Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 9-3] እግዚአብሄር ያዕቆብን መውደዱ ስህተት ነውን? ‹‹ሮሜ 9፡30-33››

‹‹ሮሜ 9፡30-33›› 
‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አህዛብ ጽድቅን አገኙ፡፡ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፡፡ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም፡፡ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፡፡ እነሆ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት እኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ፡፡››
 
 
ጌታችን ሁላችንንም ሲጠራ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሐጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፡፡›› (ማቴዎስ 9፡13) የራሳቸውን ጽድቅ ለሚከተሉ ሰዎች የደህንነት ስጦታ እንዳልተፈቀደላቸው መገንዘብ ይገባናል፡፡ ይህንን ለማስወገድም በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን አለብን፡፡
 
ሮሜ 9፡13 እግዚአብሄር ያዕቆብን እንደወደደ ኤሳውን ግን እንደጠላ ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በምስጋና ለተቀበሉ ሰዎች እግዚአብሄር የራሱ ሕዝብ የሚያደርጋቸውን የሐጢያቶች ስርየት ስጦታ እንደዚሁም በረከት ሰጥቶዋቸዋል፡፡ ሁላችንም የእርሱን ጽድቅ አውቀን በእግዚአብሄር ማመን አለብን፡፡
 
ለሁላችንም የተሰጠንን የእግዚአብሄር ጽድቅ ቃል ማወቅና መረዳት ይገባናል፡፡ ሰው ከሐጢያቱ መዳን ከፈለገ በመጀመሪያ የራሱን ጉድለቶችና ድክመቶች እንደዚሁም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማወቅ አለበት፡፡ የእርሱን ጽድቅ ማወቅና ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሄር የእርሱ ጽድቅ የሚያስፈልጋቸው ለሲዖል የታጩ ሰዎች እንደሆኑ ነግሮናል፡፡ ሐጢያቶቻችንን ማወቅና በሐጢያቶቻችን ምክንያትም በሲዖል ከሚደርስብን ቅጣት ማምለጥ የማንችልበት የእግዚአብሄር ቁጣ እንደሚገጥመን መገንዘብ ያስፈልገናል፡፡
 
ነገር ግን በጌታችን ጥምቀት፣ በመስቀል ላይ ሞቱና ትንሳኤው አማካይነት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በልባችን መቀበል እንችላለን፡፡ በዚህ ጽድቅ ማመን የሚችሉት የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያውቁ ብቻ ናቸውና፡፡ ይህ የሆነው የእግዚአብሄር ጸጋና ፍቅር ብዙ የሃይማኖት ሰዎች በተሳተፉባቸው የንስሐ ጸሎቶች ወይም የአምልኮ ሕይወት ሊገኙ የሚችሉ ስላልሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የሰጠው የሐጢያቶች ስርየት የእርሱን ጽድቅ ለሚያወድሱና ለሚያምኑ ሁሉ የተሰጠ ነው፡፡
 
ሁላችንም በውዴታ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለማመን ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ መቀበል ትፈልጋላችሁን? በእግዚአብሄርና በሕጉ ፊት ብቁ አለመሆናችሁን እመኑ፡፡ በሐጢያቶቻችሁ ምክንያት ከእግዚአብሄር ቁጣ በታች እንደሆናችሁና የእርሱ ጽድቅ እንደሚያስፈልጋችሁ ተገንዘቡ! በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስታምኑና በልባችሁ ስትቀበሉት የእግዚአብሄር ጽድቅ የእናንተ ይሆናል፡፡ ይህንን እውነት ልታውቁ ይገባል፡፡
 
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ልቦና ግራ የተጋባና ባዶ ሆኖ የተቆለፈ ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር አስተሳሰቦቻችን ከመጀመሪያው ግራ የተጋቡ እንደነበሩ ነግሮናል፡፡ (ዘፍጥረት 1፡2) የሰዎች አስተሳሰቦች ከመጀመሪያው ግራ የተጋቡት ለምንድነው? በእግዚአብሄር ላይ የተነሳው የወደቀው መልአክ አእምሮዋቸውን በማወክና ባዶ በማድረግ ሰዎች የእግዚአብሄርን የጽድቅ ቃል እንዳያምኑ ስላገዳቸው ነው፡፡ ሐጢያት ወደ ሰው ልብ የገባው ለዚህ ነው፡፡ (ዘፍጥረት 3፡1-8)
 
