Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 11] እስራኤል ይድን ይሆን?

ሮሜ 11፡1 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲህ እግዚአብሄር ሕዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ፡፡ አይደለም፤ እኔ ደግሞ እስኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና፡፡›› በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር እስራኤሎችን አልተዋቸውም፡፡ ጳውሎስ ራሱም እስራኤላው ነበርና፡፡
 
እግዚአብሄር በሮሜ 11፡2-5 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም፡፡ መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን በእግዚአብሄር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ አታውቁምን? ጌታ ሆይ ነቢያትህን ገደሉ፤ መሰዊያዎችህንም አፈረሱ፡፡ እኔም ብቻዬን ቀረሁ፡፡ ነፍሴንም ይሹአታል፡፡ ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበኣል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች አስቀርቻለሁ፡፡ እንደዚሁም በአሁኑ ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ፡፡››
  
ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጠይቋል፡- ‹‹መጽሐፍ ስለ ኤልያስ የሚለውን አታውቁምን?›› እዚህ ላይ ጳውሎስ ውሎ አድሮ ሐጢያቶቻቸውን በሚወስድው የእግዚአብሄር ጽድቅ የሚታመኑ ብዙ እስራኤሎች የመኖራቸውን እውነታ እየጠቆመ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለኤልያስ በተነገረው የእግዚአብሄር ቃል ከእስራኤሎች መካከል ብዙዎቹ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው እንደሚቀበሉ ይነግረናል፡፡ እኛ በዚህ ቃል እናምናለን፡፡
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹7›› ቁጥር ምልዓትን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሄር ይህንን ዓለም በስድስት ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አረፈ፡፡ እግዚአብሄር ጉልበታቸውን ለበኣል ያላንበረከኩ ሰባት ሺህ ሰዎችን ለማስቀረት ቃል ገባ፡፡ ይህ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው በመቀበል ብዙ እስራኤሎች ደህንነትን ይቀበላሉ ማለት ነው፡፡
 
ጳውሎስ በእስራኤሎችና በአሕዛቦች መካከል ያለውን ልዩነት ሲያብራራ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ብዙዎቹ እንደሚድኑ አብራርቷል፡፡
እነርሱ ለመውደቅ ተሰናክለዋልን?
 
ጳውሎስ በሮሜ 11፡6-12 ላይ እስራኤሎች ኢየሱስ አዳኛቸው የነበረ የመሆኑን እውነታ በሚገባ ተቀብለው ቢሆን ኖሮ የአሕዛቦች የደህንነት ዘመን የሚባል ባልኖረም ነበር ይላል፡፡ እስራኤሎች ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ባለማመናቸው እግዚአብሄር አሕዛቦች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የመዳን ዕድል እንዲኖራቸው ፈቀደ፡፡ በዚህም እግዚአብሄር እስራኤሎች በኢየሱስ አምነው ልጆቹ በሆኑት በአሕዛቦች እንዲቀኑ አቀደ፡፡ ያን ጊዜ እስራኤሎች ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው መቀበል ጀመሩ፡፡ ውሎ አድሮም ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥም መሲሃቸው የመሆኑን እውነታ ተቀበሉ፡፡
 
 
ሥሩ ቅዱስ ስለሆነ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው፡፡ 
 
ሮሜ 11፡13 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ፡፡ እኔ የአሕዛብ ሐዋርያ እንደ መሆኔ መጠን አገልግሎቴን አከብራለሁ፡፡›› ጳውሎስ የአሕዛብ ሐዋርያ በመሆኑ አገልግሎቱን እንደሚያከብር ተናግሮዋል፡፡ ዳግም በተወለዱት አሕዛቦች በማስቀናት የራሱን የሥጋና የደም ሰዎች ለማዳንም ፈለገ፡፡
 
‹‹የእነርሱ መጣል ለዓለም መታረቅ ከሆነ ከሙታን ከሚመጣ ሕይወት በቀር መመለሳቸው ምን ይሆን? በኩራቱም ቅዱስ ከሆነ ብሆው ደግሞ ቅዱስ ነው፡፡ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹም ደግሞ ቅዱሳን ናቸው፡፡›› (ሮሜ 11፡15-16) ይህ ምንባብ የእስራኤሎች ስር የሆነው አብርሃም በቃሉ በማመን ከዳነና የእግዚአብሄርን ጽድቅ ካገኘ የአብርሃም ቅርንጫፎች የሆኑት እስራኤሎችም መዳን ይችላሉ ማለት ነው፡፡
 
