በክርስቲያን እምነት ላይ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤
ርዕስ 1፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ፤
1-26. የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማብራሪያ ልታቀርብልኝ ትችላለህን?
መርፌ ውጭ አንድ ቦታ ላይ ቢወድቅብን ምናልባትም በጠፋበት አካባቢ እንፈልገው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውስጥ ብሩህ ስለሆነ ብለን ቤት ውስጥ መፈለጋችን ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው፡፡ በዘመኑ ቤተክርስቲያኖች ውስጥም እንዲሁ ያሉ ግራ የሚያጋቡ አንዳንድ ሰዎች አገኛለሁ፡፡ ስለ ምዕመናን የውሃ ጥምቀት ፍጻሜ በሌላቸው መከራከሪያዎች ውስጥ በቀላሉ ተሳትፈው እያሉ ‹‹ኢየሱስ ለምን በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ?›› የሚለውን ይህንን አስፈላጊ ጥያቄ ፈጽሞ አይጠይቁም፡፡ እንዲህ ካለው ዝንባሌ የተነሳ በዛሬው የክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ የቤተክርስቲያን ድርጅቶችና አንጃዎች አሉ፡፡
ማብቂያ የሌላቸውን እነዚህን ክርክሮች ወደ ፍጻሜ ለማምጣት ራሳችንን ከግርግሩ መንደር ማውጣትና መርፌያችንን ወደጣልንበት ስፍራ መመለስ ይገባናል፡፡ እውነትን ከልባችን የምንሻ ከሆንን ራሳችንን ከአካባቢው ማራቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም ይህንን በሐይማኖት መንደር ውስጥ ልናገኘው አንችልምና፡፡ ሐዋርያት በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ላይ ብዙ ትኩረት ያደረጉት ለምንድነው? እነርሱ ከኢየሱስ የተቀበሉት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ምስጢራዊ እውነት በመላው ዓለም ተሰብኮ ነበር፡፡
ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› (ዮሐንስ 3፡5) መጽሐፍ ቅዱስ እርሱ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ሊያድነን በውሃና በደም እንደመጣ ይነግረናል፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡6) የደሙ ትርጉም የመስቀል ላይ ሞቱ ነው፡፡ ታዲያ ‹‹ውሃ›› ስትል ምን ማለትህ ነው? አጥማቂው ዮሐንስ ለምን ኢየሱስን አጠመቀው? ከጥምቀቱ በፊትስ ለምን ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› (ማቴዎስ 3፡15) ብሎ አወጀ?
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በተለይም የኢየሱስን ጥምቀት እንደተረዳህና እንደምታምን ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ ስለሰጣቸው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አንዳንድ አጫጭር ማብራሪያዎች ይኸውልህ፡፡ ሐዋርያት ወንጌልን በሰበኩ ጊዜ በኢየሱስ ጥምቀት ላይ እጅግ ታላላቅ ትኩረቶችን አድርገዋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፡- መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ሐጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሳ፡፡›› 91ኛ ቆሮንቶስ 15፡3-4)
‹‹መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ሐጢአታችን ሞተ›› ምን ማለት ነው? ይህ ማለት የእርሱ ሞት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር በሰጠው ዘዴ መሰረት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አሰተሰርዮዋል ማለት ነው፡፡ ዕብራውያን 10፡1 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፡፡›› በዘሌዋውያን 1፡3-5 ላይ ያለውን አይነተኛ መስዋዕት እንመልከት፡፡ ሐጢያተኛው የሐጢያቶቹን ስርየት ለማግኘት የሚቃጠለውን መስዋዕቱ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይገባዋል፡፡
1) ነውር የሌለበት መስዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡ (ዘሌዋውያን 1:3)
