Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[2-7] የኒቆላውያን ትምህርት ተከታዮች፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 2፡12-17 ››

የኒቆላውያን ትምህርት ተከታዮች፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 2፡12-17 ››
 
 
የበለዓም መንገድ፡፡ 
 
እዚህ ላይ በእስያ ከሚገኙት ከሰባቱ ቤክርስቲያኖች መካከል የጴርጋሞን ቤተክርስቲያን የኒቆላውያንን ትምህርት የሚከተሉ አንዳንድ አባሎች እንደነበሩዋት ተነግሮዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ዓለማዊ ሐብትና ዝና በማካበት ፍላጎት ብቻ የተወጠሩ ስለነበሩ ነፍሳትን የማዳን ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ በተለይ አገልጋዮች መጨረሻቸው ይህንን የኒቆላውያንን ትምህርት መከተል እንዳይሆን በጣም መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ በለዓም ቅዱሳን ዓለምን እንዲያመልኩ በማድረግ ወደ ጥፋት መራቸው፡፡
 
እግዚአብሄር ድል ለሚነሱት የተሰወረውን መናና ነጩን ድንጋይ እንደሚሰጥ የተስፋ ቃሉን ሰጣቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ ማለት ዓለምን የሚከተሉ መጋቢዎች መጨረሻቸው መናውን ማጣት ይሆናል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ መና ማለት ‹‹ተወዳጁ የእግዚአብሄር ቃል›› ማለት ነው፡፡ የተሰወረውን መና ማጣት ማለትም በቃሉ ውስጥ የተሰወረውን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማጣት ማለት ነው፡፡
 
ዳግመኛ የተወለዱ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ዓለምን ሲከተሉ የቃሉን መገለጥ ያጣሉ፡፡ ይህ የሚያስፈራ ትዕይንት ነው፡፡ ይህ አደጋ ያስፈራኛል፡፡ እናንተም ልትፈሩት ይገባል፡፡ እግዚአብሄር ድል ለነሱት የተሰወረውን መናና ነጩን ድንጋይ እንደሚሰጣቸው ነግሮናል፡፡ ነገር ግን ከዓለም ጋር በመስማማት ለዓለማዊ ዝና ወይም ተድላ የሚማረኩ ለዓለም ያደሩ ሰዎች ግን ይህ መና አይሰጣቸውም፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፡፡ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፡፡ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለው አዲስ ስም ተጽፎአል፡፡›› የእግዚአብሄር ቃል እንደምን እውነት ነው! ዓለምን የሚወዱ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ባለማመናቸው ከሐጢያቶቻቸው ያልዳኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ክርስቶስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ ይቅር ያላቸው የመሆኑን እውነት የማያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡
 
አንዳንዶች በኢየሱስ የሚያምኑት በእውቀት ደረጃ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻቸውን ስለወሰደላቸው እንደጸደቁ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስለሌለ እምነታቸው ባዶ ነው፡፡ ይህ በእውቀት ላይ የተመሰረተ እምነት ነው፡፡ አንድ ሰው በትክክል ደህንነትን ተቀብሎ ከሆነ የዓለምን ነገሮች -- ዓለማዊ ዝናን፣ ክብርን፣ ሐብትን ወይም ሥልጣንን ተዋግቶ ማሸነፍ አለበት፡፡ ዓለምን ማሸነፍ ማለት ዳግመኛ እንድንወለድ የፈቀደልንን የእግዚአብሄርን ቃል አጥብቆ መያዝ፣ የዚህን ዓለም ሐብትና ክብር የሚሹትን መታገልና በልባችን ውስጥም መንፈስ ቅዱስን መጠበቅ ነው፡
 
እግዚአብሄር የዳኑትንና በልባቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚያድርባቸውን ሰዎች ስሞች በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እንደሚጽፍ ነግሮናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ‹‹ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፡፡ እነሆ አሮጌው አልፎዋል፤ እነሆም ሁሉ አዲስ ሆንዋል፡፡›› ዳግመኛ የተወለዱና መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው የሚያድርባቸው ሰዎች እነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ በፊት ሆነው እንደነበሩት እንዳይደሉ ያውቃሉ፡፡ አሮጌው ማንነታቸው አሁን በውሃውና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በማመን አዲስ ፍጥረት እንደሆነ ራሳቸው ይገነዘባሉ፡፡ በእምነታቸውም ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እንደተጻፈ ያውቃሉ፡፡ የተሰወረውን የእግዚአብሄር መና ማየት የሚችሉት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ እነዚህ የእግዚአብሄር አገልጋዮችና ቅዱሳን የእግዚአብሄርን የእውነት ቃል ማለትም ያማረውን የእግዚአብሄር ድምጽ የሚሰሙት በዚህ መንገድ ነው፡፡
እስራኤሎች ወደ ተስፋይቱ የከንዓን ምድር ከመግባታቸው በፊት አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይቅበዘበዙ በነበረበት ጊዜ መና ተሰጥቶዋቸው ነበር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መሰረት መናው እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ነበር፡፡ እስራኤሎች በማለዳ ሲነሱ የመኖሪያቸው መሬት ሌሊቱን ሁሉ በረዶ የጣለ ይመስል በመና ተሸፍኖ ነበር፡፡ እስራኤሎች መናውን ሰብስበው በማለዳ ተመገቡት፡፡ ይህ የየቀን ምግባቸው ነበር፡፡ ምናልባት ጠብሰውት ይሆናል፡፡ ምናልባት ቀቅለውት ይሆናል፡፡ ወይም ጋግረውት ይሆናል፡፡ የሆኖ ሆኖ እስራኤሎች 40 ዓመት በምድረ በዳ ሲቅበዘበዙ ቋሚ ምግባቸው ይህ ነበር፡፡
 
መናው ልክ እንደ ድንብላል ዘር ትንሽዬ ስለነበር አንዲት ቅንጣት መና በመብላት የሚጠግብ ሰው የለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ሌሊቱን በቂ መና ስለሰጠ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ለቀኑ የሚያስፈልገው ተሟልቶለታል፡፡ ከአንድ ቀን የሚያንስ ወይም የሚበልጥ አልተሰጣቸውም፡፡ ምክንያቱም መናውን ማቆየት አይቻልምና፡፡ በስድስተኛው ቀን ግን እግዚአብሄር በሰንበት ቀን መናውን እንዳይሰበስቡ ለሁለት ቀን የሚበቃቸውን መና ሰጣቸው፡፡
 
 
የሕይወት እንጀራ፡፡ 
 
የእግዚአብሄር ቃል መናችን፤ የሕይወት እንጀራችን ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ለነፍሳችን የሚሆን እንጀራ ማለትም የሕይወት እንጀራ አለ፡፡ በአንድ ምንባብ ውስጥ ትልቅ እንጀራ ታገኛላችሁ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ታላቁ የእግዚአብሄር ፈቃድ በመጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ ውስጥ እጅግ ኢምንት በሆኑት ዝርዝሮችም ውስጥ ሳይቀር ይገኛል፡፡
 
ከዓለም ጋር ስምምነት ላላደረጉ የእግዚአብሄር አገልጋዮችና ቅዱሳን እግዚአብሄር የሕይወትን እንጀራ ሰጥቶዋቸዋል፡፡ ለእያንዳንዳችንም ይህንን ሥጋዊና መንፈሳዊ ረሃባችንን የሚያስታግስ የዕለት እንጀራ መስጠት ቀጥሎዋል፡፡
እስራኤሎች ምድረ በዳው ለምግባቸው የሚሆን ምንም ነገር ባያበቅልም በዚህ መና ምክንያት በ40 የመቅበዝበዝ ዓመታት ወቅት ፈጽሞ አልተራቡም፡፡ ልክ እንደዚሁ እግዚአብሄር የኒቆላውያንን ሥራ ለናቁት የሚመገቡትን የተሰወረ መና እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል፡፡ እንደ ሐብትና ሥልጣን ያሉትን ዓለማዊ ነገሮች ለማይሹ የእግዚአብሄር አገልጋዮችም እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ዳግመኛ እንዲወለዱ የፈቀደላቸውን ያማረ ቃል የሕይወትን ቃል ሰጥቶዋቸዋል፡፡
 
በዘመኑ የክርስትና ማህበረሰባት ውስጥ የተንሰራፋውን የኒቆላውያንን ምግባር መጥላትና መተው አለብን፡፡ ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎችን እምነት መከተል የለብንም፡፡ ከዓለም ጋር ለመስማማትም አሻፈረኝ ማለት አለብን፡፡ ሥጋችን የሥጋን ነገሮች መሻቱና መንፈሳችንም የመንፈስን ነገር መሻቱ የእግዚአብሄር ሕግ ቢሆንም የኒቆላውያንን ትምህርት ግን እምቢ ማለት፣ ከዓለም ጋር የሚመሳሰሉ ምግባሮችንም ሁሉ መጥላትና እግዚአብሄር የሰጠንን የእውነት ቃል በማመን የእግዚአብሄርን መና መመገብ አለብን፡፡ አሁን ጻድቃን እንደሆንንና በልባችን ውስጥም መንፈስ ቅዱስ እንዳለን በማወቅ ሁላችንም በእምነት መኖር አለብን፡፡
 
ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ዓለምን መዋጋት አለባቸው፡፡ ኒቆላውያንን መዋጋት አለባቸው፡፡ እናንተም በሚገባ እንደምታውቁት በጣም ብዙ ሰዎች፤ የዘመኑ መጋቢዎች የራሳቸውን ሐብትና ዝና ይሻሉ፡፡ ራሳቸውን ያወድሳሉ፡፡ ከዓለም ጋር ይስማማሉ፡፡ በዓለማዊ መንገዶችም ስኬታማ ለመሆን ይሞክራሉ፡፡ እነዚህን ሐሰተኛ ነቢያቶች መዋጋት አለብን፡፡
 
እኛ የራሳችን ሥጋ አለን፡፡ ስለዚህ ዓለማዊ ትርፎችን የመሻት ፍላጎት አለን፡፡ ነገር ግን በውስጣቸው መንፈስ ቅዱስ ያላቸው ሰዎች በልባቸው ዓለምን መከተል እንደማይችሉ ማወቅ፣ የዓለምን ነገሮች መካድና በእምነት ብቻ መኖር አለባቸው፡፡ ልባችሁ ዓለምን ከሚከተሉ ጋር ከተቆራኘ፣ እምነታቸውን የሚደግፍ ከሆነና እነርሱ ዓለምን እንደሚሹት ዓለምን የምትሹ ከሆናችሁ መጨረሻችሁ የበለዓምን መንገድ መከተል ይሆንና ወደ መጨረሻው ጥፋታችሁ ትሮጣላችሁ፡፡ ዓለምን ስትከተሉ እምነታችሁን ታጣላችሁ፡፡ እግዚአብሄር እንደዚህ ያሉትን ሰዎች ከአፉ እንደሚተፋቸው ተናግሮዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከእንግዲህ ወዲህ መና አይበሉም፡፡ መጨረሻቸውም እምነታቸውን ሙሉ በሙሉ ማጣት ይሆናል፡፡
 
እግዚአብሄር የጴርጋሞንን ቤተክርስቲያን የነቀፈው አባሎችዋ የበለዓምን ትምህርት በመከተላቸው ነው፡፡ እግዚአብሄር የጴርጋሞንን ቤተክርስቲያን አገልጋይ የነቀፈው እርሱ በልቡ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ዳግመኛ የተወለደ አገልጋይ ቢሆንም በዓለም ለመታወቅ በመሻቱና ልክ ዓለማዊ ሰው እስኪመስል ድረስ ቤተክርስቲያኑን በማገልገሉ ነው፡፡ ያም ብቻ አይደለም፤ ያንኑ ተመሳሳይ እምነት በመንጋዎቹ መካከል በመትከልም አስቶዋቸዋል፡፡ የዚህ ዓይነት አገልጋይ ዳግመኛ ካልተወለደ ዓለማዊ መጋቢ የሚሻል አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ምንባብ ላይ ብቸኛው ፍላጎታቸው በዓለማዊ ትርፎችና የቤተክርስቲያንን መዝገቦች በማበልጠግ ዙሪያ ለሚሽከረከር የእግዚአብሄር አገልጋዮች ግልጽና ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያን ሰጥቷል፡፡ ‹‹ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ፡፡››
 
 

ወደ ጥፋት የሚነዳችሁ እምነት፡፡ 

 
ሰው እግዚአብሄርን ከተዋጋ ምን ይፈጠራል? ይህንን ለአፍታ እንኳን አስቡት፡፡ ይህ ወደ ጥፋት የሚወስድ እጅግ ፈጣኑ መንገድ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ ‹‹ሁለት አፍ ያለው ስለታም ሰይፍ ያለው›› ማለት የእግዚአብሄር ቃል ሁለት አፍ ያለው ሰይፍ ነው ማለት ነው፡፡ ማንም ብትሆኑ ግድ የለም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ከተመታችሁ በእርግጥም ትሞታላችሁ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ‹‹ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን የሚለይ›› እና የሚወጋ የሰይፍ ሐይል ነው፡፡ (ዕብራውያን 4፡12) ሰዎች በውሃውና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የቀረበውን ቤዛነት ይለብሱ ዘንድ የልብን ስሜትና አሳብ ይመረምራል፡፡
 
በኢየሱስ ቢያምኑም በሕግ አክራሪነት ወጥመድ ውስጥ የወደቁ ብዙዎች አሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ በሕጉ ተመትተው ሞተዋል፡፡ ይህንን አሳዛኝ ውጤት ለማስወገድ እንዲህ ያለውን ዓለማዊ እምነት መዋጋትና ማሸነፍ አለብን፡፡ የእግዚአብሄር ሰራተኞች ሐሰተኛ ትምህርቶችን ድል ማድረግ አለባቸው፡፡ መንጎቻቸውም በእነዚህ ውሸቶች እንዳልተታለሉ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ዓለምን የሚወድና በወጥመዱ ውስጥ የወደቀ ማንም ሰው እምነቱ ሲጠፋ ይመለከታል፡፡
 