በዚህ ሁኔታ ጳውሎስ ዳግም የተወለዱ አሕዛቦች መመካት እንደሌለባቸው ያስጠነቅቃቸዋል፡፡ ምክንያቱም በወይራው ዛፍ ላይ በመተከል አዲስ ሕይወት የተሰጣቸው የተሰበሩ የበረሃ ወይራ ሆነው የእግዚአብሄር ቅዱስ ሕዝብ ሆነዋልና፡፡ ሮሜ 11፡18 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በቅርንጫፎቹ ላይ አትመካ፤ ብትመካባቸው ግን ሥሩ አንተን ይሸከማል እንጂ ሥሩን የምትሸከመው አንተ አይደለህም፡፡››
እኛ ከሐጢያቶቻችን የዳንነው በእግዚአበሄር ጽድቅ በማመን ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ብንተው ግን እኛም እንተዋለን፡፡ ይህንን ማድረግ የለብንም፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለማዳን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ፈጽሞዋልና፡፡ እኛም በእርግጥ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናልና፡፡ የዳንነው በሥራችን ሳይሆን ፍጹም በሆነው የእግዚአብሄር ጽድቅ በማመናችን ነው፡፡ እኛ አሕዛቦች በተሰበሩት የእስራኤሎች ቅርንጫፎች ላይ በመተካት በእርሱ ጽድቅ ላይ ባለን እምነታችን የእርሱ ሕዝብ ሆነናል፡፡
      
 

በእግዚአብሄር ድቅ ስለምናምን ጸንተን መቆም እንችላለን፡፡ 

 
ስለዚህ በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ክርስቲያኖችና አሕዛቦች ሁለቱም የእርሱ ሕዝቦች ሆነው በኢየሱስ ላይ መተከል ይችላሉ፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ ካላመንን ከእርሱ ቅን ፍርድ የተነሳ በሐጢያቶቻችን ሞትን እንሞታለን፡፡ ጳውሎስ ይህንን አስቀድሞ ለእስራኤሎች አስጠነቀቀ፡፡ ነገር ግን እኛም ከማስጠንቀቂያው ውጪ አይደለንም፡፡
 
እግዚአብሄር ለእኛ ለአሕዛቦች ራራልን፡፡ በጽድቁም ፈጽሞ አዳነን፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያውቁና የሚያምኑ ሰዎች ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ድነዋል፡፡ የዘመኑ ክርስቲያኖች በሙሉ ኢየሱስ አዳኛቸው መሆኑን ቢናገሩም ፈጽሞ ባዳናቸው የእግዚአብሄር ጽድቅ የማያምኑ ከሆኑ ይጠፋሉ፡፡
 
ሮሜ 11፡23-24 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እነዚያም ደግሞ በአለማመናቸው ጸንተው ባይኖሩ በዛፉ ውስጥ ይገባሉ፡፡ እግዚአብሄር መልሶ ሊያገባቸው ይችላልና፡፡ አንተ በፍጥረቱ የበረሃ ከሆነ ወይራ ተቆርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ ይልቁንስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም?›› በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር ሰው ሁሉ በእርሱ ጽደቅ እንዲያምን ይመራው ዘንድ የሚችልበት ሐይል አለው፡፡ ያ ሐይል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት በእግዚአብሄር ጽድቅ ውስጥ ቃል ተገብቷል፡፡
    
እስራኤሎችና አሕዛቦች በምግባሮቻቸው የእግዚአብሄር ልጆች አልሆኑም፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን የቻሉት የእርሱ ልጆች በሚያደርጋቸው ጽድቁና ተስፋ በማመን ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ከሕግ የሚገኘውን ጽድቅ ፈጽሞ አግልሎታል፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ እስራኤሎችና አሕዛቦች የሚድኑት በእግዚአብሄር ጽድቅ ላይ ባላቸው እምነት ነው፡፡ እኛ በምናሰራጨው ወንጌል አማካይነት የሚፈጸመው ታላቁ የእግዚአብሄር ደህንነት በረከት ይህ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ሐይል በጽድቁ ውስጥ የተሰጠው የእምነት ተስፋው ነው፡፡
 
