Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[3-4] የእርሱን ልብ የሚያስደስቱ የእግዚአብሄር ባሮችና ቅዱሳን፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 3፡7-13 ››

የእርሱን ልብ የሚያስደስቱ የእግዚአብሄር ባሮችና ቅዱሳን፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 3፡7-13 ››
 
 
አሁንም በዚህ ዓለም ላይ የፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ዓይነት ቤተክርሰቲያኖች አሉ፡፡ 
 
እዚህ ላይ እግዚአብሄር በእስያ ከነበሩት ከሰባቱ ቤተክርስቲያኖች መካከል በጌታ እጅግ የተመሰገነችውና የተወደደችው ቤተክርሰቲያን የፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን እንደነበረች ይነግረናል፡፡
 
በዚህም ዘመን በእስያ ላሉት ቤተክርስቲያኖች የተናገረው አምላክ በእነርሱ እንዲሰራባቸውና እንዲደሰትባቸው የእርሱ ቤተክርስቲያኖች ልክ እንደ ፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ይሆኑ ዘንድ እንደሚፈልግ ማየት እንችላለን፡፡ በዚህም ዘመን ቢሆን ቢሆን በእግዚአብሄር የተመሰገኑ ቤተክርስቲያኖች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እየሰበኩ ነው፡፡
 
ዛሬም እንደ ያኔው ለእግዚአብሄር ታማኝ የሆኑ ቅዱሳን አቅማቸው ውስን ቢሆንም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚሰብኩ ቤተክርስቲያኖች አባል ናቸው፡፡ እግዚአብሄር በእነዚህ ሰራተኞች ይደሰታል፡፡ ማናቸውም እጆቻቸውን በመጫን አጋንንቶችን ማስወጣት ወይም ትንቢት መናገር አይችሉ ይሆናል፡፡ ማናቸውም የተለየ የመናገር ክህሎት የላቸው ይሆናል፡፡ የማሳመን ሐይልም አልተሰጣቸው ይሆናል፡፡ እነርሱ የሚያደርጉት ብቸኛው ነገር ኢየሱስ ብቻ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለአንዴና ለዘላለም እንዳስወገደና የሐጢያት ፍርዳችንንም በሙሉ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ወደ ክርስቶስ እንደተላለፉ ማመንና መስበክ ነው፡፡
 
እነዚህ ሰራተኞች ጌታን የሚከተሉ እርሱን የሚያመልኩና ፈቃዱን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባላቸው እምነት የሚታዘዙ ምዕመናን ናቸው፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚሰብኩበት እምነትና ግለት ነው፡፡ ይህንን ወንጌልን የማሰራጨት ሥራ መስራት የጌታን ልብ እንደሚያስደስት ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም ጌታ በእርግጥም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለማስወገድ በዮሐንስ ተጠምቋል፡፡ በመስቀል ላይ ተሰቅሎዋል፡፡ ዳግመኛም ከሙታን ተነስቷልና፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ጌታን ብቻ ያመሰግናሉ፡፡ እርሱንም ብቻ ይከተላሉ፡፡
 
እኛ የምንፈልገው ነገር ቢኖር ይህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለሁሉም ሰው እንዲዳረስና ሁሉም ሰው ከሐጢያቶቹ ሁሉ እንዲድን ነው፡፡ እግዚአብሄር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመላው ዓለም እንድንሰብክ በድንቅ ሁኔታ ፈቅዶልናል፡፡ ብዙ ፍሬዎች ይወለዱ ዘንድም እንዲህ ባርኮናል፡፡ በመጨረሻው ዘመን ሰማዕትነታችንን መቀበል የምንችልበትን እምነትንና የንጥቀታችንንና በሺህው ዓመት መንግሥት ውስጥም የሕይወትን በረከት ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሄር ለጌታ ሰማዕት እንድንሆንም ፈቅዶልናል፡፡ በፊተኛው ትንሳኤ ዕድል እንዲኖረንና የሰማይን ክብር እንድንለብስም ፈቅዶልናል፡፡
 
አሁን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመስበክ ራሳችንን ቀደሰን የሰጠን ሰዎች በእግዚአብሄር የተወደደችው ቤተክርስቲያን አባሎች ነን፡፡
 
