Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[3-6] ለደቀ መዝሙርነት የሚሆን እውነተኛ እምነት፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 3፡14-22 ››

ለደቀ መዝሙርነት የሚሆን እውነተኛ እምነት፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 3፡14-22 ››
 
የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን እምነት በጌታ ሊተፋ የሚገባው እምነት ነበር፡፡ ስለዚህ በእምነታቸው ባለጠጎች ይሆኑ ዘንድ በእሳት የነጠረውን ወርቅ ከእርሱ እንዲገዙ መከራቸው፡፡ ይህ ለብ ያለ እምነት በዚህ ዘመን ባሉ ጻድቃን መካከልም ሊታይ ይችላል፡፡ እነርሱ እምነታቸውን የተቀበሉት በነጻ ስለሆነ እምነታቸው ምን ያህል ክቡር እንደሆነ አይረዱም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በእሳት እንደነጠረ ወርቅ ያለውን እምነት ሊሰጣቸው የግሳጼና የምክር ቃልን ለጻድቃን ተናገረ፡፡ ጌታ በእስያ ያሉት ሰባቱም ቤተክርስቲያኖች በሙሉ ተመሳሳይ የሆነ አንድ እምነት ይኖራቸው ዘንድ እንደፈለገ ከምንባቡ መረዳት እንችላለን፡፡ ጌታ ጆሮ ያላቸው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርስቲያናቱ የሚለውን እንዲሰሙ አዞዋል፡፡
 
የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ቁሳዊ ሐብታቸው ከእግዚአብሄር መንፈሳዊ በረከቶች ጋር ተመሳሳይ እንደሆነና ለእምነታቸውም የሚከፈል መሆኑን በማሰብ ራሳቸውን በማታለል ውስጥ ጠልቀው ተዘፍቀው እንደነበር ከ3፡17 እናያለን፡፡ እግዚአብሄር ለዚህ የተታለለ ጉባኤ መንፈሳዊ ድህነቱንና ጉስቁልናውን በሐይለ ቃል ጠቆመው፡፡
 
የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን በእምነት የበለጠገች መስላ ታይታ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እምነት አልባና ደሃ ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡ እምነቷ ለብ ያለ ነበር፡፡ በመንፈሳዊ ዕብሪትም የተሞላች ነበረች፡፡ ኢየሱስን ከመውደድ ይልቅም ዓለምን ትወድ ነበር፡፡
 
ዮሐንስ ራዕይ 3፡14-22 ስለ ደቀመዝሙር ሕይወት ይናገራል፡፡ የኢየሱስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት የክርስቶስን ቃል የሚታዘዙና የሚከተሉ ሰዎች ናቸው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ሁሉ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ለመሆን የበቁ ናቸው፡፡ እግዚአብሄር የደቀመዝሙርን ሕይወት እንድንኖር ከሁላችንም ይፈልጋል፡፡ ይህ የደቀ መዝሙር ሕይወት በተጨባጭ ለእኛ እንደተሰጠን መገንዘብ አለብን፡፡
 
በምንባቡ ውስጥ ጌታ የደቀ መዝሙርን ሕይወት የማይኖሩ ቅዱሳኖችን እንደሚተፋቸው ተናግሮዋል፡፡ በቁጥር 15-16 ላይ እንዲህ ተመዝግቦዋል፡- ‹‹በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ፤ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር፤ እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድ ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው፡፡›› የዳኑ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት በራድ ወይም ትኩስ ካልሆኑ ይህ ሊያመላክት የሚችለው መንፈሳዊ ድህነታቸውን ብቻ ነው፡፡ እንደዚሁም እነዚህ ሰዎች ገና የደቀ መዝሙርን ሕይወት አያውቁም፡፡ ነገር ግን ዳግመኛ የተወለደ ሰው ሁሉ የደቀ መዝሙርን ሕይወት መኖር አለበት፡፡ እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻችን ተዋጅተናል፡፡ የእኛ ደህንነት ይህ ነው፡፡
 
ከደህንነታችንና ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ ምን ተሰጥቶናል? ጌታን መምሰል የሚጥር፣ የእርሱን ትዕዛዞች የሚከተልና የሚታዘዝ ቃሉን የሚሻ ሕይወት ተሰጥቶናል፡፡ የደቀ መዝሙር ሕይወት ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይህንን ደቀ መዝሙርነት ከቅዱሳኑ በመጠየቅ የሎዶቅያን ቤተክርስቲያን ‹‹በራድ ወይም ትኩስ›› እንዳልሆነች በመናገር ገሰጻት፡፡
 