ሮሜ 11፡26-27ን እንመልከት፡- ‹‹እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- መድሃኒት ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ሐጢአተኝነትን ያስወግዳል፡፡ ሐጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፡፡››
 
እግዚአብሄር በዘመን መጨረሻ ላይ ውሎ አድሮ እስራኤሎችን እንደሚያድን ቃል ገብቷል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ራሱ ከእስራኤሎች አእምሮ ውስጥ ክፋትንና ርኩሰትን በማስወገድ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው ያምኑ ዘንድ እንደሚያደርጋቸው ተስፋ ሰጥቷል፡፡ የታመኑ ቅድመ አያቶች ቢኖሩዋቸውም እስራኤሎች ራሳቸው ደህንነትን አላገኙም፡፡ ነገር ግን በቅርቡ ወደፊት እግዚአብሄር ልባቸውን በመንካትና በእርሱ ጽድቅ እንዲያምኑ በማድረግ ሊያድናቸው ፈቅዶዋል፡፡
     
 

እግዚአብሄር ሁላችንንም ይምር ዘንድ ሁላችንም በአለመታዘዝ ዘግቶናል!  

 
በጣም ጥልቅ የሆነውን ቁጥር 32ን እናንብብ፡- ‹‹እግዚአብሄር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና፡፡›› ሁሉም በእግዚአብሄር ላይ አምጾዋል፡፡ ማንም እርሱን ሙሉ በሙሉ ሊታዘዘው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር ሁላችንንም በአለመታዘዝ የዘጋን ሊራራልንና ሊወደን ስለፈለገ ነው፡፡ ይህ በጣም አስገራሚና አስደናቂ እውነት ነው፡፡
  
በዚህ ምንባብ አማካይነት እግዚአብሄር ሰዎችን ለምን በአለመታዘዝ እንደዘጋቸው መረዳት እንችላለን፡፡ የእርሱ ቸርነት ምንኛ አስገራሚ ነው! እግዚአብሄር ፍጹም በሆነው ጽድቁና በሚምረው ፍቅሩ ሊያለብሰን ዓመጸኞች አድርጎ አስቀመጠን፡፡ አስገራሚ የሆነውን አሳቡን በማመን አመስጋኞች መሆን እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር የጽድቁን ፍቅር ይለግሳቸው ዘንድ እስራኤሎችንም በአለመታዘዝ ዘጋቸው፡፡ እስራኤሎች አሁንም ኢየሱስን ከናዝሬት የወጣ የማይረባ ሰው አድርገው ሲመለከቱት ብዙዎቹ የአሕዛብ ክርስቲያኖች ደግሞ ገንዘብ የመሰብሰቢያ መሳርያ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡
 
የእግዚአብሄርን መሃሪ ፍቅር ሰዎች ወደ ሲዖል ከመውረድ በቀር ምርጫ የላቸውም፡፡ እግዚአብሄር አስቀድሞ የሚነደውን ሲዖል ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወደ ሲዖል ሲወርዱ ማየት አይፈልግም፡፡ ምክንያቱም በጣም ያዝንላቸዋልና፡፡ ‹‹እንዴት ወደ ሲዖል እወረውራችኋለሁ?›› ወደ ደህንነት የሚመጡት አህዛቦች ቁጥር ሲሞላ ከእስራኤሎች ብዙዎቹ የክርስቶስ ተቃዋሚ በመጨረሻው የሰባቱ ዓመት አጋማሽ መከራ ወቅት ሲያሳድዳቸው ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ወደ ማመን ይመጣሉ፡፡ ወደፊት ኢየሱስን የእግዚአብሄር ጽድቅ አድርገው የሚያውቁ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ምዕመናኖች ከእስራኤሎች መካከል ይነሳሉ፡፡
 