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመላው ዓለም እንዴት መሰበክ እንደምንችል እናስብ፡፡ እግዚአብሄር ወንጌልን የመስበክን በር ቀድሞውኑም እንደከፈተ ለቤተክርስቲያኖቹ ተናግሮዋል፡፡ እግዚአብሄር የጀመረውን ማንም ሰው ሊያቆመው ስለማይችል እርሱ ሁሉን እንደሚፈጽም በሚገባ የተረጋገጠ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምነውን ሰዎች ይህንን የጥምቀቱን ወንጌል በመላው ዓለም እንድንሰብክ ፈቅዶልናል፡፡ ዛሬም ቢሆን የእርሱ ቤተክርስቲያኖች በዚህ ምድር ላይ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማሰራጨት ሥራቸው ተባርከዋል፡፡ የግል ችሎታቸውን ሲመለከቱ በጉድለቶች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል ፍቅር ስላላቸው እግዚአብሄር ጽኑዓን አድርጎ በመቁጠር አብሮዋቸው ይሰራል፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ እነዚህን የመሰሉ ቤተክርስቲያኖች ያሉ መሆናቸው ለዓለም ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ እግዚአብሄር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማሰራጨቱን ሥራ ለእነርሱ በአደራ ሰጥቶዋቸዋል፡፡ እነርሱ የሚያደርጉትንም ሌላ ማንም ሰው ሊያቆመው እንደማይችልም አረጋግጦዋል፡፡ እነርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በዓለም ላይ በየቦታው ይሰብካሉ፡፡ ይህ ወንጌልም በመላው ዓለም ይሰራጫል፡፡ እግዚአብሄር ያበረታቸዋል፡፡ ይጠብቃቸዋል፤ አብሮዋቸውም ይሰራል፡፡ እግዚአብሄር ራሳቸውን ከዚህ ሥራ ጋር በማቆራኘት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በዓለም ላይ ላሉ አገሮች በሥጋዊውም በመንፈሳዊም የሚያሰራጩ ሰዎችን ሲባርካቸው እናያለን፡፡
 
እኛ በጽሁፍና በኤሌክትሮኒክ መጽሐፎቻችን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በዚህ ዓለም በእያንዳንዱ ማዕዘን እየሰበክን ነው፡፡ ይህንን እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ እናደርገዋለን፡፡ ጌታም የክርስቶስ መንግሥት በዚህች ምድር ላይ እስክትመጣ ድረስ በእኛ መስራቱን ይቀጥላል፡፡ እግዚአብሄር በጽሁፋችን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል 6.5 ቢሊዮን ለሚሆነው የዓለም ሕዝብ እንድንሰብክ ያስችለናል፡፡ እግዚአብሄር ሁላችንንም ይባርክ!
 
እኛ እግዚአብሄር የሚደሰትበትን ሥራ ለመስራት ሁልጊዜም ለመንፈሳዊ ጦርነት የተዘጋጀን መሆን አለብን፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ባሮቹን እንዲያጠነክርና እንዲባርክ እለምነዋለሁ፡፡ እንደ ጌታችን ያለ ታማኝ የለም፡፡ እኛ የምናምንበት እውነተኛው ወንጌል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እንደሰጠን ያለ ግልጽና ፍጹም የሆነ ደህንነት ሊሰጠን የሚችል ሌላ እውነት በዚህ ዓለም ላይ እንደሌለ አምናለሁ፡፡
 
 
የራዕይ መጽሐፍ ድል ለሚነሱ የተሰጠ የተባረከ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር ‹‹ድል ለነሳው ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ›› ብሎ ነግሮናል፡፡ ይህ እውነት እግዚአብሄር እነዚህ ሰዎች በሺህው ዓመት መንግሥቱ ውስጥ እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ‹‹ድል የነሳው›› የሚለው የሚያመለክተው በመጨረሻው ዘመን ጸረ ክርስቶስን በእውነት በኩል በመዋጋት እምነታቸውን የሚጠብቁትንና ዛሬም በእውነት ቃል ላይ ባላቸው እምነት የሐሰተኛ ወንጌል ተከታዮችን ተዋግተው ድል የሚነሱትን ሰዎች ነው፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመላው ዓለም በመስበክ ክፉን በበጎ ማሸነፍ አለብን፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ቃል ላይ ባለን እምነታችን ከዋሾዎችና ከሐሰተኛ ትምህርቶች ጋር ታግለን ድል መንሳት አለብን፡፡
 
ዋሾዎችን ታግለን ለማሸነፍ ሁልጊዜም የውሃውንና የመንፈሱን ቃል ማሰላሰል አለብን፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አሁን አምነን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ነጽተን ከሆነ ከዋሾዎች ጋር የምናደርገው ትግላችን ከዚህች ቅጽበት አንስቶ ጀምሮዋል፡፡ በእውነተኛው ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሐሰተኛ ወንጌል ከያዙት ጋር ተዋግተው ድል ያደርጉዋቸዋል፡፡
 
እኛ ሁልጊዜም እንዲህ ላሉት የሐሰተኛ ወንጌል ተከታዮች መስበክ አለብን፡፡ ለምን? ምክንያቱም የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ሐይል ሐሰተኛ እምነታቸውን አስወግዶ አዲስ ሕይወትን ያመጣላቸዋልና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ክፉን በበጎ እንድናሸንፍ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ እነዚህን ነፍሳቶች ከሐጢያቶቻቸው የሚያድናቸውን መልካሙን የመንፈሳዊነት ተጋድሎዋችንን ከቶውኑም መተው የለብንም፡፡
 