ብዙዎቹ የዘመኑ ቤተክርስቲያኖች የሚታወቁት እንደ ቤተክርስቲያናት ሳይሆን እንደ ንግድ ሥራዎች ነው፡፡ ይህ አሳዛኝ ነገር ግን ውስጥን ጠልቆ የሚገባ መግለጫ ነው፡፡ እነዚህ ቤተክርስቲያናት እንደ ንግድ ሥራዎች የታዩት ለምንድነው? ምክንያቱም የዘመኑ ቤተክርስቲያኖች ዓለማዊ እሴቶችን ለመከተልና ለማምለክ የመጀመሪያዎቹ ሆነው ዓለምን በመሻት በጣም ባተሌዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ፈጽሞ የሥጋ ፍላጎት የላቸውም እያልሁ አይደለም፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ምዕመናኖችም ቢሆኑ የሥጋ ፍትወት አላቸው፡፡ ይህ ፍትወት ግን በእምነታቸው ተገድቦዋል፡፡ የማያምኑ ሰዎች ሥጋዊ ፍላጎታቸውን ከሙሉ ልባቸው እንደሚሹ እነርሱ የሥጋን ነገሮች አይሹም፡፡
 
ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች የራሳቸውን መስፈርቶች አስቀምጠው በእነዚህ መስፈርቶች ወሰን ውስጥ መደሰት በሚችሉበት በእያንዳንዱ ነገር እየተደሰቱ ሕይወታቸውን ይኖራሉ፡፡ ጣዖት አምልኮና ልቅ የፆታ ብልሹነት ለእነርሱ ተፈጥሮአዊ ብቻ ነው፡፡ የከፋው ደግሞ ከእነርሱ አንዳንዶቹ ለዲያብሎስ መስገዳቸው ነው፡፡ ዳግም የተወለዱ ሰዎች ከእነዚህ አንዱን ያደርጋሉን? አያደርጉም! እነርሱ እንዲህ ያሉ ነገሮችን በፍጹም አያደርጉም፡፡ ምክንያቱም ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች እነዚህ ምግባሮች ምን ያህል የረከሱና የተበላሹ እንደሆኑ ያውቃሉና፡፡ እኛ ዳግመኛ የተወለድን ሰዎች በመሰረቱ የዓለምን ክብርና የራሳቸውን እያንዳንዱን ሥጋዊ ፍላጎቶች ከሚሹ የተለየን ስለሆንን ራሳችንን በዓለማዊ ትርፎች ሞልተን ሕይወታችንን መኖር የለብንም፡፡
 
የኒቆላውያንን ሥራ የሚከተሉ ሰዎች የዚህን ዓለም ሐብት የሚፈልጉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለመኖር ማግኘትና ሐብታም መሆንም ቢሆን በእርግጥ ምንም ስህተት የለውም፡፡ ነገር ግን የሕይወታችሁ ብቸኛው ዓላማ ማከማቸት ከሆነና ወደ ጣዖት አምልኮ ውስጥ ወድቃችሁ መጨረሻችሁ በስስታችሁ መነዳት ከሆነ እምነታችሁ እንደሚጠፋ የተረጋገጠ ነው፡፡ ለገንዘብ የሚያገለግሉና የዓለምን ሐብት ለማግኘት ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች የኒቆላውያንን ሥራ እየተከተሉ ነው፡፡ በመጨረሻ እነዚህ በዓለም ይማረካሉ፡፡ በእግዚአብሄር እንደሚያምኑ ቢናገሩም ልባቸው ገና ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻቸው መቤዠት ይኖርበታል፡፡
 
 
አራት ዓይነት የልብ መሬቶች፡፡ 
 
የማቴዎስ ወንጌል ኢየሱስ ዘሮቹ በአራት ዓይነት መሬቶች ላይ ስለወደቁበት ዘሪ ምሳሌን ይነግረናል፡፡ ዘሮቹ የወደቁበት የመጀመሪያው መሬት መንገድ ዳር ነው፡፡ ሁለተኛው ድንጋያማ ስፍራ ነው፡፡ ሦስተኛው እሾሃማ መሬት ነው፡፡ አራተኛው መልካም መሬት ነው፡፡ እያንዳንዳቸውን እንመልከታቸው፡፡
 
መንገድ ዳር የሚያመለክተው የደነደነ ልብን ነው፡፡ ይህ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ይሰማል፡፡ ነገር ግን ፈጥኖ ወደ ልቡ ስለማይወስደው ወፎች ይነጥቁታል፡፡ በሌላ አነጋገር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ሊፈቅድለት የሚችለውን የደህንነት ቃል የሚመለከተው ከእውቀት አንጻር ብቻ ስለሆነ ወፍ (ሰይጣን) ቃሉን ነጥቆ ይወስደዋል፡፡ እምነቱም ማደግ አይጀምርም፡፡
 
ድንጋያማው መሬትስ ምን ማለት ነው? ይህ የሚያመለክተው ቃሉን በደስታ ቢቀበሉም ለረጅም ጊዜ የማይቆዩትን ሰዎች ነው፡፡ ምክንያቱም ጥልቀት በሌለው መሬት ውስጥ ሥር የላቸውምና፡፡ በሌላ በኩል በእሾሆች መካከል የተዘራው ዘር የሚያመለክተው ለዚህ ዓለም የሚጨነቁትን ሰዎች ነው፡፡ ከጅማሬው በደስታ የተቀበሉትን ቃል የባለጠግነት መታለል ያንቀዋል፡፡
 
በመጨረሻም በመልካሙ መሬት ላይ የተዘሩት የእግዚአብሄርን ቃል ሙሉ በሙሉ በመቀበልና በመከተል በልባቸው ፍሬዎችን የሚያፈሩትን ነው፡፡
 
የእናንተን ልብ የሚያመለክተው ከእነዚህ መሬቶች የትኛው ነው? ልባችሁ የቃሉን ዘር ለማብቀል ፈጽሞ ያልተዘጋጀውን የመንገድ ዳር ዘር የሚመስል ከሆነ ተጠርጎ ይወሰዳል፡፡ ወይም በወፎች ይለቀምና ይህንን የቃሉን በረከት ፈጽሞ ያሳጣችኋል፡፡ እኛ የሐጢያት ዘሮች ስለሆንን በእግዚአብሄር ቃል ባይሆን ኖሮ በእርሱ ዘንድ ዋጋ የሌለን ሰዎች እንሆን እንደነበርን መረዳት ይገባናል፡፡ በሌላ በኩል ልባችን እንደ ድንጋያማው መሬት ከሆነ የቃሉ ዘር ሥር መስደድ ስለማይችል ዝናብን፣ ነፋሳትን ወይም ድርቅን አይቋቋምም፡፡ እነዚህ ሰዎች መሬታቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ የእግዚአብሄርን ቃል ምንም ያህል በደስታ ቢቀበሉም መብቀል የማይችልና ትንሽ ችግር ሲገጥመው የሚጠወልግ ከሆነ የመጀመሪያው አቀባበላቸው ፈጽሞ ዋጋ የለውም፡፡
 
የእሾሃማውን መሬት ልብም እንደዚሁ ድል ማድረግ አለብን፡፡ ለሕይወታችን አስጊ የሆኑትን እሾሆች መታገልና መቁረጥ አለብን፡፡ ዝም ብላችሁ ከተዋችኋቸው እሾሆቹ ወዲያውኑ ይሸፍኑንና የጸሐይ ብርሃንን ይከለክሉናል፡፡ ይህ የቃል ዛፍ ጸሐይ ካላገኘና በአፈር ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮች ለእሾሆቹ የሚሰጥ ከሆነ ይሞታል፡፡
 
በሕይወታችን ችግሮችና መከራዎች ሲገጥሙን በድፍረት ድል ልናደርጋቸው ይገባናል፡፡ መንገዳችንን የሚያጥሩትንና ፊቶቻችንን የሚሸፍኑትን እሾሆች ሕይወታችን በዚህ ላይ የተመረኮዘ መስሎ እስኪሰማን ድረስ በሙሉ ጉልበታችን መታገል አለብን፡፡ የዚህ ዓለም ገንዘብ ወደኋላ ሲጎትተን ወይም ዝናው ሲያሰጋን ሁሉንም መታገልና ማሸነፍ አለብን፡፡ የዓለም ጭንቀትና ስስታምነቱ ነፍስን ስለሚገድል ሁልጊዜም ልናሸንፋቸው ይገባናል፡፡ እንዲህ ያለ የድል መንፈሳዊ ሕይወት ስንኖር ሥጋችንና ነፍሳችን ይፋፋሉ፡፡ ምክንያቱም ከእግዚአብሄር ዘንድ የጸሐይ ብርሃንና ምግብ ያገኛሉና፡፡
 
ዳግም የተወለዱ ቅዱሳንና የእግዚአብሄር አገልጋዮች ሁልጊዜም ከዓለም ጋር የሚደረግ ተጋድሎ አለባቸው፡፡ ስለዚህ ኒቆላውያንን መከተል የለብንም፡፡ ኒቆላውያን ለሕዝቡ አገልግሎቶችን በመስጠት ውስጥ በጣም ይሳተፉ እንደነበር ይነገራል፡፡ ነገር ግን በዓለም ውስጥ ያለውን ሕዝብ ማገልገል የቤተክርስቲያን ዋናው ዓላማ አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያን ዋና ዓላማ ማህበራዊ አገልግሎት ማበርከት ነው ብሎ ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው፡፡
 
 
በድፍረት ተቃወሙ! 
 
እግዚአብሄር እኛ የዓለም ጨው እንደሆንን ነግሮናል፡፡ ይህንን ሲል ምን ማለቱ ነው? እግዚአብሄር የዓለም ጨው እንደሆንን ሲነግረን በዓለም ተፈላጊዎች ነን ማለት ነው፡፡ የጨው ዓላማ ሐጢያተኞች ከሐጢያቶቻቸው ድነው የእግዚአብሄር ልጆች በመሆን ሰማይ መግባት ይፈቀድላቸው ዘንድ የውሃውንና የክርስቶስን ደም ቃል ለእነርሱ መስበክ ነው፡፡ ጨው ለጣዕም እንደሚያስፈልግ ሁሉ ዓለምም ዳግመኛ የተወለዱ ጻድቃኖችን እንደ ጨው ይፈልጋቸዋል፡፡ በሌላ አነጋገር ዳግመኛ የተወለዱ ጻድቃን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ቃል መስበክና ሰዎችንም ወደ ደህንነት መምራት አለባቸው፡፡ እኛ የዚህን የጨው ሚና መፈጸምና ነፍሳቶች ዳግመኛ እንዲወለዱ መርዳት አለብን፡፡ ሐጢያተኞችን ወደ ጻድቃን መለወጥ አለብን፡፡
 
እውነተኛዋ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ምንድነች? እውነተኛዋ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ሰዎች እርሱን ለማምለክ የሚሰበሰቡባት ነች፡፡ እግዘአብሄርን የሚያመሰግኑት በዚህ ስፍራ ነው፡፡ ወደ እርሱ የሚጸልዩትም በዚህ ስፍራ ነው፡፡ ፈተና ሲመጣ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ሊቋቋሙት ይገባል፡፡ ቅዱሳኖችም እንደዚሁ ከሰይጣን የሚመጡትን የዓለም ፈተናዎች መቋቋም መቻል አለባቸው፡፡ ዲያብሎስ ‹‹እምነታችሁን እርሱት፤ ባለጠጋ አደርጋችኋለሁ! ዳግመኛ የተወለዱ ምዕመናን ወዳሉባት ቤተክርስቲያን መሄድ አይኖርባችሁም፡፡ የእኔ ከሆኑት ቤተክርስቲያኖች ወደ አንዱ ኑና ሽማግሌዎች አደርጋችኋለሁ!›› በማለት ይፈትናችሁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሁልጊዜም ጻድቃንን ለማሰናከልና ወደ ራሱ ወጥመዶች ስቦ ለማስገባት ስለሚሞክር እምነታችንን እስከ መጨረሻው ድረስ መጠበቅ እንችል ዘንድ ሁልጊዜም እርሱን ለመዋጋትና ለማሸነፍ ዝግጁ መሆን አለብን፡፡
 
ሐሳዊ እምነት ያላቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ የዳኑትን ሰዎች በቁሳዊ ነገሮች ለመፈተን ይሞክራሉ፡፡ በገንዘብና በዝና ይፈትናሉ፡፡ ሰይጣን ዓለማዊ ዕሴቶችን ያሳየንና እምነታችንንና እግዚአብሄርን እንድንተው ይነግረናል፡፡ እንዲህ ባለ ጊዜ ሊኖረን የሚገባው ጌታ የሚያስፈልጉንን ሁሉ እንደሚያሟላልን የሚያምን እምነት ነው፡፡ በዚህ እምነትም የሰይጣንን ፈተናዎች በድፍረት መቃወምና ማሸነፍ እንችላለን፡፡
 
የበረከቶች ስር የሚገኘው ከእግዚአብሄር ዘንድ ነው፡፡ በመንፈሳዊም በሥጋዊም የሚባርከን እግዚአብሄር ነው፡፡ የሰውን ዘር የሚባርከው ዲያብሎስ እንዳልሆነ ስለምናውቅ እርሱን እንታገለዋለን፡፡ ከራሳችን ፍላጎቶች ጋር የምንዋጋባቸው ወቅቶችም አሉ፡፡ ልባችን በዚህ ዓለም ማዕበል እንዲወሰድ በምንፈቅድ ጊዜ ስስትና ፍትወት ብቅ ስለሚሉ ራሳችንንም መታገል አለብን፡፡ በእምነታችን ላይ አሻጥር የሚሰሩ ሰዎችንም መዋጋት አለብን፡፡ የእኛ ዕጣ ፋንታ ከዓለማዊ ሐይላት ሁሉ ጋር መንፈሳዊ ተጋድሎዎችን ማድረግ ነው፡፡
 
ለምን? አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ውጊያ ካልተጠመደ እምነቱ በማናቸውም ሁኔታዎች ሞቷል ማለት ነው፡፡ ዓለም እስከሚያበቃና የጻድቃንና የሐጢያተኞች የፍርድ ቀን እስከሚጠናቀቅ ድረስ እምነታችንን ለማጥፋት የሚሰሩ ማታለያዎች ይኖራሉ፡፡ ያለ ማቋረጥ በመንፈሳዊ ውጊያዎች መጠመድ የሚገባን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚቃወሙትንና እምነታችንን ለማጥፋት የሚሹትን የምንታገሳቸው ከሆነ መጨረሻችን ሕይወታችንን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ማጣት ይሆናል፡፡ ከእምነታችን ውጭ አንዳች ሌላ ነገር እንዳይሰለጥንብን የሚያደርግ ጠንካራ ቆራጥነት ከሌለን ያለንን ሐብት በሙሉ ከማጣታችንም በላይ እግዚአብሄርም ይተወናል፡፡ ጠላቶቻችንን ተዋግተን ለማሸነፍ ከእኛ ጋር ማን እንደቆመና ማን እንደሚቃወመን በግልጽ መለየት መቻል አለብን፡፡ አንዳችን ለሌላችን ለጋሶች መሆን ቢገባንም ጠላቶቻችንን በእኛ ላይ አንዳች ነገር ለመሞከር መድፈር እስከማይችሉበት ደረጃ ድረስ ጽኑዎች መሆን አለብን፡፡
 
