Search

የመገናኛው ድንኳን ጥናት፤

የዕጣኑ መሰውያ

የዕጣኑ መሰውያ
 
የዕጣኑ መሰውያ ከግራር እንጨት የተሰራና ርዝመቱና ወርዱ አንድ ክንድ (45 ሳንቲ ሜትር፤ 1.5 ጫማ) ቁመቱ ደግሞ 2 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ነበር፡፡ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ የተቀመጠው የዕጣኑ መሰውያ ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠና ዙሪያውን የወርቅ ክፈፍ ያለው ነበር፡፡ ከክፈፉ በታች ለሸከም የሚያገልሉ መሎጊያዎችን የሚይዙ አራት የወርቅ ቀለበቶች ተደርገውበታል፡፡ በዚህ የዕጣን መሰውያ ላይ ከቅዱሱ ቅብዓ ዘይትና ከጣፋጩ ዕጣን በስተቀር ሌላ አንዳች ነገር አይደረግም፡፡ (ዘጸዓት 30፡22-25)   
የዕጣኑ መሰውያ የጸሎት ዕጣን ለእግዚአብሄር የሚቀርብበት ቦታ ነው፡፡ ነገር ግን በዕጣኑ መሰውያ ላይ ከመጸለያችን በፊት አስቀድመን በዚህ መሰውያ ላይ ለመጸለይ ብቁ መሆናችንንና አለመሆናችንን ማወቅ አለብን፡፡ ቅዱስ ወደሆነው አምላክ ለመጸለይ ብቁ መሆን የሚሻ ማንኛውም ሰው በመጀመሪያ በእምነት ከሐጢያቶቹ በመታጠብ ሐጢያት አልባ መሆን አለበት፡፡ ይህንን ለማድረግ አንድ ሰው በሚቃጠለው መስዋዕትና በመታጠቢያው ሰን ከሐጢያቶቹ ሁሉ በእምነት መንጻት አለበት፡፡ 
እግዚአብሄር የሐጢያተኞችን ጸሎቶች አይሰማም፡፡ (ኢሳይያስ 59፡1-3) ለምን? ምክንያቱም እግዚአብሄር የሚቀበለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የታጠቡትን ብቻ ነውና፡፡ እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው እውነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አንጽቶናል፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር የሚደሰተው የጻደቃንን ጸሎቶች በመስማት ብቻ ነው፡፡ (መዝሙረ ዳዊት 34፡15፤1ኛ ጴጥሮስ 3፡12)