በእግዚአብሄር የተፈጠረ አንድ መልአክ በእግዚአብሄር ላይ እንደተነሳ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ይህ መልአክ በራሱ ጉልበትና ዕቅድ የእግዚአብሄርን ዙፋን ለመቀማት ሞከረ፡፡ አመጹ ሲከሽፍ ከታደለው ስልጣኑ ተባረረ፡፡ ከዚያም ይህ የወደቀ መልአክ የሰውን ዘር አታልሎ አሳሳተው፡፡ በእግዚአብሄርም ላይ እንዲነሳ አደረገው፡፡ ይህ መልአክ ሰይጣን ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህ ትምክህተኛ መልአክ አሁንም በሁሉም ዓይነት የትምክህትና የዓመጽ መንገዶች በምዕመናንና በማያምኑ ሰዎች ውስጥ ይሰራል፡፡ እርሱ ሰውን በማሳት የእግዚአብሄርን የጽድቅ ቃልና ሥልጣኑን ተገዳደረ፡፡
ዲያብሎስ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንዳያምኑ ሁልጊዜም ውሸቶችን እንደ መውጪያ መንገድ ያቀርባል፡፡ ብዙዎች በዲያብሎስ ተታልለው የራሳቸውን ጽድቅ ለማቆም ፍሬ አልባ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ እርሱ የሰው ዘር በሐጢያት እንዲወድቅ በማድረግ በተደናገረና ባዶ በሆነ አእምሮ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡
 
 

በእግዚአብሄር የተሰጠው የሐጢያቶች ስርየትና ጽድቅ፡፡ 

 
በሰይጣን ክፉ ፈተና በሐጢያት የወደቀው የሰው ዘር ደህንነት በሰው ጉጉት ወይም በራሱ ጽድቅ ላይ የተመረኮዘ አይደለም፡፡ ነገር ግን በጣም ብዙ ሰዎች የራሳቸውን ድካሞች ሳይገነዘቡ በእግዚአብሄር ላይ እያመጹ በከንቱ ከሐጢያቶቻቸው ለማምለጥ አጥብቀው ይሞክራሉ፡፡ እግዚአብሄር የራሳቸውን ጽድቅ የሚሹትን፤ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በራሳቸው ሰናይ ምግባሮች ለማግኘት የሚሞክሩትን ወቅሶዋቸዋል፡፡ ደህንነት ለእነዚህ ሰዎች አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ጽድቁን ለመስጠት የፈቀደው ሐጢያተኞች መሆናቸውን ለሚያውቁና እውነተኛውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ለሚያምኑ ብቻ ነው፡፡
 
የእግዚአብሄር ሉዓላዊ ፈቃድ በመሰረቱ ከሰው አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ ጳውሎስ ሰው በውጫዊ የሃይማኖትና የቤተክርስቲያን አምልኮ መገለጦች፣ በሌሊት ጸሎቶች፣ በማለዳ ጸሎቶች፣ በጾም፣ በስጦታ፣ በንስሐ ጸሎትና ወ.ዘ.ተ የላቀ ቢሆንም የራሱን ሐጢያቶች ማንጻት እንደማይችል ነግሮናል፡፡
 
የሕግ ሥራ ከሐጢያቶቻችን ሊያድነንና የእግዚአብሄርንም ጽድቅ የራሳችን ሊያደርግልን እንደማይችል እግዚአብሄር ነግሮናል፡፡ ምዕራፍ 9 ቁጥር 32-33 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፡፡ እነሆ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት እኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ፡፡››
 
ስለዚህ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለመቀበል በኢየሱስ ጥምቀትና በእግዚአብሄርና በሰው ዘር መካከል መስዋዕት በሆነበት የመስቀል ላይ ደሙ ማመን አለብን፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለማግኘት የራሳችሁን ጽድቅ መጣል ያለባችሁ መሆኑን መረዳት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ኢየስስን አዳኛችን አድርገን ስንመሰክር በነጻ የተሰጠንን የእግዚአብሄር ጽድቅ መጣል የለብንም፡፡
 