በራድም ሆነ ትኩስ ያልሆነ እምነት ለብ ያለ እምነት ነው፡፡ በራድም ሆነ ትኩስ ሳይሆን ለሰው ብዙ ምቾት የሚሰጥ ይህ ለብ ያለ እምነት ምን ዓይነት እምነት ነው? በሁለቱም መንገዶች ለመኖር የሚሞክር እምነት ነው፡፡ ለብ ያለ እምነት ያላቸው ሰዎች የዳኑ ቢሆኑም የኢየሱስን ፈቃድ የማይከተሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ኢየሱስን ፈቃድ የማይከተሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ኢየሱስን የሚከተሉ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን አይከተሉትም፡፡ በሌላ አነጋገር በአጥሩ ላይ በሁለቱም ወገን የተንጠለጠሉ ሰዎች ያላቸው እምነት ለብ ያለ እምነት ተብሎ ይተራል፡፡
 
ዓለም እንዲህ ያለውን እምነት ጠቢብ እምነት ብሎ ይጠራዋል፡፡ ይህ እምነት በዓለማዊ አገባብ ጠቢብ ሊሆን ይችላል፡፡ ጌታ የሚተፋው ግን የዚህ ዓይነቱን እምነት ነው፡፡ ይህ በራድ ወይም ትኩስ ያልሆነ እምነት ምን ዓይነት እምነት እንደሆነ ጥሩ የሆነ መረዳት ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ እምነታቸው ለብ ያለ ሰዎች የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያኖች ከሚሰሩት ሥራዎች ጋር አይተባበሩም፤ አይነጠሉምም፤ ያደርጋሉም፤ አያደርጉምም፡፡ የእምነት ሕይወታቸው እንደዚህ ስለሆነ የማቆሚያው ምልክት 60 ከሆነ ራሳቸውን በትክክል 60 ላይ ያስተካክላሉ፡፡ አይጨምሩም አይቀንሱም፡፡ 
 
የእምነት ሕይወታቸው እንዲህ የሆኑ ሰዎች መንፈሳዊ ድሆች ናቸው፡፡ ቁጥር 17-18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐብታም ነኝና ባለጠጋም ሆኜአለሁ፤ አንድም አያስፈልገኝም የምትል ስለሆንህ ጎስቋላና፣ ምስኪንም፣ ደሃም፣ ዕውርም፣ የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ ባለጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፣ ተጎናጽፈህም የራቁትነትህ ሐፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፣ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ፡፡››
 
እምነታቸው ለብ ያለ ሰዎች ዓለማዊ ብልጥግናቸውን አድርገው ይወስዱታል፡፡ በእርግጥ ምስኪን፣ ደካማና ድሃ እንደሆኑ ቢሰማቸውም ሙሉ በሙሉ አያውቁትም፡፡ እነዚህ ራሳቸውን የማያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡ ለራሳቸው ‹‹ደህና ነኝ፡፡ ቅን፣ ብልህና በሌሎችም የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለዚህ ብድንም እንደዚህ መኖር ለእኔ ጥሩ ነው›› ብለው ያስባሉ፡፡ ሕይወታቸውንም በራሳቸው መስፈርት ይኖሩታል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለዓለም ታማኝ ናቸው፡፡ ለእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ግን ታማኝ አይደሉም፡፡ እምነታቸው ለብ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እንደሚተፋቸው ተናገረ፡፡
 
ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡት ፈተናውን ከመውደቅ ለማምለጥ እንጂ ሌላ የላቀ ዓላማ ኖሮዋቸው አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያን አገልግሎት እስከሚያበቃ ድረስ ይቆዩና አገልግሎቱ እንዳለቀ ወዲያውኑ ሾልከው ይሄዳሉ፡፡ በቤተክርስቲያን ሥራዎች ውስጥ ከቶውኑ በፈቃዳቸው አይሳተፉም፡፡ ቢሳተፉም በጣም አነስተኛ ተሳትፎ መሆኑን ያረጋግጣሉ፤ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን አያደርጉም፡፡ አያደርጉም ነገር ግን ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ መንፈሳዊ ድሆች የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡
 
