Search

የቪዲዮ መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

ለመዳን አስቀድመን (ዘማሪ፦ መስፍን ብርሃኑ)

  • Teferi Oshine
  • Ethiopia
  • 06/02/2024 5123

ለመዳን አስቀድመን ኃጢአቶችንን
ማወቅ አለብን
ለመዳን አስቀድመን ክፋቶቻችንን
መገንዘብ አለብን።
(1)
ኃጢአት ሰሪ መሆናችንን
ሁል ጊዜ አመንዛሪ መሆናችንን
ሁል ጊዜ ሰራቂ መሆናችንን
እንድናውቅ ይፈልጋል እግዚአብሔር ራሳችንን።
(2)
ይፈልቃል ከእኛ ልብ በየቀኑ የኃጢአት ዓይነት
ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነት
መጎምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራት
ስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና፣ ምቀኝነት
እነዚህ ኃጢአት ይፈልቃሉ ዘውትር ከእርኩስ ልባችን
መዳን ከቶ አንችልም ካላወቅን ራሳችንን።
(3)
አውቃለሁ ኃጢአቴን፣ የኃጢአቴንም ደመወዝ
አመለጥኩኝ ባንተ ኢየሱስ ፣ ዳንኩኝ እኔ ከሞት መዘዝ
በውኃና በደም መጥተህ በአንዴ እኔን አጸደቅከኝ
በዘላለም ቤዛነትህ በአዲስ ኪዳን ምህረት ማርከኝ።
በዓመፃዬ ጽድቅህን አይቻለሁና
አመሰግናለሁ ኢየሱስ ይድረስ ለአንተ ምስጋና።
(4)
ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርግርነቱን
ይለውጥ ዘንድ ይችላል ወይ የተፈጥሮ ማንነቱን
ምንም ያህል ብንለፋ ከሰል አጥበን አናነጣም
በሕግ ኑሮ ብንታገል የልብ ኃጢአት ከቶ አይጠራም
ከቶም አንጸድቅም በጽድቃችን
በትንቢት ቃል ተጽፎ አለ የክፉ ዘር መሆናችን።
(5)
መዳኛችን የእኛ ቤዛ አዲስ ፍጥረት ምንሆንበት
በኢየሱስ ጥምቀትና በሞቱ ላይ ያለን እምነት
የእግዚአብሔር ጽድቅ ትምክታችን የሚያቆመን የቆምንበት
የዘላለም ተስፋችን ነው ብድራቱን ምናይበት።