‹‹እግዚአብሄር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና፡፡›› ይህ አስገራሚ ምንባብ እግዚአብሄር ሐጢያተኞች ሁሉ በእርሱ ጽድቅ በማመን እንዲድኑ እንደፈቀደላቸው ያብራራል፡፡
 
እግዚአብሄር ለጳውሎስ በቂ ቁጥር ያላቸው አሕዛቦች በመከራው ወቅት ሰማዕታት በሚሆኑበት ጊዜ እስራኤሎችን ንስሐ እንዲገቡና በክርስቶስ እንዲያምኑ እንደሚያደርጋቸው ነግሮታል፡፡ ጳውሎስ በሮሜ 11፡33 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእግዚአብሄር ባለጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፤ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፡፡››
 
እውነተኛ ጥበብና መለኮታዊ ቸርነት ሁሉ የሚመጣው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ እርሱ ገና ከመጀመሪያው ሰዎችን ሁሉ ደካማ ፍጡራኖች አድርጎዋቸዋል፡፡ ይህም ደህንነትን እንድንቀበል የፈቀደልንን የእግዚአብሄር ጥበብ ያሳያል፡፡ ከዚህ የተነሳ በመጨረሻው ዘመን በእርሱ ማመን እስራኤሎችንም እንኳን ያድናል፡፡ ሁላችንም ወደ ቆሻሻና ወደ እሳት ከመጣል በቀር ምርጫ አልነበረንም፡፡ እግዚአብሄር ግን ራሱ ባቀደውና በፈጸመው ጽድቁ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አዳነን፡፡ እግዚአብሄር እኛ ሰዎች በሙሉ በሰይጣን ተፈትነን የእግዚአብሄርን ሕግ በጣስን ጊዜ በብሉይ ኪዳን የመገናኛው ድንኳን የመስዋዕት ስርዓት መሰረት ሐጢያተኞች በሙሉ በእርሱ ጥምቀትና ደም እንዲድኑ ፈቀደ፡፡
 
ታዲያ የእግዚአብሄርን ጥበብ ለመቃወም የሚደፍር ማነው? ‹‹ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፡፡ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፡፡ አሜን›› እግዚአብሄር ምህረቱን ይሰጠን ዘንድ እኛን በአለመታዘዝ የመዝጋቱን ይህንን እውነት መረዳት ማን ይችላል? እግዚአብሄር ይህንን በማድረጉ ተሳስቷል ብሎ ለመናገር የሚደፍር ማነው? ማንም የለም! ክብርና መለኮታዊ ቸርነት ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም የእርሱ ናቸው፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ጻፈ፡- ‹‹የጌታን ልብ ያወቀው ማነው? ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማነው? ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፡፡ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን አሜን፡፡›› (ሮሜ 11፡34-36)
 
እኛ በጉድለቶች የተሞላን ብንሆንም የምንኖረው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ወንጌል የሚቃወሙ ሰዎች የእርሱ ጠላቶች ናቸው፡፡ ያ ትክክል ነው! እነዚህ ሰዎች በእኛ መካከልም ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ማናችንም እንዲህ ባለው ፈተና ውስጥ እንዳንወድቅ መጸለይና መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ ወንጌልን የሚቃወሙ ሰዎች በዚህና በሚመጣው ዓለም ይጠፋሉ፡፡
 
እስራኤሎች በኢየሱስ የሚያምኑበት ዘመን ቀርቦዋል፡፡ በዚህ ምድር ላይ የሚኖረው ስድስት ቢሊዮን ሕዝብ ወደ እግዚአብሄር ቢመለስና ደህንነትን ቢያገኙ ምንኛ ግሩም ነበር? በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ጻድቃን መመልከት ያለውን ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ለእስራኤሎች የታቀደውን የእግዚአብሄርን ሥራም ጭምር ነው፡፡ በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር ላይ ለመኖርም እምነታቸውን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ጻድቃን ሁልጊዜም በእምነትና በተስፋ መኖር አለባቸው፡፡
 
እስራኤሎች ክርስቶስን አዳኛቸው የሚያምኑበት ቀን እየቀረበ ስለማውቅ እግዚአብሄርን አመስግናለሁ፡፡
 
ጌታ ኢየሱስ ቶሎ ና!