አሁንም ቢሆን ጌታ ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው የሚመሰክሩ ብዙዎች አሁንም ሐጢያተኞች ሆነው ቀርተዋል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ጽድቅ በሚገልጠው ወንጌል አላመኑምና፡፡ ሰዎች ሕጉን በመከተል የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማግኘት አይችሉም፡፡ በእግዚአብሄር የጽድቅ ቃል የሚያምኑ ሰዎች የራሳቸውን ጽድቅ ምኞት መጣል አለባቸው፡፡ ኢየሱስ በራሳቸው የሕግ ሥራዎች ደህንነታቸውንና የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለተከተሉ ሰዎች የዕንቅፋት ድንጋይ እንደሆነባቸው ልታስታውሱ ይገባል፡፡
 
በእግዚአብሄር የተሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው የሚያምኑትን የሚያድን እውነት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚከተሉትን የሚያጅብ መሆን አለበት፡፡ ለደህንነትና ለዘላለም ሕይወት እጅግ የሚያስፈልገው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ በተገለጠው የእግዚአብሄር የጽድቅ ቃል ማመን ነው፡፡ ይህ ቃል በክርስቲያኖች መካከል የሐጢያቶችን ስርየት መቀበል የማይችለው ማን እንደሆነ ይገልጥልናል፡፡ በዚያው ጊዜም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚቀበሉ የመሆናቸውን እውነት ያስተምረናል፡፡
ስለዚህ ትክክለኛው እምነት እግዚአብሄር የተወሰኑ ሰዎችን ያለ ቅድመ ሁኔታ በመልቀም ወደ ሲዖል እንደሚወረውራቸው ያልወሰነ የመሆኑን እውነታ መረዳት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሄር በእርግጥ አንዳንዶችን ወድዶ ሌሎችን በግብታዊነት ጠልቶ ከሆነ ሰዎች ጽድቁን አያከብሩትም፡፡
እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ሐጢያተኞችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን የደህንነትን ጽድቅ ሕግን በመደንገግ የእርሱን ፍቅር የመልበስ ታላቅ በረከት ሰጥቶናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሄር ጽድቅ በተነገረው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ፊት የራሱን ጽድቅ መጣል አለበት፡፡ እግዚአብሄር ጽድቁን የሰጠው በእርሱ ለሚያምኑበት ብቻ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ሰዎች በራሳቸው ጽድቅ ራሳቸውን ከሐጢያት ማዳን ይችሉ ዘንድ አልፈቀደላቸውም፡፡ ማንም ሰው በኢየሱስ እንደሚያምን ቢናገርም የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የእግዚአብሄር ጽድቅ መሆኑን ሳያምን ይህንን ጽድቅ አይቀበልም፡፡ (ዮሐንስ 3፡1-8)
 
ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ የእግዚአብሄር ጽድቅ ሆነዋል፡፡ ኢየሱስ የራሳቸውን ጽድቅ ለሚከተሉ የማሰናከያ ዓለት የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ የሚያምኑ ምዕመናን የራሳቸውን ጽድቅ በሚከተሉበት ጊዜ የእግዚአብሄርን ጽድቅ እየረገጡ እንደሆኑ መገንዘብና መረዳት አለባቸው፡፡ ሐጢያተኛ በእግዚአብሄር ጽድቅ ሳያምን የሰማይን በር አልፎ መግባት አይችልም፡፡ እኛ በኢየሱስ ያመንን በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የሐጢያቶቻችንን ስርየት መቀበል አለብን፡፡
 
ወደዚህ ምድር የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ የሐጢያተኞች አዳኝና በራሱ የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ኢየሱስ በውሃውና በመንፈሱ ቃል ሐጢያቶቻችንን ይቅር ባለው በዚህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ከልባችን ማመን አለብን፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ምዕመናን እርሱ ከዮሐንስ የተቀበለውን ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን የእግዚአብሄር ጽድቅ አድርገው ማመን አለባቸው፡፡ ሰማይ መግባት የሚችሉት በተጻፈው የውሃና የመንፈስ ቃል የሚያምኑ ብቻ ናቸው፡፡
        
 