የነፍሳቶች መዳን በረከት የሚገኘው በመንፈሳዊ ተጋድሎዋችን ውሰጥ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነታችን ሁልጊዜም ዋሾዎችን በመዋጋትና በማሸነፍ የዘላለም ሕይወትን ፍሬዎች በሙሉ ለእግዚአብሄር መስጠት እንችላለን፡፡
 
 
ጌታ ከበለሲቱ ዛፍ ምሳሌ እንድንማር ነግሮናል፡፡ 
 
የበለሲቱ ዛፍ የምታመላክተው የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ እያንዳንዱ አገር ብሄራዊ አበባ ወይም ዛፍ እንዳለው ሁሉ እስራኤልን የምታመላክተውም የበለስ ዛፍ ነች፡፡ እስራኤል ችምችም ያሉ ቅጠሎች ሲበዙባት የዓለም መጨረሻ በጣም እንደሚቀርብ መረዳት አለባችሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእስራኤል መንግሥት በዚህ ምድር ላይ እንደገና ሲገነባና ሐያል መንግሥት ሲሆን ጌታ እንደሚመጣ ይነግረናል፡፡
 
በዚህ ዘመን ጋዜጦች በእስራኤሎችና በፍልስጤማውያን መካከል ያለውን ግጭት በሚዘግቡ ታሪኮች የተሞሉ ናቸው፡፡ እስራኤል በአሁኑ ጊዜ ታሪካዊ ክልልዋን ይዛ ታላቅ ሐይል ሆናለች፡፡ እስራኤል ወደፊት ትነሳ ወይም ትውደቅ ሁሉም በእግዚአብሄር ቃል መሰረት ይፈጸማል፡፡ እስራኤል ከምድረ ገጽ ስትጠፋ የጌታ ዳግመኛ ምጽዓት በዚህ ምድር ላይ የሚፈጸመው ያን ጊዜ መሆኑን መረዳት አለባችሁ፡፡ ጌታ የበለስ ዛፍ በምታቆጠቁጥበት ጊዜ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር የዚህን ዓለም ፍጻሜ በእስራኤል መመለስና መከናወን ይተነብያል፡፡ የዓለምን ተፈጥሮአዊ ሥነ ምህዳር የሚያወድሙ ጥፋቶችም እንደዚሁ የዘመኑን መጨረሻ ይተነብያሉ፡፡
 
እያንዳንዱ ሰው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እምነት እንዲይዝና እንዲጠብቅ እግዚአብሄር ተናግሮዋል፡፡ የእግዚአብሄር ዓላማዎች ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እምነት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ድነዋል፡፡ ጌታ እንዲህ ነግሮናል፡- ‹‹እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁልጊዜ ትጉ፡፡›› ሉቃስ 21፡36) በራሳችን ጉልበት ሊመጣ ካለው መከራ ማምለጥ አንችልም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ቃል በማመን ልናሸንፈው እንችላለን፡፡ አሁን ራሳችንን የምናገኘው እየቀረበን ላለው የመከራ ዘመን ለሰማዕትነት የሚያገለግለንን እምነታችንን በማዘጋጀት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡
 
ክርስቲያኖች የዘመኑ መጨረሻ ሲመጣ በታላቁ መከራ ውስጥ እንደማያልፉ የሚያስቡ ከሆነ እምነታቸው በአያሌው ተሳስቷል፡፡ በቅድመ መከራ ንጥቀት ትምህርት ማመን የለብንም፡፡ ይህ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የራቀ ነው፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በተለይም የራዕይ መጽሐፍ የሰባቱ ዓመት መከራ የመጀመሪያው ሦስት ዓመት ተኩል ካለፈ በኋላ የቅዱሳን ሰማዕትነት እንደሚመጣ ይነግረናልና፡፡ ቅዱሳኖች በሰባቱ ዓመት የመከራ ዘመን ውስጥ እንደማያልፉ ማሰባቸው በጣም አደገኛና ስሁት ወደሆነ እምነት ይመራቸዋል፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች በታላቁ መከራ አጋማሽ ውስጥ እንደሚያልፉ መረዳት አለባችሁ፡፡
 
ጠቅለል ያለውን የእግዚአብሄር ቃል ስናጤን ጻድቃን በዚህ ዓለም ላይ የሚቆዩት እስከ መቼ ነው? እነርሱ በምድር ላይ የሚቆዩት ሰይጣን ሐጢያተኞችን ምልክቱን እንዲቀበሉ እስከሚጠይቅበትና ቅዱሳንም በጸረ ክርስቶስ ሰራዊት ሰማዕት እስከሚሆኑበት ጊዜ ድረስ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃልና በትክክለኛው እምነት የተገለጠው እውነት ይህ ነው፡፡
 