ኒቆላውያን ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነርሱ ልንታገሳቸውም ሆነ አብረናቸው ልንሰራ የማንችላቸው ‹‹የሰይጣን ማህበር›› ስለሆኑ ጠላቶችን ናቸው፡፡ እኛ የሐጢያቶቻችንን ይቅርታ ያገኘን ሰዎች በጣዖት አምልኮ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትንና ቁሳዊ ትርፎችን ለማካበት ብቻ የሚሹትን ኒቆላውያንን መታገስ የለብንም፡፡ በምትኩ ሕይወታችንን ጌታንና በዚህ ምድር ላይ የእግዚአብሄርን መንግሥት ለመገንባት የሚሰራውን የጽድቅ ሥራውን ለማገልገል ቀድሰን መስጠት አለብን፡፡
 
 
አስቀድሞ የእግዚአብሄርን መንግሥት መፈለግ፡፡ 
 
ኢየሱስ የሥጋ ሥራዎቻችንን ከማስቀደም ይልቅ የእግዚአብሄርን ሥራዎች እንድንሰራ በመምከር ‹‹አስቀድመን የእግዚአብሄርን መንግሥትና ጽድቁን እንድንፈልግ›› ነግሮናል፡፡ እኛ ዳግመኛ የተወለድን ሰዎች መንፈሳዊ ፍላጎቶች አሉን፡፡ እነዚህ የሥጋ ፍላጎቶች ሳይሆኑ የመንፈስ ፍላጎቶች ናቸው፡፡ አስቀድመን የእግዚአብሄርንና የመንግሥቱን ሥራዎች የምንሰራው በዚህ መንገድ ነው፡፡ አስቀድመን እግዚአብሄርን እናገለግላለን፡፡ የሥጋንም ሥራዎች ደግሞ እንሰራለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ሰው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም፡፡›› በሌላ አነጋገር የምንኖረው በሥጋችን ብቻ ሳይሆን በሥጋና በመንፈስ ነው፡፡ በእነዚህ በሁለቱ መካከል ሚዛናዊ መሆን መቻል አለብን፡፡ በዚህ ምድር ላይ ዋናው ነገር የእኛ ደስታ ነው ብለን በማሰብ የኒቆላውያንን ሥራ የምንከተል ከሆንን መጨረሻችን የራሳችንን ጥፋት መጋፈጥ ይሆናል፡፡ አስቀድመን መንፈሳዊ ፍላጎቶቻችንን መሻት ያለብን ለዚህ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች የሰማይና የሲዖል ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ ሁሉ ይበሳጫሉ፡፡ ‹‹በሲዖል ነበራችሁን? በራሳችሁ ዓይኖች አይታችሁት ታውቃላችሁን?›› በማለት ይጠይቃሉ እነዚህ ጥያቄዎች የሚመጡት ግን ከሰይጣን አስተሳሰቦች ነው፡፡ እንዲህ የሚያስበው ተራው ሕዝብ ብቻ አይደለም፡፡ ሥነ መለኮት በማጥናት ዓመታቶችን ያሳለፉ አብዛኞቹ መጋቢዎችም መንጎቻቸው አንዳች የሰማይ ተስፋና እንዴት ዳግመኛም እንደሚወለዱም እውቀት ሳይኖራቸው ያገለግሉዋቸዋል፡፡ ይህ እጅግ የሚያሳዝንና በጣም የሚያስከፋ ሁኔታ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ማረጋገጫዎች የሌላቸውና ራሳቸው ዳግመኛ ያልተወለዱ እነዚህ አገልጋዮች ስለ እግአብሄር ምንም የማያውቁ ሰዎችን ዳግመኛ እንዲወለዱ ሊመሩዋቸው አይችሉም፡፡ ብዙ ነፍሳቶች በሰይጣን አስተሳሰቦች ተይዘው እግዚአብሄርን እየተቃወሙ ሳሉ በሰማይም ከማያምኑም ሆነ ስለ ራሳቸው መዳን እርግጠኞች ካልሆኑ መጋቢዎች ምን ሊማሩ ይችላሉ?
 
‹‹የሰይጣን ዙፋን ባለበት›› ማለት ሰይጣን አሁን መላውን ዓለም ይገዛል ማለት ነው፡፡ የምንኖርበት ዘመን የዚህ ዓይነት ነው፡፡ የምሽት ሰማዮችን በሚያብረቀርቁ መስቀሎች የሚያበሩና ልክ የንግድ ሥራ እንደሚያከናውኑም ቤተክርስቲያኖቻቸውን የሚያስተዳድሩ ኒቆላውያን በሞሉበት የዓለም ዘመን ላይ እየኖርን ነው፡፡ እግዚአብሄር እነዚህ የእርሱ ቤተክርስቲያኖች ሳይሆኑ ‹‹የሰይጣን ማህበር›› እንደሆኑ ነግሮናል፡፡ የዛሬው ዓለም በሰይጣን አስተሳሰቦች ተጠምደው የዚህን ዓለም ስስት በሚሹ አገልጋይ ነን ብለው በሚያስመስሉ፣ ቤተክርስቲያን በሚሄዱና የጌታን ስም በሚጠሩ ብዙ ሰዎች ተሞልታለች፡፡ ነገር ግን የነፍሳቸው ዳግመኛ ውልደትና ለሰማይ ያላቸው ተስፋ ከረጅም ጊዜ በፊት ጠፍቷል፡፡ አሁን የምንኖርበትና ጌታን የምናገለግልበት ዓለም የዚህ ዓይነት ዓለም ነው፡፡
 
 

ዳግመኛ ካልተወለዱ ጋር የሚደረግ መንፈሳዊ ተጋድሎ፡፡ 

 
እኛ እዚሁ ‹‹የሰይጣን ዙፋን ባለበት›› በዚህ ምድር ላይ እየኖረን ነው፡፡ በተጠንቀቅ ቆመን እምነታችንን መጠበቅና ተግዳሮት በገጠመን ጊዜም ጠላቶቻችንን በጀግንነት መጋፈጥ አለብን፡፡ ጌታችን እስከሚመጣበት ቀን ድረስ በውሃውና በደሙ ዳግመኛ እንድንወለድ በፈቀደልን ወንጌል በማመን ‹‹ነጩን ድንጋያችንን›› ማለትም እምነታችንን በጥንቃቄ መጠበቅ ይገባናል፡፡
 
የእግዚአብሄር ቃል የሆነውን መና በመመገብ በሕይወት መኖር ይገባናል፡፡ ያንን ለማድረግ የኒቆላውያንን ሥራ መዋጋትና ማሸነፍ አለብን፡፡ ልንቃወማቸው ይገባናል፡፡ ገንዘብንና ዓለማዊ ዝናን ብቻ ከሚሹት መራቅ አለብን፡፡ ድክመቶቻቸውን መታገስና ይቅር ማለት ብንችልም እውነትን ከሚቃወሙና ገንዘብን ብቻ ከሚሹ እንደዚህ ካሉ ሰዎች ጋር እንኳንስ የእግዚአብሄርን ሥራዎች ልንሰራ ይቅርና አብረን እንጀራን ልንቆርስ አንችልም፡፡
 
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግመኛ የተወለዱት ሰዎች ስሞች ተጻፉት የት ነው? የተጻፉት በሕይወት መጽሐፍ ላይ ነው፡፡ በዚህ ነጭ ድንጋይ ላይ አዲስ ስም መጻፍ ማለት ምን ማለት ነው? የእግዚአብሄር ልጆች ሆነናል ማለት ነው፡፡ ይህንን አዲስ ስም ‹‹ከተቀበለው በቀር›› ማንም እንደማያውቀውም ተጽፎዋል፡፡ ይህ ማለት የኢየሱስን ደህንነት የሚያውቁት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፡፡ ሐጢያተኞች እንዴት ጻድቃን መሆን እንደሚችሉ አያውቁም፡፡ ሐጢያቶቻቸው እንዴት እንደተወገዱላቸው የሚያውቁት ከኢየሱስ አዲሱን ስማቸውን የተቀበሉ ብቻ ናቸው፡፡
 
ኒቆላውያንን መታገል አለብን፡፡ ሌላ ሰውን ሳይሆን ኒቆላውያን መታገል አለብን፡፡ የምንባቡ መሰረታዊ አሳብ በእግዚአብሄር ቢያምኑና የእውነትን ቃል ቢያውቁም አሁንም ድረስ የእግዚአብሄርን ቃል በአለመታዘዝና በመቃወም ቀጥለው ለሥጋቸው ገንዘብን፣ ቁሳዊ ትርፎችን፣ ሐብትንና ዝናን የሚሹትን ኒቆላውያንን መታገልና ማሸነፍ አለብን፡፡
 
ከራሳችን ጋርም መታገል አለብን፡፡ በከንቱነታችን ወይም ትምክህታችን ምክንያት እግዚአብሄርን መከተል የማንችል ከሆንን እንዲህ ያለውንም ልብ ልንታገለው ይገባናል፡፡ ዳግመኛ ሳይወለዱ በኢየሱስ እናምናለን ከሚሉ ሰዎች ጋርም በመንፈሳዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ አለብን፡፡
 
እኛ ከእግዚአብሄር ክብር የጎደልን ብንሆንም ጌታ በውሃውና በደሙ አድኖናል፡፡ በዚህ ቃል በማመን እምነታችንን መጠበቅና ለሰጠን ፍጹም የሆነ ደህንነት ምስጋናን በማቅረብ ሕይወታችንን እንደ እግዚአብሄር አገልጋዮች መኖር አለብን፡፡ ሁላችንም እስከ መጨረሻው ድረስ በእምነት ተዋግተው እንደሚያሸንፉ ሰዎች እንሁን፡፡
 
 
ድል የሚነሱ መና ይሰጣቸዋል፡፡ 
 
በሰው ታሪክ ውስጥ እጅግ ትልቁ የመሰወር ጉዳይ የሚመጣው ንጥቀት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ የኢየሱስ ዳግመኛ ምጽዓትም በክርስቶስ በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ከፍተኛ ጉጉት የሚፈጥር ጉዳይ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ‹‹ቅዱሳን ሲነጥቁ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰዎች መሰወር ይሆናል፡፡ በሁሉም የሕይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ ፓይለቶች፣ የባቡር ተቆጣጣሪዎችና የታክሲ ሹፌሮች ሲሰወሩ፣ አውሮፕላኖች ከሰማይ ወድቀው ሲከሰከሱ፣ ባቡሮች ሐዲዳቸውን ሲስቱ፣ አውራ መንገዶች በአደጋዎች ሲጨናነቁ፣ ዓለም በሁሉም ዓይነት አደጋዎችና ጥፋቶች ትጥለቀለቃለች›› ብለው ያስባሉ፡፡ ታሪኩን በእነዚህ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ንጥቀት (ራፕቸር) የሚል ርዕስ ያለው አንድ መጽሐፍ ባለፉት ጊዜያት ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ መጽሐፍ ሆኖ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ቅዱሳን በሚነጠቁበት ጊዜ ይሰወራሉ ብለው አምነዋል፡፡ ስለዚህ እነርሱ ንስሐ በመግባት እምነታቸውን ለንጥቀታቸው ቀን ከማዘጋጀታቸውም በላይ ከእነርሱ አንዳንዶቹ ትምህርታቸውንና ሥራቸውን አቁመዋል፡፡ ይህ የሚያስቅ ክስተት አይደለም፡፡
 
በቅርቡ የቅድመ መከራን ንጥቀት ትምህርት የተቀበለ አንድ የሐይማኖት ድርጅት ጉባኤው ያለውን ሐብት ንብረት ሁሉ ለቤተክርስቲያን በመስጠት መሪዎቻቸው የተነበዩትን የንጥቀት ቀን ብቻ እንዲጠበቁ አድርጎ ነበር፡፡ በእርግጥ የተነበዩትና በጉጉት የተጠበቀው ቀን እንደ ማንኛውም ሌላ ቀን በማለፉ የጠበቁት ሁሉ ምንም ያመጣው ነገር የለም! ከልባቸው ያመኑትና የጠበቁት እያንዳንዱ ነገር ውሸት መሆኑ ተረጋገጠ፡፡
 
ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዶቹ በግትርነት በ1999 ዓ.ም የንጥቀታቸው ቀን አድርገው ሌላ ቀን በማወጅ ጠበቁ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ በፊቱ ሁሉም በውሸት እንደተታለሉ ተረጋገጠ፡፡ መሪዎቻቸውም ባልተፈጸመው ትንቢታቸው ስላፈሩ ዳግመኛ የክርስቶስን የምጽዓት ጊዜ በጭራሽ ላለመወሰን ወሰኑ፡፡ የቅድመ መከራ ንጥቀት ትምህርት ምን ያህል ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ፈጽሞ እንደማይስማማ ከእነዚህ ሁነቶች ማየት እንችላለን፡፡
 
በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ እጅግ አስፈላጊው ጉዳይ የኢየሱስ ዳግመኛ ምጽዓትና የቅዱሳን ንጥቀት ነው፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ተመልሶ በመምጣት ምዕመናኖቹን በአየር ላይ ነጥቆ መውሰዱ ለታመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ ትልቁ ተስፋና ጥበቃ ነው፡፡ ክርስቲያኖች በእምነታቸው የክርስቶስን መመለስ በጉጉት መጠበቃቸው ተገቢ ነው፡፡ ከልቡ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ጌታ የሚመጣበትን ቀን በታላቅ ተስፋና ጉጉት መጠበቅ አለበት፡፡
 
ፈጽሞ ከማይጠበቅ እምነት ይልቅ የጌታን ዳግመኛ ምጽዓትና ንጥቀት የሚጠብቅ የእምነት ዓይነት መያዝ የተሻለ ነው፡፡ በመጨረሻው ዘመን የሚያምኑ የራዕይ ጠባቂዎች ከትክክለኛው መንገድ የሳቱት ለንጥቀታቸው ውስን ቀንና ጊዜን በማስቀመጣቸው ነው፡፡ በቀመራቸው መሰረት ላይ ብዙዎቹ በዳንኤል 9 እንደዚሁም በዘካርያስ ውስጥ ያለውን የሰባውን ሳምንት ትንቢት በተሳሳተ መንገድ መተርጎማቸውና ራሳቸው በተበዩዋቸው ቀኖች ላይ መምጣታቸው ነው፡፡
 