2) እጆቹን በመስዋዕቱ ራስ ላይ መጫን ነበረበት፡፡ (ዘሌዋውያን 1፡4) እዚህ ላይ የእግዚአብሄርን ሕግ ግልጽ ማድረግ ይገባናል፡፡ በመስዋዕቱ ራስ ላይ እጆችን መጫን ሐጢያቶቹን ወደ እርሱ ላይ ለማስተላለፍ የእግዚአብሄር ሕግ ነው፡፡
3) ሐጢያቱን ለማስተሰረይ መስዋዕቱን ማረድ ነበረበት፡፡ (ዘሌዋውያን 1፡5)
አሮን በስርየት ቀን ሁለቱንም እጆቹን ሕያው በሆነው ፍየል ራስ ላይ ጭኖ ሐጢያቶቻቸውን ሁሉ በሚመለከት የእስራኤልን ልጆች በደሎችና መተላለፎች ሁሉ በእርሱ ላይ ይናዘዛል፡፡ በፍየሉም ራስ ላይ ያኖራቸዋል፡፡ (ዘሌዋውያን 16፡21) በዚያን ዘመን አሮን የእስራኤል ወኪል ነበር፡፡ እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ የሚጭነው እርሱ ብቻ ነው፡፡ የእስራኤሎች (ወደ 2-3 ሚሊዮን አካባቢ) ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ይተላለፉ ነበር፡፡ የብሉይ ኪዳን መስዋዕት ሊመጡ ያሉ በጎ ነገሮች ጥላ ነበር፡፡ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ሊቀድሰን በእግዚአብሄር ፈቃድ ራሱን አቀረበ፡፡
በመጀመሪያ ኢየሱስ ነውር የሌለበት የእግዚአብሄር በግ ለመሆን የሰው ሥጋ ለብሶ መጣ፡፡ እርሱ የእግዚአብሄር አንድያ ልጅና ‹‹የባሕርዩ ምሳሌ›› (ዕብራውያን 1፡3) ነው፡፡ ስለዚህ ለሰው ዘር ሁሉ የሚሆን የሐጢያት መስዋዕት ለመሆን ብዙ ሆነ፡፡
ሁለተኛ አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ አጠመቀው፡፡ ጥምቀት የተሰጠው ‹‹እጆችን በመጫን›› መልክ ነው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስም የአሮን ዘርና የሰው ዘር ሁሉ ወኪል ነው፡፡ ዮሐንስ በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ እጆቹን ሲጭን እግዚአብሄር በደነገገው ሕግ መሰረት የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ ተላለፉ፡፡ ኢየሱስ ዮሐንስን ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› በማለት አጠመቀው፡፡ በመጨረሻ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ ተላለፉ፡፡ በማግስቱ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ ጮኸ፡- ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡29)
ሦስተኛ ኢየሱስ ‹‹ተፈጸመ!›› (ዮሐንስ 19፡30) በማለት ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ስርየት በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ በእግዚአብሄርም ፊት እኛን ጻድቃን ለማድረግ ዳግመኛ ከሙታን ተነሳ፡፡ የሐጢያት መስዋዕት የሚቀርበው ለሐጢያቶች ይቅርታ እንደሆነ ይታወስ፡፡ አንድ ሐጢያተኛ መስዋዕቱን ከማረዱ በፊት እጆቹን በራሱ ላይ መጫን ነበረበት፡፡ በሌላ አነጋገር አንዲት ደረጃ፣ ቢረሳ እጆቹን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ማኖሩን ቢገድፍ ዓመጽን በማድረጉ ምክንያት አይድንም ነበር፡፡ አንድ ክርስቲያን የኢየሱስ ጥምቀት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቅ ከሆነ ይህ ሰው በልቡ ውስጥ ሐጢያቶች ያሉበት በመሆኑ በራሱ እምነት መዳን አይችልም፡፡
አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የሚያውቁት የእርሱን ገሚስ የጽድቅ ምግባር ብቻ ነው፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያው መልዕክቱ ውስጥ ወንጌልን ግልጽ አድርጎታል፡፡ ‹‹በውሃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በውሃውና በደሙ እንጂ በውሃው ብቻ አይደለም፡፡ መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረውም መንፈስ ነው፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 5፡6) የእርሱ ጥምቀት ለደህንነታችን ያለውን የጽድቅ ምግባሩን ለማጠናቀቅ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚደግፉ ብዙ ምንባቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል መመለስ ይገባቸዋል፡፡