የቁጣ ዕቃዎችና የምህረት ዕቃዎች ሆነን እንደተከፋፈልን ተነግሮናል፡፡ 

 
ጌታ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?›› (ማቴዎስ 16፡26) ሰው የዘላለምን ሕይወት የሚያጣ ከሆነ ማንም ይሁን በዚህ ዓለም ላይ ያገኛቸው ክንውኖች ከንቱ ናቸው፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ደም ካላመነ ዓለምን ወይም አጽናፈ ዓለማትን ሁሉ ድል ቢያደርግ ምንም ጥቅም የለውም፡፡
 
የሥነ መለኮት ትምህርቶች ምንም ያህል በከፍተኛ ደረጃ ቢዳብሩም ይህንን ጽድቅ መቀበልና ማመን የሚቻለው የእግዚአብሄርን ጽድቅ በሚፈጸመው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ምዕመናን ከሐጢያቶቻቸው ነጻ መውጣት የሚችሉት የእግዚብሄርን ጽድቅ በማመን ሲቀበሉት ብቻ ነው፡፡
 
በዚህ ዘመን በእግዚአብሄር ጽድቅ እናምናለን የሚሉ ሰዎች በእያንዳንዱ የማለዳ ጸሎት ስብሰባ ላይ ለሐጢያቶቻቸው የሚያለቅሱ ምዕመናኖችን ማየት የተለመደ ነው፡፡ እነርሱ በተጨባጭ በእግዚአብሄር ጽድቅ አያምኑም፡፡ በእርሱ ጽድቅ ውስጥ ባለው ደህንነት የማያምን እንዲህ ያለ እምነት የስም እምነት እግዚአብሄርን የሚያስቆጣ እንጂ የሚያስደስት እንዳልሆነ መረዳት አለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በመቃወማቸው የእርሱ ጠላቶች ሆነው ይቀራሉ፡፡
 
ዮሐንስ 3፡5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› በውሃውና በመንፈሱ ወንጌልና በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን የሐጢያት ችግሮቻችሁን ሁሉ መፍታት የሚገባችሁ ለዚህ ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሐጢያቶችን ስርየትና ጽድቁን ሊሰጣችሁ የሚችል የእግዚአብሄር ጽድቅ ሆንዋል፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያጸድቃችሁ የእምነት ዓይነት እንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ ይህንን ጽድቅ የያዘውን የውሃውንና የመንፈሱን ቃል መከተልና ማመን አለባችሁ፡፡ ልባችሁ በእግዚአብሄር ጽድቅ እንዲሞላ ከፈለጋችሁ የራሳችሁን ጽድቅ መጣል እንደሚገባችሁም መገንዘብ አለባችሁ፡፡ ጳውሎስ ለእስራኤሎችና ለአሕዛቦች የነገራቸው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማግኘት ከፈለጉ የራሳቸውን ጽድቅ ከመከተል መቆጠብ የሚገባቸው መሆኑን ነው፡፡
እግዚአብሄር አብርሃም በአምላክ ጽድቅ በማመኑ የእምነቱ ፍሬ ይሆን ዘንድ ልጅን ሰጠው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ተገልጦዋል፡፡ በጽድቅ ቃል የሚያምን ማንኛውም ሰው ጻድቅ ሰው ይሆናል፡፡ የይስሐቅ ሚስት ርብቃ ከይስሐቅ መንታዎችን ጸነሰች፡፡ እነርሱ ከመወለዳቸው ወይም በጎ ወይም ክፉ ሳያደርጉ ‹‹ታላቁ ለታናሹ ይገዛል›› ተብሎ ተነገራት፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ምንባብ አንብበው እግዚአብሄር ቅን አምላክ አይደለም በማለት ደምድመዋል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ ድምዳሜ ነው፡፡
 
ይህ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሄር ያዕቆብና ኤሳው ገና በርብቃ ማህጸን ውስጥ ሳሉ የወደፊት እምነታቸውን አስቀድሞ ስላወቀ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ምስጢር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ተሰውሮዋል፡፡ ኤሳው በራሱ በጎ ምግባሮች የሚመካ ሰው ስለነበር እግዚአብሄር በእርሱ ጽድቅ ከማመን ጋር ምንም የሚያገኘነው ነገር እንደሌለ አየ፡፡ እግዚአብሄር እርሱን የጠላው ለዚህ ነው፡፡ በሌላ በኩል ያዕቆብ በእግዚአብሄር ጽድቅ ያመነና ክብሩን ሁሉ ጠቅልሎ ለእርሱ ብቻ የሰጠ ሰው ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እርሱን ከመውደድ በቀር ሌላ ምንም ማድረግ አልቻለም፡፡
 