ጳውሎስ በ1ኛ ተሰሎንቄ 4 ላይ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ቅዱሳን እርሱን ለመገናኘት በአየር እንደሚነጠቁ ይናገራል፡፡ ስለዚህ በእውነት በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች የንጥቀታቸውን ቀን መጠባበቃቸው ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ለንጥቀት ስሌት ማስላትና የተወሰነ ቀን ማስቀመጥ በጣም ስህተት ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሄርን ጥበብ ቸል የማለት የትምክህታቸው ነጸብራቅ ነውና፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን በሰው ሰራሽ የሒሳብ ቀመሮች ለመፍታትና ለመረዳት መሞከር ታላቅ ስህተት ነው፡፡
 
ታዲያ እውነተኛው ንጥቀት የሚሆነው መቼ ነው? ራዕይ 6 የቅዱሳንን ንጥቀት ይናገራል፡፡ በዚህ መሰረት ከሰባቱ የአግዚአብሄር ዘመኖች በአራተኛው ዘመን ማለትም በሐመሩ ፈረስ ዘመን የቅዱሳን ሰማዕትነት ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ በአምስተኛው ዘመን ላይ ንጥቀት ይሆናል፡፡ የቅዱሳን ንጥቀት በስፋት ተብራርቷል፡፡ ጊዜው ሲመጣም በእርግጥ ተጨባጭ ይሆናል፡፡
እግዚአብሄር ለሰው ዘር ሰባት ዘመኖችን ያቀደ ሲሆን ከእነዚህ የመጀመሪያው የአምባላዩ (ነጩ) ፈረስ ዘመን ነው፡፡ ይህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሚጀምርበትና ድል ማድረግ የሚቀጥልበት ዘመን ነው፡፡ ሁለተኛው ዘመን የዳማው (የቀዩ) ፈረስ ዘመን ነው፡፡ ይህ ዘመን የሰይጣንን ዘመን ጅማሬ ያስታውቃል፡፡ ሦስተኛው ዘመን ዓለም በሥጋዊና በመንፈሳዊ ረሃብ የሚመታበት የጉራቻው (ጥቁሩ) ፈረስ ዘመን ነው፡፡ አራተኛው ዘመን የሐመሩ ፈረስ ዘመን ነው፡፡ ይህ ዘመን ጸረ ክርስቶስ የሚገለጥበትና ቅዱሳኖችም ሰማዕት የሚሆኑበት ዘመን ነው፡፡ አምስተኛው ዘመን ቅዱሳኖች ሰማዕትነታቸውን ተከትሎ ትንሳኤ የሚያገኙበትና የሚነጠቁበት ዘመን ነው፡፡ ስድስተኛው ዘመን እግዚአብሄር ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋውን የመጀመሪያውን ፍጥረት ማለትም ይህንን ዓለም ይዞዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ እግዚአብሄር ከቅዱሳኑ ጋር ለዘላለም ለመኖር የሺህ ዓመቱን መንግሥትና አዲሱን ሰማይ ምድር የሚከፍትበት ሰባተኛው ዘመን ይመጣል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እነዚህን ሰባት የተነጣጠሉ ዘመኖች ለሰው ዘር አስቀምጦዋል፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሄር ያስቀመጠላቸውን እነዚህን ሰባቱን ዘመኖች ማወቃቸውና ማመናቸው ትክክል ነው፡፡
ባለፈው ምዕተ ዓመት መጨረሻ ላይ በኮርያ ብቻ የክርስቶስን ዳግመኛ ምጽዓትና የንጥቀታቸውን ቀንና ጊዜ ራሳቸው ለይተው ያስቀመጡ ሰዎች ከ100,000 በላይ ይገመታሉ፡፡ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ኮርያውያን ክርስቲያኖች ናቸው ይባላል፡፡ ከእነርሱ መካከል ወደ 100,000 የሚሆኑት የኢየሱስን ምጽዓትና የራሳቸውን ንጥቀት ጠብቀዋል፡፡ በሌላ አነጋገር የእግዚአብሄርን ቃል በተጻፈው መሰረት አምነው የጌታን ምጽዓት የጠበቁ አክራሪ አማኞች ናቸው፡፡ ከ12 ሚሊዮን ውስጥ 100,000 ብቻ ከ1 በመቶ ያነሰ ነው፡፡
 
ነገር ግን ችግራቸው እግዚአብሄር ለእነርሱ ያስቀመጠላቸውን ዘመኖች በትክክል ያልተረዱ መሆናቸው ነው፡፡ ብዙዎቹ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በትክክል ባለመረዳታቸው በራሳቸው የተሳሳተ እውቀት ላይ የተመሰረተውን የክርስቶስን ዳግመኛ ምጽዓትና የቅዱሳኖችን ንጥቀት ተመርኩዘው ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ለማሰላት ሲሞክሩ እንዲህ ያሉ ስህተቶችን ሰርተዋል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልዕክት የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ ከአእምሮዋችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም›› (2ኛ ተሰሎንቄ 2፡2) በማለት አስጠነቀቃቸው፡፡
 
ከታሪክ አንጻር ብዙዎች የእግዚአብሄርን ዕቅድ ባለማወቅ ቀጥለው በከንቱ ደጋግመው የተሳሳቱ ቀኖችን ወስነዋል፡፡ የተሳሳተውን እምነታቸውን ማስተካከል እንደሚያስፈልግ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ክፉኛ ልገስጻቸው ፍላጎት የለኝም፡፡ የምሻው ላርማቸው ብቻ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም የውድቀታቸው መንስኤ እግዚአብሄር ለሰው ዘር ያስቀመጣቸውን ሰባቱን ዘመኖች አለማወቃቸው ነው፡፡ የኢየሱስን ዳግመኛ ምጽዓት በተሳሳተ መንገድ ያሰሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ቁጥሮች በሰውኛ አገባቦች ብቻ በማየት በተሳሳተ መንገድ ስለተረዱዋቸውና ስለተጠቀሙባቸው ነው፡፡
 
ይህ ስህተት በኮርያውያን ቤተክርስቲያኖች ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በቀረው ዓለምም የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ምድር ከተለያዩ ክፍሎች ሁሉ የተወጣጡና ከእነርሱም አንዳንዶቹ የታወቁ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተመሳሳይ ዓይነት ስህተት ሰርተዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ በኢየሱስ አምነው ራሳቸው የወሰኑትን የንጥቀት ቀን የጠበቁ ሁሉ እግዚአብሄር ለእነርሱ ያለውን ያልተሳሳተውን ትክክለኛ ዕቅድ ይረዱ ዘንድ ልቤ የእግዚአብሄርን ዕቅድ ሊመሰክርላቸው ተመኝቷል፡፡ እነርሱም ደግሞ በእግዚአብሄር የመነጠቅ በረከት እንዲሰጣቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
 
በእግዚአብሄር በኩል የሚሆነው እውነተኛው ንጥቀት የሚመጣው የሐመሩ ፈረስ ዘመንና የቅዱሳን ሰማዕትነት ካለፈ በኋላ ነው፡፡ በዚህ የሐመሩ ፈረስ ዘመን የሰባቱ ዓመት ታላቅ የመከራ ጊዜ ሲጀምር ጸረ ክርስቶስ የዓለም እጅግ ብርቱ መሪ ሆኖ ይመጣና በዓለም ላይ ይነግሳል፡፡
 
ታላቁ መከራ ሲጀምር ጸረ ክርስቶስ ቅዱሳኖችን ማሳደድ ይጀምርና በሰባቱ ዓመት ጊዜ አጋማሽ ጫፍ ላይ እስኪደርስ ድረስ በታላቁ መከራ የመጀመሪያ አጋማሽ ማለትም በመጀመሪያው ሦስት ዓመት ተኩል ላይ የበለጠ ያጠነክረዋል፡፡ ቅዱሳን እምነታቸውን ለመከላከል ሰማዕት የሚሆኑት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ ሰማዕት የሆኑት ቅዱሳኖች ትንሳኤን የሚያገኙበትና የሚነጠቁበት ስድስተኛው ዘመን ይመጣል፡፡
 
በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ዘመናትን በሚገባ ማወቅ አለባቸው፡፡ በቅድመ መከራ ንጥቀት ወይም በአጋማሽ መከራ ንጥቀት በማመን አለማመናቸው ላይ ተመርኩዞ የእምነት ሕይወታቸው ሊለወጥ ይችላል፡፡ ምዕመናኖች ንጥቀታቸውን በትክክለኛ እምነት በጥበብ ይጠብቁ ይሆን ወይም አእምሮዋቸውን ራሳቸው በመረጡት የማይረባ ቀን ላይ እንዲያተኩር የማድረጉን ስህተት ይሰሩ ይሆን ይህ ሁሉ የሚመረኮዘው እምነታቸወን የመሰረቱት በእግዚአብሄር ቃል ላይ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ ነው፡፡
 
በራዕይ ቃል ላይ የተሰጡትን እነዚህን ትምህርቶች ረጋ ብላችሁ ብታዩዋቸው ተገቢ የሆኑት ዕቅዶች ምን እንደሆኑ በትክክል ማግኘት ስለምትችሉ ለጥያቄዎቻችሁ ሁሉ ትክክለኛውን መልስ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ትክክለኛ የሆነ የንጥቀት መረዳት ከሌላችሁና በትክክል መጠበቅ ከተሳናችሁ ያን ጊዜ እምነታችሁ ይፈርሳል፡፡
 
የቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ የተብራራው ትምህርታዊ አቋሞቹን ስኮፊልድ ሪፈረንስ ባይብል በሚለው መጽሐፉ ውስጥ በዘዴ በማስገባት የመጀመሪያው ሰው በሆነው አሜሪካዊ የቃለ እግዚአብሄር ሊቅ በስኮፊልድ ነበር፡፡ ይህ ማመሳከሪያ መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ተተርጉሞ በመላው ዓለም ጥቅም ላይ ውሎዋል፡፡ የቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ በስፋት የተሰራጨው የስኮፊልድ ሪፈረንስ ባይብል ባሳደረው ተጽዕኖ ምክንያት ነው፡፡ የስኮፊልድ ሪፈረንስ ባይብል የአንዲት ሐያል አገር ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆነ የቃለ እግዚአብሄር ሊቅ የተጻፈ በመሆኑ መጽሐፉ በብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በርካታ ቁጥር ባላቸው ክርስቲያኖች ተነቦዋል፡፡
 
ስኮፊልድ ራሱ የቅድመ መከራ ንጥቀት እሳቤው በመላው ዓለም ተፈላጊ ይሆናል የሚል አሳብ አልነበረውም፡፡ ውጤቱ ግን የቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ በአብዛኛው የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ማግኘቱ ነው፡፡ ነገር ግን የስኮፊልድ የቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ ብቅ ከማለቱ በፊት በክርስቲያኑ ዓለም የተስፋፋው እምነት የድህረ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ ነበር፡፡ 
 
የድህረ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ ክርስቶስ በሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ ማብቂያ ላይ መጥቶ በዚያን ዘመን የሚገኙትን ቅዱሳኖች ይነጥቃቸዋል የሚል መላ ምት ያቀርባል፡፡ ከዚህ የተነሳ ብዙ ሰዎች ከንጥቀትና ከጌታ ዳግመኛ ምጽዓት በፊት ስላለው መከራ ታላቅ ፍርሃት ነበራቸው፡፡ ተሐድሶውያን ከምስባካቸው ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ ምጽዓት ሲሰብኩ ሰዎች በሐጢያቶቻቸው በማልቀስና በመጨነቅ ወደ ንስሐ ሮጡ፡፡ ራሳቸውንም በማያቋርጥ የንስሐ ጸሎት ጠመዱ፡፡ ስለዚህ ብዙውን ጊዜ አብዝቶ የሚያለቅስ ሰው አብዝቶ የተባረከ ሰው የመሆን መለኪያ ሆነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በኢየሡስ ቢያምኑም እጅግ ብዙ ዕንባዎችን አፍስሰዋል፡፡
 
ነገር ግን ይህ የቀድሞው የድህረ መከራ ንጥቀት እምነት ቀስ በቀስ በቅድመ መከራ ንጥቀት ተተካ፡፡ ይህ ለምን ሆነ? ሰዎች ከድህረ መከራ ንጥቀት ወደ ቅድመ መከራ ንጥቀት መገልበጣቸው ወሰን የሌለውና ይበልጥ የሚያጽናና ሆነው አገኙት፡፡ ወደዚህ መገልበጣቸው ሁሉም የሚያልፉበት እንደሆነ የሚጠብቁትን ችግርና መከራ በሙሉ ከመጋፈጥ ያስቀርላቸዋልና፡፡ የታላቁ መከራ አስፈሪ ችግሮች በእነርሱ ላይ ከመድረሳቸው በፊት በአየር ለመነጠቅ መምረጣቸው ብዙም የሚያስገርም አይደለም፡፡ በዚህ መንገድ የቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ ልክ እንደ ሰደድ እሳት ተሰራጨ፡፡ ምክንያቱም በታላቁ መከራ ስቃዮች ውስጥ ከማለፍ አስፈሪ ትዕይንት ይልቅ በይበልጥ የሚዋጥ አመቺ እምነትን አቅርቦዋልና፡፡
 
ሰዎች ከመራራው ይልቅ ጣፋጩን እንደሚመርጡ ሁሉ እምነታቸውን በሚመለከትም እንዲሁ የሚመርጡት ቀላሉን ነው፡፡ ሊቃውንቶች ካቀረቡዋቸው የተለያዩ ጽንሰ አሳቦች መካከል ለጣዕማቸው የሚስማማቸውን መርጠው ማመን ይወዳሉ፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች እንዲህ በቀላሉ በቅድመ መከራ ንጥቀት ጽንሰ አሳብ በማመን ያበቁት ለዚህ ነው፡፡ ይህንን የቅድመ መከራ ንጥቀት አመለካከት የደገፉ ሰዎች ለመነጠቅ አካላቸውንና ልባቸውን ያለ ነቀፋ ንጹህ አድርገው መጠበቅ እንደነበረባቸውም አስበዋል፡፡ ስለዚህ በእምነት ሕይወታቸው በጣም የጋሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን አንድ ከበድ ያለ ስህተት በቅድመ መከራ ንጥቀት ላይ ያላቸውን እምነታቸውን አናግቶታል፡፡ በኢየሱስ ያላቸው እምነትና የጌታን ምጽዓት መጠበቃቸው የሚያስመሰግን ቢሆንም ነገር ግን ሁለት ከባድና አደገኛ ስህተቶችን ሰርተዋል፡፡
 