 

በመጨረሻው ዘመን የሚመጣው ታላቁ መንፈሳዊ ተጋደሎ፡፡ 

 
የጻድቃን እምነት ውጤት እግዚአብሄር በፈቀደው በታላቁ መከራ ውስጥ በግልጽ ተብራርቷል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እምነት ሳይኖራችሁ በመጨረሻው ዘመን ከሰይጣን ጋር በምታደርጉት ተጋድሎ እውነተኛ ድል ልትቀደጁ አትችሉም፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜም የመጨረሻው ድል የጻድቃን እንደሚሆን መረዳት አለባችሁ፡፡ የዓለም መጨረሻ ሲቃረብ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባላቸው እምነታቸው እውነተኛ አሸናፊዎች ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ከመምጣቱ በፊት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመላው ዓለም የመስበኩን ሥራ ማጠናቀቅ አለብን፡፡
 
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ጌታችንን ማስደሰት አለብን፡፡ የመጨረሻውን ድል የሚሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የእምነት ቃል አብሮን አለ፡፡ እግዚአብሄር የዓለምን መጨረሻ በግልጽ እየተነበየ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ጌታ እንደሚመጣና እስከዚያ ድረስ በዚህ ዓለም ላይ በሚቆዩት ላይ ታላላቅ ወዮታዎችን እንደሚያመጣባቸው መገንዘብ አለብን፡፡ ስለዚህ እውነተኛ እምነትን ታጥቀን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የዘመኑን መጨረሻ መቀበል አለብን፡፡ በኖህ ዘመን የዓለም መጨረሻ የመጣው ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ መሆኑን እንደተናገረ ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለሚያምኑት ሰዎችም የሺህ ዓመቱን መንግሥት በእምነት እንዲጠብቁ ነግሮዋቸዋል፡፡
 
ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምኑ የዘመን መጨረሻውን ዓለም ችግሮች መፍታት አይችሉም፡፡ በሚቻለው ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለብን፡፡ በዚህ የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማያምኑትን ሰዎች እግዚአብሄር ከቶውኑም አይታገሳቸውም፡፡ እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን የመጨረሻ ደረጃ ላይ በዚህ ዓለም ላይ እጅግ አስፈሪ መቅሰፍቶችን ያወርዳል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ሰዎች ከእግዚአብሄር የጽድቅ ፍርድ ማምለጥ ስለማይችሉ አሁኑኑ በዚህ ወንጌል ማመን አለባቸው፡፡
 
ስለዚህ ከእግዚአብሄር ፍርድ ለማምለጥ እያንዳንዱ ሰው ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ማወቅና በልቡ ማመን ያለበት መሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ከዚህ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል በቀር ሌላ እውነተኛ ወንጌል የለም፡፡ ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ ይህ ዓለም አሁን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በጣም ያስፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም በሐጢያት ልማድ ውስጥ ሰጥሞ እየኖረ ነውና፡፡
 
በዚህ በመጨረሻው ዘመን ለወደፊቱ የሚሆን ምንም ዓይነት ዋስትና ስለሌለ ሰዎች በየቀኑ ሐጢያቶችን በመስራትና ደስታቸውን በመከተል ብቻ ይኖራሉ፡፡ ለሰው ዘር እውነተኛው ተስፋ የሚገኘው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃል ውስጥ ነው፡፡ እውነተኛ ተስፋችንን የሚሰጠንም ይህ ቃል ብቻ ነው፡፡ ይህ ዓለም ግን እግዚአብሄርን የማይፈልግ ዓለም እየሆነ ነው፡፡ ሐጢያተኞች ሆናችሁ በቅርቡ ስለ ሐጢያቶቻችሁ በእግዚአብሄር የሚፈረድባችሁ ከሆናችሁ ኢየሱስ የሰጠውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከሙሉ ልባችሁ ማመን አለባችሁ፡፡ ያን ጊዜ ከሚያስፈራው የእግዚአብሄር ፍርድ መዳን ትችላላችሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉንም ሰው ከሐጢያቶቻቸው ንስሐ እንዲገቡ፣ ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዲቀበሉ ይመክራል፡፡
 
