Search

በክርስቲያን እምነት ላይ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤

ርዕስ 1፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ፤

1-28. አንተ ብዙውን ጊዜ ቸል በሚባለው የኢየሱስ ጥምቀት ላይ ትኩረትን ከማድረግህ በስተቀር ይህ እኔ ቀድሞውንም ሳምነው የነበረ ነገር ነው፡፡ ታዲያ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዲህ ልዩ የሚያደርገው ምንድነው?  

‹‹መዳን›› ማለት የሐጢያቶችን ሁሉ ስርየት መቀበል ማለት ነው፡፡ ዳግም መወለድ ማለትም ደግሞ ነው፡፡ አንድ ሐጢያተኛ በሕይወት ወንጌል በማመን ጻድቅ ሲሆን ‹‹እርሱ/እርስዋ በኢየሱስ ደህንነት አማካይነት ከውሃና ከመንፈስ ተወለደ/ች›› እንላለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ በተዋጁትና ዳግም በተወለዱት ላይ ይወርድና የእግዚአብሄር ልጆች እንደሆኑ ይመሰክራል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተመሳሳይ ነው፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት መቀበል፣ መዳን፣ ዳግም መወለድ፣ የእግዚአብሄር ልጅ መሆንና ጻድቅ ሰው መሆን ተመሳሳይ ነገሮች ናቸው፡፡   
ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ መንገድም እውነትም ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ማንም ወደ አብ አይመጣም፡፡›› (ዮሐንስ 14፡6) ይህ የሚያመላክተው እኛ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት የምንችለው የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ በሆነው በኢየሱስ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እንዴት ሐጢያቶቻችንን ሁሉ እንዳነጻና ወደ እርሱ መንግሥት መግባት የሚገባን የእርሱ ሕዝቦች አድርጎ እንደቆጠረን ማወቅ ይኖርብናል፡፡   
ሆኖም አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የእርሱን ስም መጥራት ብቻ ሊያድናቸው እንደሚችል አሁንም ያስባሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ሳይገልጡ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ሊያድነን ያደረገውን ነገር ሳያውቁ በኢየሱስ ያምናሉ፡፡ እግዚአብሄር መለወጥ ወይም የጥላ መዞር የሌለበት መንፈስና ቅዱስ አምላክ ነው፡፡ እኛ ግን የምንኖረው ሐጢያተኛ ሕይወትን ነው፡፡ ወደ ጌታ መንግሥት መግባት የሚቻለው በኢየሱስ አማካይነት ብቻ ነው፡፡ ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው የመንፈስ ሕይወት ሕግ›› (ሮሜ 8፡1-2) እምነት አማካይነት በእርሱ ማመን እንችላለን፡፡     
ብዙ ሰዎች ለደህንነት ምን እንዳደረገ እንኳን አያውቁም፡፡ በፋንታው ‹‹ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ!›› በማለት ዕውር ሆነው በከንቱ በእርሱ ያምናሉ፡፡ የዳኑ እንደሆኑም ያስባሉ፡፡ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ አሁንም ሐጢያቶች አሉባቸው፡፡ በኢየሱስ ላይ እምነት ቢኖራችሁም በልባችሁ ውስጥ አሁንም ሐጢያት ካለ ታዲያ የዳናችሁት ከምንድነው? አንድ ሰው ‹‹ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን እንዴት አነጻ?›› ብሎ ቢጠይቅ ብዙ ሰዎች ‹‹ምናልባትም በመስቀል ላይ ሳያነጻቸው አይቀርም›› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ‹‹በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት አለን›› ለሚለው ጥያቄም ‹‹በእርግጠኝነት! በዚህ ምድር ላይ ፈጽሞ ከሐጢያት መላቀቅ የሚችል ማን ነው?›› ይላሉ፡፡ 
የኢየሱስ ስም ‹‹ሕዝቡን ከሐጢአቶቻቸው የሚያድን አዳኝ›› (ማቴዎስ 1፡21) ማለት ነው፡፡ ከሐጢያት ለመዳን በኢየሱስ እናምናለን፡፡  