በመጀመሪያ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምኑ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት እያለባቸው ጌታን መጠበቃቸው ነው፡፡ እነርሱ የመስቀሉን ደም ብቻ አጥብቀው በመያዝ ተደገፉበት፡፡ ነገር ግን በየቀኑ የሚፈጽሙዋቸውን ሐጢያቶች ፈጽሞ ሊያስተሰርይ የሚችል የንስሐ መጠን የለም፡፡ ነገር ግን የክርስቶስን ዳግመኛ ምጽዓት ቀንና ሌሊት ጠብቀዋል፡፡ ከሐጢያቶቻቸው ንስሐ ለመግባት፣ ሌሊቱን ሙሉ ለመጸለይ፣ የምስጋና ዝማሬዎችን ለመዘመርና ንጥቀታቸውንም በጋራ ለመጠበቅ በቤተክርስቲያኖቻቸው ውስጥ አንድ ላይ ተሰብስበዋል፡፡ ንጥቀታቸውን እንዲህ መጠበቃቸውና መናፈቃቸው ምንም ስህተት የለውም፡፡ ነገር ግን ትክክለኛ እምነት ሳይኖራቸው ማለትም በእግዚአብሄር ፊት ልጆቹ ሆነን እንድንቆም በሚፈቅድልን ብቸኛ እምነት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምኑ የመጠበቅን ከባድ ስህተት ፈጽመዋል፡፡
 
ሁለተኛው ስህተት ከእነርሱ አንዳንዶቻቸው ምንም ዓይነት ትክክለኛ የሆነ የእግዚአብሄር ዕቅድ መረዳት ሳይኖራቸው ኢየሱስ በቅርብ የሚመጣበትን ቀን በግብታዊነት ማወጃቸው ነበር፡፡ ይህ ብዙ ምዕመናን እርሱን በከንቱ እንዲጠብቁት ከማድረጉም በላይ በክርስትና ላይ መጥፎ ስሜቶችን በመፍጠርና በማያምኑ ሰዎችም መካከልም ክብሩን በማዋረድ በማህበረሰብ ውስጥ ሁሉንም ዓይነት ግራ መጋባት ፈጥሮዋል፡፡
 
በእነዚህ ሁለት ስህተቶች ምክንያት ሰዎች በትጋት የጠበቁት ንጥቀት ፈጽሞ ተግባራዊ ባልሆነ ጊዜ ብዙ ሰዎች ስለ ንጥቀት መጥፎ ነገር እንዲያስቡ በማድረግ ይበልጥ ከእውነት እንዲርቁ ገፋፋቸው፡፡ አሁን ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ ምጽዓት ለመነጋገር ትክክለኛው ጊዜና የእርሱ ምጽዓት ሲቃረብ ማንም ስለዚህ ነገር ዳግመኛ አይናገርም፡፡ ምስጋና ሁሉ ፈራቸውን ለለቀቁ ጥቂቶች ውርደት ይሁን፡፡ አሁን እየተነጋገርንበት ያለነው ምንባብ እግዚአብሄር በዮሐንስ በኩል ለጴርጋሞን ቤተክርስቲያን መልአክ የጻፈውን ነበር፡፡ እግዚአብሄር እምነታቸውን በሰማዕትነታቸው እስከ መጨረሻው ድረስ የጠበቁትን የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋይና ቅዱሳኖችን አመስግኖዋቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የጴርጋሞንን ቤተክርስቲያን ማመስገኑን ተከትሎም አንዳንድ ወቀሳዎችንም ሰንዝሮዋል፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ በአባሎችዋ መካከል ዓለምን የሚከተሉ ነበሩባትና፡፡ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኒቱ ንስሐ እንድትገባ የነገራትና አለበለዚያ ፈጥኖ በመምጣት እንደሚቀጣቸው የተናገረው ለዚህ ነው፡፡
እዚህ ላይ እግዚአብሄር በዮሐንስ በኩል በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያኖች በሙሉ በጋራ የተናገረውን ነገር ማሰብ አለብን፡፡ ‹‹መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፡፡›› ይህ ማለት እግዚአብሄር እውነቱን በአብያተ ክርስቲያኖቹና በአገልጋዮቹ በኩል ለቅዱሳኖቹና ለነፍሳቶች መናገሩን አረጋግጦዋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ለጴርጋሞን ቤተክርስቲያን የተናገረው ይታወስ፡፡ ‹‹መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፡፡ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፡፡ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሌለ አዲስ ስም ተጽፎዋል፡፡››
 
‹‹ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ›› በሚለው ሐረግ ላይ ትኩረት እናድርግ፡፡ ይህ ማለት ጌታን በእውነት የሚጠብቁ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጠላቶች ማሸነፍ አለባቸው ማለት ነው፡፡ ዓለምን የሚከተሉትን መዋጋትና ከእነዚህ የዓለም ወዳጆችም መለየት አለባቸው ማለት ነው፡፡ በለዓምን የሚከተሉ ሰዎች ሐሰተኛ ነቢያቶችን የሚከተሉ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በሐጢያተኛ ስስታምነታቸው የዓለምን ባለጠግነቶች ብቻ የሚሹ በመሆናቸው የበለዓም ትምህርት ተከታዮች ብሎ እንደጠራቸው እግዚአብሄር ነግሮናል፡፡
 
ሁሉም ቤተክርስቲያን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን አይደለም፡፡ ብዙዎቹ የዘመኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ይቀበላሉ፡፡ ነገር ግን እርሱ አምላክ መሆኑን አያምኑም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ዓለም እንደፈጠረ የማያምኑም ብዙዎች አሉ፡፡
 
በተጨማሪም ብዙ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱት ቁሳዊ በረከቶችን ለማግኘት ነው፡፡ እጅግ ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ለጉባኤዎቻቸው ብዙ ገንዘብ ለቤተክርስቲያን ቢሰጡ እንደሚባረኩ ይነግሩዋቸዋል፡፡ በእነዚህ የሐሰት ትምህርቶች የተታለሉ ብዙ ምዕመናን ለቤተክርስቲያን የሚሰጡት የሥጦታዎቻቸው ብዛት የእምነታቸው ነጸብራቅ እንደሆነ በተጨባጭ ያስባሉ፡፡ ከእነርሱ ብዙዎቹ ሥጦታዎችን በመስጠትና በየጊዜው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ብቻ ታማኝ ምዕመናን መሆናቸው ተረጋግጦላቸዋል፡፡ ከዚህም በላይ ከእነርሱ አንዳንዶቹ በየጊዜው በቤተክርስቲያን ውስጥ በመገኘታቸውና በማገልገላቸው የድቁና ወይም የሽምግልና የአመራር ሥልጣኖች ተሰጥቶዋቸው ትላልቅ ቼኮችን በስጦታ መልክ ያበረክታሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ እኛ ልንላቀቃቸው የሚገቡን የበለዓም መንገዶች ናቸው፡፡
 
እንዲህ ያለውን እምነት መዋጋት አለብን፡፡ ከተሰወረው መና መመገብ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ቤተክርስቲያናችሁ በእርግጥ የእግዚአብሄርን ቃል የምትከተል ቤተክርስቲያን መሆን አለመሆንዋን መለየት አለባችሁ፡፡ እንደዚያ ካልሆነች ልትዋጉዋትና ልታሸንፉዋት ይገባችኋል፡፡ እውነተኛ የእግዚአብሄር ቃል የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት መመገብ የምትችሉት ይህንን በማድረግ ብቻ ነው፡፡
 
ዳግመኛ መወለድ የምትችሉት የተሰወረ መና ከሆነው የውሃና የመንፈስ ቃል ስትመገቡ ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተሰጠውን የእውነት ቃል መመገብ የምትቀጥሉት ዳግመኛ በመወለድ ብቻ ነው፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች የእግዚአብሄር ቃል ምን እንደሆነ የሚወያዩት በሕብረት ሆነውም በመስማት፣ በማየትና በመከፋፈል ሊመገቡ የሚችሉት በዚህ መንገድ ነው፡፡
 
በእግዚአብሄር ለመነጠቅ ከልባችሁ ፍላጎት ካላችሁ፤ በእርግጥ ከልባችሁ ዳግመኛ ለመወለድ ከፈለጋችሁ በስም ብቻ ቤተክርስቲያን ወደሆነ ስፍራ በመሄድ መቀጠሉ ሞኝነት ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ባልሆነ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመገኘት እውነተኛውን የእግዚአብሄር ቃል በፍጹም መመገብ አትችሉም፡፡ ምን ያህል ለረጅም ጊዜ--ለመቶ ዓመት፣ ለሺህ ዓመት ወይም ከዚያ ለበለጠ ጊዜ ወደዚያ ቤተክርስቲያን ብትሄዱም በደህንነታችሁ ትክክለኛ መንገድ ላይ የሚያቆማችሁ ምንም ነገር አይኖርም፡፡
 
እነዚህ ሰዎች በእምነት ዳግመኛ ሊወለዱ የማይችሉ ከመሆናቸውም በላይ መጨረሻው የመጀመሪያ መጠይቅ የሆነውን ሳይፈጽሙ ማለትም ዳግመኛ ሳይወለዱ ንጥቀታቸውን የመጠበቅ የሞኝ ስህተት መስራተ ይሆናል፡፡ የዚህ ዓይነቱ እምነት በአጭሩ የተሳሳተ ነው፡፡ ምንም ያህል የክርስቶስን መምጣት በጉጉት ብትጠብቁ ምንም ያህል ጌታን በእርግጠኝነት በልባችሁ ብትወዱት፣ ምንም ያህል ሕይወታችሁን ለኢየሱስ አሳልፋችሁ ለመስጠት ፈቃደኞች ብትሆኑም እነዚህ ሁሉ ዋጋ ቢስ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጌታን አይገናኙትም፡፡ ለእግዚአብሄር ያላቸው ፍቅር ምላሽ የማይሰጥ ፍቅር ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡
 
እግዚአብሄር በእስያ ለሚገኙት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ‹‹ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ›› ብሎ የተናገረው ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለ ምንም ትግል የእውነት ቃሉን መያዝ እንደምንችል አልነገረንም፡፡ ውሸቶችን ተዋግተን ድል ካልነሳናቸው የሕይወት ቃል የሆነውን መና መብላት አንችልም፡፡ ምንም ያህል በታማኝነት በቤተክርስቲያናችሁ ተገኝታችሁ የነበረ መሆኑ ፋይዳ የለውም፡፡ እውነትን የማታውቁ ከሆናችሁ እስከ አሁን ድረስ ያወቃችሁት በሙሉ ውሸት ነው ማለት ነው፡፡ እውነትን ስትፈልጉ እነዚህን ውሸቶች ተዋግታችሁ በማሸነፍ ልታመልጡዋቸው ይገባል፡፡ የሕይወትን መና መብላት የምትችሉት የእግዚአብሄርን ቃል የምትመሰክረዋንና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የምትሰብከዋን ቤተክርስቲያን በማግኘት ከዚህ እውነት ጋር ስትገጣጠሙ ብቻ ነው፡፡
 
የውሃውንና የመንፈሱን ቃል እውነት ወደ ልባችን ውስጥ ከመቀበል የሚከለክለን ምንም ነገር የለም፡፡ የዚህን የውሃውንና የመንፈሱን ቃል የሚሰብኩና የሚሰሙ ሰዎች ልቦች የተቆራኙ ናቸው፡፡ በሁሉም ልቦች ውስጥም መንፈስ ቅዱስ ይኖራል፡፡
 
እግዚአብሄር ድል ለሚነሱት ከተሰወረው መናው እንደሚሰጠን ቃል ገብቷል፡፡ ስለዚህ ከእርሱ ጋር በምናደርገው ትግል ሰይጣንን ማሸነፍና ውሸታሞችንም ተዋግተን ድል ማድረግ አለብን፡፡ ዘላለማዊ ሕይወትን የምትፈልጉ ከሆነ በእውነት ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ፡፡ በእግዚአብሄር መነጠቅ የምትፈልጉ ከሆናችሁ ትክክለኛ እምነት ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ የዚህን ዓለም ብዙ ውሸታሞች እንደዚሁም በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ የሚገኙትን ዋሾዎች መታገልና ማሸነፍ አለባችሁ፡፡
 
እምነታችሁ የጥርጥር ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው ወገን በመዋለል የሚቀጥልና በተሰጠው ጊዜ በሚፈስስ በማናቸውም ፍሰት የሚጎተት መሆን የለበትም፡፡ ቤተክርስቲያናችሁ የእግዚአብሄርን ቃል በተጻፈው መሰረት የምትሰብክ ቤተክርስቲያን ካልሆነች ወደዚያች ቤተክርስቲያን መሄድ ማቆም አለባችሁ፡፡ እግዚአብሄር በመናው ቃሉ በውሃውና በመንፈሱ የእውነት ቃል በኩል የሚገናኛቸው ልባቸው እውነትን የሚወድና የሚከተል ሰዎችን ብቻ ነው፡፡
 
በሴሚናሪ ውስጥ እየተማርሁ በነበርሁ ጊዜ በጣም ጥሩ ተማሪ ነበርሁ፡፡ አንድም ጊዜ ከክፍል ቀርቼ አላውቅም፡፡ ውጤቶቼም እጅግ በጣም ጥሩ ነበሩ፡፡ በታማኝነትና በትጋት ሳጠና ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ የማላውቃቸው በጣም ብዙ ነገሮች ነበሩ፡፡ እኔ ኢየሱስን ከማግኘቴና በእርሱ ከማመኔ በፊት ከመላው ቤተሰቤ ጋር የቡዲስት እምነት ተከታይ ስለነበርሁ በወቅቱ ስለ እርሱ ያለን ዕውቀት በጣም ውሱን ነበር፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ለመማር በጣም ጉጉት ነበረኝ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ዕውቀት ስለተጠማሁ በሴሚናሪ ውስጥ የሚገኙትን ብዙ ፕሮፌሰሮች ብዙ ጥያቄዎቸን በመጠየቅና መልሶቻቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥማቴን እንደሚያረካልኝ ተስፋ በማድረግ ከእነርሱ መማርን ፈለግሁ፡፡
 