የዓለም መጨረሻ ሰዎች በልተውና በሐጢያት ውስጥ ተኝተው ሳያውቁት ወደ እሳትና ዲን ባህር የሚገቡበት ጊዜ ነው፡፡
 
ሰዎች እግዚአብሄር የሰጣቸውን የሐጢያት ደህንነት መቀበል አለባቸው፡፡ ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳያውቁ እንዴት ከሐጢያቶቻቸው ይድናሉ? ሰው ሁሉ በሐጢያቶቹ ምክንያት የሚያስፈራውን የእግዚአብሄር ፍርድ እንደሚቀበል ማወቅና የውሃውና የመንፈሱ ወንጌልም የቤዛነት እውነትና የበረከት ቃል መሆኑን መገንዘብ አለበት፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ የዓለም ፍጻሜ በየትኛው ትክክለኛ ቀንና ሰዓት እንደሚሆን አይነግረንም፡፡ የዓለምን መጨረሻ ሰዓት መደበቅ የእግዚአብሄር ጥበብ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይህንን የመጨረሻውን ሰዓት ገልጦ ቢሆን ኖሮ ታላቅ ጥፋት ይከሰት ነበር፡፡ እግዚአብሄር የፍርድን ቀን ከሰዎች የደበቀው ለዚህ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የወሰነው ጊዜ ሲመጣ ሁሉም ነገር በእርሱ ይፈጸማል፡፡ ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆነ ዓለምም ይጀምራል፡፡
 
እግዚአብሄር በዋናው ምንባብ ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹የትዕግስቴን ቃል ስለጠበቅህ እኔም ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ ከሚመጣው የፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ፡፡›› ይህ ቃል እግዚአብሄር ቅዱሳኖችን ከሰማዕትነታቸው በኋላ በዚህ ዓለም ላይ ከሚወርዱት ከሰባቱ መቅሰፍቶች እንደሚያድናቸው ተስፋ የሰጠበት ቃል ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ቅዱሳኖች በመጨረሻው ዘመን በጸረ ክርስቶስ ሰማዕት ከመሆን ወይም ከመሰደድ ነጻ ይወጣሉ ማለት አይደለም፡፡ ብዛት ያላቸው ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባለማመናቸውና የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ባለመቀበላቸው አስፈሪው የእግዚአብሄር ፍርድ ይገጥማቸዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ሐጢያተኛ ነፍሳቸው ወደ ሲዖል ይወርዳል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር አስቀድሞ ቅዱሳን ሰማዕት እንዲሆኑ ይፈቅዳል፡፡ ምክንያቱም አስፈሪ ከሆኑት መቅሰፍቶች የሚያድናቸው ይህ ሰማዕትነት ነውና፡፡
 
 

በመጨረሻው ዘመን መከራ ውስጥ ሰዎች የሚቀበሉት ምልክት ምን ዓይነት ነው? 

 
መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የጸረ ክርስቶስን ስም የያዘ ምልክት እንደሚቀበሉ ይናገራል፡፡ የራዕይ ቃልም እንደዚሁ የጸረ ክርስቶስን ምልክት በግምባራቸው ወይም በቀኝ እጃቸው የሚቀበሉ ሰዎች ወደ እሳትና ዲን ባህር እንደሚጣሉ ይነግረናል፡፡ እነርሱ ይህንን የጸረ ክርስቶስን ስም ምልክት በመቀበል ለዘላለም የሰይጣን አገልጋዮች ይሆናሉ፡፡ የእሳቱና የዲኑ ባሀር ሐጢያት ላለባቸው ሰዎች የተዘጋጀ ነው፡፡
 
ሰዎች በእምነት አማካይነት ከሐጢያቶቻቸው መዳን የሚችሉበት የጸጋው ዘመን አሁን እያለፈ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰማዕታት በመጨረሻው ዘመን እንደሚነሱ ይናገራል፡፡ የእነዚህ ሰማዕታት ስሞች በሕይወት መጽሐፍ ላይ ስለተጻፈ እነርሱ የጸረ ክርስቶስ ስም ያለበትን ምልክት ወዲያውኑ ይጥሉታል፡፡
 
እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሁሉም በዚህ ሰዓት ሰማዕት እንደሚሆኑ ይነግረናል፡፡ ጻድቃን የሆኑ ሰዎች በዘመን መጨረሻ የሚገጥማቸውን ሰማዕትነት መፍራት የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ሰማዕት ከሆኑ በኋላ ለሚጠብቃቸው የሺህ ዓመት መንግሥት እግዚአብሄርን ማመስገን አለባቸው፡፡
 
የጸረ ክርስቶስን የስም ምልክት መቀበል ጌታችንን የመካድ የክህደት ድርጊት ስለሆነ ልንተወው ይገባናል፡፡ ሁላችንም ሰማዕት ለመሆን መነሳት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም በዚህ ጊዜ በእግዚአብሄር ላይ ያለንን እምነታችንን መጠበቅ ለእግዚአብሄር ክብርን መስጠት ነውና፡፡ ጌታችን ለቅዱሳን ችግሮችን ሁሉ የሚያሸንፉበትን ጉልበት እንደሚሰጣቸው ነግሮናል፡፡
 
 
የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መስበክ የሚገባት እንዴትና እስከ መቼ ነው? 
 