ስለዚህ እግዚአብሄር ያዕቆብን የወደደውና ኤሳውን የጠላው በእውነት ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ እግዚአብሄር በአምላክ ጽድቅ ሳያምን በራሱ ጉልበት እንደተመካው እንደ ኤሳው ያሉ ሰዎችን አይወድም፡፡ ነገር ግን ድክመቶቹን አውቆ በራሱ ጽድቅ ብቻ እንዳመነው እንደ ያዕቆብ ባሉ ሰዎች ይደሰታል፤ ይወዳቸውማል፡፡
 
ሰዎች ብዙውን ጊዜ እግዚአብሄር እንዴት በይስሐቅ ላይ ይህንን ያደርጋል ብለው በመጠየቅ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በተሳሳተ መንገድ ይረዳሉ፡፡ እግዚአብሄር አንዳንዶቹን ወድዶ ሌሎቹን ከጠላ በእግዚአብሄር ዘንድ አንድ የተሳሳተ ነገር መኖር አለበት ብለው ያስባሉ፡፡ በኢየሱስ ለማመንም አሻፈረኝ ይሉ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም እርሱንም ፍትህ አልባ አምላክ አድርገው ይመለከቱታልና፡፡
    
ነገር ግን እግዚአብሄር እንዴት ዓመጸኛ ሊሆን ይችላል? ሰው እግዚአብሄር ዓመጸኛ ነው ብሎ የሚያስብ ከሆነ ይህ ስለ እግዚአብሄር ጽድቅ ትክክለኛ ግንዛቤ እንደሌለው የሚያንጸባርቅ ብቻ ነው፡፡ እንዲያውም በእግዚአብሄር ፊት የከፋ ስህተት የሚሰሩት በእግዚአብሄር ጽድቅ ባለማመን የእርሱን ጽድቅ በራሳቸው ጽድቅ የሚሸፍኑ ሰዎች መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ጽድቁን በእግዚአብሄር ጽድቅ ፊት በመጣል በውሃውና በመንፈሱ ወንገል ቃል ማመን አለበት፡፡
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ በያዘው የደህንነት ቃል ለማመን ብቸኛው መንገድ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ዓመጸኛ ነው የሚለው አባባል በእርሱ ዕቅድና ቅድመ ውሳኔ ውስጥ የተቀመጠውን ጥልቅ የእግዚአብሄር አሳብ ከማያውቀው ድንቁርናችሁ የመነጨ የአስተሳሰባችሁ ብልጭታ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር የጽድቅ ዕቅድ የእርሱን ጽድቅ በፊታችን መግለጥ ነበር፡፡ እግዚአብሄር የመንታዎቹን የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስቀድሞ ስላወቀ በዚያ መሰረት በጽድቁ አቅዶ ያመነውን ለመውደድ ወሰነ፡፡
 
በእርሱ ዕቅድ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሄር ጽድቅ መረዳትና ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሄር በያዕቆብና በኤሳው መካከል የጠራው ማንን ነው? ጌታችን ‹‹ጻድቃንን ሳይሆን ሐጢያተኞችን ለመጥራት እንደመጣ›› ተናግሮዋል፡፡ በሌላ አነጋገር የእግዚአብሄር ጽድቅ እንደ ያዕቆብ ያሉ ሰዎችን ይጠራል፡፡ ኤሳው ግን ለእግዚአብሄር የጽድቅ ጥሪ ምላሽ ካለመስጠቱም በላይ በራሱ ጽድቅም ተመክቶ ነበር፡፡ ኤሳው ሲጠላ ያዕቆብ ግን ለእግዚአብሄር የጽድቅ ጥሪ ምላሽ የሰጠ ሰው የሖነው ለዚህ ነበር፡፡
 
እነዚህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍቅር በሚያውቀውና በሚያምነው እምነት ውስጥ ሆነው ግንዛቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍቅር በትክክል ሳያውቅ የእግዚአብሄርን የቅድመ ውሳኔ እንቆቅልሽ ለመፍታት የሚሞክር ሰው ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይወድቅና ይጠፋል፡፡
 