ሆኖም ከእነርሱ አንዳቸውም ግልጽ የሆነ መልስ አልሰጡኝም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸው ለሚደነቁ ፕሮፌሰሮች ጥያቄዎችን ሳቀርብ ጥያቄዎቼን በመመለስ ፋንታ ባለኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ያመሰግኑኝ ነበር፡፡ በሴሚናሪዎች ውስጥ ፕሮፌሰሮች ቃሉን አይሰብኩም፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸውን የራሳቸውን ‹‹ጽንሰ አሳቦች›› ያስተምራሉ፡፡ ነገር ግን ከብሉይ ኪዳን የሥነ መለኮት ትምህርት እስከ ስነ አመክንዮ የሥነ መለኮት ትምህርት፣ እስከ ክርስትና ታሪክ፣ ከካልቪኒዝም እስከ አርሜኒያኒዝም፣ ከትምህርተ ክርስቶስ እስከ ትምህርተ መንፈስ፣ ከመቅድማዊ ጥናቶች እስከ ዝርዝር ማብራሪያዎች ድረስ ጽንሰ አሳቦቻቸው በሙሉ የሰው አስተሳሰብ ውጤቶች ብቻ ነበሩ፡፡ የሚያስተምሩት ሊቃውንቶች የደገፉዋቸውን የተለያዩ ጽንሰ አሳቦች ብቻ ነው፡፡ በኮሌጅ ዓለማዊ የጥናት መስካችሁ ውስጥ ከምትማሩዋቸው የተለያዩ ጽንሰ አሳባዊ ምልከታዎች የተለዩ አይደሉም፡፡
 
እኔ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ያልነበረኝ ሰው ነበርሁ፡፡ የዕውቀት ስልጠናዬ ምንም ያህል ጥልቅ ቢሆን ወይም ብዙዎች ሰፊ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቴ ላይ አሳባቸውን ቢሰነዝሩ ፋይዳ የለውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንና ሥነ መለኮትን አብዝቼ ባጠናሁ ቁጥር ስለ መንገድ ብዙ ጥርጥሮች ተፈጠሩብኝ፡፡ ውሎ አድሮ እኔ ፈጽሞ አላዋቂ ሰው እንደሆንሁና እንደገና ከምንም መጀመር እንዳለብኝ በራሴ ተገነዘብሁ፡፡ ስለዚህ በወቅቱ በምማርባቸው ክፍሎች ውስጥ እንግዳና አሳፋሪ እንደሆኑ የተቆጠሩ ጥያቄዎችን ማንሳት ጀመርሁ፡፡ ከእነዚህ አንዱ ይህ ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ?›› ለዚህ ጥያቄ በጭራሽ ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀው ሐጢያቶቻችንን በገዛ ሥጋው ላይ ለመሸከም የመሆኑን ትክክለኛ መልስ ማንም የሰጠኝ አልነበረም፡፡
 
ኢየሱስ በአምስት እንጀራና በሁለት አሳዎች ብቻ አምስት ሺህ ሰዎችን በመገበበት ዓይነት የፈጸማቸውን ተዓምራቶች በሚመለከትም ጥያቄዎች ነበሩኝ፡፡ ስለዚህ ‹‹ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን አሳዎች ሲባርክ በአንድ ጊዜ የእንጀራና የአሳ ክምር ሆኑ ወይስ ምግቡ ለእያንዳንዱ ሰው ሲከፋፈል እየበዛ ሄደ?›› በማለት ጠየቅሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ እንደ እነዚህ ዓነት ጥያቄዎችን በማንሳቴ ዘለፋና ወቀሳ ተሰንዝሮብኛል፡፡
 
‹‹ሥነ መለኮት ማለት ይህ ነው፡፡ እየተማርን ያለነው ፈረንሳዊው ካልቪን ያስቀመጣቸውን ብልሃት በታከለበት መንገድ በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ጽንሰ አሳብና ማብራሪያዎች ነው፡፡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ነገር አናውቅም›› ወደሚል ግንዛቤ የመጣሁት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ የብዙ ቤተክርስቲያኖችን ዕትሞች በማሰባሰብና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማነጻጸር ራሴን ጥልቅ በሆነ ምርምር መጥመድ ጀመርሁ፡፡ እንዲያም ሆኖ ምንም ነገር አላገኘሁም፡፡
 
የሁሉም ድምዳሜ ሰዎች በኢየሱስ ሲያምኑ ሐጢያቶቻቸው ቀስ በቀስ ይጠፋሉ፤ ምክንያቱም በንስሐ ጸሎቶቻቸው ይቀደሳሉና፤ ሲሞቱም ሙሉ በሙሉ ሐጢያት አልባ ሆነው ሰማይ ይገባሉ የሚል ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡ የቤተክርስቲያን ልዩነቶች ከቁጥር የሚገቡ አይደሉም፡፡ የሁሉም መሰረታዊ የሆነው ተመሳሳይ ድምዳሜ ክርስቲያኖች የንስሐ ጸሎቶችንና በሒደት ላይ የተመሰረተ ቅድስናን በመከተል እንዲቀጥሉ የሚያደፋፍር ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ከቃሉ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ አባባሎች የእግዚአብሄር ቃል ከተናገረው ውጭ ናቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት ተንበርክኬ የእርሱን እውነት ፈለግሁ፤ ለመንሁም፡፡
 
እግዚአብሄር እውነተኛውን የውሃና የመንፈስ ወንጌልን ያስተማረኝ በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ይህ እውነት አስገረመኝ፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነት በ66 የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች ውስጥ እንደሚገኝ ባወቅሁ ጊዜ የታወሩት ዓይኖቼ ተከፍተው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በግልጽ ማየት ጀመርሁ፡፡ ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን እንዴት እንደተቀናጁም ተረዳሁ፡፡ ይህንን እውነት ባገኘሁ ጊዜም መንፈስ ቅዱስ ወደ ልቤ መጣ፡፡ ይህንን እውነት ከተመለከትሁና ከተረዳሁ በኋላ ልቤን ያሳመሙ፣ አብዝተው የተጫኑኝ በጣም ብዙ ሐጢያቶች አስገራሚና ድንቅ በሆነው የእግዚአብሄር የፍቅርና የጸጋ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ብን ብለው ጠፉ፡፡
 
ትንሽዬ ድንጋይ ጸጥ ባለ ሐይቅ ላይ ስትወረወር የውሃ ማዕበሎች እንደሚፈጠሩ ሁሉ ሰማያዊ ደስታና ብርሃን ወደ ልቤ ገባ፡፡ ብርሃን ስል የቃሉ እውነት ምን እንደነበር ተገነዘብሁ ማለቴ ነው፡፡ በዚህች የግንዛቤ ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወደ ልቤ ገባ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በግልጽ ወደ ማየት ደረስሁ፡፡ ከዚህች ቅጽበት ጀምሮ ሁልጊዜም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መስበኬን ቀጠልሁ፡፡
 
እስከዚህች ቀን ድረስ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በልቤ ውስጥ ጸንቶ አጽናንቶኛል፤ አበርትቶኛል፡፡ ልቤንም ሁሌም ንጹህ አደርጎ ጠብቆልኛል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ወደ መመገብ የመጣሁት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ ፍቺውን ተረድቼ በቃሉ ላይ ዕርፍ ስል ልቤን የሚሞላ ሰላማዊ በረከት ይመጣል፡፡ ልቤም በፈንታው በዚህ የጸጋ ባህር ውስጥ መዋኘት ይጀምራል፡፡ ልቤ እንዲህ በዚህ በረከት እንደተሞላ ሁሉ እናንተም በእርሱ ዳግመኛ የመወለድ ደህንነት ስታምኑ የእግዚአብሄር ቃል ወደ ጸጋውና በረከቱ ያስገባችኋል፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስን ከፍቼ በቃሉ ላይ ስውል ጭንቀቶቼና ዕረፍተ ቢስ የሆኑት አስተሳሰቦቼ በሙሉ ብን ብለው ይጠፉና ልቤ በደስታና በሰላም ይሞላል፡፡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በምጠይቅ ጊዜ ሁሉ ሁሌም እግዚአብሄር በቃሉ ውስጥ በትክክል ምን ማለቱ እንደሆነ መመለስ እችላለሁ፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል የሚመገበው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማወቅና በማመን ብቻ ነው፡፡ ሰው ዳግመኛ መወለድ የሚችለው የእግዚአብሄርን ቃል በመመገብ ብቻ ነው፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ከእንግዲህ ወዲህ በልባቸው ውስጥ የቀረ ሐጢያት ስለሌለባቸው ጌታ ወደዚህ ምድር ቢመጣም በመጨረሻ በአየር ይወስዳቸው ዘንድ ለንጥቀታቸው ዝግጁ ናቸው፡፡
 
 
ወደ ንጥቀት ሊመራን የሚችለው እምነት፡፡ 
 
የውሃውንና የመንፈሱን ወንገል አውቀን በማመን መዳናችንን ከተቀበልን በኋላ የምንጠብቀው ንጥቀትን ነው፡፡ ስንጠብቅም እግዚአብሄር የወሰናቸውን ዘመናቶች በግልጽ ተረድተን መጠበቅ አለብን፡፡ እግዚአብሄር የወሰናቸው ዘመናቶች ሰባቱ ዘመኖች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል የሰማዕትነቱ ዘመን የሐመሩ ፈረስ ዘመን ነው፡፡ የሐመሩ ፈረስ ዘመን እግዚአብሄር ከወሰናቸው ከሰባቱ ዘመኖች አራተኛው ነው፡፡ አሁን በሌላ በኩል እየኖርንበት ያለንበት ዘመን የጉራቻው (የጥቁሩ) ፈረስ ሦስተኛ ዘመን ነው፡
 
ትልቅ ተራራን ስንወጣ ካርታውን መሪያችን አድርገን እንደገፍበታለን፡፡ ነገር ግን ይህንን ካርታ በመጠቀም የምንፈልገው ስፍራ ላይ በትክክልና በሰላም ለመድረስ በመጀመሪያ ስፍራችን ምን እንደሆነ አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡ ካርታ በማንበብ የተካናችሁ ብትሆኑ ወይም ካርታው ራሱ ትክክለኛ ቢሆን የት እንዳላችሁ የማታውቁ ከሆነ ካርታው ጥቅም የለውም፡፡ ወዳሰባችሁበት ቦታ በሰላም መድረስ የምትችሉት ስፍራችሁን ስታውቁ ብቻ ነው፡፡
 
መቼ እንደምትነጠቁ ማወቅ የምትችሉትም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት በማመን ብቻ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የተረጋገጠው የንጥቀት የጊዜ ወሰን ከሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ አጋማሽ ጥቂት አለፍ ያለ ማለትም መከራው በጀመረ በሦስት ዓመት ተኩል ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በመጀመሪያ ይህንን ዩኒቨርስ ሲፈጥር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያቀደው ይህንን ነው፡፡
 
እግዚአበሄር አንድ ልጁን ወደዚህ ምድር የላከበት፣ እንዲጠቀም፣ በመስቀል ላይ እንዲሞትና እንዲነሳ ያደረገበት በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነው የደህንነት ዕቅዱ ብቸኛው ዕቅድ አይደለም፡፡ ነገር ግን እርሱ ዩኒቨርስ ከፍጥረት እስከ ፍጻሜው ድረስ የወሰነለት የሰባት ዘመናቶችን ጊዜ አስቀምጦዋል፡፡ ቤቶቻችንን ከመገንባታችን በፊት ንድፎችን እንሰራለን፡፡ የንግድ ሥራዎቻችንን ከመስራታችን በፊትም አስቀድመን እናቅዳለን፡፡ እንዲያውም በተሻለ መልኩ በቀን ውስጥ የምናደርጋቸውን ነገሮች ለአደራጆቻችን ተራ እናሲዛለን፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር ይህንን ዩኒቨርስ፣ ሰውን እናንተንና እኔን በኢየሱስ ክርስቶስ የፈጠረን ያለ ዕቅድ ነውን? በእርግጥ አይደለም! የፈጠረን በዕቅድ ነው!
 
ይህ ዕቅድ በራዕይ ቃል ውስጥ በሚገባ ተገልጦዋል፡፡ ይህንን ቃል ገልጠን ስናነበው የእግዚአብሄር ዕቅድ በትክክል ምን እንደሆነ ማግኘት እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የብዙ ሺህ ዓመታቶች ዕድሜ ቢኖረውም አሁንም ድረስ ያልተጨመረበትም ሆነ ያልተቀነሰበት የማይለወጥና የማይቀየር እውነት ነው፡፡ ይህንን የማያውቁና ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች አሁንም ድረስ በእግዚአብሄር ቃል የተገለጠልንን እውነት ሳያውቁ ቀርተዋል፡፡ ነገር ግን በቃሉ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን እውነት ማግኘትና መረዳት ይችላሉ፡፡
 
እግዚአብሄር መናውን ድል ለሚነሱት እንደሚሰጥ የሚናገረው ምንባብ እግዚአብሄር በቃሉ ላይ ብርሃን የሚያበራው የእውነት ቃሉን በማወቅ እውነትን ከውሸት ለይተው በሚያስተውሉና ውሸቶችን ሁሉ ድል በሚነሱ ሰዎች ላይ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ከውሸቶች አምልጠው እውነትን ያገኙ ሰዎች ይህንን እውነት በመስበክ እነዚህን ውሸቶች ማሸነፍ አለባቸው፡፡ እግዚአብሄር በወንጌል ለሚያምኑ ሰዎች መናውን የመመገብ በረከት እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል፡፡ ‹‹ድል ለነሳው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፡፡ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፡፡ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል፡፡››
 
እዚህ ላይ የተሰወረው መና የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ በሌላ በኩል ነጩ ድንጋይ ስሞቻችን በሕይወት መጽሐፍ ላይ ይጻፋሉ ማለት ነው፡፡ ሰዎች እግዚአብሄር በሰጣቸው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ሲያምኑ ልባቸው ይለወጣል፡፡ ልባቸው በመንፈስ ቅዱስ ቃል ሲሞላ በልባቸው ውስጥ ያሉት ሐጢያቶች በሙሉ ይጠፋሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ በውሃውና በመንፈሱ ከነጹ በኋላ ስሞቻቸው በነጩ ድንጋይ ላይ ይጻፋል፡፡
 