ጌታችን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንድናሰራጭ የፈቀደልን እሰከ መቼ ነው? መልሱ በታላቁ መከራ ውስጥ ሰማዕት እስከምንሆንበት ጊዜ ድረስ ነው የሚል ነው፡፡ እግዚአብሄር ጻድቃን እስከዚያ ድረስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይሰብኩ ዘንድ ወንጌልን የመስበኩን በር ወለል አድርጎ ከፍቷል፡፡ ጻድቃን ይህ የሰማዕትነታቸው ዘመን እስኪመጣ ድረስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መስበክ ይቀጥላሉ፡፡ ይህንን ተከትሎም አስፈሪዎቹ መቅሰፍቶች በዚህ ምድር ላይ ይወርዳሉ፡፡
 
በአሁኑ ጊዜ ጻድቃንና ሐጢያተኞች ጌታ በሰጣቸው ውብ ተፈጥሮ ተከበው ይኖራሉ፡፡ የመከራው ዘመን እስኪመጣ ደረስ ጻድቃን እምነታቸውን ንጹህ አድርገው መጠበቅና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከሰበኩ በኋላም ጌታን መጠባበቅ ይገባቸዋል፡፡ ጻድቃን የወንጌልን እርሻ መንከባከብ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የአውሬውን ምልክት እንድንቀበል በምንገደድበት በመጨረሻው ዘመን ጌታችን በሰጠን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባለን እምነት ዓለማዊ ሰዎችን ተዋግተን ማሸነፍ አለብን፡፡ በዘመኑ መጨረሻ በጸረ ክርስቶስ ሰማዕት በምንሆንበት ጊዜ እምነታችን ያሸንፋል፡፡ የጻድቃን ሕይወት በጌታ ይታመናል፡፡ ከፈተናው ሰዓት የሚጠብቃቸው ስለመሆኑ የሚናገረውን የጌታን ቃል አምነው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ወንጌልን ቢሰብኩ እግዚአብሄር የድል ሕይወትን ይሰጣቸዋል፡፡ ጻድቃን እውነተኛ ደህንነት የሚሰጠውን ወንጌል ዛሬም ነገም በየስፍራው መስበክ አለባቸው፡፡
 
ሁላችንም የጌታችንን መምጣት መጠበቅና የሺህው ዓመት መንግሥት ሲመጣልን የሚጠብቀንን ሽልማት ለማግኘት ለእርሱ ታማኝ መሆን አለብን፡፡ ጌታ ወደዚህ ምድር ሲመጣ የሺህው ዓመት መንግሥት ለጻድቃን ይሰጣል፡፡ ያን ጊዜ ጻድቃን ከጌታ ጋር አብረው የእግዚአብሄርን ክብር ይለብሳሉ፡፡
 
አሁን ግን ይህንን ማድረግ የማንችልበት የመጨረሻው ቅጽበት እስኪመጣ ድረስ በዚህ ምድር ላይ ሳለን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስበክ መቀጠል አለብን፡፡ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው የሚያድነው ወንጌል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነተኛ የሐጢያት ደህንነት የሚገኝበት ወንጌል ነው፡፡
 
ጻድቃን በዚህ ምድር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እየሰበኩ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ከኖሩ በኋላ ከጌታ ጋር ይገናኛሉ፡፡ ለሺህ ዓመትም ይነግሳሉ፡፡ የሺህ ዓመት መንግሥት ሲያበቃም ወደ ዘላለማዊው የእግዚአብሄር መንግሥት ገብተው ለዘላለም ከጌታ ጋር ይኖራሉ፡፡ እኔ ጌታን በእምነት አመሰግነዋለሁ፡፡ ይህንን ተስፋ ስለሰጠን ጌታን ከዚህም በላይ አብዝተን ልናመሰግነው ይገባናል፡፡
 
የፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ሐይልዋ ጥቂት ቢሆንም የጌታን ስም ያልካደችና የጌታን ፈቃድ የተከተለች ጌታ በተለየ መንገድ የወደዳት ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡
 
እግዚአብሄር ለዚህች ለፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን ከፈተናው ሰዓት የመትረፍን ልዩ በረከቱን ሰጥቶዋታል፡፡ ይህ በረከት የሐጢያት ስርየት፣ በሺህው ዓመት የመኖርና የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ መንግሥት የመውረስ በረከት ነው፡፡ አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች ሆነው የቀሩ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሄር በረከቶች ይገለላሉ፡፡ ጻድቃን ግን ለሺህ ዓመት ይነግሳሉ፡፡
 