ጌታ ለእነዚህ ሰዎች የሚከተለውን ምክር ሰጥቶዋል፡፡ ‹‹ባለጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፣ ተጎናጽፈህም የራቁትነትህ ሐፈረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፣ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ፡፡›› ባለጠጋ ለመሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ እንዲገዙ ነግሮዋቸዋል፡፡
 
በእርግጥ ጌታን ለመከተል ከፈለጋችሁና በእርግጥ እርሱ እምነታችሁን እንዲያመሰግን የምትፈልጉ ከሆነ እምነታችሁን መማር አለባችሁ፡፡ እምነትን መማር የምትችሉት እንዴት ነው? እምነትን መማር ያለባችሁ መሥዋዕትነትን በመክፈልና በቃሉ በማመን ነው፡፡ ምንባቡ በእሳት የነጠረውን ወርቅ እንድንገዛ ይነግረናል፡፡ ይህ ማለት የእግዚአብሄርን ቃል በማመንና በመከተል መሸነፍ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ስናደርግ ልባችን ይነጥራል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነት መሆኑን የሚገነዘብና ከሙሉ ልቡ የሚያምን እምነትንም ይሰጠናል፡፡ ይህ እምነት ልክ እንደ ንጹህ ወርቅ ነው፡፡
 
እውነተኛ እምነት ለማግኘት መስዋዕትነትን መክፈል አለብን፡ መስዋዕትነትን ሳንከፍል እምነትን መማር አንችልም፡፡ በሌላ አነጋገር በመከራዎች ውስጥ ሳናልፍ ፈጽሞ እምነትን መማር አንችልም፡፡ የእምነት ሰዎች ለመሆን፣ የጌታ ደቀ መዝሙር ሕይወትን ለመኖርና በእምነታችን ለመባረክ በእርግጥ የምንፈልግ ከሆንን መስዋዕትነትን መክፈል አለብን፡፡ መስዋዕትነት ሳይከፈል በፍጹም እዚህ ላይ መድረስ አይቻልም፡፡
 
ከጅማሬው ጠንካራ እምነት ያለው ማነው? ማንም የለም፡፡ ቤተክርስቲያን ስለ ቃሉ የምታስተምራቸውና የምትመራቸው ሰዎች እምነትን ስለማያውቁ ነው፡፡ የቤተክርስቲያንን ምሪት መታዘዝና በእምነት መከተል አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ ግን ችግርን ያቅፋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ትዕግስት ያስፈልጋል፡፡ የቃሉን ምሪት ሕብረትና ትምህርት በመቀበል የእምነት ሰዎች መሆን በመስዋዕትነት የታጀበው ለዚህ ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች እምነትን ለመማር ቢፈልጉም መስዋዕትነት መክፈል ስለማይፈልጉ እውነተኛ የነጠረ እምነት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ጌታ በእምነት ባለጠጎች እንሆን ዘንድ በእሳት የነጠረውን ወርቅ ከእርሱ እንደንገዛ እየነገረን ነው፡፡
 
ይህ ቃል ምን እንደሆነ መረዳት የምትችሉት ከቀደሙት ቅዱሳን እምነት ስትማሩና ሕይወታቸውን ስትከተሉ ብቻ ነው፡፡ ቃሉን በጽንሰ አሳብ ደረጃ ብቻ የምትሰሙና የሚያዛችሁን በትክክል የማትከተሉ ከሆናችሁ በምስክርነት፣ በጸሎት ወይም በስብሰባዎች ውስጥ እየተሳተፋችሁ በተጨባጭ ተግባራዊ የማታደርጉዋቸው ከሆናችሁ እምነትን መማር አትችሉም፡፡ እምነታችሁ ትንሽ ስለሆነች እምነታችሁ ያን ያህል መጥፎ እንዳልሆነች በዓለማዊ መስፈርታችሁ ትለካላችሁ፡፡ ለራሳችሁ ‹‹ድኛለሁ፤ ገንዘብ አለኝ፡፡ በዓለማዊ አገባብ ደህና ነኝ፡፡ ስለዚህ ከሌሎች የተሻልሁ መሆን ይገባኛል፡፡ አዎ ከእነዚህ ሰዎች የተሻልሁ ለመሆኔ እርግጠኛ ነኝ›› ብላችሁ ታስባላችሁ፡፡
 