እግዚአብሄር ቅድመ ውሳኔን ያስቀመጠው የጽድቁን ፍቅር ለመግለጥ ነው፡፡ ያዕቆብ ድክመቶቹን አውቆ በእግዚአብሄር የጽድቅ ቃል ያመነ ሰው ነበር፡፡ እግዚአብሄር ያዕቆብን መውደዱና ኤሳውን መጥላቱ ትክክል ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቀና ዕይታ ሰው ሁሉ ቁጣው ይገባዋል፡፡ ነገር ግን በጽድቁ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ደህንነቱን ሰጥቶናል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የእርሱን ምህረት የለበሱ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ ደህንነታቸው አድርገው የሚያምኑ እንጂ በራሳቸው ጽድቅ የሚመኩ ሰዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች ‹‹በሐጢያቶቼ ለሲዖል መኮነን ይገባኛል፡፡ ጌታ አምላክ ሆይ ማረኝ፡፡ ጽድቅህንም አስተምረኝ›› የሚሉ ሰዎች ናቸው፡፡
 
እግዚአብሄር የሐጢያቶችን ስርየት የሚሰጠው በእርሱ የጽድቅ ፍቅር ለሚያምኑ ሰዎች ብቻ ነው፡፡ እርሱ አስቀድሞ ለእኛ የገለጠው ልጆች የምንሆንበት የእግዚአብሄር ዕቅድ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያዕቆብን የወደደበትንና ኤሳውን የጠላበትን ዕቅድ በተሳሳተ መንገድ መረዳት የለባችሁም፡፡ በማናቸውም አጋጣሚ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በትክክል ሳትረዱ ቀርታችሁ ከሆነ በእርሱ ጽድቅ ውስጥ ባለው የዕግዚአብሄር የጽድቅ ፍቅር ደግማችሁ ለማመን ጊዜ አሁን ነው፡፡
 
እኔ በእግዚአብሄር ጽድቅ አምናለሁ፡፡ የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍቅር በትክክል የሚያስተውሉ ሰዎች በእርሱ ጽድቅ ውስጥ ባለው የእግዚአብሄር የጽድቅ መሰናዶ በትክክል ያምናሉ፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓለም ላይ የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍርድ በትክክል ተረድተው የሚያምኑበት ቢኖሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች እግዚአብሄርን በተሳሳተ መንገድ በመረዳት ተቀስፈዋል፡፡
 
እነዚህ ሰዎች እግዚአብሄር ኤሳውን እንደጠላ ስለሚናገር አንዳንድ ሰዎች ዕጣ ፈንታቸው በእግዚአብሄር መጠላት ይመስል በግብታዊነት በእርሱ ተጠልተዋል ብለው ያስባሉ፡፡ አምላካችን ግን እንዲህ ያለ ጨካኝ አምላክ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ትክክለኛ ዳኛ ነው፡፡ በጽድቁም ጻድቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን የጽድቅ ምህረቱንና ፍቅሩን ሊሰጠን ይፈልጋል፡፡
 
እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጽድቁን ሊሰጥ ፈለገ፡፡ በጽድቁ ለሚያምኑት ምህረቱን አልብሶ ልጆቹ አድርጎዋቸዋል፡፡
 
ይህ እውነት ኢየሱስ እንዲህ ብሎ በተናገረበት በአዲስ ኪዳን በማቴዎስ 9፡12-13 ላይ ተገልጦዋል፡፡ ‹‹ሕመምኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድሃኒት አያስፈልጋቸውም፡፡ ነገር ግን ሄዳችሁ ምህረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ተማሩ፡፡ ሐጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፡፡›› ጤነኞች ባለ መድሃኒት የማያስፈልጋቸው መሆኑን ማሰባቸው ግራ ያጋባቸው ይሆናል፡፡ ሰዎች ጤነኛ በሆኑ ጊዜ የሐኪሞችን አስፈላጊነት እንደማይረዱ ሁሉ በእርሱ በማመን የእግዚአብሄርን ጽድቅ በልባቸው የመቀበሉን ጠቀሜታም አይረዱም፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውን ጽድቅ በመከተል ይባዝናሉ፡፡
 