ነገር ግን በኢየሱስ ብናምንም አሁንም ድረስ በልቦቻችን ውስጥ ሐጢያት ካለ አሁንም ለሐጢያት ባርነት የተሸጥንና በዚያው መሰረትም የምንኮነን ሐጢያተኞች ነን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም፡፡›› (ሮሜ 8፡1) ስለዚህ በልቡ ሐጢያት ያለበት ሰው ገናም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ አልሆነም፡፡ አሁንም ድረስ በኢየሱስ ቢያምኑም ያልዳኑና ከደህንነት የራቁ ሐጢያተኞች ሆነው ለምን ይቀራሉ? በኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻቸውን በእርሱ ላይ ሳይኖሩ በመስቀሉ ደም ብቻ ስለሚያምኑ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ድረስ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት አለ፡፡ ኢየሱስም ሐጢያቶቻቸው ምንም ቢሆን በመስቀል ላይ ሞቷል፡፡    
በኢየሱስ ጥምቀት በሚያምኑ ክርስቲያኖችና በእርሱ በማያምኑ ሰዎች መካከል አቢይ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ አንዳንዶች በኢየሱስ ጥምቀት ላይ እምነትን ይዘው ቤዛነትን አግኝተው ጻድቃን ሲሆኑ ሌሎች ግን አሁንም ድረስ በዚህ ላይ እምነት ሳይኖራቸው አሁንም ደረስ ሐጢያተኞች ሆነው ቀርተዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐጢያተኛ ላይ አይመጣም፡፡ እርሱ የሚመጣው በውሃውና በመንፈሱ ዳግም በተወለደ ጻድቅ ሰው ላይ ነው፡፡     
ስለዚህም ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ወይስ ክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን?›› (ሮሜ 6፡3) ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሐጢያቶቻችንን እንደወሰደ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ጥምቀት ካላመንን ሐጢያት አልባ የሆነ ልብ እንዳለን መመስከር በፍጹም አንችልም፡፡ እንደዚያ ብናደርግ ከሕሊናችን ጋር የሚጋጭ ውሸት ለእግዚአብሄር እየነገርነው ነው፡፡  
በእርሱ ጥምቀት በማመን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ካላስተላለፍን አሁንም ድረስ በልቦቻችን ውስጥ ሐጢያት አለ፡፡ የኢየሱስን ጥምቀትና መስቀል ወንጌል የማያምኑ ሰዎች ሕግ አክራሪነት ውስጥ ወደ መውደቅ ያዘነብላሉ፡፡ የከፉ ሐጢያተኞችም ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ምንም ነገር ቢያደርጉም ጥቅጥቅ ባሉ ተራሮች ላይ ሄደው ቢጸልዩ ወይም በጸሎት ስብሰባዎች ላይ ይቅርታን ለማግኘት ከልባቸው ቢጸልዩም አሁንም ድረስ በልባቸው ውስጥ የቀሩ ሐጢያቶችን ያገኛሉ፡፡  
ኢየሱስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡ በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢትን አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡ የዚያን ጊዜም፡- ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ ዓመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡›› (ማቴዎስ 7፡21-23) 
‹‹ዓመጸኞች›› የሚለው የሚያመለክተው ማንን ነው? ይህ የሚያመላክተው በመስቀሉ ብቻ ስላመኑ በልባቸው ውስጥ ፍጹም የሆነውን ቤዛነት ያልተቀበሉትን ሰዎች ነው፡፡ ያ ከእግዚአብሄር ያልሆነ ግርድፍ እምነት ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት እንዳዳነን እውነቱን ካላመንን ዓመጸኞች ነን፡፡ የኢየሱስን ጥምቀትና መስቀል ከማወቃችንና ከማመናችን በፊት ትክክለኛ እምነት አለን ማለት አንችልም፡፡ 
ኢየሱስ ሰዎች ዳግም መወለድ የሚፈልጉ ከሆነ ያ የሚቻለው በውሃና በመንፈስ አማካይነት ብቻ እንደሆነ ተናግሮዋል፡፡ ሰዎች መዳን የሚችሉት በኖህ መርከብ ውስጥ ገብተው ቢሆን ኖሮ ብቻ እንደሆነ ሁሉ እናንተም የሐጢያቶቻችሁን ሁሉ ስርየት መቀበልና እውነተኛ የታመነ ሕይወት መኖር የምትችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስታምኑ ብቻ ነው፡፡ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጭ የሐጢያቶቻችሁን ይቅርታ መቀበልም ሆነ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን አትችሉም፡፡