ጌታ በሰማዕትነታቸው አማካይነት ጻድቃንን ከዚህ ምድር ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚያም እጅግ ታላላቅ የሆኑትን መቅሰፍቶች በዚህ ዓለም ላይ ያወርዳል፡፡ እግዚአብሄር በጎውን ከክፉው ለመለየትና ሐጢያተኞችን ለመኮነንና ለማጥፋት ይህንን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር ጻድቃንን በተለይም ሐይላቸው ጥቂት ቢሆንም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ቃሉን የሚጠብቁትንና ወንጌልን የሚሰብኩትን ይወድዳቸዋል፡፡ እንዲህ ያለ እምነት ያላቸውና እንዲህ ባሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የሚገኙ ቅዱሳን በእርግጥም ብሩካን ናቸው፡፡ እግዚአብሄር በእነዚህ ጻድቃን ቅዱሳኖች ተደስቷል፡፡
 
እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከሙሉ ልባቸው አምነው ከሰይጣን ጋር በመዋጋት ድል ለሚያደርጉት ሰዎች ሽልማት እንደሚሰጣቸው ተናግሮዋል፡፡
 
በዚህ ምድር ላይ በኢየሱስ እናምናለን እያሉ በሰይጣን የተታለሉ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ በኢየሱስ ወደዚህ ምድር መምጣት ሐጢያተኞችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው የሚያድነው የደህንነት ሥራ እርሱ በሰራቸው ሁለት የጽድቅ ሥራዎቹ ተከናውኖዋል፡፡ በእነዚህ ሥራዎች የሚያምነው እምነት እርሱ በዮርዳኖስ ወንዝ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ እንደወሰደ፣ እነዚህን የዓለም ሐጢያቶችም በመስቀል ላይ በመሸከም ይህንን የደህንነት ሥራ እንደፈጸመና ለእነዚህ ሐጢያቶችም በራሱ ደም እንደተኮነነ ያምናል፡፡ ሐጢያተኞችን ያዳነው የደህንነት ወንጌል፤ የሐጢያት ስርየት ወንጌል ይህ ነው፡፡
 
ነገር ግን እምነት የሚጎድላቸው ሰዎች ‹‹በኢየሱስ ጥምቀት ሳያምኑ ሐጢያት አልባ ነን›› የሚሉ ሰዎች ይሆናሉ፡፡ እንዲህ ያለው እምነት ውሸት ነው፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ሰዎች እነርሱ ጌታን የሚወዱትን ያህል ማንም ጌታን እንደማይወድ ይናገራሉ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ግን ራሳቸውን ሐጢያተኞች አድርገው ይገልጣሉ፡፡ ነገር ግን ጌታችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከሚያምኑት ውጪ ሌላ ማንንም ሰው ሰማይ ይገባ ዘንድ ከቶውኑ አይፈቅድም፡፡ በጌታ የሕይወት መጽሐፍ ላይ የሚጻፉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ብቻ ናቸው፡፡
 
እግዚአብሄር የሰጠው የሐጢያት ደህንነት ‹‹ሰው በሚያደርገው›› የሚገኝ ሳይሆን ‹‹ሰው በሚያምነው›› የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ እምነት የመጀመሪያው ምልከታ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅና አዳኛችን መሆኑን ማመን ሲሆን ሁለተኛው የኢየሱስን ጥምቀትና የመስቀል ላይ ደሙን የደህንነታችን ምሉዕና ወሳኝ ድርጊቶች አድርገን ማመን ነው፡፡ በክርስቶስ ትንሳኤና በዳግመኛ ምጽዓቱም ደግሞ ማመን አለብን፡፡
 
ማቴዎስ 7፡21-23 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡ በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡ የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡›› ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች የሚክዳቸው ለምንድነው? ምክንያቱም ሐጢያት ያለባቸው ሰዎች በጌታ የሕይወት መጽሐፍ ላይ አይጻፉምና፡፡ በዚህ ዘመን ኢየሱስ አዳኛችን መሆኑን እናምናለን የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አያምኑም፡፡
 
ስለዚህ ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ አልተጻፉም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሐጢያተኞች ሐጢያቶቻቸውን ሁሉ ተሸክመው ወደ ጌታ መንግሥት ለመገባት ይሞክራሉ፡፡ ሆኖም ሊገቡ አይችሉም፡፡ አንዳንድ ሰዎች በጣም ደፋሮች ስለሆኑ ሐጢያት ቢኖርባቸውም ሰማይ መግባት እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሄር ባቀረበው ደህንነት አያምኑም፡፡ ነገር ግን በራሳቸው ትምክህት በፈጠሩት የደህንነት ዓይነት ያምናሉ፡፡ የተሳሳተ እምነት ያላቸው ሰዎች ኢየሱስ እግዚአብሄር መሆኑንም ሆነ ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በራሱ ላይ የወሰደና እነዚህንም ሐጢያቶች በመስቀል ላይ የተሸከመ የመሆኑን እውነታ አያምኑም፡፡ እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን የሚመለከቱትና የሚያምኑት ከአራቱ የዓለም ታላላቅ ጠቢባን እንደ አንዱ አድርገው ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ቢያምኑም ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ ጌታ ግን ለእነዚህ ሰዎች የሚሰጠው አንዳች ነገር አለው፡፡ ‹‹ግን ምንድነው?›› ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል፡፡ የሚጠብቃቸው ሌላ ሳይሆን ሲዖል ነው!
 