እግዚአብሄር ከተቀበለው ሰው በቀር ይህንን አዲስ ስም ማንም እንደማያውቀው ነግሮናል፡፡ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይቅርታን ያገኙ ሰዎች ልባቸው በውስጡ የቀረ አንዳችም ሐጢያት እንደሌለበትና ስሞቻቸውም በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እንደተጻፈ መረዳት አለባቸው፡፡ እውነተኛውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በዚህ ሁኔታ በማወቅና ደህንነታቸውን በመቀበል ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ብቻ ጌታንና እውነቱን ማወቅ ይችላሉ፡፡ ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች ገና ዳግመኛ መወለድ እንደሚኖርባቸው አያውቁም፡፡ ዳግመኛ የተወለዱት ግን እነዚህ ሰዎች ገና የእግዚአብሄርን መና እንዳልተመገቡና ስሞቻቸው በነጩ ድንጋይ ላይ እንዳልተጻፈ በቀላሉ መለየት ይችላሉ፡፡
በእርግጥ መነጠቅ ትፈልጋላችሁን? መነጠቅ የምትፈልጉ ከሆነ መናውን ለመመገብ የበቃችሁ መሆን አለባችሁ፡፡ መናውን ለመመገብ መብቃት ስል በውሃውና በመንፈሱ ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ ማለቴ ነው፡፡ መናውን ለመመገብ ውሸቶችን በእምነታችሁ መዋጋትና ድል መንሳት አለባችሁ፡፡ሐሰተኛ አስተማሪዎች ለሐጢያተኞች ደህንነትን አያመጡም፡ ነገር ግን ነፍሳቸውንና ቁሳዊ ሐብቶቻቸውን ይበዘብዛሉ፡፡ እነዚህን የዘመኑን ክርስትና ሐሰተኛ ቤተክርስቲያኖች፣ ሐሰተኛ ነቢያቶችና ሐሰተኛ አገልጋዮች ተዋግተን ማሸነፍ አለብን፡፡
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመርኩዘን ኢየሱስን እንዴት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ፣ ለምን እንደተጠመቀ፣ ለምን የዓለምን ሐጢያቶች እንደወሰደ፣ ለምን በመስቀል ላይ እንደሞተና ለምን ዳግመኛ ከሙታን እንደተነሳ ማወቅ አለብን፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር በሥጋ መጥቶ ለምን እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዳደረገ በትክክል ማወቅ አለብን፡፡ ኢየሱስ በትክክል ማን እንደሆነም ማወቅ አለብን፡፡ ሐሰተኛ ቤተክርስቲያኖች ግን እነዚህን እውነቶች በማስተማር ፋንታ በራሳቸው ሥልጣን ወደ እነርሱ የሚመጣውን ማንኛውንም ሰው ‹‹ቅዱስ›› ብለው ይጠሩታል፡፡ የሚጠይቁት ነገር ቢኖር ‹‹በኢየሱስ ታምናለህን?›› የሚል ብቻ ነው፡፡ መልሱ ‹‹አዎ አምናለሁ›› የሚል ከሆነ እነዚህ ሐሰተኛ ቤተክርስቲያኖች ወዲያውኑ ቅዱሳን ብለው ይጠሩዋቸውና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያጠምቁዋቸዋል፡፡ ከዚያም ለዚያ የሚያብረቀርቅ አዲስ የቤተክርስቲያን ሕንጻ ማሰሪያ በሚያደርጉት የስጦታዎች ልመና ከምስጋና ስጦታዎች ጀምሮ እስከ ልዩ ስጦታዎች ድረስ ሁሉንም የስጦታ ዓይነቶች ከእነርሱ መሞጭለፋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያኖች በገንዘብ ላይ ብቻ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ትልቅ የሚያብረቀርቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻ የመገንባት ስስታቸውም በሙሉ የሐሰተኛ ቤተክርስቲያኖች ናቸው፡፡
 
መናውን ስንመገብ እነዚህን ሐሰተኛ ቤተክርስቲያኖችና ሐሰተኛ ትምህርቶችን የሚያስተምሩትን ሰዎች መታገል አለብን፡፡ በጦርነታችን ውስጥ ከተሸነፍን ከእንግዲህ ወዲያ ቅዱሳን ካለመሆናችንም በላይ በእግዚአብሄር አንነጠቅም፡፡ የእግዚአብሄር ቅዱሳን አለመሆን ማለት የእግዚአብሄር ልጆች አለመሆን ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ለ100ኛ ጊዜ ቢመጣ እንኳን አንነጠቅም፡፡
 
ማቴዎስ 25 ከእነርሱ አምስቱ ብልህ አምስቱ ደግሞ ሰነፎች ስለሆኑ አስር ቆነጃጅት ይነግረናል፡፡ መብራታቸውን ይዘው ዘይት ያልያዙትና የሙሽራው መምጣት ከተነገረ በኋላ ብቻ ሊገዙ የሄዱት አምስቱ ሙሽሮች ምን ያህል ሰነፎች እንደነበሩ ይነግረናል፡፡ እኛ አስቀድመን ዘይት ያዘጋጀን ብልህ ሙሽሮች መሆን አለብን፡፡ ዘይት የሚያዘጋጅ እምነት መያዝ ስል በኢየሱስ ፊት መናውን ለመመገብ የበቃን መሆንና ውሸታሞችን የምናሸንፍና በውሃውና በመንፈሱ ቃል ዳግመኛ የምንወለድ መሆን አለብን ማለቴ ነው፡፡
 
ስብከት ስንሰማ መጋቢው የእግዚአብሄርን ቃል እየሰበከ ስለ መሆን አለመሆኑ ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡ ቤተክርስቲያን ገንዘብዋን የምታውለው እግዚአብሄር እንደሚፈልገው ማለትም ለራስዋ ሳይሆን ለሥራዎቹ መሆኑን መጠየቅ ያስፈልገናል፡፡ በሌላ አነጋገር የእግዚአብሄርን ቃልና ትምህርቶቹን በመስበክ የከንፈር አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቤተክርስቲያኖች ይሰለቹዋችሁ፡፡
 
በንግግራቸውና በንስሐቸው ምንም ያህል ሰናይ ቢሆኑም ይበልጥ የሚደሰቱት ከማንኛውም ሌላ ነገር ይልቅ ትላልቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎችን በመገንባት ከሆነ ድሆችን ይረዱ እንደሆነ ወይም ለባለጠጋው ያጎበድዱ እንደሆነና ነፍሳቶችን የማዳን አንዳች ፍላጎት ያሳዩ እንደሆነ ምግባሮቻቸው በእርግጥ ለምን እንደቆሙ ይነግሩዋችኋል፡፡ እግዚአብሄር ዓይኖችና ጆሮዎች የሰጣችሁ ለራሳችሁ እንድታዩና እንድትፈርዱ ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችሁ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን እንዳልሆነች ድምዳሜ ላይ ስትደርሱ ፈጥናችሁ ከእርስዋ ለመውጣት አታመንቱ፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ ባለች ቤተክርስቲያን ውስጥ መገኘት ወደ ሲዖል ለመውረድ ከመሞከር ጋር ተመሳሳይ ነውና፡፡ የራሳችሁንም ሕይወት ልታጡ ትችላላችሁ፡፡
 
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ምን ያህል ሰናይ እንደሆነ ታውቃላችሁን? ይህንን እውነት ማለትም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስታውቁና በልባችሁ ስትቀበሉ ሙሉ በሙሉ አዲስ ሰው ትሆናላችሁ፡፡ ከዚህ በፊት ምድራዊ የነበሩ ሰዎች አሁን ሰማያዊ ይሆናሉ፡፡ በአጋንንቶች ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎችም አሁን ነጻ ይወጣሉ፡፡
 
አጋንንቶች በልባቸው ውስጥ ሐጢያቶች ወዳለባቸው ሰዎች ገብተው ነፍሳቸውን በማሰቃየት በሐጢያቶቻቸው ያስሩዋቸዋል፡፡ ጌታ ግን ወደዚህ ምድር መጥቶ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ፡፡ እርሱ ሐጢያቶቻችንን ፈጽሞ ስለወሰደ አጋንንቶች ከእንግዲህ ነፍሳችንን ማሰቃየት ወይም መስረቅ አይችሉም፡፡ ይህንን ወንጌል ስታውቁና ስታምኑ አጋንንቶች የሚወጡትና ሕይወታችሁ የሚለወጠው ለዚህ ነው፡፡
 
በሌላ አነጋገር የዓለም አገልጋዮች የነበሩ ሰዎች ከዚህ ባርነት ነጻ ወጥተዋል፡፡ እግዚአብሄርም ሐጢያተኞችን ጻድቅ የማድረግ ድንቅ ሥራ በመስራት ምድራዊ የነበሩትን ሰዎች ሰማያዊ እንዲሆኑ ዳግመኛ እየሰራቸው ነው፡፡ ጌታ ሲመለስም ወደ መንግሥቱ ይወስዳቸዋል፡፡
 
ምድራዊ ሕይወታችን የእኛ ፍጻሜ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በአምሳሉ ከፈጠረን በኋላ በዚህ ምድር ላይ ያስቀመጠን ለአጭር ጊዜ ብቻ እንድንኖር አይደለም፡፡ በእርግጥ የሥጋ ሕይወት በጣም አጭር ነው፡፡ ትምህርት ስንጨርስ በ20ቹ አጋማሽ ላይ ደርሰናል፡፡ ለሕይወታችን መሰረት በመጣልም 30ቹ ላይ እንደርሳለን፡፡ የምንገነባበት ይህ መሰረት ዝግጁ ሲሆንልን በ40ዎቹ ወይም በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ ነን፡፡ በመጨረሻ አሁን ረጋ ማለትና በሕይወት መደሰት እንችላለን ብለን ራሳችንን በምናስብበት ደረጃ ላይ ስንደርስ ዕድሜያችን በሙሉ አልፎ ወደ ፍጻሜው እንቃረባለን፡፡ አበቦች በማለዳ ፈክተው በቀትር እንደሚጠወልጉ በመጨረሻ ሕይወትን ጨበጥን ብለን ስናስብ ዘመናችን ማለፉንና የምንጠብቀውም እየተቃረበ ያለውን ፍጻሜውን ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡
 
ሕይወት እንግዲህ ይህንን ያህል አጭር ነው፡፡ ነገር ግን ይበልጥ የሚያሳዝነው ይህንን የሕይወትን አጭርነት የማያውቁ በጣም ብዙ ሰዎች መኖራቸው ነው፡፡ የሥጋ ሕይወታችን ፍጻሜ ግን የእኛ ፍጻሜ አይደለም፡፡ የነፍሳችን መንፈሳዊ ሕይወት ጅማሬ ነው፡፡ ለምን? እግዚአብሄር አጭሩን ምድራዊ ሕይወታችንን የሚክስ ይመስል የሺህ ዓመት መንግሥቱን ብቻ ሳይሆን ለዘላለም የምንኖርባቸውን አዲስ ሰማይና ምድርም አዘጋጅቶልናል፡፡ ይህ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ቃል ዳግመኛ ለተወለዱት ብቻ የለገሰው የዘላለም ሕይወት በረከት ነው፡፡
 
መነጠቅ የምትችሉት የተሰወረውን መና ስትበሉና ስማችሁ በነጩ ድንጋይ ላይ ሲጻፍ ብቻ ነው፡፡ በታላቁ መከራ ወቅት ሰይጣንን ማሸነፍ የሚችሉት የእርሱን መና የተመገቡ ብቻ ስለመሆናቸው እግዚአብሄር ነግሮናል፡፡ ስሞቻቸው በነጩ ድንጋይ ላይ የሚጻፈውም እንዲህ ድል የነሱት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህ ድል ያልነሱት ስለ ንጥቀት ሊያልሙም ሆነ ዳግመኛ ስለመወለድ ሊያልሙ አይችሉም፡፡
 
አንድን ዋጋ ያለውና የከበረ ነገርን ለማግኘት ታላላቅ መስዋዕትነቶች ይከፈላሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ወርቅ ነው፡፡ ወርቅን ለማግኘትና ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት ጊዜና መስዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ሰዎች አንዲት የወርቅ ቁራጭ ሳያገኙ በወርቅ ጉድጓዶች ውስጥ ሞተዋል፡፡ የከበረ ወርቅን ማውጣትም እንደዚሁ ብዙ ድካሞችን ይጠይቃል፡፡ ቀኑን ሙሉ አንድ መኪና ሙሉ አፈር ጭሮ የሚገኘው የአንድ ደቂቃ የወርቅ መጠን ብቻ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ይህ በማንኛውም ወንዝ ላይ ሊደረግ የሚችል አይደለም፡፡ በመጀመሪያ የወርቅ አፈር የሚገኝበትን ወንዝ ማግኘት አለባችሁ፡፡ በሌላ አነጋገር ወርቅን ለማግኘት ብርቱ ጥረትን አንዳንድ ጊዜም ዕድሜያችሁን ይጠይቃል፡፡ ታዲያ ሰዎች ወርቅን ለማግኘት ብዙ የሚለፉት ለምንድነው? ይህንን የሚያደርጉት ወርቅ ሕይወታቸውን እንኳን አደጋ ላይ እስከ መጣል ድረስ ዋጋ ያለው እንደሆነ ስለሚያስቡ ነው፡ 
 
ነገር ግን እኛ የእግዚአብሄር ልጆች የመሆናችን እውነታ ከወርቅና ከብር የበለጠ ዋጋ ያለውና የከበረ ነው፡፡ ወርቅ ለሥጋችሁ አንዳች አላፊ ደስታን ይሰጥ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን ግን ፈጽሞ የማያበቃ ዘላለማዊ ደስታን ይሰጣችኋል፡፡ በመጨረሻው ዘመን ለመነጠቅ፣ የሺህውን ዓመት መንግሥትና የአዲሱን ሰማይና ምድር ሐብት ብልጥግናና ክብር በደስታ ለማጣጣምና ይህንን ሕይወት ለዘላለም ለመኖር አሁን በዚህ ምድር ላይ ያሉትን ውሸታሞች በሙሉ በመዋጋት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምናችሁ እምነታችሁን መጠበቅና ድላችሁን መቀዳጀት አለባችሁ፡፡
 
