቼ ሻይ ቡና ብዬ ዶርሜ ገባና ላይብረሪ ሄጄካጠናው ቡሃላ ብዙ ጊዜ ስለእምነቴ አስባለው።እንዲህ እንዲህእያልኩ የመጀመሪያ አመት ፍሬሽ ማንነቴን ጨረስኩና ወደቤተሰብ ጋር ለመሄድ በተሰናዳሁበት ወቅት አንድ በጣምየምወደው ከክርስቲያን ቤተስብ የሆነ ዶርምሜቴ፤ዳኒ ወክእናድርግ ብሎኝ 6 ኪሎን ለቀን ወደ ፬ ኪሎ ማዝገም ጀመርን፤ድንገት ግን አራት ኪሎ ስንደርስ አንድ ወጣት መንፈሳዊ መፅሀፍበሃያ አያ ብር ብቻ! ሲል ጓደኛዬ  "ዳኒ ክረምቱንእንድናነበው ለምን መንፈሳዊ መፅሀፉን አንገዛውም"አለኝ።በነገራችን ላይ ጓደኛዬ ከእኔ እጅጉን የተሻለ አንባቢነው።ለመንፈሳዊ ነገሮች ያለው ጥማት እኔን እራሱ ያስከነዳል። በቃ መፅሀፉን ገስተን ሁለታችንም ወደየቤተሰቦቻችንመረሽን።ክረምቱን እኔ ትንሽ እሱ በደንብ አንብቦ ሁለተኛ አመትላይ ተገናኘን ። ከዛም አስቀድመን ተደዋውለን ስለነበር ለፌሎእንዲመቸን ከሌሎች ክርስቲያን ተማሪዎች ጋር አንድ ዶርምያዝን። ጓደኛዬ የኔንና የራሱን መፅሀፍ አንብቦ ጨረሰ።ሌላምተጨማሪ ራሱ ፀሐፊው የፃፈውን ሁለት መፅሀፍ አነበበ።ከዛም ፌሎ እርግፍ አድርጎ ተወና ከትምህርቱ በላይ መፅሀፍቅዱስን ማጥናት ጀመረ። እኔና ሌሎች ዶርም ሜቶቹ ፌሎእንዳይቀር መከርነው።አልሰማንም።ጭራሽ አንድ ቀን እኔ "እኛበጌታ የሆንን ሰዎች" እያልኩ ሳወራ።"ዝም በል ባክህ አንተአልዳንክም" ብሎ አስደነገጠኝ።"ኸረ ባኪህ እኔማ ድኛለው"አልኩት።"እኔም የዳንኩት አሁን ነው አትሸወድ" አለኝ።ኸረፍልስፍና ጀመርሽ? በማለትም ላልሰማው ጆሮዬን ደፍኜ ለአንድሴሚስተር ያህል ተከራከርኩት።ፌሎ ስሄድ ምሰማቸው ስብከቶችማስተዋል ጀመርኩ፤የህግ ት/ት እና ምድራዊ ስኬትን ሚያራግቡ ናቸው።አንድ ቀን እስቲ ዝም ብዬ በጭፍን ከምቃወመው ላዳምጠውብዬ የተረዳውን እንዲነግረኝ ጠየኩት እርሱም እንዲህ በማለትዳግም የምወለድበትን እውነታ ነገረኝ፦ እኛ ሰዎች የምንድነው አስቀድመን ስለኃጢያቶቻችን ስናውቅነው።የምንወለደው 12 ኃጢያቶችን በልባችን ይዘን ነው(ማር7:20-23) ።አለኝ ክፍሉን አወጣውና አነበብኩት።እውነትነው እኔ በዘመኔ ስሰራቸው የነበሩ ኃጢያቶች ናቸው።"እነዚህንኃጢያቶች በልብህ እንዳሉ ታምናለህ?"ሲለኝ።"በሚገባ" አልኩት። "እስከለተሞትህስ እንደምትሰራቸው ታምናለህ?" ሲለኝ አዎን አልኩት ።እኔ ግን በኢየሱስ አምናለሁ እኮ አልኩት። ታምናህ እኔም አምን ነበር ታውቃለህ ግን ዳግመኛ አልተወለድኩም ነበር ። አንተም ዳግመኛ አልተወለድክም ። ይህን ሲለኝ ትንሽ እንደመብሸቅ አልኩና " እንደውም ልንገርህ እኔ በስህተት መንገድ ከሆንኩ ኢየሱስ እንደጳውሎስ ተገልጦ ተመለስ ይበለኝ ። " አልኩት ያኔ እንዲህ አለኝ " እግዚአብሔር የሚናገረን እኛ በምንፈልገው መንገድ ሳይሆን እርሱ በፈለገው መንገድ ነው አለኝ ።ያኔ በልቤ ለማመን ወሰንኩ ። በዚህ ወቅት በዮሐንስ መልዕክት ላይ የተጻፈ አንድ የnlm መጽሐፍ አንብቤጨርሼ ነበር ።ስለብሉይ ኪዳን የስርየት ህግ ፣ስለህግ አላማ ፣ ስለኢየሱስ ጥምቀት ፣ ስለመስቀል ሞቱና ዘላለማዊ ስርየቱ ፣ ስለንስሃ ጸሎት አላስፈላጊነት፣ ስለሰው ጽድቅና የእግዚአብሔር ጽድቅ ልዩነት አወኩ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለየው ። ድኜ ቀረው ።ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ኃጢአቶቼን ሙሉ በሙሉ እንደወሰደልኝ አውቄ በልቤ ስቀበል ፤ኢየሱስ በመስቀል ተሰቅሎ በውኃና በደም በደሎቼን እንደደመሰሳቸው እንደተኮነነልኝ ሳምን ፤ኢየሱስ በትሣዬው አዲስ ፍጥረትና ኃጢአት አልባ እንዳደረገኝ በልቤ ሳምንድኜ ቀረው ።አሁን ላዳነኝ ለዚህ ጌታ ከወንድሞቼና እህቶች  ጋር  በመሆን የወንጌልን ስራ እየሰራው አለው።ስለሁሉ ጌታ ኢየሱስ የተመሰገነ  ይሁን! !Daniel Tesfaye Heramo, Ethiopia

    • Daniel Tesfaye Heramo
    • Ethiopia
    • 10/30/202139
  • ቁ.1

    Congregation song in Amharic

    Title: He has blotted all my sin.   He has blotted all my sinsHe has blotted all my iniquitiesI have now becameHis righteous, holy and perfect sonI have got the everlasting life through Him. The second song about praising God. Praise (8×)praise for His baptismPraise for His crucificationPraise Him for He has blotted all our sins.   The New Life Mission · ሐጢያቶቸን በሙሉ - He Has Blotted All My Sin

    • Kassahun Ayele
    • Ethiopia
    • 10/24/202147