ሐጢያቶቻችን ይቅር የተባሉልን እኛ ጻድቃኖች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነታችን ዋሾዎችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ተዋግተን ልናሸንፍ ይገባናል፡፡ ጻድቃን የሚያምኑት የተበላሸ እውነትን አይደለም፡፡ እኛ ጌታ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ ማንም ያለውን ቢልም በጌታችን ያመንበትን የእውነተኛውን ወንጌል እምነታችንን ከቶውኑም አንተወውም፡፡ ጻድቃን የሚያምኑት እውነተኛው ቃል በግል ከእግዚአብሄር የተሰጠ ነው፡፡ የሐጢያቶቻችንን ስርየት ተስፋ የሰጠው ራሱ እግዚአብሄር ነው፡፡ ጻድቃን በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ በማመን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ድነዋል፡፡ ሐጢያተኞች ስለ እኛ በሚናገሩት ነገር ውስጥ አንዳች የሚጠቅም ወይም ዋጋ ያለው ነገር አለን? በፍጹም የለም! ጻድቃን በእግዚአብሄር ቃል በማመን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያላቸውን እምነት መጠበቅ አለባቸው፡፡
 
አሁን የተፈጥሮ ጥፋቶች ዘመን ነው፡፡ ብዙ ባልራቀው ወደፊት በዚህ ምድር ላይ የኒውክሌር ጦርነት ይከሰታል፡፡ የተፈጥሮ ጥፋቶችም እጅግ በላቀ አውዳሚ መጠን ይከሰታሉ፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋዮች በዚህ ዓለም ላይ እየመጣ ያለውን ነገር በግልጽ አይተው መስበክ አለባቸው፡፡ የዓለም ፍጻሜ በድንገት ሊመጣ እንደሚችል መረዳት አለባችሁ፡፡ በዓለም ላይ የኒውክሌር ጦርነት ሲፈነዳ፣ የተፈጥሮ ጥፋቶችም ከልክ በላይ ሲያልፉና የአውሬው ምልክትም በእኛ ላይ ሲበረታ ማለትም የሰማዕትነታችን፣ የትንሳኤያችንና የሺህው ዓመት መንግሥት ምስረታ ሲመጣ ይህ ክርስቶስ ወደ ምድር የሚመጣበት ጊዜ ይሆናል፡፡ ሁሉም ነገር በጌታ ይሆናል፤ ይጠናቀቅማል፡፡
 
ማንም ምን ይበል እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በእግዚአብሄር ቃል ማመንና ይህንን እምነት መጠበቅ አለብን፡፡ መከራዎቹ ምንም ይሁኑ ጌታን ስንከተል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያለንን እምነታችንን በትክክል መጠበቅና ማሰራጨት አለብን፡፡
 
የጌታን ቀን ተስፋ በማድረግ ሕይወታችንን እንኑር፡፡ ሐጢያተኞች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሐጢያት ይቅርታቸውን እንዲያገኙ እናዘጋጃቸው! ጌታችን አስቀድሞ ለጻድቃን የተጠበቁትን የሰማይ በረከቶች ሁሉ አዘጋጅቶ እየጠበቀን ለመሆኑ አምናለሁ፡፡ የሙታን ትንሳኤና የቅዱሳን መለወጥ ከመድረሱ በፊት ለዚያ ቀን መዘጋጀት አለብን፡፡ ሕይወታችሁ ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ማጉረምረማችሁን አቁማችሁ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እመኑ፡፡
 
አስቀድማችሁ የእውነትን ወንጌል አውቃችሁ ሳለ በዚህ ወንጌል ለማመን እምቢተኞች ሆናችሁ መጨረሻችሁ ሲዖል ይሆን ዘንድ እንዴት ትመርጣላችሁ? በሕይወት ባዶነት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመውደቅ ፋንታ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባለን እምነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ በመዳን ለሺህው ዓመት መንግሥት መዘጋጀት አለብን፡፡ ልክ እንደ ፊላደልፊያ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሄር በተመሰገነው የእምነት ዓይነት ከኖርን በኋላ ጌታን በአየር ላይ እንደምንገናኘው የተረጋገጠ ነው! ሐሌሉያ!