ወርቅ የሚመስለውን እውነተኛ እምነት በእርግጥ መማር የምትፈልጉ ከሆነ መስዋዕትነትን መክፈል አለባችሁ፡፡ መታዘዝና መከተል ቀላል ነውን? መታዘዝ መሰዋዕትነትን ይጠይቀቃል፡፡ መስዋዕትነትን መክፈል ቀላል ነውን? በእርግጥ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከመተፋት ለማምለጥ መስዋዕትነትን በመክፈል መታዘዝ አለባችሁ፡፡
 
ነገር ግን እውነተኛ እምነትን ሳይማሩ መንፈሳዊ ድሆች የሆኑ ሰዎች በፍጹም መስዋዕትነትን መክፈል አይፈልጉም፡፡ ሰው ለመታዘዝ በመጀመሪያ አስተሳሰቡን ማፍረስ አለበት፡፡ እንደዚህ ማድረግ ካልቻለ ጊዜ እየነጎደ ቢሄድም ልቡ በመንፈሳዊ ጉስቁልና ይቀጥላል፡፡ እነርሱ እምነተ ጎዶሎ መሆናቸውን ሳያውቁ ከእነርሱ በፊት በእምነት የተጓዙትን ቅዱሳኖች ከጀርባ ሆነው ይወቅሱዋቸዋል፡፡ እውነተኛውን እምነት መማር አለባችሁ፡፡ መንፈሳዊ ተጋደሎ ውስጥ ገብታችሁ በእግዚአብሄር ወገን ሆናችሁ ስትዋጉ እምነታችሁ ይነጥራል፡፡ መንፈሳዊ ምርኮም ታገኛላችሁ፡፡ መንፈሳዊ የድል ሕይወት ለመኖርም ምን እንደሚጠይቅ ትገነዘባላችሁ፡፡ ይህንን እምነት ልታውቁት የምትችሉት በትክክል ስትለማመዱት ብቻ ነው፡፡
 
ነገር ግን እውነተኛ እምነትን ሳይማሩ መንፈሳዊ ድሆች የሆኑ ሰዎች በፍጹም መስዋዕትነትን መክፈል አይፈልጉም፡፡ ሰው ለመታዘዝ በመጀመሪያ አስተሳሰቡን ማፍረስ አለበት፡፡ እንደዚህ ማድረግ ካልቻለ ጊዜ እየነጎደ ቢሄድም ልቡ በመንፈሳዊ ጉስቁልና ይቀጥላል፡፡ እነርሱ እምነተ ጎዶሎ መሆናቸውን ሳያውቁ ከእነርሱ በፊት በእምነት የተጓዙትን ቅዱሳኖች ከጀርባ ሆነው ይወቅሱዋቸዋል፡፡ እውነተኛውን እምነት መማር አለባችሁ፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ገብታችሁ በእግዚአብሄር ወገን ሆናችሁ ስትዋጉ እምነታችሁ ይነጥራል፡፡ መንፈሳዊ ምርኮም ታገኛላችሁ፡፡ መንፈሳዊ የድል ሕይወት ለመኖርም ምን እንደሚጠይቅ ትገነዘባላችሁ፡፡ ይህንን እምነት ልታውቁት የምትችሉት በትክክል ስትለማመዱት ብቻ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር ‹‹ራቁትነትህንም ሆነ ድህነትህን አታውቅም፡፡ ድነሃል፤ ነገር ግን እምነትህ ለብ ያለ ነው፡፡ ይህንን ወይም ያንን አይደለም፡፡ በእጅህ ያለው ብቸኛው ነገር የወረወርከው ደህንነት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ ምንም ነገር የለህም›› በማለት የሎዶቅያን ቤተክርስቲያን አገልጋይ ገሰጸው፡፡
 
የእግዚአብሄር አገልጋዮች ወይም መንፈሳዊ ፋና ወጊዎቻችን የደቀ መዝሙርነትን ሕይወት ሳይኖሩ ጊዜ በማሳለፍ ብቻ የእምነት ፋና ወጊዎቻችን ሆነዋልን? አልሆኑም! እነርሱ ለጌታ ሲሉ በሁሉም ዓይነት ችግር፣ በደስታና በሐዘን ውስጥ አልፈዋል፡፡ እግዚአብሄር ከእናንተ በፊት የነበሩትን ውሎ አድሮ እናንተ በምታልፉባቸው ነገሮች ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ ይመራችኋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ከእናንተ በፊት የእምነትን መንገድ በተከተሉት ሰዎች አማካይነት የሚያስተምራችሁና የሚመራችሁ የመሆኑን እውነት ማመን አለባችሁ፡፡