ሐጢያተኞች ግን የራሳቸውን ጽድቅ ትተው በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን አለባቸው፡፡ እናንተ በእግዚአብሄር ፊት ያዕቆብን ወይም ኤሳውን ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ማን መሆን ትፈልጋላችሁ? የእግዚአብሄር ሽልማትና ቅጣት በእግዚአብሄር የጽድቅ ደህንነት በማመናችሁ ወይም በአለማመናችሁ ውሳኔ ላይ ይመሰረታል፡፡
  
 
እግዚአብሄር የተሳሳተው ምንም ነገር የለም፡፡ 
 
እያንዳንዱ ሰው በፍጥረቱ ተፎካካሪ ፍጡር ነው፡፡ አንዳንዶች በጣም የተማሩና የተሳካላቸው አንዳንዶቹም ለሌሎች በጎ ምግባሮችን ያደረጉ ሰዎች ይሆኑ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ጽድቅ መረዳትና እምነት ከሌላቸው በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው --እናንተና እኔ እስራኤሎችም ሳይቀሩ -- በእግዚአብሄር ፊት ለሲዖል የተኮነንን ነበርን፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ በጥረቶቻችን፣ በሥራዎቻችን ወይም በብርታታችን ሳይሆን በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመናችን ብቻ ጸድቀናል፡፡
 
እግዚአብሄር ሳያዳላ ለእያንዳንዱ ሰው በተገቢው ሁኔታ የጽድቅ ፍቅሩን ስለሰጠ በዚህ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ መዳን ይችላሉ፡፡ እግዚአብሄር እናንተ እንደምታስቡት ዓመጸኛ አምላክ አይደለም፡፡
 
ሰው የእግዚአብሄርን የደህንነት በረከት የመቀበሉ ጉዳይ ይህንን በረከት ይቀበላል ወይስ አይቀበልም በሚለው ውሳኔው ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የቁጣ ዕቃዎች ሲሆኑ ሌሎች የምህረት ዕቃዎች የሚሆኑት ለዚህ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ያዕቆብ የምህረት ዕቃ ሲሆን ኤሳው ግን የቁጣ ዕቃ ሆነ፡፡
 
ነገር ግን አንዳንድ የሥነ መለኮት ምሁራንና መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ እግዚአብሄርን ያንጓጥጣሉ፡፡ ‹‹ተመልከቱ! እግዚአብሄር ፈርዖንን የቁጣ ዕቃ አላደረገውምን? ያዕቆብንና ኤሳውን ተመልከቱ! ሸክላ ሠሪው ያደረገውን ተመልከቱ! እግዚአብሄር አንድን ሰው ገና ከጅማሬው የክብር ዕቃ አላደረገውምን? ይህ የዕጣ ፈንታ ጉዳይ ብቻ ነው!›› ይላሉ፡፡ ሥነ አመክንዮዋቸው የሚከተለው ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከመወለዳቸው በፊት አስቀድሞ የእግዚአብሄር ልጆች ለመሆን ተመርጠዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ለመልበስ አስቀድመው የተወሰኑትና የተመረጡት እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄር ልጆች ሲሆኑ ሌሎቹ ግን ለሲዖል ታጭተዋል፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ ጥቃት የደረሰበት በዚህ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ግን ጽድቁን ለሰው ሁሉ ሰጥቶዋል፡፡ በዚህ የሚያምኑትንም ያለ አንዳች አድልዎ መርጦዋቸዋል፡፡
 
ከዚህ ቀደም ብሎ የእርሱ ሕዝብ ባልነበርን ጊዜ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ጸደቅን፡፡ በቃሉ አማካይነት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ስለጸደቅን እግዚአብሄር እምነታችንን ሊቀበለው ይችላል፡፡ የእግዚአብሄርን አስገራሚ ሐይል የሚያሳየው የወንጌል እውነት ይህ ነው፡፡
 
ከቀድሞውም እግዚአብሄር በውስጣችን አልነበረም፡፡ እርሱንም አናውቀውም፡፡ ሁላችንም ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ግን የእርሱ ሕዝብ ሆነናል፡፡ እኛ የምናምንበት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ጎዶሎ ሳይሆን ምሉዕና ፍጹም ወንጌል ነው፡፡ ጽድቁን ልናገኝ የምንችልበትን እውነት ስለሰጠን እግዚአብሄርን ልናመሰግነው ይገባናል፡፡
 