በዚህ ምድር ላይ እምነታችንን እንድናጣ ለማድረግ በመሞከር ልባችንን ለመስረቅ ሁልጊዜም አጋጣሚዎችን የሚጠብቁ በጣም ብዙ ውሸቶች አሉ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ የሚያምኑና እውነቱም በልባቸው ውስጥ ያሉ ሰዎች እምነታቸው ምንኛ ክቡር እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ የዚህን እምነት ክቡርነት ስለሚያውቁም ይህንን ከእነርሱ ለመስረቅ የሚሞክሩትን የሐሰት ትምህርቶች በሙሉ ይዋጋሉ፡፡ ይህንን እምነት እየናፈቁ ሊደርሱበት ያልቻሉ ሰዎች ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ብናውቅ፤ ወደ በጉ የሰርግ እራት እንድንገባና የእርሱን የዘላለም ሕይወት በረከት እንድንቀበል የሚሸፍነን እምነት ይህ ብቻ እንደሆነ ብናውቅ ሙሉ በሙሉ የእኛ ባደረግነውና ማንም ሰው ፈጽሞ ከእኛ እንዲወስድብን ባልፈቀድንም ነበር፡፡ የዚህ ዓይነት እምነት ተዋጊና አሸናፊ እምነት ነው፡፡
 
ክቡር የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መጠበቅ ትችሉ እንደሆነ ለማረጋገጥ የራዕይን ቃል ትክክለኛ ዕውቀትና መረዳት ማሰራጨት አስፈላጊ እንደሆነ አምኛለሁ፡፡ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳኖችንም ለማሳትና ለማደናገር የራዕይን ቃል ለመጠቀም እንደሚሞክሩ ተረድቻለሁና፡፡ የራዕይን ቃል በስብከቶቼና በመጽሐፎቼ የምሰብከው በመጨረሻው ዘመን የእምነት ሕይወታችሁን በትክክለኛ ዕውቀትና አመኔታ መኖር እንድትችሉ ለማረጋገጥ ነው፡፡
 
የራዕይ መጽሐፍ አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ያቀርባል፡፡ ነገር ግን የራዕይ ቃል የእግዚአብሄርን የተሰወረ መና መብላት ለማይችሉትና በልባቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ለሌላቸው ሰዎች ምንም አይገልጥላቸውም፡፡ ከዘመኑ መጨረሻ ምልክቶችና የእያንዳንዱ ክርስቲያን ተስፋ ከሆነው ንጥቀት እስከ አዲሱ ሰማይና ምድር ድረስ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ አስገራሚ ዕቅድ ተጽፎዋል፡፡ ነገር ግን ምስጢራቱን እንዲያው ዝም ብሎ ለማንኛውም ሰው በማይገልጠው የእግዚአብሄር ጥበብ ምክንያት ራዕይ ሁሉም ሰው ሊረዳው የማይችለው አስቸጋሪ ቃል ሆንዋል፡፡ የራዕይን ቃል መረዳት የሚችሉት የእግዚአብሄርን መና የተመገቡትና በውሃውና በመንፈሱ ዳግመኛ በመወለድና ውሸቶችን ድል በመንሳት ስሞቻቸው በነጩ ድንጋይ ላይ የተጻፉ ሰዎች ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም፡፡
 
ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች ባለማወቃቸው ስለ ቅድመ መከራ ንጥቀት ወይም ድህረ መከራ ንጥቀት የሚናገሩትና በአሁኑ ጊዜ የሺህው ዓመት መንግሥት ምሳሌያዊ ብቻ ነው የሚሉ አንዳንድ ሰዎች የሚገጥሙን ለዚህ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነት ነው፡፡ ታላቁ መከራ ሳይኖርም ንጥቀት እንደማይኖር በግልጽ ይናገራል፡፡ ቃሉ ንጥቀት እንደማይኖር ብግልጽ ይናገራል፡፡ ቃሉ ንጥቀት የሚሆነው ከሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ አጋማሽ ትንሽ አለፍ ብሎ ከቅዱሳን ሰማዕትነትና ከትንሳኤያቸው በኋላ እንደሆነም ይነግረናል፡፡
 
የተለመደውን የቀን ተቀን ሥራ እየሰሩ መነጠቅ-- የአውሮፕላን አብራሪዎች በድንገት መሰወር፣ እናቶችም በመላው ዓለም ከእራት ማዕዶቻቸው ላይ መሰወራቸው -- ሊሆን እንደማይችል ስነግራችሁ አዝናለሁ፡፡ በፋንታው ንጥቀት የሚሆነው በምድር ላይ ታላላቅ ጥፋቶች በሚሆኑበት የመሬት መናወጥ ምድርን በሚያናውጥበት፣ ከዋክብቶች ከሰማይ በሚወድቁበትና ምድርም በምትሰነጥቅበት ጊዜ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ንጥቀት በጠራራ ጸሐይ ሰላም በሆነ ቀን የሚሆን ነገር አይደለም፡፡
 
ከዋክብቶች ገና አልወደቁም፡፡ የዓለም አንድ ሦስተኛው አልተቃጠለም፡፡ ባህርም ገና ወደ ደም አልተቀየረም፡፡ ይህንን ስል ምን ማለቴ ነው? አሁን ገና የንጥቀት ጊዜ አይደለም ማለቴ ነው፡፡ እግዚአብሄር ንጥቀት ከመምጣቱ በፊት ሁላችንም የምናውቃቸውን ምልክቶች እንደሚሰጠን ነግሮናል፡፡ እነዚህ ምልክቶች በዚህ ምድር ላይ የሚመጡት ጥፋቶች ናቸው፡፡ የባህርና ወንዞች ሲሶ ወደ ደም ይቀየራል፡፡ የዛፎች ሲሶ ይቃጠላል፡፡ ከዋክብቶች ይወድቃሉ፡፡ ውሃ ለመጠጣት አስቸጋሪ ይሆናል፤ ወ.ዘ.ተ፡፡
 
ዓለም እንደዚህ በታላላቅ መዓቶች ሲጥለቀለቅ ጸረ ክርስቶስ ሁሉን ለማስተካከል ብቅ ይላል፡፡ በመጀመሪያ ድንቅ የሆነ የዓለም መሪ ሆኖ ብቅ ይልና ውሎ አድሮ ዓለምን በአምባገነን ሥልጣኑ የሚገዛ ጨቋኝ መሪ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የጸረ ክርስቶስ ጨቋኝ አገዛዝ በዓለም ላይ በሚንሰራፋበት በዚህ ጊዜ ጌታ ቅዱሳኖቹን ለመውሰድ እንደሚመጣ ይነግረናል፡፡ ታላላቅ የተፈጥሮ ጥፋቶች ሳይሆኑና ጸረ ክርስቶስም ገና ሳይገለጥ ንጥቀት አይሆንም፡፡
 
በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር ቃል የገባልን እነዚህ ምልክቶች ገና ተግባራዊ ሳይሆኑ ሊነጠቁ እንደሆነ በማሰብ ሥራቸውን የሚያቆሙ፣ ወደ ትምህርት ቤት የማይሄዱና ኑሮዋቸውን በሙሉ ቀጥ አድርገው የሚያቆሙ ሰዎች ተሳስተዋል፡፡ በዚህ መንገድ መታለል የለባችሁም፡፡ ምክንያቱም ይህ በሰይጣን የውሸቶች ወጥመድ ውስጥ መግባት ነውና፡፡
 
እነዚህ የሐሰት ትምህርቶች እኛን ለማጥመድ ያስቀመጡትን እያንዳንዱን ነገር ተዋግተን ማሸነፍ አለብን፡፡ በሐሰት ትምህርቶች ላይ ማሸነፍ የሚችለው ብቸኛው እምነት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን እምነት ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ከእነዚህ ሐጢያቶች ሰንሰለት የሚፈቱት ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ በወሰደው በኢየሱስ ጥምቀት የሚያምኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ ስለወሰደና ሐጢያቶቻችንን ባነጻው ደሙ ስለገዛን ጌታ ባደረገልን በእነዚህ ነገሮች በእምነትና በእምነት ብቻ በማመን የእርሱን ፍጹም ደህንነት አግኝተናል፡፡ በዚህ ቃል የሚያምኑ ሰዎች አሁን የእግዚአብሄር ልጆች ሆነዋል፡፡ እግዚአብሄር ለእነርሱ ባዘጋጃቸው ዕቅዶች ሁሉ ውስጥም ድል ያደርጋሉ፡፡
 
በሌላ በኩል በኢየሱስ እናምናለን እያሉ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ያለባቸውና ጌታን ሲያገለግሉም የራሳቸውን ስስት ብቻ የሚሹ ዋሾዎች የሚጠብቃቸው ብቸኛው ነገር ከሰይጣን ጋር አብረው የሚጋፈጡት ቅጣት ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌላችን በጣም ክቡር የሆነው ለዚህ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን የተሰወረ መና መብላት የሚችሉትና በመጨረሻም ውሸቶችን ሁሉ ድል ነስተው ወደ ሺህው ዓመት መንግሥትና ወደ አዲስ ሰማይና ምድር የሚገቡት ይህንን ወንጌል የሚያውቁና በእውነተኞቹና በሐሰተኞቹ ወንጌሎች መካከል መለየት የሚችሉ ብቻ ናቸው፡፡ ሊያድናችሁ ተስፋ ሊሰጣችሁና በዘላለም ሕይወት ሊባርካችሁ የሚችለው ተጨባጭ እውነት ምን እንደሆነ ቃሉን በማንበብ ለራሳችሁ ተመልከቱ፤ ተገንዘቡት፡፡ በእርሱም ታመኑ፡፡ ድል አድራጊው እምነት ይህ ነው፡፡
 
በመንፈሳዊ ተጋድሎዋችን ድል ማድረግ ለእኛ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ተጋደሎ ውስጥ መሸነፍ ቀላል ሽንፈት ማለት ብቻ ሳይሆን ለሲዖል መታጨት ማለት ነውና፡፡ በሌሎች ተጋድሎዎች ውስጥ ከሽንፈት ልናገግም እንችላለን፡፡ በዚህ የእምነት ተጋድሎ ውስጥ ግን የማገገም ዕድል የለም፡፡ ስለዚህ እውነት ምን በመሆኑና በራሳችሁ አስተሳሰቦች፣ በሥጋችሁ ፍትወትና በሐሰተኛ አስተማሪዎች ውሸቶች መካከል መለየት መቻል አለባችሁ፡፡ በቃሉ ብርሃን በወቅቱ ትክክለኛውን ዕውቀት በመያዝ እምነታችሁን ለመጨረሻው ዘመን ማዘጋጀት አለባችሁ፡፡
 
እግዚአብሄር የሰባቱን መለከቶችና የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች አዘጋጅቷል፡፡ ታላቁን መከራም በእኛ ላይ ፈቅዶዋል፡፡ ዓለም ተወዳዳሪ በሌላቸው የተፈጥሮ ጥፋቶች ስትመታ -- ታላላቅ እሳቶች ሲያወድሙ፣ ከዋክብቶች ሲወድቁ፣ ባህሮች፣ ወንዞችና የውሃ ምንጮች ወደ ደም ሲቀየሩ -- ጸረ ክርስቶስ ይገለጣል፡፡ ይህ የሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ ጅማሬ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችኋል፡፡ የቅዱሳን ሰማዕትነት ትንሳኤና ንጥቀት የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች ከመውረዳቸው በፊት ነገር ግን የመጨረሻው መለከት በሚነፋበት በሰባቱ መለከቶች መቅሰፍቶች ፍጻሜ ላይ ይሆናሉ፡፡ 
አራተኛው የእግዚአብሄር ማህተም ሲፈታ ጸረ ክርስቶስ ቅዱሳን እንዲክዱ ይጠይቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ላይ የተጻፈ -- ማለትም መናን የተመገቡና ስሞቻቸው በነጩ ድንጋይ ላይ የተጻፉ ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳን -- በጀግንነት ሰማዕት ይሆናሉ፡፡ ይህ ክብርን ሁሉ ለጌታ የሚሰጥ የመጨረሻውና እጅግ ታላቁ እምነት ነው፡፡ ይህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑና በዚያ መሰረት የሚኖሩ ሰዎች የድፍረት እምነት ነው፡፡ በአጭሩ እኛ በመንፈሳዊ ተጋድሎዋችን ድል አድራጊዎች መሆን የምንችልበት እምነት ይህ ነው፡፡
 
ጠላቶቻችንን ማንኛውንም ዋጋ ከፍለን ልናሸንፋቸው ይገባናል፡፡ ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ ዋሾዎችን ተዋግተን ማሸነፋችንን መቀጠል አለብን፡፡ እንደዚያ ለማድረግ የእግዚአብሄርን መና የሚመገብና እስከ መጨረሻው ድረስ የጌታችንን ቃል የሚሰብክ የሕይወት ዓይነት ልንኖር ይገባናል፡፡ እግዚአብሄር ድል ለሚነሱት ክብሩንና ባርኮቶቹን ሊሰጣቸው ቃል ገብቷል፡፡ ለምዕመናን እጅግ ታላቅ ተስፋ የሆነው እግዚአብሄር በአየር ላይ የሚያነሳው እምነትና የሺህው ዓመት መንግሥትና የአዲሱ ሰማይና ምድር እርግጠኝነት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚፈቅዱት በእግዚአብሄር ቃል ላይ ባላቸው እምነት ውሸቶችን ሁሉ በማሸነፍ የእግዚአብሄርን የተሰወረ መና ለተቀበሉት ብቻ ነው፡፡
 
በእርግጥ ክቡር የሆነው ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ያንን ለማግኘት ያላቸውን ሁሉ ይሸጣሉ፡፡ ጠብቀው ሊያቆዩትም ታላላቅ መስዋዕትነቶችን ይከፍላሉ፡፡ እነዚህ መስዋዕትነቶች ለእኛ ደስታ እንጂ ስቃይ ስላልሆኑ ይህም በመጨረሻ ሁሉን ነገር የሚሰጠን በዋጋ የማይታመን ሐብት ስለሆነ እንጠብቀው ዘንድ ሁሉን ነገር ለእርሱ ስንል ብንተው ያኮራናል፡፡
 
የሺህ ዓመቱን መንግሥትና አዲሱን ሰማይና ምድር ተስፋ በማድረግ እንድትቀጥሉ በዚህ ተስፋም ባላንጣዎችን ሁሉ ድል እንድታደርጉና በመጨረሻም በታላቅ ደስታና ሐሴት አሸናፊዎች ሆናችሁ ብቅ እንድትሉ ምኞቴና ጸሎቴ ነው፡፡