Search

የመገናኛው ድንኳን ጥናት፤

ቅድስቱ ስፍራ

ቅድስቱ ስፍራ
 
ሳንቃዎቹ
 
የመቅደሱ ዕቃዎች
 
የመገናኛው ድንኳን 13.5 ሜትር (45 ጫማ) ርዝመትና 4.5 ሜትር (15 ጫማ) ስፋት ያለው ሲሆን ቅድስትና ቅድስተ ቅዱሳኑ ተብለው በሚጠሩ ሁለት ክፍሎች ተከፍሎዋል፡፡ በቅድስቱ ውስጥ መቅረዙ፣ የሕብስቱ ገበታና የዕጣኑ መሰውያ ያሉ ሲሆን በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ደግሞ የምስክሩ ታቦትና የስርየት መክደኛው ይገኛሉ፡፡ 
ቅድስቱንና ቅድስተ ቅዱሳኑን የያዘው የመገናኛው ድንኳን በሁሉም ወገን ዙሪያውን 70 ሳንቲ ሜትር (2.3 ጫማ) ስፋትና 4.5 ሜትር (15 ጫማ) ርዝመት ባላቸው የግራር እንጨት ሳንቃዎች የተከበበ ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ በወርቅ የተለበጡ አምስት የግራር እንጨት ምሰሶዎች ይደረጋሉ፡፡ አንድ ሰው ከውጪው አደባባይ ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባበት የመግቢያው በር ራሱ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተሰራ ነው፡፡ 
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ እያንዳንዳቸው 2.5 ሜትር (7.4) ጫማ ርዝመት ያላቸው ስልሳ ምሰሶዎች ተተክለው ነበር፡፡ በስተ ምስራቅ ያለው የአደባባዩ መግቢያ በርም እንደዚሁ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተሰራ ነበር፡፡ ማንኛውም ሰው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ መግባት የሚችለው በዚህ በውጪው አደባባይ በር ውስጥ በማለፍ ብቻ ነበር፡፡ በዚህ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ የሚቃጠለው መስዋዕት የሚቀርብበት መሰውያና የመታጠቢያው ሰን ይገኛሉ፡፡
አንድ ሰው እነዚህን ሁለቱን ካለፈ በኋላ 4.5 ሜትር (15 ጫማ) ርዝመት ወዳለው የመገናኛው ድንኳን በር ይደርሳል፡፡ ይህ የመገናኛው ድንኳን በር የናስ ኩላቦች ያሉዋቸው አምስት ምሰሶች አሉት፡፡ የመገናኛው ድንኳን በር ልክ እንደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ በተሰሩና በአምስቱ ምሰሶዎች ጫፍ ላይ  በተሰሩ የወርቅ ኩላቦች ላይ የተንጠለጠሉ ነበሩ፡፡ ይህ መጋረጃ የመገናኛውን ድንኳን በስተ ውስጥና በስተ ውጪ የሚለይ መለያ ነበር፡፡ 
እግዚአብሄር በ48 ሳንቃዎች በተሰራው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ አደረ፡፡ እግዚአብሄር ከመገናኛው ድንኳን በላይ በተገለጠው የደመና አምድ በቀን በእሳት አምድ ደግሞ በሌሊት ለእስራኤል ሕዝብ ሕልውናውን ገለጠ፡፡ እግዚአብሄር ራሱ ባደረበት በቤተመቅደሱ ውስጥም የእግዚአብሄር ክብር ስፍራውን ሞልቶት ነበር፡፡ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ የሕብስቱ ገበታ፣ መቅረዙና የዕጣኑ መሰውያ የነበሩ ሲሆን በቅድስተ ቅዱሳኑ ደግሞ የምስክሩ ታቦትና የስርየት መክደኛው ነበሩ፡፡ እነዚህ ለተራው የእስራኤል ሕዝብ የተከለከሉ ስፍራዎች መግባት የሚችሉት ካህናቶችና ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበሩ፡፡ 
በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያሉት ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ መቅረዙ የተሰራው ከወርቅ ነበር፡፡ የሕብስቱ ጠረጴዛም እንደዚሁ ከወርቅ የተሰራ ነበር፡፡ የቤተመቅደሱ ቁሳቁሶችና ባለ ሦስት ወገን ግድግዳዎቹ ሁሉ የተሰሩት ከንጹህ ወርቅ ስለነበር የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል ሁልጊዜም ብሩህ ሆኖ ያበራ ነበር፡፡ 
የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል በዚህ መንገድ ወርቃማ በሆነ ብርሃን ማብራቱ የዳኑት ጻድቃን የከበረውን የእምነት ሕይወታቸውን በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚኖሩ ይነግረናል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምነው የሚኖሩት ቅዱሳን በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንደሚገኘው ንጹህ ወርቅ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚኖሩት ሕይወት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ የእግዚአብሄርን ቃል የሚመገብ፣ ወደ እርሱ የሚጸልይና እርሱን የሚያመስግን፣ በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት የሚቀርብና በየቀኑም የእርሱን ጸጋ የሚጎናጸፍ የተባረከ ሕይወት ነው፡፡ ይህ ሁሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለው የእምነት ሕይወት ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ይህንን የከበረ የእምነት ሕይወት መኖር የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የዳኑ ጻድቃን ብቻ መሆናቸውን በልባችሁ ጽላት ላይ ልትጽፉት ይገባል፡፡