ሕይወታችን በችግሮች የተሞላ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የሐይሉን ታላቅነት ስላስተማረን የእግዚአብሄርን ጽድቅ መርሳት የለብንም፡፡ በመላው ዩኒቨርስ ውስጥ እጅግ ደስተኛው ሰው የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሄር ለምናምን ሰዎች ስላሴ አምላክ የምህረት አባት ነው፡፡ እርሱ ቅዱስ አምላካችን ነው፡፡ እርሱ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምነውን እምነት በእርሱ በምናምነው ሰዎች ነፍስ ውስጥ አስቀምጦታል፡፡ የእርሱን ጽድቅ በማወቃችንና በማመናችን የእግዚአብሄር ልጆችና የጸጋውና የበረከቶቹ ተቀባዮች አድርጎናል፡፡
 
ሆኖም ብዙ ሰዎች በጎ ምግባሮችን ለማድረግ በጥረቶቻቸው ተጠምደዋል፡፡ ስጦታዎችን መስጠት፣ ቤተክርስቲያንን በፈቃዳቸው ማገልገል፣ ከሌሎች ጋር በመፎካከር ለቤተክርስቲያን ከፍተኛ ገንዘብ ስጦታዎችን ማበርከት፣ እነዚህ ሁሉ በጎ ምግባሮች ናችሁ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ብቻቸውን ሊያድኑዋችሁ አይችሉም፡፡ በእነዚህ ሥራዎች ላይ ብቻ ማተኮር በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመናችሁን የሚጠቁም ሳይሆን የራሳችሁን ጽድቅ የምትከተሉ መሆናችሁን የሚጠቁም ነው፡፡ በራሳቸው የሥጋ ጥረቶች የተጠመዱ ሰዎች እግዚአብሄርን ይቃወማሉ፡፡ በእነዚህ የሥጋ ነገሮች የሚጠመዱ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ የማያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡
 
የእግዚአብሄር ደህንነት የተሰጠው በእርሱ ጽድቅ ለሚያምኑት እንጂ ለሚሮጡ እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ይህ ጽድቅ ሊገኝ የሚችለው በመሃሪው አምላካችን በማመን ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተወደድነው በሥራዎቻችን አይደለም፡፡ የእርሱን መሃሪ ፍቅር የምንቀበለው በእርሱ ጽድቅ በማመን ብቻ ነው፡፡ እውነተኛ እምነት ሙሉ በሙሉ የሚያርፈው የእግዚአብሄርን ጽድቅ አውቀን በማመን ወይም ባለማመን ላይ የሆነው ለዚህ ነው፡፡
 
እኛ ግን ከመጀመሪያው የማንረባ ሰዎች አልነበረንምን? ነገር ግን በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመናችን የከበርን ሰዎች አልሆንምን? በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን አሁን የእግዚአብሄር ልጆች በመሆናችን እውነታ በመመካት እምነታችንን እስከ መጨረሻው ድረስ መጠበቅ እንችላለን፡፡
 
በዓለም ላይ ክፋትን የሚያደርጉና እግዚአብሄር የለም የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እግዚአብሄር ግን እኛን የማረን በጽድቁ ስላመንን ነው፡፡ እኛ በእርግጥም በእግዚአብሄር ፊት የከበርን ነን፡፡ በእግዚአብሄር መመካታችንም ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ ሳለን ችግሮችና መከራዎች ይገጥሙን ይሆናል፡፡ ነገር ግን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ባለጠጎችና ደሰተኞች ነን፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ መከተልና ኢየሱስን ከፍ ማድረግ ይገባናል፡፡
 
እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን በሙሉ በፊቱ ልጆቹ፣ ሐጢያት አልባዎች ጻድቃንና ፍጹማን አድርጎዋቸዋል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ለማን እንደተሰጠ መገንዘብ አለብን፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ጉድለቶቻችንን ሁሉ ተገናኝቶ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አንጽቷል፡፡ በዚህ እውነት ማመን አለማመናችሁ ሙሉ በሙሉ በእናንተ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ እናንተም በእግዚአብሄር ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ድናችኋል፡፡ ታዲያ ምን ታደርጋላችሁ? ለማመን ያላችሁን ውሳኔ ለነገ ታስተላልፉታላችሁን?
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